TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
በትግራይ ያሉ አባቶች የፊታችን ሐምሌ 9 ቀን 2015 ዓ/ም በቅድስት ከተማ አክሱም ፅዮን የኤጲስ ቆጾሳት ምርጫ ለማድረግ ዝግጅት ላይ መሆናቸው ተሰምቷል። በክልሉ ለሚገኙ ሚዲያዎችም በስነስርዓቱ ላይ እንዲገኙ ጥሪ መቅረቡን ለማወቅ ተችሏል። በትግራይ ያሉ አባቶች ከማዕከል በመነጠል " የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤቤተክርስቲያን የመንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ከፍተኛ ቤተ ክህነት " በሚል እየተንቀሳቀሱ…
#EOTC

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ሐምሌ 5 እና 6 ቀን 2015 ዓ/ም አስቸኳይ ስብሰባ ማካሄዱ የታወቀ ሲሆን ይህን ከስብሰባው መጠናቀቅ በኃላ መግለጫ ሰጥቷል።

ቅዱስ ሲኖዶስ በመግለጫው :-

በትግራይ በሚገኙ አህጉረ ስብከት የተመደቡ አባቶች የቅዱስ ሲኖዶስ የሰላም ጥሪን ቸል ከማለት ባሻገር ሐምሌ 9 እናደርገዋለን ያሉት የኤጲስ ቆጶስነት ምርጫ ሕገ ቤተክርስቲያንን ያልተከተለ መሆኑን ገልጾ የሚመለከታቸው አካላት ሂደቱን በማስቆም ከቤተክርስቲያን ጎን እንዲቆሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን አቅርቧል።

ይደረጋል የተባለው የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን አንጻር ተገቢ ያልሆነ የቤተ ክርስቲያንን ማዕከላዊነት የሚጥስ፣ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት የሚጎዳና በጦርነት የተጎዳውን ሀብት ንብረቱ የወደመበትን ገዳማቱና አብያተ ክርስቲያናቱ የተጎዱበትን ሕዝብ የማይጠቅም ተገቢነት የሌለው በመሆኑ እንዲቆም ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

በትግራይ ክልል ተከስቶ የነበረውን ችግር የፌዴራል መንግሥትና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ችግሩን በውይይት የፈቱት መሆኑ እየታወቀ የሰላም ባለቤት የሆነችው ቤተ ክርስቲያን እስካሁን ሰላም መፈለጓ ያልተቋረጠ ቢሆንም አለመሳካቱ የሚያሳዝን በመሆኑ ለሰላም የሚደረገው ጥረት ዘላቂ መፍትሔ እስከሚገኝ ድረስ የማይቋረጥ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ገልጿል።

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ክቡር አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት እንዲሁም የፌዴራልና የክልሉ መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እየተደረገ ያለውን ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ያልተከተለ የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ እንዲያስቆሙ ብሎም ሰላም ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት በመደገፍ ችግሮቹ በውይይት እንዲፈቱ መንግሥታዊ እገዛ በማድረግ የውይይት መድረክ እንዲያመቻቹ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥሪውን አቅርቧል።

ቅዱስ ሲኖዶስ፤ " በመላው ዓለም የምትገኙ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና ሕዝበ ክርስቲያን እናት ቤተ ክርስቲያናችሁ ያስተላለፈችውን የሰላም ጥሪ ተግባራዊ ሆኖ አንድነቷ ጸንቶ ይኖር ዘንድ በጸሎት ተግጋችሁ ከቤተ ክርስቲያናችሁ ጎን እንድትቆሙ " ሲል ጥሪ አስተላልፏል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#EOTC

ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በክልል ትግራይ ጉዳይ ከተናገሩት ፦

" የኢፌዴሪ መንግሥት  ትናንት ተፈጥሮ በነበረው የቀኖና ቤተ ክርስቲያን ጥሰት ችግር (ኦሮሚያ ላይ) በውይይትና በምክክር  በከፍተኛ ኃላፊነት እንዲፈታ ማድረጉን ይታወሳል።

አሁንም በትግራይ  ክልል ባሉ የአህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳትና ሊቃውንት እየተከተሉት ያለውን መፍትሔ የማይሆነውን ችግር  በማስቆምና ሰላማዊ የውይይት መድረኮችን በማመቻቸት የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ እምነታችን ነው።

ይህ ካልሆነ ግን በታሪክ የቤተ ክርስቲያንን አንድነትን ማን ከፋፈለ ሲባል የፌደራልና የክልሉ መንግሥት የሚል የታሪክ ተወቃሽ ሆኖ በታሪክ የሚመዘገብ ይሆናል።

ስለሆነም ይህን በትግራይ ክልል ይፈጸማል የሚባለውን ከቀኖና ቤተ ክርስቲያንና ሕገወጥ የሆነ ሹመት እንዲቆም ብሎም ችግሮች በውይይት እንዲፈቱ በማመቻቸት ታሪካዊ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ ቤተ ክርስቲያን ታሳስባለች። "

(ብፅዕ አቡነ አብርሃም የሰጡት ቃል ከላይ ተያይዟል)

በትግራይ ያሉ ብፁአን አባቶች በትግራይ ከነበረው ጦርነት ጋር በተያያዘ ከማዕከል ተነጥለው " የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ከፍተኛ ቤተ ክህነት " በሚል እየተንቀሳቀሱ መሆኑ ይታወቃል።

በቅርቡ በኣክሱም በተካሄደው ስነስርዓት ለዛው ለትግራይ የሚመደቡ 5 እንዲሁም ለውጭ ሀገር 5 በድምሩ 10 የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ አካሂደው የነበረ ሲሆን በቀጣይ ሹመት ይሰጣሉ ተብሏል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ቅዱስ ሲኖዶስ በኣክሱም የተካሄደው ምርጫ አሁን እየተደረገው ያለው የሹመት እንቅስቃሴ ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን አንጻር ተገቢ ያልሆነ የቤተ ክርስቲያንን ማዕከላዊነት የሚጥስ፣ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት የሚጎዳና ሕገወጥ ድርጊት መሆኑን በመግለፅ #እንዲቆም እያሳሰበ ነው።

የፌዴራል መንግሥት እና የትግራይ አስተዳደር የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ፦ ዛሬ የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልአተ ጉባኤ ስብሰባ በጸሎት ተከፍቷል። " የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ በክልል ትግራይ ባሉ አህጉረ ስብከት ለመንፈሳዊ አገልግሎት ተመድበው የነበሩ አራት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በፈጸሟቸው የቀኖና ቤተክርስቲያን እና የሕግጋተ ቤተክርስቲያን ጥሰቶች ዙሪያ ለመወያየትና ሕግጋተ ቤተክርስቲያንን መሠረት ያደረጉ ውሳኔዎችን ለማሳለፍ ጉባኤውን…
#EOTC

የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ፅህፈት ቤት ዛሬ በተረጋገጠው የማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ ፤ " ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፤ ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ/ም በተጠራው አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ሊያቀርቡት የነበረው አባታዊ ቃለ በረከት " በሚል 6 ገጾች ያሉት መልዕክት አሰራጭቷል።

በዚህ ቅዱስነታቸው " ሊያቀርቡት ነበር " በተባለው መልዕክት ዙሪያ / ለምን እንዳልቀረበ  ዝርዝር መረጃ ፅ/ቤቱ አልሰጠም።

ከቅዱስነታቸው አባታዊ ቃለበረከት የተወሰደ


" በትግራይ ክልል ጦርነት ወቅት በጦርነቱ ውስጥ ላሉ ብፁዓን አባቶች፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ እንዲሁም ምእመናን ድምፅ መሆን አልቻልንም።

በትግራይ ክልል ያለው ታሪክና ገዳማት የቤተ ክርስቲያናችን የታሪክ መነሻ ሆነው ሳለ ከአክሱም ጽዮን ጀምሮ በመላ ትግራይ ስለ ተፈጸመው እልቂት፣ ስለ ገዳማቱ መፍረስ፣ ስለ ቅርሶች መውደም አልተቆጨንም፣ ድምጽም አልሆንም።

አንዳንድ አባቶችም በጊዜያዊ ስሜት ተነሳስተው ለተናገሩት ይቅርታ እንዲጠይቁ ለማድረግ ወይም ንግግራቸው ስህተት ነው ብለን መግለጫ ለመስጠትም አልፈቀድንም።

እኔም የሁሉም አባት እንደመሆኔ መጠን የትግራይ ክልል ሕዝብም ሕዝባችን ስለሆነ እና ቤተ ክርስቲያንም እንዳትወቀስ በማሰብ ከአንድም ሦስት ጊዜ በአጀንዳ ተይዞ እንድንነጋገርበት ለቋሚ ሲኖዶስ ሀሳብ ባቀርብም ተቀባይነት አላገኘም፡፡

የአባትነት ኃላፊነት ስላለብኝ ይህ ሁሉ ግፍና በደል እየተፈጸመ ዝም ማለት የለብኝም ብዬ በሚድያዎች ድምጼን ለማሰማት ብፈልግም ፈቃድ አልተሰጠኝም፡፡

በዚህ መሃል ባገኘኋት አጋጣሚ ' በዓለም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በትግራይ ክልል ግፍ እየተፈጸመ ነው፣ ሕዝቡ እየተጨፈጨፈ ነው፤ ገዳማትና አድባራት እየፈራረሱ ነው፣ ቀሳውስትና መነኮሳት በቤተ መቅደስ ውስጥ ሳይቀር እንደ ዘካርያስ በጭካኔ እየተገደሉ ነው፣ መተኪያ የማይገኝላቸው ቅርሶቻችንም እየወደሙ ነው... ' በማለት የተሰማኝን ኃዘን ገለጽኩ፣ መግለጫዎችንም በተደጋጋሚ ሰጠሁ፡፡

በማግስቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የሃገሪቱን ሚድያዎችን በይፋ በመጥራት፡- ' በፓትርያርኩ የተሰጠ መግለጫ የግላቸው እንጂ ቅዱስ ሲኖዶስን ወይንም ቤተ ክርስቲያንን አይወክልም ' የሚል መግለጫ ሰጡ፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስም ድርጊቱን በዝምታ ከማለፍ ውጪ ምንም ተግሳጽ ስላላስተላለፈ የትግራይ ክልል ሊቃነ ጳጳሳትና ሕዝቡ ወደ ከፍተኛ ቅሬታ እንዲገቡ ምክንያት ሆኗል። "

(የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ፅ/ቤት ያሰራጨው የቅዱስነታቸው ሙሉ መልዕክት ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ጾመ ፍልሰታ እና የቅዱስ ፓትርያርኩ መልዕክት ! በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፤ " የጾመ ፍልሰታ " መልዕክት አስተለልፈዋል። ከመልዕክታቸው የተወሰደ ፦ " . . . እንደ እግዚአብሔር ቃልም እንደ አባቶቻችን ትውፊትም የጾመ…
#EOTC

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፤ እግዚአብሔር ለኢትዮጵያ ሰላምን ይሰጥ ዘንድ ክርስቲያኖች ከመጠላላት ርቀው #በፍቅር እንዲኖሩ እና #ሰላማውያን እንዲሆኑ አሳሰቡ።

ቅዱስ ፓትርያርኩ ይህንን ያሳስቡት ዛሬ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም የጾመ ማርያም ሱባኤ ማጠናቀቂያ በዓል ላይ ነው።

ቤተክርስቲያንኗ ፤ " በኢኦተቤ በዐዋጅ ከተደነገጉት አጽዋማት መካከል አንዱ የሆነውና የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ዕርገተ ሥጋ አስመልክተው ሐዋርያት የጾሙት ጾመ ማርያም በየዓመቱ በወርሓ ነሐሴ ከመባቻው አንስቶ ባሉት 16 ቀናት ካህናት እና ምእመናን ሌሊት በሰዓታት ጸሎት፤ ቀን በሥርዓተ ቅዳሴ በመሳተፍ በሕብረት ያሳልፉታል " ብላለች።

" በዚህ በጾመ ማርያም ወይም በተለምዶ የፍልሰታ ጾም ተብሎ በሚታወቀው ወቅት በርካታ ምእመናን እንዲሁም ሕጻናት በቤተ ክርስቲያን ተገኝተው ሥርዓተ ቅዳሴውን ይከታተላሉ፤ ቅዱስ ሥጋው ክቡር ደሙን ይቀበላሉ " ስትል ገልጻለች።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ  ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖትም በዚህ ሕጻን ዐዋቂው፤ ወንድ ሴቱ የክረምት ብርድ እና ዝናብ ሳይበግረው በሕብረት በሚጸልበት የሱባኤ ወቅት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በመገኘት ሥርዓተ ቅዳሴውን በመምራት እና ምእመናንን በመባረክ ማሳለፋቸውን ተገልጿል።

ቅዱስነታቸው በዛሬው ዕለት ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋር  በገዳሙ ተገኝተው በዓሉን ያከበሩ ሲሆን በቅዳሴው መካከል ባስተላለፉት ትምህርትና ቃለ ቡራኬ " የሰላም ባለቤት የሆነው ልዑል እግዚአብሔርን ለኢትዮጵያ ሰላምን ይሰጥ ዘንድ ክርስቲያኖች ከመጠላላት ርቀው በፍቅር እንዲኖሩ እና ሰላማውያን እንዲሆኑ አሳስባለሁ " ብለዋል።

ቅዱስ ፓትርያርኩ በሱባኤው ወቅት የሀገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክተው አባታዊ የሰላም ጥሪ ማስተላለፋቸው የሚታወስ ነው፡፡ 

መረጃ እና ፎቶ ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ/ጽ/ቤት የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሀገሪቱ ያሉ ችግሮች በውይይት እና በስምምነት እንዲፈቱ በድጋሚ ጥሪ አቀረበች። ይህ ጥሪ የቀረበው ቅዱስ ሲኖዶስ የጥቅምት 2016 ዓ/ም ጉባኤውን ካጠናቀቀ በኃላ ባወጣው መግለጫ ነው። ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ " ትላንት በሰሜኑ ኢትዮጵያ የሀገራችን ክፍል በተካሄደው ጦርነት በጠፋው የሰው ሕይወትና በወደመው ንብረት ከደረሰብን ሐዘን እኛ ኢትዮጵያውያን…
#EOTC

ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  ቅዱስ ሲኖዶስ በሁሉም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስቲያናት በሙሉ ከህዳር 15 ቀን 2016 እስከ ታህሣሥ 27 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ ጸሎትና ምሕላ እንዲፈጸም መወሰኑ አይዘነጋም።

ይህንን በተመለከተ ዛሬ ቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ሰጥቷል።

ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬ መግለጫው ፤ ቤተክርስቲያን ሰላም ያሳጡን ጦርነቶችና ግጭቶች ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኙና በአጭሩ እንዲቋጩ ጥሪዋን ታስተላልፋለች ፤ እምቢ ባዮችንም ታወግዛለች ዘላቂ መፍትሄ የሚገኝባቸውን ሂደቶችንም ትቀይሳለች ብሏል።

ከዚህ በተጨማሪም ቅድስት ቤተክርስቲያን የጥላቻና ሀሰተኛ ትርክቶችን እንደምታወግዝ አስገንዝቧል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ " የአሁኑ ጸሎተ ምኅላ የሚደረገው ፦
- አለመግባባት በምክክር፣  በውይይት፣ በመደማመጥ እንዲፈታ፤
- መከራን በመረዳዳት እንድንሻገር፣ እንደየ ኃላፊነታችን የሚጠበቅብንን ለመወጣትና የሕዝባችንን ጥያቄ ለመመለስ እንድንችል፣ ችግራችን ሁሉ ተፈትቶ ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ ከሃሊው አምላክ እንዲያግዘን በአንድነት ለመጮኽ ነው፡፡ " ብሏል።

የጾም፣ የጸሎትና የምኅላ አዋጁ ዓለማው መንፈሳዊ ብቻ እንደሆነ ያስገነዝበው ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ የሚድያ፣ የትምህርትና የፍትሕ፣ መሰል ተቋማት ይህንን በመረዳት በሚያስፈልገው ሁሉ እንዲተባበሩ በቅድስት ቤተክርስቲያን ስም አሳስቧል።

(ተጨማሪ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia