TIKVAH-ETHIOPIA
የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 2 ቀን 2014 ዓ.ም ይሰጣል። የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 2 ቀን 2014 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን አገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጄንሲ አስታወቀ። የአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጄንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ፤ የ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ…
#Update
ከ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና #በወረቀት እንደሚሰጥ የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ለ @tikvahuniversity ገልጿል።
የኤጀንሲው የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ረዲ ሽፋ በ @tikvahuniversity በኩል ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽ በሰጡበት ወቅት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናው በወረቀት እንደሚሰጥ ገልፀዋል።
አቶ ረዲ ፤ በዘንድሮው ፈተና የኢኮኖሚክስ የትምህርት አይነት እንደማይኖር የገለፁ ሲሆን የመልቀቂያ ፈተናው ከትግራይ ክልል በስተቀር በሁሉም ክልሎች ይሰጣል ብለዋል።
በተለያዩ ቦታዎች ተፈናቅለው የሚገኙ ተማሪዎችን በተመለከተም ለተነሳላቸው ጥያቄ ፥ "ሁኔታው ተጠንቶ ወደ ፊት አቅጣጫ ይቀመጣል" የሚል ምላሽ ሰጥተውናል።
ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ : t.iss.one/joinchat/RYD_4tbNBwRoKR2h
@tikvahethiopia

Photo
" ከመስከረም 7 እስከ 10/ 2016 የማካካሻ (Remedial) ትምህርት ፈተና ይሰጣል " - ትምህርት ሚኒስቴር
ትምህርት ሚኒስቴር የማካካሻ (ሬሜዲያል) ፈተና ከመስከረም 7 እስከ 10/ 2016 እንደሚሰጥ ለሁሉም የመንግሥት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ አሳውቋል።
ፈተናው በ30 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚከናወን ይሆናል።
የሚሰጠው ፈተና የማካካሻ ትምህርታቸውን አጠናቀው ከሰኔ 26 እስከ 30/2015 ዓ.ም የተሰጠውን የማዕከል ፈተና ላልወሰዱ ተማሪዎች መሆኑ ተገልጿል።
ሚኒስቴሩ ፤ ከመስከረም 7- 10/2016 ዓ.ም ከማዕከል የሚሰጠው ፈተና #በወረቀት የሚሰጥ መሆኑን አሳውቋል።
በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስደው ውጤታቸው ከ50 % በታች ሆኖ ወደከፍተኛ ትምህርት መግባት ያልቻሉ እና በአንጻራዊነት የተሻለ ውጤት የነበራቸው ወደ 200ሺ የሚጠጉ ተማሪዎች በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአንድ ሴሚስተር የማካካሻ ትምህርት መውሰዳቸው ይታወቃል።
የማካካሻ (ሬሜዲያል) ፈተና የሚሰጠው ተማሪዎቹ በተቋማት እና በማዕከል የሚሰጠውን ምዘና ወስደው በሚያስመዘግቡት ውጤት መሠረት ከ2016 ዓ.ም ፍሬሽማን ተማሪዎች ጋር የከፍተኛ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ነው።
#MoE