#ጉጂ
ላለፉት ስምንት ዓመታት የጉጂ አባገዳ በመሆን ያገለገሉት አባ ገዳ ጂሎ ማንዶ ለአዲሱ አባገዳ የ " ባሊ " ስልጣን የማስረከብ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።
በአሁኑ ወቅት በርካታ ህዝብ በአዶላ ከተማ አቅራቢያ " ሜኤ ቦኮ አርዳ ጂላ " በተሰኘው ስፍራ በባህላዊ ትውፊት መሰረት የሚከናወነውን 75ኛውን የስልጣን ርክክብ መርሐ ግብር ለመታደም ተሰባስቧል።
የአበገዳ ስልጣን ርክክብና ተተኪ አበገዳ የመመረጡ ሂደት እጅግ ሚስጥራዊ ከሚባሉት ክንውኖች መካከል አንዱ ሲሆን፤ ተተኪውን አባገዳ የሚታወቀው በመጨረሻው የዕለቱ መርሐ ግብር መቋጫ ላይ ብቻ ነው። #ኢፕድ
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ኢትዮጵያ
እናት ፣ መኢአድ፣ ኢሕአፓ እና አንድ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲዎች ፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኢትዮጵያ ፈራሚ የሆነችበትን የሳሞአ ስምምነት አሁን ባለበት ሁኔታ እንዳያፀድቅ ጥሪ አቀረቡ።
" ግብረሰዶም ከባህላዊና ሃይማኖታዊ እይታ ባሻገር በኢትዮጵያ የወንጀል ህግም በወንጀልነት የተቀመጠ ነዉ " ያሉት ፓርቲዎች ከዚህ አኳያ ግብረሰዶምን በማወቅም ይሁን ባለማወቅ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚያበረታታ ፣ የሚደግፍ ማንኛዉም ተግባር ወይንም ስምምነት ከአገራችን ባህል፣ ወግ፣ ሃይማኖት በተቃራኒ ከመሆኑም ባሻገር የወንጀል ተግባርን ማበረታታትና መደገፍም ጭምር ነዉ ብለዋል።
እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ራሳቸውን ቋሚ ተመጽዋች እና እርዳታ ለማኝ ላደረጉ አገራት የሳሞአ አይነት ድብቅ ተልዕኮ ያላቸው ስምምነቶችን መቃወም ማለት ምን ማለትና የሚያስከትለዉም መዘዝ የት ሊደርስ እንደሚቻል እንረዳለን ሲሉ ገልጸዋል።
ይህም ሆኖ እንደ ሕዝብ ባህላችን፣ እሴታችንና ወጋችንን ጠብቀን በምንከተላቸዉም እምነቶች ከፈጣሪ ትእዛዝ በተቃራኒዉ ባለመቆም ሊከተል የሚችለዉን መዘዝ መጋፈጥ እንደ አገር የምንፈተንበት ትልቅ ፈተና ነው ብለዋል።
ፓርቲዎቹ ፤ " ይህ ፈተና ዛሬ በዚህ መልክ አገራችንን የገጠማት ቢሆንም አገራችን ኢትዮጵያ ከዚህ የላቀ ብዙ ፈተናዎችን በድል አልፋና እዚህ የደረሰች በመሆኗ ዛሬም ሸብረክ ልትል እንደማይገባ አጽንኦት ሰጥተን ልናሳስብ እንወዳለን " ብለዋል።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዉስጡ ትዉልድ አምካኝና አገርና ማንነትን አጥፊ የሆነ ይዘት ያለውን ስምምነት ከተቻለ በዚህ ረገድ የሚነሱ አንቀጾች እንዲወገዱ ወይንም እንዲታረሙ ይህን ማድረግ ካልተቻለ ደግሞ ሙሉ በሙሉ ስምምነቱን እንዳያጸድቅ አሳስበዋል።
(የፓርቲዎቹ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

#GetachewKassa
በይበልጥ " ሀገሬን አትንኳት " ፣ " ውብ አዲስ አበባ " ፣ " የከረመ ፍቅር " በተሰኙት ዘመን አይሽሬ የሙዚቃ ስራዎች የሚታወቀው አንጋፋው ድምፃዊ ጌታቸው ካሳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
ድምፃዊ ጌታቸው ባደረበት ህመም የካቲት 12 ሆስፒታል ውስጥ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
ሀገሬን አትንኳት ...
" የብዙሃን እናት መጠጊያ የምንላት
እማማ ናትና ሀገሬን አትንኳት።
በዓድዋ በማይጨው ጀግኖች የሞቱላት
ህፃን ሽማግሌ የተሰየፈላት
ደመ መራራና ቁጡነት ያለባት
ጎጆዬ ናትና #ኢትዮጵያን ❤ አትንኳት !
ዘርዓይ ደረስ ወንዱ በሮሞ የቆመላት
ጀግኖች በጦር ሜዳ ወጥተው የቀሩላት
እኔም በተጠንቀቅ አለሁሽ የምላት
ጥቁሯን አፍሪካዬን ኢትዮጵያን አትንኳት። "
NB. አንፋጋው ድምፃዊ ጌታቸው የተጫወተው ' ሀገሬን አትንኳት ' የተሰኘው ዘመን አይሽሬ ስራ በአንጋፋው ደራሲና ገጣሚ ጋሽ አበራ ለማ የተፃፈ ነው።

#ጉጂ ላለፉት ስምንት ዓመታት የጉጂ አባገዳ በመሆን ያገለገሉት አባ ገዳ ጂሎ ማንዶ ለአዲሱ አባገዳ የ " ባሊ " ስልጣን የማስረከብ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው። በአሁኑ ወቅት በርካታ ህዝብ በአዶላ ከተማ አቅራቢያ " ሜኤ ቦኮ አርዳ ጂላ " በተሰኘው ስፍራ በባህላዊ ትውፊት መሰረት የሚከናወነውን 75ኛውን የስልጣን ርክክብ መርሐ ግብር ለመታደም ተሰባስቧል። የአበገዳ ስልጣን ርክክብና ተተኪ አበገዳ…
#Update
አባገዳ ጃርሶ ዱጎ 75ኛው የጉጂ ኦሮሞ አባ ገዳ በመሆን ስልጣን (ባሊ) ተረከቡ።
ዛሬ በተካሔደው 75ኛው የጉጂ ኦሮሞ አባ ገዳ ስልጣን ርክክብ መርሀ ግብር አባገዳ ጂሎ ማንዶ ስልጣናቸውን (ባሊ) ለአባገዳ ጃርሶ ዱጎ አስረክበዋል፡፡
በየስምንት አመቱ በሚካሄደው የስልጣን (ባሊ) ርክክብ መርሀ ግብር መሰረት ከገዳ ሀርሙፋ ወደ ገዳ ሮበሌ ሽግግር መደረጉን ኦቢኤን ዘግቧል።

በቅርብ ቀን https://t.iss.one/+BiR6VdrAieQ3NzRk አሳታፊ በሆኑ አዝናኝ የሽልማት ዝግጅቶች ይጠብቁን፡፡
የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ፡ https://t.iss.one/+BiR6VdrAieQ3NzRk
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን!
#GlobalBankEthiopia #OurSharedSuccess #BankInEthiopia #GBE

እንኳን ደስ አላችሁ!
የተረክ በM-PESA 4ተኛ ዙር አሸናፊዎች ሽልማታቸውን ተረክበዋል!
የአዲስ አበባ ልጆች መኪና እና ባጃጁን እጃቸው አስገብተዋል፤
የድሬ ፣የጅግጅጋ እና የካራሚሌዎቹም ሽልማታቸውን ተረክ አድርገዋል!
ሳንሸልማችሁማ አንላቀቃትም!
M-PESA ላይ እንመዝገብ፣ በM-PESA እንገበያይ፣ ቀጣይ እድለኛ አሸናፊዎች እንሁን።
🔗 የM-PESA ሳፋሪኮምን መተግበሪያ በዚህ ሊንክ ያውርዱ፡ https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia
ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም የቻት ግሩፕ @SafaricomETForum እንዲሁም @SafaricomETCare
24/7 መጠየቅ ይቻላል!
#SafaricomET
#FurtherAheadTogether
#MPESASafaricom #TerekBeMPESA

#ኮሬዞን " ሪፈር ብትባልም አምቡላንስ በማጣቷ ምክንያት #መንታ ልጆቿን አጥታለች " - ነዋሪዎች " እኛ አካባቢ ትንንሽ ነገሮችን አጋኖ እና ሌላ አቀላቅሎ የማቅረብ መሠረታዊ ችግሮች አሉ " - አቶ ታደለ አሸናፊ በአዲሱ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ኮሬ ዞን ሳርማሌ ወረዳ የመዋቅር ጥያቄ በሚነሳባቸው ቀበሌዎች የታሰሩ ባለስልጣናት ጭምር ከእስር አለመፈታታቸው እንዲሁም የህክምና አገልግሎት ክፍተት…
“ አዲሱን ሹፌር ሊገድሉት ሲያሳድዱት ሴቶች ቀሚስ አልብሰው ነው የሸኙት ሌሊት ” - የኮሬ ዞን ጤና መምሪያ ቢሮ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን “ በተደጋጋሚ እየፈጸመ ያለውን መዋቀር ጥያቄ ሽፋን በማድረግ በቡኒቲ ክላስተር የወላድ እናቶች ስቃይ ዛሬም ቀጥሏል ” ሲሉ አንድ ነዋሪና የመንግስት ሠራተኛ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
የጉዳዩን አሳሳቢነት አስመልክተው ሰሞኑን ስለተመለከቱት ጉዳይ ሲገልጹም፣ “ ከአልፋጮ ቀበሌ ወ/ሮ ነፃነት ቦጋለ የተባሉ ወላድ እናት ምጥ ተይዘው በአንቡላስ እጦት ምክንያት ወደ ሆስፒታል መድረስ አልቻሉም፡፡ ከብዙ እንግልት በኋላ ወደ ሰገን መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል (ጉማይዴ) ቢደርሱም አልተሳካላትም ” ብለዋል።
“ የሆስፒታሉ ጤና ባለሙዎች የእናት እና የጨቅላውን ሕይወት ለማትረፍ ርብርብ ቢደረግም ከአቅማቸው በላይ በመሆኑ፣ ሕይወታቸውን ለማትረፍ በህዝብ ማመላለሻ መኪና 4,000 ብር ከፍለው ወደ ካራት ሆስፒታል ተልከዋል ” ብለው፣ እናትየዋ በሰላም ቢገላገሉም በአንቡላንስ እጥረት ከፍተኛ እንግልትና ከእጥፍ በላይ ለሆነ የትራንስፖርት ወጪ መዳረጋቸውን አስረድተዋል።
“በቅርቡ ከአልፋጮ ቀበሌ አንዲት እናት አምቡላንስ ባለመኖሩ መንታ ልጆቿን ማጣቷ የሚታወስ ነው” ያሉት መረጃ አቀባዩ፣ “እናቶችን እና ጨቅላ ሕፃናትን ከሞት ለመታደግ መንግስት ፖሊሲ ቀርፆ እየተንቀሳቀሰ ቢሆንም ትኩረት በመነፈጉ የእናቶች ስቃይ እየተባባሰ ቀጥሏል” ነው ያሉት።
አክለውም፣ “የኮሬ ዞን የመንግሥት አካላትም ከማሾፍ እና ከማፌዝ በተጨማሪ አምቡላንሶችን የካድሬ ማመላለሻ በማድረግ በሰው ልጅ ህይወት መቀለዳቸውን ተያይዘዋል” ሲሉ ተችተዋል።
የዞኑ ጤና መምሪያ ቢሮ ምን ምላሽ ሰጠ ?
ጉዳዩን በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው አንድ ስሜ ባይጠቀስ ያሉ የኮሬ ዞን ጤና መምሪያ ቢሮ ባለሥልጣን ፥ ለአካባቢው ነዋሪዎች አምቡላንስ ተሰጥቷቸው እንደነበርና የአጠቃቀም ችግር እንዳለባቸው አስረድተዋል።
ቅሬታ አቅራቢዎቹ፣ “አምቡላንሱን ቀምተውናል። የቀሙን ደግሞ ‘ለምን የክላስተር ጥያቄ አነሳችሁ’ ብለው ነው” ሲሉ ላቀረቡት ወቀሳም፣ “የአንቡላንስ መወሰድ ሌላ፣ የመዋቅር ጥያቄ ሌላ። አይገናኝም” ብለዋል ባለሥልጣኑ።
“3 ቀበሌዎች ትንሽ ከዋና ከተማው ይርቃሉ፣ ለማዘዝም አይመችም በሚል። ተወዳድሮ አንድ ልጅ (የአምቡላንስ ሹፌር) ሲያልፍ፣ ‘አይደለም ማለፍ ያለበት የእኛ ልጅ ነው’ ብለው ፈርመው አመጡ። በ3ኛው ወር ላይ 5 ክላሽ (ሕገወጥ መሣሪያ) በአምቡላንስ ላይ ጭኖ ኮንሶ ላይ ተያዘ። ልጁ በዚሁ ምክንያት ከሥራ ተባረረ” ብለዋል።
አምቡላንሱን ኮንሶ ዞን አልመልስም ቢልም ተከራክረው እንዳስመለሱ፣ አምቡላንሱ ከተመለሰ በኋላም ሌላ ሹፌር ቀጥረው አምቡላንሱን ወደ ቡኒት ክላስተር እንደላኩ፣ይሁን እንጂ ከላኩ በኋላም፣ ወጣቶቹ “አዲሱን ሹፌር ሊገድሉት ሲያሳድዱት ሴቶች ቀሚስ አልብሰው ነው የሸኙት ሌሊት” ሲሉ ከሰዋል።
“ሹፌሩ ቀሚስ ለብሶ ከወጣ በኋላ ቁልፉን ወሰዱና ባለ 5 ክላሽ ጭኖ ለተገኘው ሹፌር ሰጡ። ይሄ ነው ያለው ችግር እንጂ እነርሱን አምቡላንስ የከለከለ የለም” ብለው፣ 2 አምቡላንሶች እንደተመደቡላቸው፣ እዚያ ለማሳደር ዋስትና እንደሌላቸው አስረድተዋል።
ችግሩ እንዲቀረፍ ለምን አታወያዩአቸውም ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽም፣ ሰሞኑንም ውይይት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። ከዚህ በተጨማሪ ለጉዳዩ ምን ምላሽ እንዳለው ለመጠየቅ ወደ ክልሉ ጤና እና ጸጥታ ቢሮ የተደረገው ሙከራ ባለሥልጣናቱ ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ለጊዜው ሀሳባቸውን አልተሳካም።
ዘገባውን የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

#Update " ተማሪዎች ላይ የደረሰ ጉዳት የለም " - የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሁነኛ አካል በአማራ ክልል ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበበ ግዮን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሚገኙ ተማሪዎች ማክሰኞ ጥር 28 ቀን ከምሽቱ 2፡30 ገደማ ታጣቂዎች በካምፓሱ ውስጥ ተኩስ መክፈታቸውን፣ ተማሪዎቹ ከግቢው እንዲወጡም ማስጠንቀቂያ መስጠታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸው፣ የሚመለከተው አካል ሰላም ወዳለበት…
" ዩኒቨርሲቲው የሚጠራም ከሆነ የማይጠራም ከሆነ አቋሙን ያሳወቀን " - ተማሪዎች
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለ2016 ዓ/ም አዲስ ገቢ ተማሪዎች ጥር 21 ቀን 2016 ዓ/ም ያደረገውን ጥሪ ባላወቁት ምክንያት አራዝሞት እንደነበር፣ ይሁን እንጂ ከዚያ ወዲህም “ ኑም ” ሆነ “ አትምጡ ” ባለማለቱና የትምህርት ጊዜው እያገፋ በመሆኑ ጭንቀት ውስጥ መሆናቸው ውሳኔውን እንዲያሳውቃቸው ተማሪዎቹ ዩኒቨርሲቲው ይጠየቅልን ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
አንድ ተማሪ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ “ዩኒቨርሲቲው የሚጠራም ከሆነ የማይጠራ አቋሙን ያሳወቀን” ብሏል።
ተማሪዎቹን ወክሎ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ማብራሪያ የሰጠ ሌለኛው ተማሪ ፤ “ እኛ የ2016 ዓ/ም ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደብን Freshman እና Remedial ተማሪዎች ነን። ነገር ግን አስካሁን ከሌሎች የአማራ ክልል በተለዬ የእኛ ካምፓስ ለተማሪዎቹ ጥሪ አላደረገም ” ሲሉ አማሯል።
ዩኒቨርሲቲው ጥር 21 ቀን 2016 ዓ/ም ጥሪ አድርጎላቸው እንደነበር ያስታወሰው የሁሉንም ተማሪዎች ቅሬታ አቅራቢው፣ “ ባልታወቀ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ እንደተራዘመ ከተነገረን ወር ሊሞላን ነው ” ብሏል።
በመሆኑም፣ መጥራት የሚችሉ ከሆነ ጥሪ እንዲያደርጉ፣ መጥራት የማይችሉ ከሆነ ደግሞ ተማሪዎቹ በመጠበቅ ጊዜያቸውን እንዳያባክኑ እንዲያሳውቁ፣ እንዲሁም በቅርቡ መቅደላአምባ ዩኒቨርሲቲ እንዳደረገው ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ካለ ዩኒቨርሲቲው ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመድባቸው ጠይቋል።
“ ከእነዚህ አማራጮች ውጪ ግን ‘ተማሪዎች ጠብቁ’ የሚል መልስ መስጠት እንደማይቻል ይታወቅልን። ምክንያቱም ከዚህ በላይ ትዕግስት ሊኖረን ስለሚይችል። በዕድሜያችንና በሞራላችን እየተቀለደ ነው ያለው ” ሲልም የተማሪዎቹ ተወካይ አሳስቧል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸው አንድ የዩኒቨርሲቲው አካል በሰጡት ቃል፣ “ ዩኒቨርስቲው አሁን አልጠራም ማለትም አይችልም (ምክንያቱም አልጠራም ቢል ከትምህርት ሚኒስቴር ግዳጅ አለበት)። ጠርቶ እንዳያስገባ ደግሞ አካባቢው ላይ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ኃይሎች እያደረጉ ያሉትን ነገር በዓይናችን እያዬን ነው ” ሲሉ ተማሪዎቹ ዩኒቨርሲቲው አሁንም ይታገሱ እንዲላቸው ሳይሆን ቁርጡን እንዲያሳውቃቸው ላቀረቡት ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።
“ ዩኒቨርሲቲው የማይጠራበት ምክንያት፣ አሁን አካባቢው ላይ ያለው ነገር ጥሩ ስላልሆነ ነው። በጸጥታ ችግር ከጤና እና ከአግሪካልቸር ግቢዎች ለቀው ወደ ፔዳና ፖሊ ካምፓሶች የተደረቡ ተማሪዎች Still ትምህርት አልጀመሩም። አሁን አዲስ ተማሪዎችን ቢጠራ የት ላይ ነው የሚያደርጋቸው? ” ሲሉም ጠይቀዋል።
“ ማስተባበሪያ ክላስ ራሱ ጠቦን እየተቸገርን ነው። የዶርም እጥረት አለ። ተማሪዎቹ ወደዬ ግቢያቸው እስካልተመለሱ ድረስ” ያሉት እኚሁ አካል ፣ “አሁንም ፔዳ (Main campus) ያለው ሁኔታ አስጊ ነው። ‘እስከ ነገ ሐሙስ ‘ለቃችሁ ውጡ’ የሚል ወሬ ስለመጣ ዩኒቨርሲቲው አዲስ ተማሪዎችን መጥራት አይችልም። የመጡት እየተሰቃዩ ነው። እነዚህም መጥተው ከሚሰቃዩ ቢረጋጉ ነው የሚሻላቸው ” ሲሉ አሳስበዋል።
መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

" ዩኒቨርሲቲው የሚጠራም ከሆነ የማይጠራም ከሆነ አቋሙን ያሳወቀን " - ተማሪዎች የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለ2016 ዓ/ም አዲስ ገቢ ተማሪዎች ጥር 21 ቀን 2016 ዓ/ም ያደረገውን ጥሪ ባላወቁት ምክንያት አራዝሞት እንደነበር፣ ይሁን እንጂ ከዚያ ወዲህም “ ኑም ” ሆነ “ አትምጡ ” ባለማለቱና የትምህርት ጊዜው እያገፋ በመሆኑ ጭንቀት ውስጥ መሆናቸው ውሳኔውን እንዲያሳውቃቸው ተማሪዎቹ ዩኒቨርሲቲው ይጠየቅልን…
#BDU
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ እስካሁን ጥሪ ባልተደረገላቸው የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጉዳይ ላይ ከተቋሙ ተጨማሪ ምላሽ አግኝቷል።
በዚህም ተቋሙ ፤ " ተማሪዎቹን ለመጥራት አስቻይ ሁኔታዎች እየተጠበቀ ነው። " ብሏል።
" አሁን ያለው ሁኔታ ተማሪዎቹን ለመጥራት እየተገመገመ ነው። ተማሪዎቹ በትዕግስት ይጠብቁ። " ሲል አሳውቋል።
ተጨማሪ ዝርዝር የምናጋራችሉ ይሆናል።
@tikvahuniversity @tikvahethiopia