TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ትግራይ - ያልመከኑ የጦር መሣሪያዎች !

" መቐለ ወደ #ስድስት_ቦታዎች አሁን ራሱ ያልመከኑ ቦንቦች አሉብን። … እስካሁን ድረስ ሞትና አደጋ 1,038 ነው በቢሯችን የያዝነው " - የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ

ባለፉት 2 አመታት የነበረው ከፍተኛ ጦርነት በግንባር ብቻ ሳይሆን በትግራይ ክልል ውስጥ ባሉ የተለያዩ ቦታዎች ላይም ስለተካሄደ አርሶ አደሮችን ጨምሮ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ህፃናትና የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ባልመከኑ የጦር መሣሪያዎች ሞትና የአካል ጉዳት አደጋዎች እየደረሱባቸው መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከትግራይ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ ሰምቷል።

የትግራይ ጤና ቢሮ ፤ የድንገተኛ ሕክምና አስተባባሪ አቤንዘር እፀድንግል (ዶ/ር) ስለ ጉዳዩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲያስረዱ፣ " በትምህርት ቤቶች፣ በሕዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎች፣ መቀሌ ወደ ስድስት ቦታዎች አሁን ራሱ ያልፈነዱ ቦንቦች አሉብን፣ ያልተነሱ ማለት ነው " ያሉ ሲሆን፣ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረቡላቸው የተለያዩ ጥያቄዎችም ማብራሪያዎች ሰጥተዋል።

ያልመከኑት የጦር መሣሪያዎች #መቐለ የት የት ቦታዎች ይገኛሉ ?

- አንደኛው #ከፕላኔት_ጀርባ አካባቢ ነው።

- ሁለተኛው ቦታ የህፃናት መጫወቻ ስፍራ የተመታበት #የአፄ_ዮሐንስ_ቤተመንግሥት_ጀርባ በኩል ነው።

- ሦስተኛው #05 አካባቢ ነው።

- ሌሎቹ ደግሞ መቐለ ውስጥ ሆነው ግን #እርሻ ቦታ ላይ ነው ያሉት።

በርግጥ በኅብረተሰቡ ላይ #አደጋን_እንደሚያደርሱ የሚገልፅ ምልክት (አጥር) ተደርጓል ግን በከፍተኛ ጥንቃቄ እና በባለሙያ መነሳት አለባቸው " ብለዋል።

ባልመከኑ የጦር መሣሪያዎች ምን ያህል ሰዎች ላይ ሞትና የአካል ጉዳት ደረሰ ?

" ሁሉንም ወደ ጤና ተቋማት አምጥተን ለማከም ሁኔታው አልተመቸም ነበር። ስለዚህ ሙሉ ዳታ የለንም።

ሙሉ ዳታ አባባሌ አንዳንዶቹ አደጋ ደርሶባቸው የሞቱ አሉ፣ ሌሎች መምጣት ያልቻሉ ብዙ ሰዎችም እንዳሉ ግምት ውስጥ ማስገባት አለብን። ባልፈነዱ የጦር መሣሪያዎች ፣ በተጣሉ ተተኳሽ እና የተቀበሩ ቦንቦች አደጋ የደረሰባቸው ባለን ዳታ መሠረት ፦

- እስካሁን ሞትና አደጋ በአጠቃላይ 1,038 ነው ያለን በእኛ በቢሯችን የያዝነው። #163 ሞት፣ 875 ደግሞ ከባድ ጉዳት ማለት ነው።

- ከ163ቱ መካከል 84ቱ ዕድሜአቸው ከ17 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናት፣ 79ኙ ደግሞ ዕድሜአቸው ከ18 በላይ የሆኑ አዋቂዎች ናቸው።

- ከ84 #ህፃናት ውስጥ 75ቱ ወንዶች፣ 9ኙ ደግሞ #ሴቶች ናቸው ብለዋል።

ችግሩ አሁንም እንደቀጠለ ነው ? አሁንም የሚመጡ አሉ ?

- አዎ አሁንም ድረስ ይመጣሉ። በተለይ ክረምት ላይ በእርሻ ሥራ መቀሳቀስ ስለሚኖር፣ በመነካካትም ሳያውቁ እያረሱ እያለ መፈዳት ያጋጥማቸው ስለነበሩ ቁጥሩ እየቀነሰ ቢሄድም አልፎ አልፎ እየመጡ ነው። ምክንያቱም በተጠናከረ ደረጃ አልተጠረገም። 

- ፈንጅ ነገሮችን የማጥራት ሥራ ካልሰራን ትልቅ ችግር ነው ያለው። የመንግሥት ተዋጊ አካሎች ትምህርት ቤቶችን እንደ አውደ ማቆያ ሲጠቀሙባቸው ስለነበር እዛ ላይ የተጣሉ ጦር መሳሪያዎች አሁን ትምህርት ሲጀምሩ #ህፃናት በተለያየ ጊዜ አደጋ ይደርስባቸዋል።

- በተለያዩ መንገዶች ሰው ተሸክሟቸው ፣ በጋሪ ፣ በፈረስ ፣ በበቅሎ ሕክምና ቦታ መድረስ የቻሉ ሰዎች እንኳ (በተለይ ደግሞ ሽረ አካባቢ የመጡ ብዙ ታካሚዎች) መድኃኒት በበቂ ሁኔታ ስላልነበረ የጤና ተቋማት በቂ ሕክምና ሊሰጧቸው ባለመቻላቸው ብዙ ያጣናቸው አሉ።

- አካል ጉዳተኞችም ሆነዋል ሕክምና ቢደረግላቸው መትረፍ እየቻሉ ግን የሰርጀሪ እቃዎች እጥረት ስለነበረ አካል ጉዳተኛ የሆኑት በርከት ያሉ ሰዎች ናቸው። በአጠቃላይ በነበረው ሁኔታ ከባድ ነበር ግን አሁን ባለዉ ሁኔታ በተቻለ መጠን ባለን አቅም አገልግሎት እየሰጠን ነው።

ከመድኃኒት እጥረቱ ጋር በተያያዘ የአካል ጉዳተኛ የሆኑ ሰዎችን በቁጥር ደረጃ መግለፅ እችላለን ?

- በቁጥር እንኳ ያስቸግራል፣ ግን እኔ የማስታውሳቸው ወደ ሦስት #ህፃናት በአንድ ወቅት ገብተው የሕክምና እቃዎችን ማግኘት ስላልተቻለ ለአካል ጉዳት ተጋልጠዋል። ይህ በአንድ ወቅት ብቻ ነው። በተጠና መልኩ ግን ብዙ ሊሆኑ ይችላሉ በቁጥር ደረጃ አጋጣሚ አልያዝነውም።

ምን ተሻለ ?

- አንደኛ ከሁሉ በላይ በመጀመሪያ እንዲህ አይነት መሣሪያዎችን መነካካት እንደሌለባቸው ህፃናት፣ ማኅበረሰቡ ማወቅ እንዳለባቸው ትምህርት መሰጠት አለበት።

- የፈንጅ #አምካኝ ባለሙያዎች በስፋት በማሰማራት በእያንዳንዱ ቦታዎች ተሰብስበው ያልመከኑ የጦር መሣሪያዎች መወገድ አለባቸው ፤ በየአካባቢው በጣም በርከት ያሉ #ያልተነሱ ፈንጂዎች አሉብን።

- ከተነሱ ነው በዘላቂነት መፍትሄ የሚገኘው። ሕዝብ ባለበት ቦታ ምንም አይነት ጦርነት አለማካሄድ ላለማካሄድ የሚደነግጉ መርሆዎችም መከበር አለባቸው። የህዝብ መገልገያ ቦታዎች ለወታደራዊ አላማ አለማዋል እንሰ እሪኮመዴሽንም መወሰድ አለበት።

ዘገባው በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የተላከ ነው።

@tikvahethiopia
#መቐለ

" የሰሌዳ ቁጥር የሌላቸው ተሽከርካሪዎች ዋነኛ የፀጥታ መደፍረስ መነሻና ለትራፊክ ወንጀል መቆጣጠር አስቸጋሪ ሆኖውብኛል " - የመቐለ ከተማ ትራፊክ ፓሊስ

የመቐለ ከተማ የትራፊክ ፓሊስ መምሪያ ሃላፊ ኢንስፔክተር ሃይለስላሴ ተኽሉ ለ104.4 የመቐለ ኤፍኤም ሬድዮ በሰጡት ቃል ፤ የሰሌዳ ቁጥር የሌላቸው ተሽከርካሪዎች ዋነኛ የፀጥታ የትራፊክ አደጋ መፈጠር መነሻ ሆነዋል ብለዋል። 

በአሁኑ ጊዜ ማንኛውም ተሸከርካሪ የሰሌዳ ቁጥር ሳይኖረው እንዳይንቀሳቀስ የሚያግድ መመሪያ መውጣቱ ተከትሎ ያለ ሰሌዳ ቁጥር የሚንቀሳቐሱ ተሸከርካሪዎች ቁጥራቸው የቀነሰ ቢሆንም ፤ በክልሉ ያለው የሰሌዳ ቁጥር የመስጠት እጥረት ችግሩ ሙሉ በሙሉ እንዳይቀረፍ እንቅፋት መፍጠሩን ገልፀዋል።

የሰሌዳ ቁጥር እያላቸው ሆን ብለው ሰሌዳቸው ፈትተው የሚያሽከረክሩ አሽከርካሪዎች እንዳሉና ፤ ለምንና እንዴት እንደዚህ እንደሚያደርጉ የመከታተልና የማጣራት ስራ እየተሰራ ነው ያሉት ኢንስፔክተሩ  የሰሌዳ ቁጥር ሳይኖራቸው ወንጀልና የትራፊክ ጥሰት ሲፈፅሙ ተከታትሎ ለመያዝ አደጋች እንደሆነ አብራርተዋል።  

የትራፊክ ደንብ ጥሰት የፈፀመ ተሽከርካሪ በተቆጣጣሪ የትራፊክ ፓሊስ ባለውና በተለመደው አሰራር የህግ ተገዢ የሚያደርግና የሚያስተምር ቅጣት ለመቅጣት አንድ እንጂ ሁለቱ ሰሌዳ ቁጥሮቹ አይፈቱም ያሉት ኢንስፔክተሩ ፤ ያለ ሰሌዳ ቁጥር ሲንቀሳቀሱ ተገኝተው ሲጠየቁ ትራፊክ ፈታብኝ ብለው የሚያመሃኙት ልክ እንዳልሆነ በመገንዘብ ህዝቡ በመቆጣጠርና ለሚመለከተው የህግ አካል ጥቆማ በመስጠት የበኩሉ እንዲወጣ አሳስበዋል። 

በከተማዋ ያለ መንጃ ፍቃድና በተጭበረበረ የሃሰት (ፎርጅድ) መንጃ ፍቃድ ማሽከርከር በዚህ ላይ ፍጥነት ተጨምሮበት ከጊዜ ወደ ጊዜ ከባድ የሆነ የትራፊክ አደጋ በመበራከት ላይ እንደሆነ  የጠቀሱት ሃላፊው : ይህንን መልክ ለማስያዝ ህብረተሰብ ያሳተፈ ስራ በመሰራት ላይ ነው ማለታቸው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ሬድዮ ጣቢያውን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።
                                      
@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#መምህራን #ትግራይ " ጥያቄያችን የመኖር ጥያቄ ነው ፤ መሰረታዊ የመምህራን ጥያቄ በአግባቡ ይመለስ ፤ እጅግ ተቸግረናል የ17 ወራት ውዙፍ ደመወዛችን ይከፈለን " ሲሉ የእንዳ ስላሰ ሽረ ከተማና አከባቢዋ መምህራን  በሰላማዊ ሰልፍ ጠየቁ። መምህራኑ " መሰረታዊ ጥያቄዎቻችን " ያሉዋቸው እንዲመለሱላቸው ታህሳስ 7/2016 ዓ.ም በሰላማዊ ሰልፍ ጠይቀዋል።  መነሻቸው ሽረ ስታድዮም በማድረግ በከተማዋ…
#ትግራይ #መቐለ #መምህራን

" ባዶ ሆዳችሁን ስሩ የሚል መጨረሻ የሌለውና ለመቀበል የሚከብድ ስለሆነብን ነው ስራ ያቆምነው " - መምህራን

በመቐለ ከተማ በመንግሥት ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ መምህራን ፤ " 17 ወራት ውዙፍ ደመወዛችን ካልተከፈለን አናስተምርም " ብለው የስራ ማቆም አድማ አድርገዋል።

ተማሪ ሄመን ሰለሙን በመቐለ ሓወልቲ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የሓየሎም መለስተኛ ትምህርት የ8ኛ ክፍል ተማሪ ስትሆን ፤ ታህሳስ 13 /2016 ዓ.ም በትምህርት ቤትዋ የወላጆች በዓል ከተከበረ በኃላ ከትምህርት መአድ መስተጓጎሏን ተናግራለች።

ምክንያቱ ደግሞ የትምህርት ቤትዋ መምህራን " 17 ወራት ዉዙፍ ደመወዛችን ካልተከፈለን አናስተምርም " ብለው የስራ ማቆም አድማ በማድረጋቸው ነው።

የተማሪ ሄመን ሰለሙን አስተያየት በመቐለ የመንግስት ትምህርት ቤቶች የሚማሩ በ10 ሺዎች  የሚቆጠሩ ተማሪዎች ይጋሩታል።

ተማሪዎቹ ትምህርት ካቆሙ ቀናት ተቆጠረዋል።

እንደ ተማሪ ሄመን የመሰሉ በ10 ሺህ የሚቆጠሩ ተማሪዎች ፤ በከተማው በግል ትምህርት ት/ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች ጠዋት ተንስተው ወደ እውቀት ገበያ ሲያመሩ በማየት አዝነው ሲበሳጩ የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የቤተሰብ አባል ታዝቧል።

የስራ ማቆም አድማ ያደረጉ መምህራም ፤ " ባዶ ሆዳችሁን ስሩ የሚል መጨረሻ የሌለውና ለመቀበሉ የሚከብድ ስለሆነብን ነው ስራ ያቆምነው " ብለዋል።

ጉዳዩን በተመለከተ ለመቐለ ኤፍ ኤም ቃሉን የሰጠው የመቐለ ከተማ አስተዳደር ፤ " መምህራኑ ጥያቄያቸው ሳይሆን ፤ ለጥያቄያቸው መፍትሄ ብለው የወሰዱት እርምጃ ጎጂ ነው " ብሎታል።

የተማሪ ወላጆች በበኩላቸው ፤ " መምህራኑ ጥያቄ ማንሳታቸው እንደ ችግር የሚቆጥር ባይሆንም ፤ የነገ አገር ተረካቢ የሆኑ ህፃናት ተማሪዎች በመቅጣት ጥያቄያቸው ለመፍታት መፈለጋቸው ግን የከፋ የስህተት መንገድ ነው " ብለዋል።

ምሁራን ፤ " መምህራኑ ስለ ደመወዛቸው መጠይቅ ብቻ ሳይሆን የህፃናት ተማሪ ልጆቻቸው ቀጣይ አድልም ከግምት ማስገባት ነበረባቸው " ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል።

በመቐለ ከተማ በሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶች የሚያስተምህሩ መምህራን ስለወሰዱት ስራ የማቆም እርምጃ የክልሉ ትምህርት ቢሮ መግለጫ አሰጣለሁ ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ተከታትሎ ያቀርባል። 

ታህሳስ 7/2016 ዓ.ም ፤ " ጥያቄያችን የመኖር ጥያቄ ነው ፤ መሰረታዊ የመምህራን ጥያቄ በአግባቡ ይመለስ ፤ እጅግ ተቸግረናል የ17 ወራት ውዙፍ ደመወዛችን ይከፈለን " በማለት  የእንዳ ስላሰ ሽረ ከተማና አከባቢዋ መምህራን  በሰላማዊ ሰልፍ መጠየቃቸው መዘገባችን ይታወሳል።

መረጃው ከመቐለ ኤፍ ኤም ሬድዮ እና ከመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የተላከ ነው።
                                   
@tikvahethiopia            
#መቐለ

የስፖርት ውርርድ (ቤቲንግ) ቤቶች በመቐለ ከተማ እንዲዘጉ እየተደረገ ነው።

በመቐለ የቤቲንግ ቤቶች ከቅዳሜ ታህሳስ 20/2016 ዓ.ም ጀምሮ ተዘግተዋል።

ጨዋታው የፀጥታ አካላት በከተማዋ ሁሉም አከባቢዎች እየዞሩ ነው እንዲዘጋ ያዘዙት።

የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል በቤቲንግ መጫወቻ ቤቶች ስለተወሰደው የመዝጋት እርምጃ ምክንያት የተጣራ መረጃ ለማግኘት ጥረት ቢያደርግም ለጊዜው አልተሳካም። ጥረቱ ግን ይቀጥላል። 

የፀጥታ አካላት በቤቲንግ ቤቶች ላይ የወሰዱት የመዝጋት እርምጃ የህዝቡ አስተያየት ምን እንደሚመስል የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል በማህበራዊ የትስስር ገፅ የታዘበው አጋርቷል።

ዮናታን ግዛቸው የተባሉ የመቐለ ነዋሪ የቤቲንግ ቤቶችን መዘጋት በተመለከተ ፅፈው ባሰራጩት ፅሁፍ አንዳንዶች እርምጃውን ሲደግፉ አንዳንዶች ደግሞ ተቃራኒ ሀሳብ ሰጥተዋል።

ገብረሂወት ተኽላይ የተባሉ አስተያየት ሰጪ " ወጣቱ ጊዜው በስራ እንዳያውል ጠምዶ የሚይዝ መጥፎ ሱስ ነው። ስለሆነም የተወሰደው እርምጃ ተቀባይነት አለው " ብለዋል። 

ቅዱስ ዜናዊ መለስ የተባለው ወጣት ደግሞ " ወጣቱ ካለበት ችግር ሰርቶ እንዳይለወጥ ቁጭ አድርጎ የሚያስውል መጥፎ ልማድ ነው። ቢሆንም ግን ለወጣቱ የሚሆን የስራ እድል ካልተፈጠ የቤቲንግ ጨዋታን በመዝጋት የሚመጣ ለውጥ አይኖርም። " ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።

መሰረት ታደሰ የተባሉ ነዋሪ ደግሞ ፤ " ከመዝጋት ጨዋታው በህጋዊ መንገድ ተነጋግሮ መቀጠል ነው የሚመረጠው " ብሏል።

" አስገደድዶ ተጫወት የሚል አለ ወይ ? " ብሎ በመቃወም የቤቲንግ ጨዋታ እንዲቀጥል አስተያየት የሰጠው ደግሞ ዲጀ ናቲ የተባለ የመቐለ ነዋሪ ነው።

የቤቲንግ ቤቶች በመቐለ ከተዘጉ ዛሬ ሁለተኛ  ቀናቸው ይዟል። አጫዋቾች ይከፈታሉ በሚል አሁንም ተስፋ አልቆረጡም።

የፀጥታ አካሉ ቤቲንግ ቤቶቹ ለጊዜው ነው የዘጋቸው ወይስ ለዘላቂ የሚለው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተከታትሎ የሚያቀርብ ይሆናል።
                                      
@tikvahethiopia            
#መቐለ
 
ከነገ ጀምሮ ለሚቀጥሉት 3 ቀናት በመቐለ ከተማ የኤሌትሪክ አገልግሎት በተለያዩ የከተማዋ አከባቢዎች ይቋረጣል።

አገልግሎቱ የሚቋረጠው በስራ ምክንያት ነው ተብሏል።

የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አገልግሎት የትግራይ ቢሮ በደብዳቤ እንዳስታወቀው ፤ ከጥር 3 እስከ ጥር 5 ቀን 2016 ዓ.ም ሦስት ተከታታይ ቀናት  በመቐለና አከባቢዋ በተለያዩ ከፍለ ከተሞች የኤሌክትሪክ ሃይል ይቋረጣል ብሏል።

መ/ቤቱ በደብዳቤው አክሎ እንደገለፀው ፤ የኤሌክትሪክ ሃይል አስተላላፊ አዳዲስ  ፓሎች ለመተክልና ለጥገና በማለም አገልግሎቱ ስለሚቋረጥ ህዝቡ ሁኔታውን አውቆ አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርግ ማሳሰቡ የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ ዘግቧል። 

በሌላ በኩል ፤ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በትግራይ በሁለት ቢሊዮን ብር ወጪ የኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎት የማስፋፍያ ፕሮጀክት በማከናወን ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የትግራይ ቢሮ የኮሙኒኬሽን ሃላፊ አቶ ግርማይ ግደይ እንዳሉት ፤ የእንጨት ፓሎት ወደ ኮንክሪትና አዳዲስ ትራንስፎርመሮች የመተካት ስራ ጨምሮ በሁለት ቢሊዮን ብር የኤሌክትሪክ ሃይል የማሻሻያ ፕሮክጀት በመከናወን ላይ ነው ብለዋል።

የማሻሻያ ፕሮጀክቱ በ14 ማህበራት ለተደራጁ 1500 ወጣቶች የስራ እድል መፍጠሩ ኃላፊው አክለው ገልፀዋል።
                                      
@tikvahethiopia