TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ... በተደጋጋሚ የማስፈራሪያ ዛቻና ገዳሙን ለቃችሁ ውጡ የሚባሉ መልእክቶች ይደርሱ ነበር " - መጋቤ ካህናት ቆሞስ አባ ሃብተ ጊዮርጊስ አስራት
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የገዳማት አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ መጋቤ ካህናት ቆሞስ አባ ሃብተ ጊዮርጊስ ዓሥራት የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አባቶች ግድያ ዙሪያ ለተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ቃላቸውን ሰጥተው ነበር።
ምን አሉ ?
- ከጥቃቱ በፊትም በተደጋጋሚ የማስፈራሪያ ዛቻና ገዳሙን ለቃችሁ ውጡ የሚባሉ መልእክቶች ይደርሱ ነበር።
➡ " ሁል ጊዜ ዛቻው ልቀቁልን ነው፤ ልቀቁልን ነው የሚሉን። ገዳሙን መነኮሳቱ ለቀው እነሱ ገብተው ሊቀድሱበት ይሁን ፣ሊያስተምሩበት ይሁን ፣ ሊያቆርቡበት ይሁን ምንም አይገባኝም "
- ከዚህ ግድያ ክስተት ቀደም ብሎ የገዳሙ መጠበቂያ መሣሪያና የመናንያኑ እህል በኃይል ተወስዷል። ገዳሙም እንዲራቆት ተደርጓል። የሚመለከተው አካል ለጉዳዩ ትኩረት ካልሰጠ ወደ ፊትም ከዚህ ያልተናነሰ ወንጀል በገዳሙ ሊፈጸም የማይችልበት ምክንያት አይኖርም።
- ምንም እንኳ ለቤተክርስቲያን አባቶች መደብደብ መሰደድና መገደል የነበረ ቢሆንም የአሁኑ ግን መሞታቸው ብቻ ሳይሆን አሟሟታቸውም ዘግናኝ ነበረ አስከሬናቸው እንኳ ተለቃቅሞ እንዲቀበር ነው የሆነው።
- ገዳማትን መጠበቅ የቤተክርስቲያኗ ኃላፊነት ብቻ ሳይሆን የመንግሥትም ኃላፊነት ነው መንግሥት ከፌደራል እስከ ክልል ባሉት የጸጥታ መዋቅሮቹ ገዳማትን እንደማንኛውም ተቋም ሊጠብቅ ይገባል።
- በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ያሉ ምእመናን በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙት የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም መናንያን በገዳሙ ሕጋዊ አካውንት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000011282222 (የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አንድነት ገዳም) ድጋፍ እናድርግ።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃው የተ.ሚ.ማ መሆኑን ይገልጻል።
@tikvahethiopia

ጠንካራ ሴት ለመሆን የሚከፈለውን ዋጋ በደንብ እንረዳለን፣ ህልምዎና ፍላጎትዎ እንዲሳካ የአደይ ቁጠባችን ያግዝዎታል! ባንካችን ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ለሆኑ ሴቶች ያዘጋጀውን አደይ ልዩ የቁጠባ ሂሳብ አቅራቢያዎ በሚገኝ ቅርንጫፍ በመክፈት የልዩ አገልግሎቶቹና ጥቅሞቹ ተጋሪ ይሁኑ።
#BankofAbyssina #WomenSavingAccount #bankinginethiopia #banksinethiopia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ

ፎቶ፦ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድና ባለቤታቸው ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ለ2 ቀናት መንግሥታዊ ጉብኝት ኬንያ ናይሮቢ ገብተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ባለቤታቸው ናይሮቢ በጆሞ ኬንያታ አውሮፕላን ጣቢያ ሲደርሱ በፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
በመቀጠል ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ የወጣቶችን የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ተሳትፎ የሚያሳይ የአይሲቲ ፓርክ ለጠቅላይ ሚኒስትር አስጎብኝተዋል።
መረጃው የጠ/ሚ ፅ/ቤት ነው።
@tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ባለቤታቸው ናይሮቢ በጆሞ ኬንያታ አውሮፕላን ጣቢያ ሲደርሱ በፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
በመቀጠል ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ የወጣቶችን የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ተሳትፎ የሚያሳይ የአይሲቲ ፓርክ ለጠቅላይ ሚኒስትር አስጎብኝተዋል።
መረጃው የጠ/ሚ ፅ/ቤት ነው።
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ፤ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶችን በጨረታ ለሽያጭ ማቅረቡ ይታወቃል። ኮርፖሬሽኑ ከዲዛይን ግንባታ ቢሮ ጋር በመሆን በመንግስት በተመደበ ካፒታል በጀት በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ተገንብተው የተጠናቀቁ ፦ ➡️ 3,146 የመኖሪያ ቤቶችን ➡️ 306 የንግድ ቤቶችን በድምሩ 3,452 ቤቶችን ባሉበት ሁኔታ ነው በጨረታ አወዳድሮ በሽያጭ ማስተላለፍ የፈለገው።…
#Update
የጨረታ መክፈቻው ተራዘመ።
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ከአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ጋር በመተባበር ያስገነቧቸውን 3,452 የመኖሪያና የንግድ ቤቶችን በሽያጭ ለማስተላለፍ የጨረታ ሰነድ በመሸጥ ላይ ይገኛል።
ኮርፖሬሽኑ ፤ ከሕብረተሰቡ መጣልኝ ባለው ጥያቄ መነሻነት የጨረታ መክፈቻ ጊዜው ለ10 ቀናት የተራዘመ መሆኑ አሳውቋል።
በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች እስከ መጋቢት 02/2016 ዓ/ም ድረስ ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 1፡30 እስከ ምሽቱ 1፡30 እንዲሁም እሁድ ከጠዋቱ 1፡30 እስከ ቀኑ 6፡00 በሁሉም ክፍለከተሞች ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በአካል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላል ተብሏል።

በማንኛውም ቦታ ሆነው በግሎባል ሞባይል ተመዝግበው አካውንትዎን ማንቀሳቀስ፣ ክፍያ መፈፀምና ማስተዳደር ይችላሉ፡፡
ግሎባል ሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ ለማውረድ ሊንኩን ጠቀሙ
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.ofss.dgbb
በሚቀርብዎ አማራጮች ያግኙን https://bit.ly/3TkrrXD
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን!
#GlobalBankEthiopia #GBE #SharedSuccess

#Infinix_Hot40
አዲሱ ኢንፊኒክስ 'Hot 40 pro' ስልክ ያለ ሃሳብ የፈለጉትን መተግበሪያ ለመጠቀም የሚያስችል ‘ Ultra speed helio G99’ የተሰኘ ፕሮሰሰር የተገጠመለት በመሆኑ በተጠቃሚዎች ዘንድ ተመራጭ ያደርገዋል!
#InfinixEthiopia #InfinixMobile #Infinix_Hot40 #Infinix_HotSeries

ፍትህ ሚኒስቴር ፤ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲን አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ አውጥቷል።
በዚሁ መግለጫ ፤ የሽግግር ፍትህ የባለሞያዎች ቡድን የተሰጠውን ኃላፊነት በወቅቱ ማጠናቀቁን ገልጿል።
የሽግግር ፍትህ ፖሊሲው የመጨረሻ ረቂቅ ስራ እንዳለቀ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ተልኮ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ በመንግስት እንደሚፀድቅ ተመላክቷል።
(መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

#Ethiopia
" የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ፈራሚዎች በቀጣይ ሳምንታት ከአደራዳሪዎች ጋር ለመወያየት መርሃ ግብር ተይዟል " - የትግራይ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት
የትግራይ ክልል የኮሚኒኬሽን ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ረዳኢ ሓለፎም የካቲት 19/2016 ዓ.ም ምሽት ለትግራይ ቴሌቪዥን በሰጡት መግለጫ ፤ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ውል ሙሉ በሙሉ ባለመተግበሩ ምክንያት የህዝብ ስቃይና ሞት መቆም አልቻለም ፤ ስለሆነም ውሉ በሙሉ እንዲተገበር የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የፌደራል መንግስትና የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ተከታታይ ውይይቶች በማካሄድ ላይ ናቸው ብለዋል።
" ሰላማዊ ፣ ዴሞክራሲያዊና ፓለቲካዊ መንገድ በመጠቀም የትግራይ ህዝብ ጥያቁዎች እንዲመለሱ መስራት ተመራጭ አማራጭ ነው " ያሉት አቶ ረዳኢ ይህንን ታሳቢ በማድግ በሚቀጥሉት ሳምንታት የፕሪቶሪያ የሰላም ውል ፈራሚዎች ከአደራዳሪዎች ለመወያየት መርሃ ግብር ተይዟል ብለዋል።
በትግራይ የተከሰተው ደርቅ ወለድ ረሃብና ሞት አስመልክቶ ከፌደራል መንግስት የነበሩ ልዩነቶች ወደ አንድ ማምጣት እንደተቻለ የገለፁት አቶ ረዳኢ ሓለፎም ፤ የጋራ መፍትሄ ለማበጀት በጋራ እየተሰራ መሆኑ አብራርተዋል።
ሃላፊው አያይዘው እንደገለጹት ፤ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ የካቲት 18 ና 19 /2016 ዓ.ም ለ2 ቀናት ባካሄደው ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎች አስተላልፏል።
ካቢኔው የኢንቨስትመንትና የኤክስፓርት መመሪያ እንዲሁም የአርበኞች ኮሚሽን አሁናዊ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ ተሻሽሎ እንዲተገበርና እንዲቋቋም ወስኗል።
የትግራይ ህዝብ በከባድ ሰው ሰራሽና ተፈጥሮአዊ ችግሮች ውስጥ እያለ ፤ በጊዚያዊ አስተዳደሩና በፀጥታ ሃይል አዛዦች ላይ እየተደረገ ያለው የተቀናጀና የተናበበ የማጥላላት ዘመቻ ያወገዘው ካቢኔው ፤ የትግራይ ህዝብና አመራሩ ከመቼውም ጊዜ በላይ በአንድነት መንፈስ ያጋጠመውን ችግር ለመፍታት እንዲረባረቡ ሲል ጥሪ አቅርቧል።
መረጃውን የትግራይ ቴሌቪዥን ዋቢ በማድረግ አዘጋጅቶ የላከው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።