TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ዓድዋ128 #ዓድዋ ፕሬዝዳንት ሥህለወርቅ ዘውዴ በታሪካዊቷ ከተማ ዓድዋ ለሚከበረው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል ላይ ለመገኘት ትግራይ ክልል ገብተዋል። ፕሬዝዳንቷ መቐለ አሉላ አባነጋ ኤርፖርት ሲደርሱ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ከመቐለ በሄልኮፕተር ወደ ዓድዋ በመጓዝ ላይ መሆናቸው በስፋት እየተነገረ ነው። የዓድዋ በዓል የፌደራል መንግስት ባካተተ መልኩ መከበር የቆመው ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ ነበር።…
#ዓድዋ

128ኛው የዓድዋ ድል በዓል በታሪካዊቷ ዓድዋ ከተማ ፕረዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት እየተከበረ ነው።

በበዓሉ ላይ የመከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ፣ ጄነራል ታደሰ ወረደ፣ ጄነራል ፃድቃን ገብረትንሳይ ፣ የሕወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤልን ጨምሮ ሌሎችም የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ ባለልስጣናት ተገኝተዋል።

በበዓሉ ላይ የአፍሪካ ሕብረት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችም በዓሉን ለማታደም በስፍራው ተገኝተዋል። መኮንኖቹ በበዓሉ ስፍራ ሲደርሱ ከፍተኛ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

በዓድዋ የሚገኘው የቲክቫህ ቤተሰብ አባል በበዓሉ ላይ ከፍተኛ የሰው ቁጥር የታደመበት መሆኑን አመልክቷል።

ፎቶ፦ በቲክቫህ ቤተሰብ አባል እና ትግራይ ቴሌቪዥን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

በታሪካዊቷ ዓድዋ እየተካሄደ ባለው የዓድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ባንዴራ የመስቀል ስነ-ሰርዓት ተካሂዷል።

የኢትዮጵያ፣ የትግራይ ክልል ፣ የአፍሪካ ህብረት ባንዴራ በፕረዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ እንዲሁም የአፍሪካ የሰላም አስከባሪ ተወካይ በሆኑት ሜጀር ጀነራል ስቴፈን ራድያ ተሰቅሏል።

የባንዲራ መስቀል ስነስርዓቱ በኢትዮጵያ 🇪🇹 ህዝብ ብሄራዊ መዝሙር ታጅቦ መከናወኑን በስፍራው የሚገኘው የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ገልጿል።

@tikvahethiopia