TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#እንድታውቁት

ከንጋቱ 11:30 አንስቶ የሚዘጉ መንገዶች !

ነገ በአዲስ አበባ ፤ በኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ አማካኝነት የተዘጋጀ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ይካሄዳል።

ሩጫው መነሻ እና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገ ሲሆን ውድድሩ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ፦

- ከቅዱስ ዑራኤል ቤተ-ክርስቲያን  ወደ መስቀል አደባባይ
- ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ
- ከአጎና ሲኒማ  ወደ መስቀል አደባባይ
- በወንጌላዊት ህንፃ ወደ ጎተራ
- ከዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን ወደ ጎተራ
- ከጎፋ ገብርኤል ወደ ጎፋ ማዞሪያ
- ከሳር ቤት ወደ ጎፋ ማዞሪያ
- ከአፍሪካ ህብረት ወደ ብልጋሪያ
- ከትንባሆ ሞኖፖል ወደ ገነት ሆቴል
- ከጥይት ቤት ወደ ጠማማው ፎቅ
- ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ ለገሃር
- ከልደታ ቤተ ክርስቲያን ወደ ለገሃር
- ከሰንጋ ተራ ወደ ለገሃር
- ከብሔራዊ ቴአትር ወደ ለገሃር
- ከሐራምቤ ሆቴል  ወደ መስቀል
- ከቤተመንግስት ወደ መስቀል
- ከካዛኝቺስ ሼል ወደ ባምቢስ የሚወስዱ መንገዶች ከንጋቱ 11፡30 ጀምሮ ውድድሩ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ፡፡

በውድድር መስመር  ግራ እና ቀኝ ለረጅምም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ ነው።

የሩጫው ተሳታፊዎች ፀጥታው የጋራ ጉዳይ መሆኑን በመገንዘብ ወደ መሮጫ ስፍራ ሲገቡ #ለፍተሻ እንዲተባበሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ  ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

@tikvahethiopia