TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AddisAbaba📍

በአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ፤ የቦሌ ክ/ከተማ ንግድ ጽ/ቤት ሃላፊ በህገ ወጥ ንግድ ምክንያት የታሽገን የንግድ ቤት እከፍትልሃለሁ በሚል 100 ሺ ብር #ጉቦ ሲቀበል እጅ ከፍንጅ መያዙን የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ፤ የንግድ ፅ/ቤት ሃላፊው አቶ አለማየሁ ዋንዴቦ ታሽጎ የነበረን የንግድ ቤት በህገ ወጥ መንገድ ለመክፈት ተስማምቶ 100 ሺ ብር ሲቀበል በህ/ሰቡ ጥቆማ መሠረት ሊያዝ መቻሉን ገልጿል።

@tikvahethiopia