TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ለጥንቃቄ

" በምዕራብ ኦሞ ዞን ባለፉት ሦስት ወራት 9,000 #ህፃናት በኩፍኝ ተጠቅተዋል። 11 ሞት ተመዝግቧል " - የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ፦
° 65 በመቶ የሚሆን #ገዳይ የወባ ዝርያ እንዳለ፣
° በአንድ ዓመት ውስጥ 101 ሰዎች በወባ እንደሞቱ፣
° ማኅበረሰቡ ወደ ሕክምና ተቋማት እንዲሄድና አጎበር የመጠቀም ልምዱን እንዲያዳብር የክልሉ ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ዳይሬክተር አቶ ተስፋፅዮን ተረፈ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ኩፍኝ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል ?

* ምዕራብ ኦሞ ዞን ባለፉት 3 ወራት 9,000 #ህፃናት በኩፍኝ ተጠቅተዋል። 11 ሞት ተመዝግቧል። በክልሉ በአንድ ዓመት ውስጥ 12,700 የኩፍኝ ኬዞች ተገኝተዋል። 

* ከሌሎች ቦታዎች በተለዬ መልኩ በምዕራብ ኦሞ ዞን አሁንም ከፍተኛ ሥራ የሚጠይቅ የኩፍኝ ወረርሽኝ ስርጭት አለ። በመቀጠልም በቤንቺ ሸኮና ከፋ ዞኖች በተወሰኑ ወረዳዎች ይስተዋላል።

* አርሶ አደሮች በሚኖሩባቸው ( #በተለይም ምዕራብ ኦሞ)፣ የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች የክትባት አሰጣጡን አፌክት ያደርገዋል።

* #አርሶ_አደሮች ባሉባቸው አካባቢዎች ላይ ችግሩ እንዲቀረፍ ለማድረግ የጤና ባለሙያዎች በአካባቢው ተንቀሳቀሰው ሕክምና እንዲሰጡ እየተደረገ ነው።
 
* የኩፍኝ ኬዞች ያሉባቸው አራት ዞኖች ናቸው። ቤንቺ ሸኮ ዞን ላይ ወደ 3,000፣ ከፋ ዞን ከ1,000 በላይ ኬዞች ነበሩ ፤ አሁን መቆጣጠር ተችሏል።

* ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ የኩፍኝ ክትባት ዘመቻ ለማድረግ ጤና ሚኒስቴር ፈቅዷል። ከአምስት ዓመት በታች ለሚሆኑ ሕፃናት ክትባት ይደረጋል።
 
ወባ በምን ደረጃ ይገኛል?

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃልፊ አቶ ኢብራሄም ተማሙ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፦

- ለሁለት ዓመታት #የወባ_ወረርሽኝ በክልሉ ተከስቶ ቆይቷል። የኩፍኝ ወረርሽኝም በተለይ በምዕራብ ኦሞ ዞን ልዩ ትኩረት ይሻል። ከእስከዛሬው ጋር ሲነጻጸር ግን ኬዞቹ እየቀነሱ ነው። ግን አሁንም ሥራ ይጠይቃል።

- የወባ ወረርሽኝ ቆዬ ስንል በርካታ ሥራዎችን ሰርተናል ከወባ ጋር ተያይዞ ወደ 1.2 ሚሊዮን የአጎበር ስርጭት ተካሂዷል። ከ6,000 ኪ.ግ በላይ እርጭት ተካሂዷል።

- አሁንም ውሃ ያቆሩ ቦታዎች ላይ እርጭት እያካሄድን ነው ፤ በጣም በተለየ መንገድ ምዕራብ ኦሞ ላይ ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ያለው ግብዓት አሰራጭተን የመከላከሉን ሥራ እየሰራን ነው።

አቶ ተስፋፅዮ በበኩላቸው ስለ ወባ ምን አሉ ?

* የተወሰኑ ወረዳዎችን ላያካትት ይችል ይሆናል እንጂ ሁሉም  ዞኖች በጣም ከፍተኛ የወባ ጫና ያለባቸው ናቸው።

* በአመት ውስጥ #በ6_ዞኖች በወባ ወደ 101 ሞት ተመዝግቧል። አሁን ግን ማኅበረሰቡ  በአቅራቢያቸው ህክምና እያገኙ ስለሆነ የህመም (የኬዝ)፣ የሞት መጠኑ በዛው ልክ ቀንሷል።

* ላለፉት ሁለት ዓመት ለዚህ መንስኤ የሆኑ ጥናቶች ለማድረግ ሞክረናል፣ የምላሽ ሥራው ተሰርቷል።

* እስካሁን ባለው በአጠቃላይ ወደ 400,054 ሰዎች በአንድ ዓመት የወባ አይነቶች ተለይተው ህክምና ያገኙ ናቸው።

* በተሰሩ ሥራዎች በተለይ ከአራት ወራት በፊት እስከ 15,000 ሰዎች በወባ ይጠቁ ነበር። አሁን ባለንበት በሳምንት በወባ የመጠቃቱ ሁኔታ ከ7,000 እስከ 6,000 ሰዎች ዝቅ ለማድረግ ተችላል።

* በመከላከል ላይ ያለ ክፍተት ነው የወባ ቁጥር ከፍ ብሎ እዲታይ እያደረገ ያለው። ምዕራብ ኦሞ ፣ ካፋ ዞን በሚገኙ አካባቢዎች ላይ አርብቶ አደሮች ናቸው በተለይ ተጋላጭ የሆኑት።

* ከጤና ኬላ ጀምሮ እስከ ከፍተኛ ሆስፒታል ድረስ የወባ ህክምና አለ።

* ሞት እያስከተለ ያለው ቆይተው ስለሚመጡ ነው። ቆይተው ሲመጡ ደግሞ በክልላችን #ከ65 ፐርሰት በላይ ፋልሲፋረም የሚባል በባህሪው #ገዳይ የሆነ ዝርያ ነው ያለው።

* በእኛ ክልል ላይ የሚበዛው ያ " ፋልሲፋረም " ነው። ሰዎች ወዳውኑ ምልክቱን እንዳዩ የመወሳሰብ ደረጃ ላይ ሳይደርስ ወደ ጤና ተቋማት ሂደው መታከም አለባቸው። ችግሩ ሲወሳሰብ ደም ሊፈልግ ይችላል፣ #ነፍሰ ጡሮችን በተለይ ወዲያው የመግደል ዕድሉ ከፍተኛ ነው።

ለ2ቱም ወረርሽኞች ለሞት አደጋው መከሰት ምክንያቱ ፦

° የሕሙማን ወደ ሕክምና #ዘግይቶ መምጣት፣

° #የጤና_ኤክስቴንሽኖች ወረርሽኝ አካባቢዎች ላይ አክቲቭ አለመሆንና በወቅቱ ለይቶ አለመላክ ነበር።

* በዘላቂነት ችግሮቹን ለማስወገድ ክልሉ የንቅናቄ መድረክ እንያዘጋጀ ነው። አሁንም ዝናብ ወጣ እየገባ እያለ ስለሆነ ለወባ መራባት እጅግ በጣም ምቹ አጋጣሚ ስለሚፈጥር ማህበረሰቡ ጥንቃቄ ሊያደግ ይገባል።

ጥንቅሩ በአዲስ አበባ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

@tikvahethiopia
75😢36🕊13😭10🙏8👏7😡4🥰1
#ለጥንቃቄ

" ተጠርጣሪው ከ50 ሺህ እስከ 600 ሺህ ብር ከእያንዳንዳቸው መቀበሉ ተረጋግጧል " - ፖሊስ

" ያለምንም ቅድመ ክፍያ ቪዛ እናስጨርሳለን ! " በሚል #ቲክቶክ በተሰኘው የማህበራዊ መገናኛ ዘዴ ሐሰተኛ መረጃ በማሰራጨት ሲያጭበረብር የነበረ ግለሰብ መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።

" ያለምንም ቅድመ ክፍያ ወደ ተለያዩ ሀገራት ለሚጓዙ ሰዎች ቪዛ እናስጨርሳለን ! " እያለ በቲክቶክ ሲያጭበረብር የነበረው ይኸው ግለሰብ ከ25 በላይ የሚሆኑ ግለሰቦችን  በማጭበርበር ከ50 ሺህ እስከ 600 ሺህ ብር ከእያንዳንዳቸው መቀበሉ ተረጋግጧል።

በቲክቶክ ሀሰተኛ የግለሰቡ ማስታወቂያ የተጭበረበሩት አብዛኞች ወደ #ካናዳ ለመጓዝ ፍላጎት አሳይተው ከተጠርጣሪው ጋር የተገናኙ ናቸው።

" ያለምንም ቅድመ ክፍያ የቪዛ ፕሮሰስ እጨርሳለሁ " ቢልም ተበዳዮችን የተለያየ ቦታ እየቀያየረ እያገኛቸው  ቪዛ እንዳለቀላቸው እየነገረ እና ሌሎች ምክንያቶችን እየሰጠ ከእያንዳንዳቸው ከ50 ሺህ እስከ 600 ሺህ ብር የሚደርስ ገንዘብ ተቀብሏል።

ተጠርጣሪው የማታለል ወንጀል እየፈፀመ መሆኑ የታወቀው " ቪዛ አልቆልሃል " ተብሎ 600 ሺህ ብር የከፈለ አንድ ግለሰብ ወደ ካናዳ ሀገር ለመሄድ አየር መንገድ በተገኘበት ወቅት #ቪዛው_ሃሰተኛ መሆኑ ከተነገረው በኋላ ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማ ነው፡፡

አሁን ላይ ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ውሎ ክስ ተመስርቶበታል።

ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ በህግ አግባብ ቤቱ ሲበረበር ሀሰተኛ ሰነዶች እና ሰነዶቹን ለማዘጋጀት ሲጠቀምባቸው የነበሩ ልዩ ልዩ ቁሳቁሶች መገኘታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ ያሳያል።

#AddisAbabaPoliceCommission

@tikvahethiopia
👏1.23K208😭132😡80🙏55😱35😢33🥰32🕊32
Audio
#ለጥንቃቄ⚠️

እንዲህ ካሉ አጭበርባሪዎች ተጠንቀቁ።

ከላይ የምትሰሙት የድምፅ ቅጂ ከአንድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የተላከ ነው።

አጭበርባሪው ደዋይ ግለሰብ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ #ዋናው_ቢሮ እንደደወለ በማስመሰል በኦንላይን ዘረፋ ለመፈፀም ሞክሯል።

የደወለው #የባንክ_ሰራተኛ ጋር መሆኑን አላወቀም ነበር።

ሰራተኛው ግለሰቡ የሚለፈልፈውን ሁሉ እስከ መጨረሻ ድረስ አዳመጠው።

በኃላም የአንድ የባንኩን ቅርንጫፍ ዋና ስራ አስኪያጅ ስምን ይጠይቀዋል።

በዚህ ግዜ ከዋናው መ/ቤት ነኝ ያለው አጭበርባሪ ምን ይዋጠው ? መቀባጠር ይጀምራል።

በመጨረሻ ውርደቱን ተከናንቦ ስልኩን ዘግቷል።

እንዲህ ያሉ የማጭበርበር ስልቶች አንድ ሰሞን እንደጉድ ተበራክተው ነበር። አሁን ደግሞ ሰሞነኛውን የንግድ ባንክን ሁኔታ ተከትሎ እንደ አዲስ ተስፋፍተዋል።

ውድ ቤተሰቦቻችን ፦
* የማታውቋቸው የግል ስልኮችን ባለማንሳት ፣
* #የሚስጥር_ቁጥሮችን ባለመስጠት እራሳችሁን ከአጭበርባሪዎች ጠብቁ። የሚመለከታቸው አካላትም ይህን ነገር እንደ ቀላል ከማየት የማጭበርበር ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች #በደወሉበት_ስልክ ክትትል በማድረግ ወደ ህግ ማቀረብ አለባቸው።

(የድምፅ ቅጂውን ለላከው የቤተሰባችን አባል ምስጋና እናቀርባለን)

@tikvahethiopia
🙏1.25K👏321192😡99🤔69😱57😭42🕊34🥰33😢24
Audio
#ለጥንቃቄ⚠️

" ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት ነው " እየተባለ ወደ ተለያዩ የባንኩ ደንበኞች ስልክ እየተደወለ የግል መረጃ መውሰድና የኦንላይን ዝርፊያ እየተሞከረ ይገኛል።

ቀደም ብሎ አንድ #አጭበርባሪ ግለሰብ (ጾታ - ወንድ) ሳያውቀው ለባንክ ሰራተኛ ደውሎ ያጋጠመውን ክስተት አጋርተናል።

የዜጎችን ሀቅና ገንዘብ አታለው ለመዝረፍ ስልክ ከሚደውሉት መካከል #ሴቶችም ስለሚገኙበት ጥንቃቄ አድርጉ።

ከላይ ባለው የድምፅ ቅጂ የምትሰሟት አጭበርባሪ ግለሰብ (ጾታ-ሴት) ከንግድ ባንክ ዋና መ/ቤት እንደደወለች በማስመሰል ፦ ደንበኞች የሞባይል ባንኪንግ ሲጠቀሙ ኔትዎርኩ please try again ፣ connection problem ፣ error ፣ service not available " የሚል ችግር እየገጠማቸው እንደሆነ ትገልጸለች።

በዚህ ምክንያት ባንኩ ከብዙ ደንበኞቹ ቅሬታ በመምጣቱ ፤ " ችግሩን በዋናው የንግድ ባንክ መ/ ቤት #ሲስተም ላይ ለማስተከል ነው " በማለት የደንበኛውን የግል መረጃዎች በመቀበልና በማታለል ዝርፊያ ለመፈፀም ሞክራለች።

አሁን ላይ እንዲህ ያሉት አጭበርባሪዎች ተበራክተዋል ተጠንቀቁ።

ለማንኛውም #የማታውቁት ስልክ የባንክ መረጃችሁን እንዳትሰጡ።

@tikvahethiopia
🤔810🙏391225😱72😡59👏49😢44🥰34🕊25😭22