TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ትግራይ

አቶ ጌታቸው ረዳ ምን አሉ ?

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ በዛሬው እለት በወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ቃለመጠይቅ ለክልሉ ሚድያዎች ሰጥተው ነበር።

በዚህም ወቅት ፤ የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ተሳትፎውበት ከፌደራል መንግስት ጋር በአዲስ አበባ ስለተካሄደው ውይይትና ውጤት አስመልክቶ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር።

አቶ ጌታቸው ፤ " ለፌደራል መንግስት የስራ አፈፃፀም ሪፓርት አቅርበናል። በአከባቢያችን ያለው ፓለቲካዊ ሁኔታ እጅግ ጥንቃቄ የሚሻ በመሆኑ እንደ አገር የውስጥ ሰላማችን መጠበቅና መንከባከብ እንደሚገባ ከፌደራል መንግስት ጋር መግባባት  ተደርሷል " ብለዋል።

ከፌደራል መንግስት በተካሄደው ውይይት በሃይል ስለተያዙ የትግራይ ግዛቶች መነሳቱ ያብራሩት ፕረዚደንቱ " በተለይ በምዕራባዊ ዞን  በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ሰፋሪዎች በሰፈሩበት፤ የፌደራል ተቋማት ዴሞግራፊ ለመቀየር በሚንቀሳቀሱበትና ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ባልተመለሱበት ፤ መፍረስ የሚገባቸው ሳይፈርሱ ፤ ህዝባችን ነፃ ባልወጣበት ሁኔታ ሪፈረንደም ማድረግ አይቻልም " ሲሉ ተናግረዋል።

በሚቀጥለው ወር መጋቢት የአፍሪካ ህብረት ፣ የተባበሩት መንግስታትና የአሜሪካ መንግስት ተወካዮች በተገኙት የፕሪቶሪያ ስምምነት አተገባበር ላይ ያተኮረ ውይይት ይካሄዳል ያሉት አቶ  ጌታቸው የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ለውይይቱ ስኬት የበኩሉ አስተዋፅኦ ለማድረግ ዝግጁ ነው ብለዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ ህወሓት መልሶ እንደ ፓለቲካ ፓርቲ የመመዝገብ ጉዳይ የሚመለከት ጥያቄም ቀርቦላቸው ምላሽ ሰጥተዋል።

በዚህም፤ ከህወሓት የፓለቲካ ፓርቲነት ምዝገባ ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድን ውሳኔ የፌደራል መንግስት እንደማይደግፈው በመግለፅ ያለው የህግ ክፍተት በአስቸኳይ ታርሞ ምዝገባው እንዲፈፀም ጉዳዩ ወደ ፍትህ ሚኒስቴር ተመርቷል ብለዋል።

መረጃውን የትግራይ ሚድያዎችን ዋቢ አድርጎ ያዘጋጀድ የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
                 
@tikvahethiopia