TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.9K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አስቸኳይ_ጊዜ_አዋጅ_ቁጥር_6_2015_በተመለከተ_ከኢትዮጵያ_ሰብአዊ_መብቶች_ኮሚሽን_ኢሰመኮ_የተሰጠ_ምክረ.pdf
916.4 KB
#EHRC

" የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6/2015 " በተመለከተ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የላከው ምክረ ሃሳብ በዚህ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የታሰሩት የምክር ቤት አባላት የት ናቸው ? በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተያዙ የም/ቤት አባላት ታስረውበት ከነበረው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የማቆያ ቦታ እንደሌሉ እና ያሉበትን ቦታ ማወቅ እንዳልቻሉ ከጠበቆቻቸው አንዱ ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት በሰጡት ቃል ተናግረዋል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እንዲሁም በምክር ቤቱ የመንግሥት ወጪ፣ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ…
#EHRC

አዋሽ አርባ ላይ ታስረው የሚገኙ አብዛኞቹ እስረኞች ለእስር የተዳረጉት #በብሔር ማንነታቸው ብቻ መሆኑን እንደሚያምኑ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለን ጨምሮ 5 የኮሚሽኑ ባለሙያዎች የሚገኙበት ቡድን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሠረት በቁጥጥር ሥር ውለው አዋሽ አርባ አካባቢ በሚገኘው የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የምዕራብ ዕዝ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፕ ውስጥ ተይዘው የሚገኙትን ታሳሪዎች ነሐሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. ጎብኝቷል።

እነዚህ ታሳሪዎች ፦
- የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ፣
- የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ዮሐንስ ቧያለው፣
- የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባል የሆኑት ዶ/ር ካሳ ተሻገር፤
- ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው፣ ጋዜጠኛ አባይ ዘውዱ፣ እና ቴዎድሮስ ዘርፉ፤
- የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባል አቶ ስንታየሁ ቸኮል፣ አቶ በለጠ ጌትነት፤
- በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ በኃላፊነት ይሠሩ የነበሩት አቶ ከፋለ እሱባለውን ጨምሮ በአጠቃላይ 53 ወንድ እስረኞች ሲሆኑ ከአዲስ አበባ ከተማና ከአማራ ክልል የተለያዩ ቦታዎች በተለያየ ጊዜ ተይዘው ከነሐሴ 15 ቀን እስከ ነሐሴ 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ ወደ አዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ የሚገኝ ጊዜያዊ / መደበኛ ያልሆነ ማቆያ ጣቢያ የተወሰዱ ናቸው፡፡

ኮሚሽኑ በተለመደው አሠራሩ መሠረት ታሳሪዎቹን ለብቻቸው አነጋግሯል፣ ቦታውን ጎብኝቷል እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸውን የፖሊስ ኃላፊዎች አነጋግሯል፡፡

የፖሊስ ኃላፊዎች ለኮሚሽኑ እንደገለጹት ፤ ታሳሪዎችን ወደዚህ ጊዜያዊ ማቆያ ጣቢያ ማምጣት ያስፈለገው አዲስ አበባ የሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ ማቆያ ጣቢያ ላይ ከፍተኛ መጣበብ በመፈጠሩ መሆኑን ገልጸዋል።

ታሳሪዎች ምን አሉ ?

እጅግ አብዛኛዎቹ ታሳሪዎች ብሔራቸው #አማራ፣ እምነታቸው ኦርቶዶክስ ክርስቲያን መሆኑንና ለእስር የተዳረጉት ደግሞ #በብሔር ማንነታቸው ብቻ መሆኑን እንደሚያምኑ ገልጸዋል።

ከፊሎቹ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተያዙበትና ቤታቸው በተበረበረበት ወቅት በራሳቸውና በቤተሰብ አባል ላይ ድብደባ፣ ብሔር ተኮር ስድብ፣ ማጉላላት፣ ዛቻና ማስፈራራት እንደደረሰባቸው ሆኖም በፌዴራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር ከሆነ በኋላ የተፈጸመ ድብደባ ወይም አካላዊ ጥቃት አለመኖሩን አመልክተዋል።

ከፊሎቹ በተለይም ከአማራ ክልል ተይዘው የመጡ ሰዎች ከተያዙበት ጊዜ ጀምሮ ቤተሰቦቻቸው የት እንዳሉ እንኳን እንደማያውቁ አስረድተዋል።

ታሳሪዎቹ የአዋሽ አርባ አካባቢ እጅግ ከፍተኛ ሙቀት ያለው በመሆኑና ከአካባቢው የአየር ጠባይ እንዲሁም ቦታው የወታደራዊ ካምፕ እንጂ መደበኛ የተጠርጣሪዎች ማቆያ ስፍራ ስላልሆነ ለጤንነታቸው፣ ለደኀንነታቸውና ለሕይወታቸው ሥጋት እንዳላቸው፣ አልባሳትን ጨምሮ ከቤተስብ የሚፈልጉትን አቅርቦት ለማግኘት እንዳልቻሉ፣ ከፊሎቹ በሥራቸውም ሆነ በግል ሕይወታቸው ፈጽሞ በፖለቲካ ነክ ጉዳይ ተሳትፎ እንደሌሉና እንዴት ለእስር እንደበቁ መገረማቸውንና መደንገጣቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ፤ ከፖሊስ ኃፊዎች ጋር ውይይት ያደረገ ሲሆን በእስር ወቅት ተፈጽመዋል ስለተባሉ የሥነ ምግባር ጥሰቶች ተገቢው ማጣራት እንዲደረግ፣ ታሳሪዎቹ ከቤተሰብ ለሚፈልጉት አቅርቦት አዲስ አበባ በሚገኘው የፖሊስ ቢሮ አማካኝነት እንዲመቻች፣ ከቤተስብ መገናኛ ስልክና ጉብኝት ለሚፈልጉም በአፋጣኝ እንደሚመቻች መግባባት ላይ ተደርሷል።

(ከኢሰመኮ የተላከልን መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#EHRC

" ቀድሞውኑ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ለዓመታት በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ አስቸጋሪ ሕይወት ይመሩ የነበሩ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች #ለሞት እና #ለአካል_ጉዳት መዳረጋቸው አሳሳቢ ነው " - ራኬብ መሰለ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በሶማሊ እና በኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ አካባቢ፣ በሁለቱ ክልሎች የጸጥታ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ የተኩስ ልውውጥ ምክንያት በአካባቢው የተጠለሉ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች እና የአካባቢው ነዋሪዎች መጎዳታቸው ዛሬ ባወጣው መግለጫ ይፋ አድርጓል።

ኮሚሽኑ ፤ መስከረም 7 ቀን 2016 ዓ.ም. በባቢሌ አቅራቢያ በኦሮሚያ እና በሶማሊ ክልል የጸጥታ ኃይሎች መካከል የተፈጠረውን የተኩስ ልውውጥ በተመለከተ ተጎጂዎችን፣ የኦሮሚያ እና የሶማሊ ክልል የጸጥታ አካላትን፣ የቆሎጂ መጠለያ ሠራተኞችን እና የሆስፒታል ባለሞያዎችን አነጋግሯል።

በአሁኑ ወቅት ግጭቱ የቆመ ቢሆንም፤ በተኩስ ልውውጡ ወቅት " ቆሎጂ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ " የሚኖሩ ቢያንስ 6 ተፈናቃዮች ተገድለዋል፣ በርካታ ሰዎች ቆስለዋል እንዲሁም በሌሎች የአካባቢው ሲቪል ሰዎች ላይ የሞት እና የአካል ጉዳት ደርሷል ብሏል።

ስለዚህም ሁለቱ ክልሎች በቅንጅት በመሥራት በአካባቢው ለተከሰተው ግጭት ምክንያት ለሆኑ ጉዳዮች ሰላማዊ መፍትሔ በመስጠት የነዋሪዎችን እና የተፈናቃዮችን ደኅንነት በዘላቂነት የማረጋገጥ ሥራ እንዲሠሩ፣ ለደረሰው ጉዳት ተጎጂዎች እንዲካሱ እና ተገቢ የሆነ ጥንቃቄ ባለማድረግ በሲቪል ሰዎች ላይ ጉዳት እንዲደርስ ባደረጉ የጸጥታ ኃይሎች አባላት ላይ አስፈላጊው ምርመራ ተደርጎ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ ያስፈልጋል ሲል አሳስቧል።

የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተፈጠረው ግጭት ወቅት በሲቪል ሰዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ የነበረባቸው መሆኑን ጠቅሰው “በተለይም ቀድሞውኑ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ለዓመታት በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ አስቸጋሪ ሕይወት ይመሩ የነበሩ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ለሞት እና ለአካል ጉዳት መዳረጋቸው አሳሳቢ ነው " በማለት ገልጸዋል።

ምክትል ዋና ኮሚሽነሯ አክለውም " በአፍሪካ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ጥበቃ እና እገዛን አስመልክቶ የተደረገው የአፍሪካ ሕብረት ስምምነት (ካምፓላ ስምምነት) መሠረት የመንግሥት የጸጥታ አካላት የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሚገኙባቸውን የመጠለያ ጣቢያዎች ደኅንነት አደጋ ላይ ሊጥሉ ከሚችሉ ተግባራት ሊቆጠቡ ይገባል " ብለዋል፡፡

@tikvahethiopia
#EHRC

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ፤ ለተፈናቃዮች መቅረብ የጀመረው የምግብ ድጋፍ ተፈናቃዮች የሚገኙበትን አሳሳቢ ሁኔታ በሚመጥን ደረጃ ሊጠናከር ይገባል ብሏል ዛሬ በላከልን መግለጫ።
 
ኮሚሽኑ የምግብ ድጋፍ አቅርቦት ወቅቱን የጠበቀ፣ በቂ፣ ተደራሽ እና የሕፃናትን ፣ ሴቶችን፣ አካል ጉዳተኞችንና አረጋውያንን ልዩ ፍላጎት ያገናዘበ ሊሆን እንደሚገባ አስገንዝቧል።

(ከኢሰመኮ የተላከልን ዝርዝር መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#EHRC

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለይም አዲሱ የክልል አደረጃጀት ተከትሎ የተለያዩ አስተዳደሮች እና መዋቅሮች መልሶ መቋቋም ወይም ተያያዥ ውሳኔዎች ሂደት ጋር የሚነሱ የደመወዝ መዘግየት እና ያለመከፈል የተመለከቱ አቤቱታዎችን፣ እንዲሁም ጥቆማዎችን መነሻ በማድረግ የሰብአዊ መብቶች ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል።

ይህ በተመለከት ከላይ የተያያዘውን መግለጫ ልኮልናል።

@tikvahethiopia