TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ🇪🇹 " ... ለሶማሊያ በችግር ጊዜ ብዙ ድጋፍ ያላደረጉ #አንዳንድ_ተዋናዮች ራሳቸውን እንደ እውነተኛ ወዳጆቿ አድርገው ለማሳየት እየሞከሩ ነው " - አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ምን አሉ ? - ኢትዮጵያ ለሶማሊያ #ሰላም እና #ደህንነት ያላትን ቁርጠኝነት በውድ ልጆቿ #ደም እና #ላብ በግልፅ አሳይታለች። - ኢትዮጵያ…
አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፦
" ... ለሶማሊያ #በችግሯ_ጊዜ ብዙ ድጋፍ ያላደረጉ አንዳንድ ተዋናዮች ራሳቸውን እንደ እውነተኛ ወዳጆቿ ለማሳየት እየሞከሩ ነው። ለዚህ ደግሞ ያነሳሳቸው ለሶማሊያ ያላቸው ወዳጅነት ሳይሆን #ለኢትዮጵያ_ያላቸው_ጥላቻ መሆኑ ግልጽ ነው። "
@tikvahethiopia

ፎቶ/ቪድዮ ፦ በኬንያ፣ ናይሮቢ በአፄ ኃይለስላሴ ስም የተሰየመ የፈጣን መንገድ መውጫ ፕላዛ ቅዳሜ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተሰምቷል።
እንደ ኬንያ መገናኛ ብዙሃን መረጃ ፤ በ " ናይሮቢ ፈጣን መንገድ " ላይ የተገነባው የፈጣን መንገድ መውጫ ፕላዛ ከባለፈው ዓመት ሃምሌ 2023 አንስቶ በቻይና እና ኬንያ ተቋራጮች ሲገነባ የቆየ ሲሆን በአካባቢው ላይ ያለውን የትራፊክ ፍሰትን ያቀላጥፋል ፤ ወደ #ናይኖቢ_ከተማ ማዕከል ለመግባትም ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ተብሏል።
ይኸው የኃይለስላሴ የፈጣን መንገድ መውጫ 5 መስመሮች እንዳሉት ተጠቁሟል።
አፄ ኃይለስላሴ #ኢትዮጵያን 🇪🇹 ለረጅም አመታት በንጉሰ ነገስትነት የመሩና የአፍሪካ አንድነት ድርጅት - OAU / የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት - AU እንዲመሰረት ግንባር ቀደም ሚና የተጫወቱ መሪ ነበሩ።

#ትግራይ
ዛሬ ጥር 13/2016 ዓ.ም በትግራይ በርካታ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎች መካሄዳቸው ተሰምቷል።
ሰልፎቹን ያካሄዱት ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎች ናቸው ተብሏል።
ሰላማዊ ሰልፈኞቹ የተደረጉት ፦
* በሸራሮ
* በሽረ
* በአክሱም
* በዓድዋ
* በተምቤን
* በዓዲግራት
* በጉሎመኸዳ
* በኢሮብ
* በመቐለና ልሎች ከተሞች ሰሆን ከጠዋት ጀምሮ በተካሄደ ሰልፍ የተለያዩ መፈክሮች ሲሰሙ ነበር።
በተለይ ከምዕራባዊ ትግራይ ሙሉ በሙሉ ፣ ከተወሰኑ ሰሜናዊ ምዕራብ ፣ ማእከላይ ፣ ምስራቃዊና ደቡባዊ ዞኖች መፈናቀላቸው የሚናገሩት ሰልፈኞቹ " ወደ ቤታችን መልሱን " ብለዋል።
ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ፦
➡ የፕሪቶሪያው ውል ሙሉ በሙሉ በአስቸኳይ ይተግበር !
➡ የፌደራልና የጊዜያዊ መንግስቱ አስተዳደሮች ሃላፊነታቸው ይወጡ !
➡ ሰርተን ለፍተን እንድንኖር ወደ ቤታችን መልሱን !
➡ የትግራይ ግዛታዊ አንድነት ይከበር !
➡ በምግብና በመድሃኒት እጦት እየተገረገፍን ነው !
➡ ከጥይት የተረፍን ድምፅ በሌለው ጥቃት እያለቅን ነው !
➡ ሰብአዊ እርዳታ ይሰጠን !
የሚሉና ሎች መፈክሮችን በመያዝ የየከተሞቹን አደባባዮች በመዞር ድምፃቸው አሰምተዋል።
በሰልፎቹ ከህፃን እስከ አዛውንት የሚገኙባቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃይች መሳተፋቸው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ከተለያዩ የትግራይ ከተሞች ያሰባሰባቸው መረጃዎች ያመለክታሉ።
በሽረ እንዳስላሰ ከተማ በተካሄደው ስልፍ የተሳተፉ አንዲት ከትግራይ ምዕራባዊ ዞን የተፈናቀሉት እናት ፤ " የእንጀራ መሰቦቻችን ባዶ ናቸው ፤ የሚበላ የሚጠጣ ስጡን ፤ መንግስት ለአይኑ ጠልቶናል ፤ ያስጠለሉን ለራሳቸው ስለተራቡ ለእኛ መስጠት ማካፈል አቆቶችዋል ፤ አድኑን ! " ብለዋል።
በሽረ ከተማ የተካሄደው ስልፍ ተሳታፊዎች ለምግባረ ሰናይ ድርጅቶች ፣ ለትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፣ ለትግራይ ዳያስፓራ ማህበረሰብ ፣ ለፌደራል መንግስትና ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በሚል ርእስ ባሰራጬት ፅሑፍ ማጠቃለያ " የፕሪቶሪያ ውል ሙሉ በሙሉ ይተግበር ! በምዕራባዊ ዞን ህዝብ ላይ በመካሄድ ያለው ድምፅ የሌለው እልቂት ይቁም ! " ብለዋል።
ይህ መረጃ እስከተዘጋጀበት ጊዜ ድረስ ሰልፎኞቹን ተቀብሎ ያነጋገረ የመንግስት ሃላፊና ተወካይ እንደሌለ የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ገልጿል።

#AddisAbaba #Exam ለአዲስ አበባ አስተዳደር አመራሮች ፣ ባለሞያዎች / ሠራተኞች የተሰጠውን የቴክኒክ እና ባህሪ ብቃት ፈተና የማለፊያ ነጥብ አምጥተው ያለፉ #የክዋኔ_ክህሎት ስልጠና ይሰጣቸዋል ተብሏል። የማለፊያ ነጥብ ማምጣት ሳይችሉ ቀርተው #ያላለፉት ደግሞ #የአቅም_ግንባታ_ስልጠና እንደሚሰጣቸው ተጠቁሟል። በተጨማሪ የማለፊያ ውጤት ያላመጡት ዝቅ ብለው እንደሚመደቡ ፤ አሁን ላይ #ስንብት…
#አዲስአበባ
ዛሬ 3,854 የመንግሥት ሰራተኞች ፈተና ተቀምጠዋል።
ዛሬ ለባህሪና ብቃት ምዘና ፈተና የተቀመጡት ፦
- የአዲስ አበባ መሬት ይዞታ ቢሮ፣
- የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ
- የከንቲባ ፅ/ቤት (ማለትም የ3 ተቋማት) ዳይሬክተሮች፣ ቡድን መሪዎች፣ ሰራተኞች እና ባለሙያዎች ናቸው።
ፈተናው በአዲስ አበባ ዩኒቪርስቲ በ6 ኪሎ ካምፓስ ውስጥ እየተሰጠ ይገኛል።
ከዚህ ቀደም 15,151 የአስተዳደሩ አመራሮች፣ ሠራተኞች / ባለሞያዎች (የ13 ተቋማት) የቴክኒክና ባህሪ ብቃት ፈተና መውሰዳቸውና ውጤቱም ይፋ መደረጉ ይታወሳል።
ፈተናውን ከወሰዱ 4,213 አመራሮች ያለፉት 1,422 መሆናቸው እንዲሁም ፈተናውን ከወሰዱ 10,257 ባለሞያዎች / ሠራተኞች ያለፉት 5,095 መሆናቸው መገለፁ አይዘነጋም።
የማለፊያ ነጥብ አምጥተው ላለፉ የክዋኔ ክህሎት ስልጠና እንደሚሰጥ ፤ የማለፊያ ነጥብ ማምጣት ሳይችሉ ቀርተው ያላለፉት ደግሞ የአቅም ግንባታ ስልጠና እንደሚሰጣቸው መነገሩ ይታወቃል።
በተጨማሪ ፤ የማለፊያ ውጤት ያላመጡት ዝቅ ብለው እንደሚመደቡ ፤ አሁን ላይ #ስንብት የሚባል ነገር እንደሌለ ፤ ስንብት የሚፈፀመው መጨርሻ ላይ ሁሉ ነገር ከተጠናቀቀና ሌላ አማራጭ ከጠፋ ብቻ መሆኑን የከተማው አስተዳደር ማሳወቁ ይታወሳል።