TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" የፋይበር ኦፕቲክስ ገመድ ላይ በደረሰ ጉዳት አገልግሎቶች ተቋርጠዋል " - የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ  ፤ በባንኩ መረጃ ማስተላለፊያ የፋይበር ኦፕቲክስ ገመድ ላይ በደረሰ ጉዳት ምክንያት በባንኩ አገልግሎቶች ላይ ማለትም ፦ በቅርንጫፎች፥ በኢንተርኔት ባንኪንግ፥ በሞባይል ባንኪንግ፥ በሲቢኢ ብር የአገልግሎት መቋረጥ እንዳጋጠመ አሳውቋል። ባንኩ በምን ምክንያት ጉዳት…
" ችግሩ ተስተካክሏል " - ንግድ ባንክ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፤ በባንኩ መረጃ ማስተላለፊያ የፋይበር ኦፕቲክስ ገመድ ላይ ተፈጥሮ የነበረው ችግር መስተካከሉን ገልጿል።

በዚህም ፦
በቅርንጫፎች፥
በኢንተርኔት ባንኪንግ፥
በሞባይል ባንኪንግ፥
በሲቢኢ ብር ላይ ተቋርጦ የነበረው አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ መጀመሩን አመልክቷል።

ባንኩ ተፈጥሮ ለነበረው የአገልግሎት መስተጓጎልም ይቅርታ ጠይቋል።

@tikvahethiopia
ወዳጆችዎ ቴሌብር ሱፐርአፕ እንዲጠቀሙ ይጋብዙ፤ ሥጦታ ያግኙ!

ቴሌብር ሱፐርአፕ https://onelink.to/fpgu4m ግርጌ ‘መለያ’ የሚለው አማራጭ ውስጥ ‘ይጋብዙ ይሸለሙ’ የሚለውን በመምረጥ በአጭር መልዕክት ወይም በማህበራዊ ሚዲያ ቴሌብር ሱፐርአፕን ያጋሩ፤ ወዳጆችዎ በመተግበሪያው ግብይት ሲጀምሩ ለእርስዎ የአየር ሰዓት እና ጥቅል የሚገዙበት የ10 ብር ስጦታ እንሸልማለን!

#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia
#AddisAbaba #የተማሪዎችምገባ

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ፤ የውሃና የመሰረተ ልማት አቅርቦቶች በትምህርት ቤቶች ውስጥ ለሚከናወነው የምገባ ሥርዓት ፈተና መሆናቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድቷል።

ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገው የነበረው በአ/አ ት/ት ቢሮ የተማሪዎች ምገባ ባለሙያ አቶ አለሙ ሀይሉ ፥ የምገባ ሥርዓቱ በመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ ትልቁ አጋዥ ነገር እንደሆነ አስረድተዋል።

የሥርዓቱ በት/ቤቶች መኖር ዘርፈ ብዙ ውጤቶች እያመጣ መሆኑን ገልጸዋል።

ነገር ግን በዚህ ሂደት አንዳንድ ተግዳሮቶች እንዳሉ አንስተዋል።

ምንም እንኳን ካሁን በፊት ከነበረው አንፃር ሲታይ በርካታ ለውጦች ቢኖሩም  #የውሃ_አቅርቦት ችግር ተግዳሮት መሆኑን  አመልክተዋል።

በተለይ ምገባ ላይ ብዙ ውሃ እንደሚያስፈልግ የገለፁት አቶ አለሙ ፤ " 5 የምገባ ቀናቶች አሉ (ከሰኞ እስከ ዓርብ) በእነዚህ ቀናት መካከል የውሃ አቅርቦቱ እንደተፈለገ የማይሆንበት ጊዜ አለ " ብለዋል።

ችግሩን ለመቅረፍም አማራጮች እየተወሰዱ መሆኑና ተጨማሪ የውሃ ታንከር ጥቅም ላይ እንደሚውል አስረድተዋል።

አንዳንድ ት/ቤቶችን በተባለው ቀንም አድሬስ ከማድረግ አኳያ ችግሮች እንዳሉ ገልጸው " ከዚያ አኳያ ውሃ ነው መታገዝ ያለበት " ሲሉ አሳስበዋል።

ሌላው በመንግሥት እንዲሁም በዓለም ባንክ የተሰሩ የምገባ አዳራሾች የመብራት አቅርቦት እንዲኖራቸው ከማድረግ ጋር ተያይዞ በተወሰነ ደረጃ ተግዳሮት እንዳለ አመልክተዋል።

ምንም እንኳን የምገባ አዳራሾች ቢኖሩም ምግብ ለማብሰያ የሚሆን #የመብራት_ኃይል አቅርቦት ላይ የተወሰኑ ተግዳሮቶች እንዳሉ ገልጸዋል።

በሌላ በኩል በት/ቤቶች ምገባ ሥራ ተሰማርተው ቤተሰብ የሚያስተዳድሩ ሰዎች በተለይ #ከኑሮ_ውድነቱ አኳያ ሲታይ የሚከፈላቸው ክፍያ " በጣም አነስተኛ ነው " በማለት ሲያማርሩ ይደመጣሉ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ይህንኑ ምሬታቸውን ለመቅረፍ ምን እየተሰራ ነው ? ሲል ጥያቄ አቅርቧል።

አቶ አለሙ ፤ " ከምገባ ክፍያ ጋር ተያይዞ እየቀረበ ያለው በየጊዜው እንደዬ ኑሮ ሁኔታው እየታዬ ይሻሻላል። " ብለዋል።

" ለምሳሌ ያለውን የኑሮ ሁኔታ ማዕከል ያደረገ ጥናት በማድረግ ወደ #23 ብር በተማሪ (በነፍስ ወከፍ) እንዲያድግ ተደርጓል " ሲሉ ገልጸዋል።

" በዚህ ዓመት ለምገባ ፕሮግራሙ መጠቀም ያለባቸው ተብሎ የተመደበው ወደ 3.2 ቢሊዮን ብር ነው " ሲሉ አክለዋል።

" በዚያ ደረጃ የተወሰኑ ማሻሻያዎች እየተደረጉ ይኬዳል ማለት ነው። ሲጀመር (የምገባው ፕሮግራሙ) በ14 ብር ነበር አሁን #23 ብር የደረሰበት ሁኔታ አለ። ለቀጣይ ደግሞ ወቅቱን ባገናዘበ ሁኔታ እየተጠና የሚሻሻልበት አሰራሮች አሉ " ሲሉ አስረድተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህን መረጃ ያገኘው የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ከሳምንት በፊት ከሌሎች ተቋማት ጋር በመሆን የምግብና ሥርዓተ ምግባ ቅንጅታዊ አሰራርን አስመልክቶ የ6 ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ሲያደርግ በነበረበት ወቅት ጥያቄ አቅርቦ ነው።

መረጃው የተዘጋጀው በአ/አ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
" የትግራይና የአማራ ሊህቃን ቆም ብለው ማሰብ አለባቸው " - አቶ ከበደ አሰፋ

የትንሳኤ 70 እንደርታ ፓርቲ ሊቀ መንበር አቶ ከበደ አሰፋ፣ በመቐለ ዙሪያ ስለሚስተዋለው፦
* የመሬት ሊዝ ሁኔታ፣
* ስለወልቃይትና ራያ ተፈናቃዮች፣
* ስለፕሪቶሪያው ስምምነት የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

አቶ ከበደ በመቐለ ዙሪያ የመሬት ጉዳይ ምን አሉ?

70 እንደርታ ውስጥ፣ እንደ አጠቃላይ መቐለና ዙሪያው ያለውን የመሬት ወረራ በልዩ ሁኔታ እንቃወማለን። ይሄ የመሬት ፓሊሲ አርሶአደሩን የሚያደኸይ ነው። ይሄም በተጨባጭ እየታዩ ነው።

የስርዓቱ ሰዎች ከአርሶ አደሩ መሬቱን በጉልበት ይቀማሉ። ለሚፈልጉት ባለሃብት ያቀርባሉ። ከባለሃብቱ የሚፈልጉትን ገንዘብ ይጠይቃሉ። በተለይ ትግራይ ውስጥ ያለው የመሬት ፓሊሲ የኪራይ ስብሳቢነት፣ የሙስና ምንጭ ነው።

በሊዝ ስም መሬት በካሬ በ85,000 ብር ይገዛሉ። ይህን 20፣ 30 ፐርሰንት እየከፈሉ ይወስዳሉ። ይሄ ገንዘብ ከሕዝቡ በሕገ ወጥ መንገድ የተወሰደ ነው። የሕዝብ ሀብት ዘረፉ፣ መልሰው የድሃውን መሬት በመግዛት ሕጋዊ እያደረጉ ነው ያሉት። ምንጩ ግን ሕገ ወጥ ነው። ጭቆናው ድርብ ነው።

ባለን መረጀ መሠረት 1867 አካባቢ መሬት የመጀመሪያው ሊዝ ተዘጋጅቷል፣ በመቐለ ዙሪያ ለምሳሌ ስራዋት፣ እግረወንበር…ብዙ ናቸው። 

ያካተቷቸው አንሷቸው ተጨማሪ 13 ቀበሌዎችን በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ወደ መቐለ አካተው፣ የእንደርታ ህዝብን መሬት ሸጠው ለመበልጸግ ዝግጅት ላይ ናቸው።

ስለተፈናቃዮች ምን አሉ ?

የትግራይና የአማራ ሊህቃን ቆም ብለው ማሰብ አለባቸው። ከምንም ነገር በላይ ለወልቃይትም ሆነ ለራያ ሕዝብም መታሰብ አለበት። ማዶና ማዶ ባሉ ሊህቃን ምክነያት ይህን ሕዝብ የጦር ሜዳ እየሆነ ነው። እየተፈናቀለ፣ የገፈቱ ቀማሽ እየሆነ ያለው ይሄ ሕዝብ ነው።

ስለኘሪቶሪያው ስምምነት ምን አሉ?

- ትግራይ ውስጥ እስቲል #ታጣቂዎች ትጥቃቸውን #አልፈቱም። እኛ መፍታት አለባቸው የሚል አቋም ነው ያለን። ለምን ዓላማ ነው ከነመሳሪያቸው እስካሁን የሚቆዩት ? ሕዝባችን ከዚህ በላይ ጦርነት የመሸከም አቅም የለውም።

- ኢትዮጵያን የመጠበቅ ኃላፊነት ያለበት መከላከያ ሠራዊት ነው። ከዛ በመለስ ያሉ ታጣቂዎች ትጥቃቸውን ይፍቱ። የፕሪቶሪያው ስምምነት አንዱ ይህ ነው። 

- ለምን እንደተቀመጡ አናውቅም ስጋት አለን።

መረጃው በአ/አ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

@tikvahethiopia
#የካቲት12 #ሰማዕታት

የካቲት 12 ጣልያን ኢትዮጵያን በወረረችበት ወቅት በጀነራል ግራዚያኒ ትዕዛዝ  የተጨፈጨፉ ኢትዮጵያዉያን የሚታሰቡበት ነዉ።

የዛሬ 87 ዓመት ግራዚያኒ የተባለዉ የጣሊያን ጀነራል  ከሀገሩ ኢጣሊያ ንጉሳዊያን ቤተሰቦች ዘንድ አንድ ልዑል መወለዱን አስመልክቶ ደስታዉን ለማክበር የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን በአሁኑ 6 ኪሎ ዩንቨርሲቲ በቀድሞዉ ገነተ ልሎል ቤተመንግሥት ሰበሰበ።

በዚህ ወቅት የፋሽሽት ኢጣሊያ ወረራ ያስቆጫቸዉ ሞገስ አስገዶም እና አብርሃ ደቦጭ የተባሉ ሁለት ወጣቶች ከተሰበሰበዉ ሕዝብ መሀል ወጥተዉ ወደ ግራዚያኒ ቦንብ ወረወሩ። 

በዚህም ግራዚያን እና በርካታ ባለስልጣናቱ ቆሰሉ። ይህ ያበሳጨዉ የፋሽስት ኢጣሊያ ጀነራል ግራዚያኒ ያለርህራሄ ኢትዮጵያዉያን እንዲጨፈጨፉ አዘዘ።

ኢትዮጵያውያኑ ሰማዕታት በፋሽሽት ኢጣሊያ የተጨረጨፉት በ1929 ዓ/ም የካቲት 12 ቀን ልክ የዛሬ 87 ዓመት ነበር።

ወጣት አብርሃ ደቦጭ እና ሞገስ አስገዶምን ጨምሮ በሦስት ቀናት ብቻ 30 ሺ ኢትዮጵያዉያን በዕለቱ ተሰውተዋል።

የሰማዕታቱ መታሰቢያ ሀውልት በአዲስ አበባ ከተማ በስድስት ኪሎ አደባባይ ላይ ቆሟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
“ በተጨማሪ ማሽነሪ/ቴክኖሎጂ የታገዘ ሥራ ለማከናወን አልተቻለም ” - የደቡብ ወሎ ዞን ኮሚዩኒኬሽን በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ "018 አለኋት" ቀበሌ በተለምዶ ቆቅ ውኃ እየተባለ በሚጠራ አካባቢ ጥር 30 ቀን 2016 ዓ/ም ሌሊት የኦፓል ማዕድን በቁፋሮ ለማውጣት ሲሞክሩ የነበሩ ከ20 በላይ ወጣቶች የቆፈሩት አለት በመናዱ ያሉበትን አልታወቀም ስለተባሉት ወጣቶች ሁኔታ ቲክቫህ ኢትዮጵያ…
" በፈንጂ እና በድማሚት ቢሞከረም ሊሳካ አልቻለም " - የከበሩ ማዕድናት አምራች ማህበር

ከ12 ቀናት በፊት በደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ፤ የኦፓል ማዕድን ለማውጣት ቁፋሮ ላይ እያሉ ዋሻ የተናደባቸው ሰዎች የሚወጡበት መፍትሔ አሁንም ድረስ አለመገኘቱን የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር እና የከበሩ ማዕድናት አምራቾች ማኅበር ተናግሯል።

ትላንት የመከላከያ ሠራዊት በአካባቢው በመገኘት የዋሻውን የላይኛው ክፍል ለማፍረስ ፈንጂ ቢጠቀምም፤ ሙከራው እንዳልተሳካ የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳደር ገልጿል።

የመከላከያ ሠራዊት መሀንዲሶች በአካባቢው ላይ የተሰማሩ ሲሆን ፤ ዋሻው የሚገኝበትን ቦታ ተመልክተው " ፈንጂ እና ድማሚት " በመጠቀም የዋሻው የላይኛው ክፍል ለማፍረስ ሙከራ ቢያደርጉም አልተሳካም ተብሏል።

የተንጠለጠውን ገደል ለመናድ አልተቻለም።

ይህ ሙከራ ከከሸፈ በኋላ እንዲወገድ የሚፈለገውን የዋሻ ክፍል " በታንክ የመምታት " ሀሳብ ከመሀንዲሶቹ በኩል መቅረቡን የከበሩ ማዕድናት አምራቾች ማኅበር ገልጿል።

ያቺ ቦታ ብትመታ እና ብትናድ ሰዎቹን ቆፍሮ የማውጣት እድል እንደሚኖር ማህበሩ ገልጿል።

ይሁንና " በታንክ መምታት " የሚለው ሀሳብን በተመለከተ እስካሁን ድረስ ውሳኔ ላይ እንዳልተደረሰ ተነግሯል።

የመከላከያ ሠራዊት አባላት መውጫ ያጡትን የማዕድን ቆፋሪዎች ለማውጣት አሁንም በአካባቢው እንደሚገኙ ተገልጿል።

በዋሻው ውስጥ መውጫ ካጡ 12 ቀናት ያስቆጠሩት የማዕድን አውጪዎች ያለ ምግብ " እስካሁን መቆየት ይችላሉ ? " ለሚለው ጥያቄ የከበሩ ማዕድናት አምራቾች ማኅበር አሁንም ተስፋ እንዳለ አመልክቷል።

" ይኖራሉ። እስከ 15 ቀን ድረስ የመቆየት እድል አላቸው። ዋሻው ውስጥ ውሃ ስላለ፤ አፈር በሉ ምንም አሉ ዞሮ ዞሮ የመቆየት እድላቸው አለ " በማለት ግለሰቦቹ በህይወት ይገኛሉ የሚል ተስፋ እንዳለው ማህበሩ ገልጿል።

መረጃው የቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ነው።
ፎቶ፦ የደቡብ ወሎ ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
Addis Ababa University- Cisco Networking Academy,
@CiscoExams www.netacad.com www.cisco.com

Online Live class - Cisco CCNA Professional Networking Course Training & Certification Preparation.

Registration Date: Feb.12 to March 8, 2024
Class start date: March 9, 2024.

Course Recognitions: CCNA trainees will receive 3 Certificate of Completion, 3 Letter of Merit, 3 Digital Badge that recognized and accepted in USA, Canada, and Europe, and you will award 58% CCNA certification exam discount voucher.

Mobile #: 0902-340070/0935-602563/ 0945-039478/
Office : 011-1-260194

Follow our telegram channel: @CiscoExams
#Amhara

በአማራ ክልል በሚስተዋለው የጸጥታ ችግር ከቱሪዝም የሚያገኙት ገቢ በመቀነሱ መነኮሳት ለመፈናቀል መገደዳቸውንና ገዳሙ የሀይቅ ውሃ ሙላት ሥጋት ላይ በመሆኑ ተጀምሮ የነበረውን ግንባታ ማስኬድ አለመቻሉን በባሕር ዳር ጣና ሀይቅ የሚገኘው የመስቀል ክብራ አንጦንስ አንድነት ገዳም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የገዳሙ እመምኔት እማሆይ ወለተ ሥላሴ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገው ነበር።

ምን አሉ ?

መነኮሳት እየተፈናቀሉ ነው። የምንተዳደው በቱሪስት ገቢ ነበር በጸጥታው ችግር ቆሟል።

በወቅታዊ ችግር ምክንያት ቱሪስት የሚባል ነገር የለም። ፍሰቱ ቁሟል። የእርሻ ቦታም የለንም። ገቢ የምናገኘው ሁሌም የቱሪስት እጅ ጠብቀን ነው።

የዕደ ጥበብ ሥራዎቻችንን ሰዎች ለበረከት እያሉ ይገዙ ነበር ይሁን እንጂ ላለፉት 6 ወራት በከፋ ችግር ውስጥ ነን።

ቀና ብንል ሰማይ ነው፣ ዝቅ ብንል ምድር ነው። በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ነው ያለነው።

በገዳሙ 40 መነኮሳት ነበሩ ፤ ነገር ግን 5 መነኮሳት በመፈናቀላቸው በገዳሙ የቀሩት 35 መነኮሳት ብቻ ናቸው። አሁንም ያሉት መነኮሳት ይሰደዳሉ የሚል ሥጋት አለኝ።
 
አጣዳፊ ችግራችን / የሚያስፈልገን የዕለት ቀለብ / የዕለት ጉርስ የዓመት ልብስ ነው። ከዚህ አልፎ የዕደ ጥበብ ውጤቶቻችን ገበያ ላይ ለማዋል ቢችሉ ከድጋፍ ጠባቂነት እንወጣለን።

በሌላ በኩል ፤ ገዳሙ በጣና ውሃ ሙላት በተለይ በክረምት ወቅት ትልቅ ስጋት ስለሚጋርጥበት በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲና በባህልና ቱሪዝም በኩል Proposal ተሰርቶ ዙሪያውን ግንባታ ተጀምሮ እንደነበር፣ ነገር ግን ግንባታ ከሚያስፈልገው 300 ሜትር የተገነባው 65 ሜትር ብቻ መሆኑን፣ በአጠቃላይ ለግንባታው ወጪ ከ12 ሚሊዮን በላይ እንደሚያስፈልግ፣ በዚህም ሁሉም ሰው ርብርብ እንዲያደርግ ተጠይቋል።

የመስቀል ክብራ አንድነት ገዳም በ1314 በፃድቁ አቡነ ዘዮሐንስ የተመሰረተና አቡኑ ለ35 ዓመታት ሲያገለግሉበት የቆዩ ገዳም መሆኑ ተነግሯል።

መረጃው የተዘጋጀው በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
#ጉጂ

ላለፉት ስምንት ዓመታት የጉጂ አባገዳ በመሆን ያገለገሉት አባ ገዳ ጂሎ ማንዶ ለአዲሱ አባገዳ የ " ባሊ " ስልጣን የማስረከብ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።

በአሁኑ ወቅት በርካታ ህዝብ በአዶላ ከተማ አቅራቢያ " ሜኤ ቦኮ አርዳ ጂላ " በተሰኘው ስፍራ በባህላዊ ትውፊት መሰረት የሚከናወነውን 75ኛውን የስልጣን ርክክብ መርሐ ግብር ለመታደም ተሰባስቧል።

የአበገዳ ስልጣን ርክክብና ተተኪ አበገዳ የመመረጡ ሂደት እጅግ ሚስጥራዊ ከሚባሉት ክንውኖች መካከል አንዱ ሲሆን፤ ተተኪውን አባገዳ የሚታወቀው በመጨረሻው የዕለቱ መርሐ ግብር መቋጫ ላይ ብቻ ነው። #ኢፕድ

@tikvahethiopia