TIKVAH-ETHIOPIA
" ምእመናንና ቱሪስቶች በተለያዩ የትግራይ አከባቢዎች ባጋጠመው ድርቅ የተጎዱ ወገኖችን ባላቸው አቅም ያግዙ " - የአክሱም ከንቲባ አክሱም እንግዶቿን አክብራ እየተቀበለች ነው። የህዳር ፅዮን በዓል ለማክበር ወደ አክሱም የሚሄድ ሰው በቆየው ትውፊት መሰረት በወጣቶች እግሩ እንዲታጠብ ይደረጋል። ይህ ተግባር የእንግዳ ተቀባይነት መገለጫ ነው። የዘንድሮ የህዳር ፅዮን በዓል ለማክበር ወደ አክሱም ያቀኑ…
ፎቶ፦ የ2016 ዓ/ም የአክሱም ፅዮን ንግስ በዓል እጅግ በድመቀ ሁኔታ ተከብሯል።
የዘንድሮው በዓል ጦርነት እንዲቆም የሰላም ስምምነት ከተፈረመ ወዲህ ሁለተኛው ሲሆን ካለፈው አመት የበለጠ ቁጥር ያለው ምዕመን በዓሉን መታደሙ ተነግሯል።
ወደ ከተማው የገቡ ቱሪስቶችም ካለፈው ዓመት የተሻለ ነው።
የፎቶ ባለቤቶች ፦ ሚካኤል መታፈሪያ እና ትግራይ ቴሌቪዥን
@tikvahethiopia

#ሶማሌክልል በሶማሌ ክልል በተከሰተው የጎርፍ አደጋ እስካሁን 28 ሰዎች ሲሞቱ ከ300,000 በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው ተጠቆመ። በሶማሌ ክልል ከ33 ወረዳዎች በላይ ተከሰተ የተባለውን የጎርፍ አደጋ በተመለከተ ተጎጂዎችና ተፈናቃዮች በምን ሁኔታ እንደሚገኙ ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቦታው እርዳታ እያደረገ የሚገኘውን Save the Childrenን ጠይቋል። የድርጅቱ ምሥራቅ ኢትዮጵያ ዳይሬክተር አቶ አብዲራዛቅ…
#ሱማሌ_ክልል
" እስካሁን ከ700 በላይ ሰዎች በኮሌራ ተጠቅተዋል። 23 ሰዎች መሞታቸው ተረጋግጧል። ከ23ቱ ወደ 11 የሚሆኑት #ህፃናት ናቸው " - አቶ አብዲሪዛቅ አህመድ
በሱማሌ ክልል በሚገኙ ተፈናቃዮች ላይ የከፋ ኮሌራ ወረርሽኝ መከሰቱን፣ ወረርሽኙን ለመከላከል የመድኃኒት እጥረት ፈተና በመሆኑ ርብርብ ካልተደረገ ከ500,000 በላይ ተፈናቃዮች በወረርሽኙ የመጠቃት ዕድላቸው ሰፊ መሆኑን ሴቭ ዘ ችልድረን (Save the children) የሱማሌ ክልል ቅርንጫፍ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጧል።
የሱማሌ ክልል ሴቭ ዘ ችልድረን ቅርንጫፍ ዳይሬክተር አቶ አብዲሪዛቅ አህመድ ምን አሉ ?
- እስካሁን #ከ700 በላይ ሰዎች በኮሌራ ተጠቅተዋል። 23 ሰዎች መሞታቸው ተረጋግጧል። ከ23ቱ ወደ 11 የሚሆኑት ህፃናት ናቸው። ከ700ዎቹ ተጠቂዎች መካከል 319ኙ ህፃናት ናቸው።
- በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ምክንያት ብዙ መጸዳጃ ቤቶች ወድመዋል። የተፈናቀሉ ሰዎች መጸዳጃ ቤት የላቸውምና ይሄ ሁኔታ በጣም አሳሳቢ ሆኗል። ተፈናቃዮቹ የሚኖሩበት ቤት የላቸውም።
ኮሌራ የተከሰተው መቼ ነው ?
- ኮሌራ ከተከሰተ ከሁለት እስከ ሦስት ወራት አስቆጥሯል። ሆኖም ግን ዝናብ መዝነብ ከጀመረ በኋላ ነው ኬዞቹ በጣም እየበዙ የመጡት።
- ሕክምና ካላገኙ #ይሞታሉ። ኮሌራ በጣም መጥፎ ተላላፊ በሽታ ነው። መድኃኒት እንዴት ይገኛል የሚለው ግን አሁንም አጠያያቂ ጥያቄ ነው።
- በተለይ ቀላፎ ወረዳ መንገዱ ስለተጎዳ አክሰስ የለም፣ የመድኃኒት እጥረት ሲያጋጥም ለማድረስ እንኳ ለትራንስፖርት ያስቸግራል። ተፈናቃናቃዮቹ በጠባብ መጠለያ ውስጥ ከአሥር ሰዎች በላይ ሆነው ተጣበው ነው የሚኖሩት። መጸዳጃ ቤት የላቸውም፣ ኮሌራው የመዛመት ዕድሉ ከፍተኛ ነው።
በጎርፍ ሳቢያ የተፈናቃዮችና የተጎጂዎች ቁጥር ጨመረ ወይስ ቀነሰ ?
-የተፈናቃዮች ቁጥር ከ300,000 ወደ #500,000፣ የተጎጂዎች ቁጥር ከ600,000 ወደ #1.4 ሚሊዮን ደርሷል። ካሉበት ቦታ እስከመቼ እንደሚቀመጡ አይታወቅም፣ ምክንያቱም ጎርፉ እስካሁን እንደቀጠለ ነው።
- ከእነዚህ ተጎጂዎች መካከል እስካሁን ድጋፍ ያገኙት #10 በመቶዎቹ ብቻ ናቸው። ቀሪዎቹ #90 በመቶዎች አፋጣኝ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል።
- የጎርፍ አደጋው እስካሁን እየተስፋፋ ነው። ብዙዎች እየተጎዱና እየተፈናቀሉ ነው። ሰሞኑን ዝናቡ ስለቀነሰ ምናልባት ከዚህ በኋላ አደጋው ሊቀንስ ይችላል የሚል ተስፋ አለ።
ምን ተሻለ ?
ከፍተኛ የሆነ እንቅስቃሴ ስላለ ማኅበረሰቡ የሚዛመትበትን መንገድ እንዲያውቅ አዌርነስ እንዲፈጠር፣ መድኃኒትና ነርስ በቂ ስላልሆነ እንዲጨመር፣ ኬዙ ያለባቸው ቦታዎች ኮሌራ ትሪትመንት ሴንተር እንዲገነባ፣ የታመመ ሰው ቶሎ ወደ ሆስፒታል እንዲደርስ የሚያስችል ቲም እንዲቋቋም አቶ አብዲሪዛቅ ጠይቀዋል።
የተከሰተው ኮሌራ ዋና ምንጩ ምን እንደሆነ መለየትና በአፋጣኝ ከምንጩ ማድረቅ ዋነኛው ተግባር መሆን እንዳለበት ጠቁመው፣ ንጹህ የውሃ ችግር ስላለ ተፈናቃዮች የተበከለ ውሃ እንዳይጠቀሙ የውሃ ሳኒታይዘር እንደሚያስፈልግም አክለዋል።
ድጋፍ ካልተገኘ በቀጣዮቹ ሳምንታት ብዙ ሰዎች ሊሞቱ ይችላሉ ያሉት ዳይሬክተሩ፣ ችግሩ ሰፊና የከፋ፣ ከመንግሥት አቅም በላይ ስለሆነ አለም አቀፍ ኤጀንሲዎች ጋር ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
መረጃውን የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ ነው።

" 4 ሰዎች ወዲያው ሲሞቱ ፤ 18 ሰዎች ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል " - ዶክተር ዑቕባይ ሓጎስ
ዛሬ ህዳር 21/2016 ዓ.ም ጠዋት በትግራይዋ የሓውዜን ከተማ አጠገብ የ4 ሰዎች ህይወት የቀጠፈ ከባድ የመኪና አደጋ አጋጥመዋል።
የሓውዜን ከተማ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ባለሞያ ተኽለማርያም ተካ ፤ አደጋው በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ሓውዜን ወረዳ ልዩ ቦታ " ቀያሕታይ " በጭነት ሲኖ መኪናና 5L የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ መካከል በተፈጠረ ግጭት የተከሰተ ነው ብለዋል።
የሓውዜን ከተማ ዋና ፓሊስ አዛዥ ሻምበል ተኽላይ እንዳሉት ደግሞ ፤ በተለያዩ አቅጣጫዎች ሲጓዙ የነበሩት ሲኖ ትራክ የጭነት መኪናና 5L ሚኒባስ የህዝብ ማመላለሻ በቁልቁለት ቦታ በመጋጨታቸው የተፈጠረ አደጋ ነው።
የአደጋው መነሻ ምክንያት በመጣራት ያለ ቢሆንም ፍጥነትና በማጠፍያ ቦታ የትራፊክ ህግ ባለማክበር የተከሰተ አደጋ መሆኑ አመላካች መረጃዎች አሉ ፤ ስለሆነም አሽከርካሪዎች መስመራቸው ይዘው በሃላፊነት መንፈስ መንዳት አለባቸው ሲሉ አክለዋል የከተማው ፓሊስ አዛዥ።
የሓውዜን የፍረሰማእታት ሆስፒታል ሜዲካል ዶክተር ዑቕባይ ሓጎስ አደጋው አስመልክተው በሰጡት ሞያዊ መረጃ ፤ በአሰቃቂ አደጋው 4 ሰዎች ወድያው ሲሞቱ ፤ 18 ሰዎች ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል።
ከከተማው ሆስፒታል አቅም በላይ የሆኑት 8 የአደጋው ሰለባዎች ሪፈር ተብለው ዓይደር መቐለ ሆስፒታል እንደተላኩ የገለፁት ሜዲካል ዳይሬክተሩ ፤ የሓውዜን ከተማ ህዝብ የአደጋው ሰለባዎች ለማዳን ያደረገው ያላሰለሰ ጥረት ምስጋና አቅርበዋል።
መረጃው በመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የተላከ ነው።

ፈጥነው ይመዝገቡ !
=============
የታታሪዎቹ/ቀጠሌዋን የሁለተኛ ዙር የአዋሽ ባንክ የስራ ፈጠራ ውድድር በበርካቶች ጥያቄ መሠረት ምዝገባው እስከ ህዳር 30, 2016 ዓ.ም መራዘሙን እየገለጽን በ Online ማመልከት ለምትፈልጉ በባንኩ ድህረ ገጽ ላይ ማስፈንጠሪያውን በመጫን 👉 https://tatariwochu.awashbank.com
እንዲሁም በአካል ማመልከት ለምትፈልጉ በአቅራቢያችሁ ወደሚገኘው የባንካችን ቅርንጫፎች በመቅረብ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ
ውስጥ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ከዚህ በተጨማሪ ከዚህ በታች በአማራጭነት በቀረቡት የመመዝገቢያ ፎርም በመሙላት ማመልከት ይችላሉ፡፡
For English : https://formfacade.com/sm/4W_WcxfNq
For Afaan Oromoo: https://formfacade.com/sm/ABVPRxLmh
For Amharic: https://formfacade.com/sm/KWWld-W-v
https://www.tiktok.com/@awashbank_tiktok

#ኢትዮቴሌኮም
✨ የመጀመሪያዋ ባለ3 እግር ተሽከርካሪ ደብረታቦር ገባች !
ሁለተኛና ሶስተኛ ዙር የጥሪ ማሳመሪያ ዕድለኞች ሽልማታቸውን ዛሬ አስረክበናል!
🎁 1 የ5ጂ ስማርት ስልክ ለአዳማዋ እድለኛ፣
🎁 2 ስማርት ቴሌቪዥኖች ለአዲስ አበባ እና ለአምቦ እድለኞች እንዲሁም
🎁 1 ባለሶስት እግር ተሸከርካሪ ደብረታቦር እድለኛ አስረክበናል!
በተጨማሪም እስከአሁን 2,352 የድምጽ ጥቅል፣ 1,030 የዳታ ጥቅል፣ 30 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው የ5000 ብር ዋጋ ያለው የኤሌክትሮኒክ ገንዘብ ሽልማት ለዕድለኞች አበርክተናል፡፡
✨ አሁንም ወደ 822 ወይም *822# በመደወል አልያም በ www.crbt.et ለአገልግሎቱ ተመዝግበው ሙዚቃዎችን ወይም መንፈሳዊ ዜማዎች እንደገዙ ወደ 645 Y ብለው በመላክ ለሚደርስዎት ጥያቄ ትክክለኛ ምላሽ በመስጠት ዕድልዎን ይሞክሩ!
#ጥሪ_ማሳመሪያ_ጥሪት_ያተርፋል!
#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia

#ሺርካ
✦ " 11 የአንድ ቤተሰብ አባላት (አያት ፣ ልጅ፣ የልጅ ልጅ ፣ የ39 ቀን ጨቅላ) ጨምሮ 17 ስዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል " - የቲክቫህ ቤተሰብ አባል
✦ " ከሟቾቹ ውስጥ ከ70 ዓመት አዛውንት እስከ 26 ቀን ህጻን ነፍሰጡር እናቶች ይገኙበታል " - ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪ (ለቪኦኤ)
✦ " ጥቃቱን ያደረሰው አሸባሪው ሸኔ ነው " - የኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን (ለቪኦኤ)
✦ " እኛ ንፁሃን ላይ ጥቃት አላደረስንም " - የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (ለቪኦኤ)
✦ " ባለሞያ መድበን ምርመራ ጀምረናል " - ኢሰመኮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ
በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ፤ ሺርካ ወረዳ ፤ በተፈጸመ ጥቃት ንጹሐን ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መሞታቸውን እና የዐይን እማኞችና መልክታቸውን ያደረሱ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል።
አንድ #የአካባቢው ነዋሪ የቤተሰባችን አባል በላኩልን መልዕክት ፤ " ህዳር 13 /2016 በግምት ከምሽቱ 2:30 አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቁ እና በታጠቁ ኢ - መደበኛ ሀይሎች በሽርካ ወረዳ ሶሌ ዲገሉ ጉና እና ጢጆ ለቡ በተባሉ የገጠር ቀበሌዎች በተፈፀመ ጥቃት 11 የአንድ ቤተሰብ አባላት (አያት ፣ ልጅ፣ የልጅ ልጅ ፣ የ 39 ቀን ጨቅላ) ጨምሮ 17 ስዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ሲገደሉ በተመሳሳይ ሰዓት በተፈፀመ በሌላኛው ጥቃት ደግሞ 11 በድምሩ 28 ሰው ሲልፍ ሁለት ህፃናት ደግሞ ቆስለው ህክምና ላይ ይገኛሉ " ሲሉ ገልጸዋል።
ቪኦኤ አማርኛ አገልግሎት ክፍል በጉዳዩ ላይ በሰራው ዘገባ በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ሦስት ቀበሌዎች ሐሙስ ህዳር 13 እና ሰኞ ህዳር 17 ቀን በተፈጸመ ጥቃት #36_ሰዎች መሞታቸውን ገልጿል።
ከሟቾቹ ገሚሶቹ የሁለት ቤተሰብ አባላት መሆናቸውን በዘገባው ጠቅሷል።
ቃላቸውን የሰጡ አንድ ስሜ አይጠቀስ ያሉ ነዋሪ ፤ " ህዳር 13 ለ 14 አጥቢያ ለቡ በተባለው ቀበሌ ላይ 11 ሰው አንድ ላይ ሰብስበው እነዚህ ታጣቂዎች አንድ ላይ ረሽነዋል። ሶሌ ዲገሉ በተባለው ቀበሌ ደሞ 17 ሰው አስሩ የአንድ ቤተሰብ አባላት ናቸው ሰብስበው ረሽነዋል። እነዚህ 17ዱ በአንድ ጉድጓድ 11ቱ በአንድ ጉድጓድ ተቀብረዋል። የዚህን ሀዘን ሳንጨርስ እንደገና በሦስተኛው ቀን ለቡ በተባለው ቀበሌ የአንድ ቤተሰብ አባላት 8 ሰዎች ረሽነዋል። እነዚህም በአንድ ጉድጓድ ተቀብረዋል " ሲሉ ተናግረዋል።
ነዋሪው አክለው፤ " ከእነዚህ ከሟቾቹ ውስጥ ከ70 ዓመት አዛውንት እስከ 26 ቀን ህጻን ነፍሰጡር እናቶች ይገኙበታል" ያሉ ሲሆን " የሦስቱ ቦታ ጥቃቶች በተመሳይ መልኩ ቤት እየገቡ አንድ ቦታ ያሉ ሰዎችን መረሸን ነው። ህጻን የለም አዋቂ የለም ገብተው መረሸን ነው። የአማርኛ ስም ያላቸው፣ የአማራ ስም ያላቸውና የኦርቶዶክስ እምነት አማኝ ላይ ያተኮረ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
ጥቃቱን ማን እንደፈጸመ የተጠየቁት ነዋሪው " ምንም የሚታወቅ ነገር የለም የታጠቁ ኃይሎች ናቸው እከሌ ልንላቸው አንችልም። " ሲሉ ምላሻቸውን ሰጥተዋል።
የኦሮሚያ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ሓላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ፣ ለጥቃቱ መንግሥት ' ሸኔ ' እያለ ከሚጠራው (እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሚለው ታጣቂ ቡድን) ተጠያቂ አድርገዋል።
ኃላፊው ለቪኦኤ በሰጡት ምላሽ " በሽርካ ወረዳ ሶሌ ዲገሉ፤ ጢጆ ለቡ፤ ሲላ ዋጂ አሸባሪው ሸኔ ንጹሐን ላይ ጥቃት ፈጽሟል። ከ2 ዓመት ህጻንን እስከ አቅመ ደካማ ሴቶችን ላይ አነጣጥሮ እኔ ባለኝ መረጃ የ27 ሰዎች ህይወት አልፏል " ብለዋል።
አክለውም " ይኼ አሸባሪ ቡድን ባሳለፍነው ሳምንት ቡኖ በደሌ ጨዋቃ ወረዳ ላይ በኢትዮጵያ የጸጥታ አካል በተወሰደበት እርምጃ ብዙ ኃይሉ ሙትና ቁስለጫ በመሆኑ ይሄንን ለመበቀል ብሎ በአርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ይሄንን ጥቃት ፈጽሟል።" ሲሉ ከሰዋል።
በመንግሥት " ኦነግ ሸኔ " የተባለውና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው የታጠቀ ኃይል ቃል አቀባይ የሆኑት ኦዳ ታርቢ ለቪኦኤ ኦሮምኛ ክፍል በሰጡት ምላሽ ውንጀላውን #አስተባብለዋል፡፡
" እኛ ኃይላችን በተባለው አከባቢ #በሰላማዊ ሰዎች ላይ የወሰደው እርምጃ፤ ያጠፋው የሰላማዊ ሰዎች ህይወትም የለም። ከህዳር 14 - 17 ድረስ በሥርዓቱ ኃይል ብዙ ሰው ተገሏል፤ ብዙ ቤትም ተቃጥሏል። ይህም በምስራቅ አርሲ ሽርካ ወረዳ ነው የተፈጸመው አዛውንቶችም ተገለዋል። ይህንን ለማድበስበስ ነው ጣታቸውን በእኛ ላይ የሚጠቁሙት " ሲሉ ተናግረዋል።
የኦሮሚያ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ሓላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ ግን ይህ ኃይል የሚፈጸጸምማቸውን ጥቃት መካድ ባህሪው ነው ሲሉ ገልጸውታል።
አስተያየታቸውን የሰጡን የቲክቫህ ቤተሰቦች ፤ " እዚሁ ወረዳ ከዚህ በፊትም ተመሳሳይ ግድያ እንደነበረ ቢታወቅም በአካባቢው ያሉ የመንግስት ታጣቂዎች ለጉዳዩ የሰጡት ትኩረት አነስተኛ ስለነበር ይህ ሁሉ ሰው ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ተጨፍጭፈዋል። የአካባቢው ህዝብም በአካባቢው ለመኖር ዋስትና ስለሌለው አካባቢውን ለቆ ለስደት እየተዳረገ ነው፡፡" ሲሉ ተናግረዋል።
በኦሮሚያ ክልል ፤ ምሥራቅ አርሲ ዞን ፤ ሽርካ ደረሰ ስለተባለው ጥቃት ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ( #ኢሰመኮ ) ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን የኮሚሽኑ የክትትልና ምርመራ ስራ ክፍል ሲኒየር ዳይሬክተር ሚዛኔ አባተ (ዶ/ር)፣ " መረጃ ደርሶናል እያየነው ነው " የሚል አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።
" አሁን ላይ በዝርዝር የምናገረው ነገር የለም። ነገር ግን እኛ ጉዳዮች እንደዚህ በሚደርሱን ሰዓት ጉዳዩን የሚከታተል ባለሙያ እንመድባለን፣ በዚህም ምርመራ እናደርጋለን። ያ ነገር የተጀመረ መሆኑን ነው መናገር የምችለው " ሲሉ ገልጸውልናል።