TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Oromia

የ8ኛ ክፍል ውጤት ይፋ ተደረገ።

የኦሮሚያ ክልል የ2015 የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑን ከክልሉ የትምህርት ቢሮ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

የ2015 ዓ/ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ከዚህ በታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጠቀም  ስማቸውን እና የID. ቁጥራቸውን በማስገባት ዉጤታችሁን ማየት እንደሚችሉ ቢሮው አሳውቋል።

Website:- https://oromia.ministry.et/#/result

Via https://t.iss.one/tikvahethAFAANOROMOO

@tikvahethiopia
#Oromia

በኦሮሚያ ክልል እስከ መስከረም መጨረሻ ድረስ 1.3 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ተፈናቅለዋል።

CDCB (Center For Development &Capacity Building ) ባወጣው ሪፖርት የቡሳ ጎኖፋን መረጃ ዋቢ አድርጎ በኦሮሚያ ክልል እስከ መስከረም ባለው ጊዜ 1.3 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች መፈናቀላቸውንና ከተመዘገቡት ተፈናቃዮች ውስጥ 859,000 (66%) የሚሆኑት ከምስራቅ ወለጋ እና ምዕራብ ወለጋ ብቻ መሆናቸውን ይጠቅሳል።

በመግለጫው የተጠቀሱት ቁጥሮች ምን ያሳያሉ ?

- የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር 1,292,323 መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 29 በመቶው ብቻ (374,448) ወደ መጠለያዎች መድረሳቸውን ያመለክታል። 71 በመቶ (916,606) የሚሆኑት በአካባቢው እና ራቅ ብለው በሚገኙ ማኅበረሰቦች ውስጥ ተበታትነው ይገኛሉ።

- 739 ትምህርት ቤቶች ከአገልግሎት ውጪ ሆነዋል።

- ከ210,000 በላይ ህጻናት ከትምህርት ውጪ ሆነዋል።

- 1,117 መምህራንና የትምህርት ባለሙያዎች ወደ ሥራቸው አልተመለሱም።

- 208 ጤና ተቋማት ሙሉ በሙሉ ወድመዋል፤  788 በከፊል ወድመዋል። ( ከእነዚህ ውስጥ 13ቱ ሆስፒታሎች ሲሆኑ የተቀሩት ጤና ጣቢያዎች ናቸው)

በዚህ አጭር መግለጫ በምዕራብ ኦሮሚያ እና መካከለኛው አከባቢ በፌዴራል መንግስት እና በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀው ራሱን የኦሮሞ ሕዝብ ነጻ አውጭ ብሎ በሚጠራውና መንግሥት " ኦነግ ሸኔ " የሚለው ታጣቂ ቡድን መካከል የተፈጠረው ግጭት፣ እንዲሁም በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ድንበር ላይ በአማራ ክልል በሚንቀሳቀሰው " ፋኖ " በመባል የሚታወቀው ታጣቂ ቡድን ጋር በሚፈጠሩ ግጭቶች ለችግሮቹ መንስዔ መሆናቸውን ይጠቅሳል።

በእነዚህ ግጭቶች በተለይ ሴቶች እና ህጻናት ለአደጋ የተጋለጡ ናቸው ያለው ይህ አጭር መግለጫ እናቶቻቸውን እና አባቶቻቸውን በድንገት የሚያጡ ህፃናት ቁጥር እየጨመረ ነው፤ ባል የሞቱባቸው ሴቶች ለዝርፊያ እና ለ አስገድዶ መድፈር (በፆታ ላይ የተመሰረተ ጥቃት) እና አካላዊ ጥቃት እየተጋለጡ መሆናቸውን ያነሳል።

"በኦሮሚያ ክልል ያለው ግጭት ውስብስብ እና አሳሳቢ ሁኔታን ፈጥሯል። ይሄን ግጭት ለማስቆም ሁሉን አቀፍ ውይይት እና ሰላም ማስፈን ያስፈልጋል። በግጭቱ ወቅት ለተፈናቀሉ እና ችግር ውስጥ ላሉ ዜጎች አስቸኳይ የተቀናጀ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል።" ሲል በCDCB የቀረበው የፓሊሲ ብሪፍ ጠይቋል።

በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ የተዘጋጀውን ሙሉ መግለጫ @tikvahethafaanoromoo ላይ ያገኙታል።

@tikvahethiopia
#Amhara #Oromia

ከ5 ዓመታት በላይ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖች በሚስተዋለው የጸጥታ ችግር ሳቢያ ወደ አማራ ክልል በመሸሽ ተጠልለው የሚገኙና ገና ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ተፈናቃዮችን ኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ቄየዎቻቸው የመመለስ ሥራ ለመስራት ሰሞኑን ባህር ዳር ከተማ ላይ ተደረገ በተባለ የጋራ ውይይት ስምምነት ላይ መደረሱን የሁለቱም ክልሎች የኮሚዩኒኬሽን ቢሮዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

የኦሮሚያ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀይሉ አዱኛ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ማብራሪያ፣ "የታሰበው በጸጥታ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ከክልላችን ተፈናቅለው አማራ ክልል የሚገኙ ተፈናቃዮችን መልሦ የማቋቋም ሥራ ነው" ብለዋል።

አክለውም፣ "በጸጥታ ምክንያት ከኦሮሚያ ወደ አማራ ክልል የተፈናቀሉ ሰዎችን ለመመለስ አብይ ኮሚቴው በሚቀጥለው ሳምንት ተገናኝቶ መሪ ዕቅዱን ያወጣል" ሲሉ አስረድተዋል።

የአማራ ክልል የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ወንድወሰን አሰፋ በበኩላቸው፣ "ሁለታችን ተቀናጅተን ለመስራት የሚቀጥለው ሰኞ ቀጠሮ ይዘናል። በዛ መሰረት ታይም ቴብሉን እናስቀምጣለን  መቼ ይመለሱ? መቼ ወደዛ እናጓጉዝ? የሚለው በቅዳችን ነው የሚመለሰው" ብለዋል።

በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ለአብነትም በሰሜን ሸዋ ዞን #ደራ_ወረዳ ከአሥር በላይ ቀበሌዎች፣ በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ታጣቂ ቡድኑ በንጹሐን ላይ ግድያ እየፈጸመ መሆኑን ነዋሪዎች እንደገለጹ፣ ይህ በእንዲህ እንያለ ተፈናቃዮች ቢመለሱ ለደኅንነታቸው ምን ዋስትና ይኖራቸዋል ? የሚል ጥያቄ ቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርቧል።

አቶ ወንድወሰን ለዚሁ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ " የጸጥታ ችግር እያለ እኛም እዲመለሱ አናደርግም። በኦሮሚያ ክልል በኩልም የጸጥታ ችግሩ አስተማማኝ ደረጃ ሳይዘልቅ ተመላሾቹ ለዳግም ችግር የሚጋለጡበትን  መገድ ሁለታችንም አንሰራም" ብለዋል።

አክለውም፣ " ሰሜን ሸዋ አካባቢ ያለው የጸጥታ ችግር ወጣ ገባ የሚል ነው እናተም እደምታውቁት አማራ ክልልም የጸጥታ ችግር አለ። ይህን በዘላቂ መፍትሔ ይሰጠዋል ብለን ነው የምናስበው፣። ሆሮ ጉድሩ ያለውም ቢሆን አሸባሪው ሸኔ  ወጣ ገባ እያለ ችግር ሊፈጥር ይችላል " ብለው፣ በቅድሚያ የጸጥታውን ችግር የምረጋግጥ ሥር እንደሚከናወን አስረድተዋል።

አቶ ሀይሉ አዱኛ በበኩላቸው፣ " የጸጥታው ችግር በተረጋገጠባቸው አካባቢዎች የማስፈሩም መልሶ የማቋቋሙም ሥራ ይሰራል። የጸጥታ ችግር ያልተረጋገጠበት አካባቢዎች ደግሞ እያረጋገጥን ነው መልሰን የምናቋቁመው፣ ዛሬ መልሰን ችግር እንዳይፈጠር ጥንቃቄ በተሞላበት አኳኋን ነው የሚሰራው " ሲሉ ተናግረዋል።

የሁለቱም ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ባለስልጣናት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በገለጹት መሠረት፣ ተፈናቃዮችን ወደነበሩበት ኦሮሚያ ክልል ከመመለስ በፊት ይህን ሥራ ለማስኬድ የተዋቀረው አብይ ኮሚቴ መረጃዎችን ያጠራል።

ያንብቡ - https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-10-27

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Amhara #Oromia ከ5 ዓመታት በላይ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖች በሚስተዋለው የጸጥታ ችግር ሳቢያ ወደ አማራ ክልል በመሸሽ ተጠልለው የሚገኙና ገና ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ተፈናቃዮችን ኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ቄየዎቻቸው የመመለስ ሥራ ለመስራት ሰሞኑን ባህር ዳር ከተማ ላይ ተደረገ በተባለ የጋራ ውይይት ስምምነት ላይ መደረሱን የሁለቱም ክልሎች የኮሚዩኒኬሽን ቢሮዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።…
#Amahra #Oromia

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከኦሮሚያ ተፈናቅለው አማራ ክልል የሚገኙ ወገኖችን ወደቄያቸው ለመመለስ ከሰሞኑን በክልሎቹ መካከል የተደረሰበትን የመግባባት ስምምነት በተመለከተ ለሁለቱም ክልል የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮዎች ተከታዮችን ጥያቄዎች አቅርቧል።

👉 ከሞት ሸሽተው ወደ አማራ ክልል የተፈናቀሉ ሰዎች ወደ ኦሮሚያ ክልል ለመመልስ ፈቃደኛ ናቸው ? ይህንን ማወቅ ተችሏል ወይ ?

👉 በመንግሥት እና በታጣቂ ቡድኑ / መንግሥት ' ሸኔ ' እያለ የሚጠራው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት/ መካከል ተጀምሮ የተቋረጠው ድርድር መቅደም አልነበረበትም ወይ ?


ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላቀረበው ለእነዚህ ጥያቄዎች የአማራ ክልል የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ወንደሰን አሰፋ ፤ ሥራው በሂድት የሚረጋገጥ እንደሆነ፣ ተፈናቃዮቹ ለመመለስ ፈቃደኛ እንደሚሆኑ፣ ድርድሩ የበላይ አካላትን እንደሚመለከት መልሰዋል።

የኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀይሉ አዱኛ በበኩላቸው፣ " ከቄያቸው፣ ከንብረቱ ተፈናቅሎ ያለ ሰው ዳግም ወደቄየው መመለስ ይፈልጋል የሚል እምነት አለኝ። ተቸግሮ እንጅ ፈልጎ የመፅዋች እጅ ለመጥበቅ የሚፈልግ ይኖራል ብለን አናስብም " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

#በተጨማሪ ፦ ለአማራ ክልል ኮሚኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ወንደሰን አሰፋ አሁንም ድረስ በንጹሐን ላይ ግድያ እየተፈጸመ መሆኑን ነዋሪዎች በሚገልፁበት ወቅት ተፈናቃዮች ቢመለሱ ለደኅንነታቸው ምን ዋስትና ይኖራቸዋል ? የሚል ጥያቄ ቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርቦ ፤ " የጸጥታ ችግር እያለ እኛም እዲመለሱ አናደርግም። በኦሮሚያ ክልል በኩልም የጸጥታ ችግሩ አስተማማኝ ደረጃ ሳይዘልቅ ተመላሾቹ ለዳግም ችግር የሚጋለጡበትን መንገድ ሁለታችንም አንሰራም " ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂ ቡድን መካከል በታንዛኒያ የሁለተኛ ዙር የሰላም ንግግር መጀመሩን " ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ " ዘግቧል። ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ባወጣው ዘገባ የሰላም ንግግሩ ጥቂት ቀናትን እንዳስቆጠረና ከሁለቱም ወገኖች የተወጣጡ የጦር አባላት ተወካዮች በተገኙበት እየተካሄደ መሆኑን ያስረዳል። ከዚህ ቀደም ራስ ገዝ ግዛት በሆነችው…
#Oromia

ምንም እንኳን እስካሁን ድረስ በመንግሥትም ሆነ በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (መንግሥት ኦነግ ሸኔ እያለ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን) በኩል ይፋዊ መግለጫ ሆነ ማብራሪያ ባይሰጥም በታንዛኒያ፣ ዳሬሰላም ውስጥ ሁለተኛው ዙር የሰላም ድርድር መጀመሩን የዲፕሎማቲክ ምንጮች ገልጸዋል።

ዲፕሎማቲክ ምንጮች እንደገለፁት ድርድሩ እየተመራ ያለው በጦር አዛዦች ነው።

የመንግሥት የተደራዳሪ ቡድን የሚመራው በሀገር መከላከያ ሰራዊት የምዕራብ ዕዝ አዛዥ በነበሩት ጄነራል ጌታቸው ጉዲና ሲሆን በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በኩል ደግሞ በኩምሳ ድሪባ (ጃል መሮ) ነው።

ጃል መሮ ከወለጋ ጫካ በኢጋድ፣ በአሜሪካ፣ በኖርዌይ መንግሥታት አስተባባሪነት ነው በአውሮፕላን ወደ #ኬንያ ከዛም ታንዛኒያ እንዲገቡ የተደረጉት።

ከጃል መሮ በተጨማሪ የደቡብ ኦሮሚያ አዛዡ ገመቹ ረጋሳ (ጃል ገመቹ አቦዬ) ከነበሩበት ቦረና አካባቢ በኬንያ አድርገው ወደ ዳሬሰላም እንዲገቡ መደረጉን የዲፕሎማቲክ ምንጮች ተናግረዋል።

ሁለተኛው ዙር የሰላም ድርድር እንዲሳካ ኢጋድ፣ አማሪካ፣ ኖርዌይ፣ ኬንያ ድጋፍ እና የማመቻቸት ስራን እየሰሩ ነው ተብሏል።

በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሰው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት መሪዎች ከመንግሥት ጋር ፊት ለፊት መገናኘታቸው ለሰላም ድርድሩ ተስፋ እንደሰጠው ተነግሯል።

@tikvahethiopia