#አሜሪካ
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አንደኛ ዓመትን አስመልክተው መልዕክት አስተላልፈዋል።
አንቶኒ ብሊንከን ምን አሉ ?
- ብሊንከን በደፈናው #ኢትዮጵያ እና #ኤርትራ ጠብ ከሚያጭሩ ድርጊቶች እንዲቆጠቡና የአካባቢውን አገራት ነጻነት፣ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ማክበር አለባቸው ብለዋል።
- የኤርትራ ኃይሎች ከትግራይ ክልል ሙሉ ለሙሉ መውጣትን እንዳለባቸው ገልጸዋል።
- ስምምነቱን ተከትሎ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር መመሥረቱን ጨምሮ የተወሰዱ በጎ እርምጃዎችን አሜሪካ እንደምትደግፍ አሳውቀዋል።
- ህወሓት ኃይሎቹ ከባድ መሳሪያቸውን ፈትተው ተዋጊዎች ማሰናበት በተጀመረበት ጊዜ በትግራይ ውስጥ ዘላቂ ሰላም ለማስፍን ተጨማሪ እርምጃዎች መውሰድ ያስፈልጋል። ለዚህም የኤርትራ ኃይሎች ሙሉ ለሙሉ መውጣት አለባቸው ብለዋል።
- ብሊንከን አሜሪካ በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በሌሎችም አካባቢዎች ያሉት ግጭቶች እንደሚያሳስባት ገልጸዋል። ያለው ነገር በቀላሉ ሊታወክ የሚችለውን የኢትዮጵያን ሰላም አደጋ ላይ እንደጣለው አመልክተዋል።
- በአገሪቱ በተለያዩ ወገኖች የቀጠለው የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እና ጥቃት፣ " የመርዛማ ንግግሮች " መስፋፋት በጦርነቱ ምክንያት የሳሳውን ማኅበራዊ ትስስር የበለጠ እየሸረሸረው መሆኑን ገልጸዋል። ለዚህም ፦
🔹አስተማማኝ የሽግግር ፍትሕ፣
🔹ሐቀኛ እና አካታች ብሔራዊ ምክክር በመላዋ አገሪቱ ተግባራዊ እንዲሆን እንዲሁም በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች የሚካሄዱትን ግጭቶች ለመፍታት ውይይት እንዲደረግ አስቸኳይ ጥሪ አቅርበዋል።
#BBC
#SecretaryofStateAntonyJBlinken
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
አንድ ዓመት ስለደፈነው የፕሪቶሪያው ሰላም ስምምነት የኢትዮጵያ መንግሥት ፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፣ ህወሓት እና ሀገራት ምን አሉ ? የኢትዮጵያ መንግሥት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፤ የፕሪቶሪያው ግጭት የማስቆም ስምምነት ዋና ዉጤት " የጦር መሣሪያ ላንቃ መዘጋቱ " እንደሆነ አሳውቋል። ሚኒስቴር ከግጭት ማቆሙ ስምምነት በኋላ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረኮች የምትጠቀስበት…
" ዳግም ወደ ግጭት ሊወስዱ የሚችሉ አከራካሪ እና አሻሚ ጉዳዮች ዙሪያ የጋራ መግባባት መፍጠር ይገባል " - ነእፓ
የወልቃይት እና የራያ አካባቢዎች ጉዳይ ህጋዊ እና ፍትሀዊ መልስ ያገኝ ዘንድ የትግራይ፣ የአማራ እና የፌዴራል መንግስት እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ / ነእፓ ጥሪ አቀረበ።
ነእፓ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አንደኛ ዓመትን አስመልክቶ በላከል መግለጫ ነው ይህን ጥሪ ያቀረበው።
ፓርቲው በላከልን መግለጫ ፤ በሰላም ስምምነቱ ያልተፈጸሙ ጉዳዮች በአፋጣኝ እንዲፈጸሙ ፤ ዳግም ወደ ግጭት ሊወስዱ የሚችሉ አከራካሪ እና አሻሚ ጉዳዮች ዙሪያ የጋራ መግባባት ለመፍጠር በተለይም የፌደራል መንግስት እና የትግራይ ከልል ጊዜያዊ አስተዳደር በከፍተኛ ኃላፊነት እና ተጠያቂነት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪውን አቅርቧል።
በጦርነቱ ምክንያት ከፉኛ የወደሙ የትግራይ፣ የአማራ እና የአፋር ክልል መሰረተ ልማቶች በተቻለ አቅም ባጠረ ጊዜ እንዲገነቡ ማእከላዊው መንግስት ድጋፍ እንዲያደርግ ብሏል።
የወልቃይት እና የራያ አካባቢዎች ጉዳይ ህጋዊ እና ፍትሀዊ መልስ ያገኝ ዘንድ የትግራይ፣ የአማራ እና የፌዴራል መንግስት እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት የበኩላቸውን እንዲያደርጉ ጥሪውን አቅርቧል።
የትግራዩን የሰላም ስምምነት እንደ ጥሩ ተሞከሮ በመውሰድ በሌሎች የሀገራችን አካባቢዎች ያሉ ግጭቶች እና ግጭት ቀስቃሽ የፖለቲካ ልዩነቶች በሰላማዊ መንገድ የሚፈቱበትን መንገድ ለመጠቀም መንግስትም ሆነ ነፍጥ አንግበው የሚታገሉ አካላት ልዩነቶቻቸውን #በድርድር ለመፍታት የበኩላቸውን እንዲያደርጉ ነእፓ በላከልን መግለጫው ይፋዊ ጥሪውን አቅርቧል።
ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ ፤ የፖለቲካ ልዩነቶችን በአፈሙዝ መፍታት እንደማይቻል የሀገራችንም ሆነ የዓለም ተሞከሮ ያሳያል ያለ ሲሆን ከአንድ አመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን በድርድር የተቋጨው የትግራይ ጦርነት ለዚህ ህያው ምስክር ነው ሲል ገልጿል።
ከዚህ ቀደም በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ሲካሄዱ የነበሩ ግጭቶች በድርድር ይፈቱ ዘንድ ጥሪ ሲያደርግ እንደቆየ ያስታወሰው ፓርቲው ዛሬም በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ያሉ ግጭቶች በአፋጣኝ ቆመው የፖለቲካ ልዩነቶች በሰላማዊ መንገድ እና " በአብሮ በማሸነፍ " መርህ አንዲፈቱ የሰላም ጥሪውን አቅርቧል።
(ፓርቲው የላከው መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

#አቢሲንያ_ባንክ
ይቅደሙ!! ተሳፋሪዎቻቸውን የአፖሎ አካውንት ለሚያስከፍቱ የሊትል አሽከርካሪዎች በ1 አካውንት የ50 ብር ኮሚሽን ያገኛሉ!
የቴሌግራም ቻነላችንን ይቀላቀሉ
https://t.iss.one/BoAEth
#Apollodigitalbank #Apollodigitalproduct #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all

ይፋዊ የቴሌብር ቴሌግራም ቻናል https://t.iss.one/telebirr ቤተሰብ ይሁኑ፤ ራስዎን ከአጭበርባሪዎች ይጠብቁ!
#ኢዜማ
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) አንድ ዓመት የሞላውን የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አስመልክቶ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ ፤ የፕሪቶሪያው ስምምነት ለሁለት ዓመታት የቆየው እና ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ውድመት ያስከተለው ጦርነት እንዲቆም እንዲሁም እንደገና የሰላም ተስፋ እንድንሰንቅ ማድረጉ በበጎ ጎኑ እናስታውሰዋለን ብሏል።
ፓርቲው ፤ ምንጊዜም ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚደረግ ጥረትን እንደሚያበረታታ ገልጾ ሥምምነቱን መልካም ጅማሮ እንደሆነ ገልጿል።
መንግሥት ከዚህ ቀደም ቅራኔዎችን በውይይት ለመፍታት ከተለያዩ ታጣቂ ቡድኖች ጋር ካደረጋቸው ስምምነቶችና የውይይት ሙከራዎች በተሻለ መልኩ የፕሪቶሪያው ስምምነት ለሕዝብ በይፋ የተገለጸ መሆኑ መልካም የሚባል ጅማሮ እንደሆነ አመልክቷል።
" ነገር ግን አፈጻጸሙ ላይ በመንግሥት በኩል በታየ ዳተኝነት እና ግልጸኝነት መጉደል እንደ፦
🔹ሥምምነቱ መፈጸም አለመፈፀሙን፣
🔹ከስምምነቱ ጋር ተያይዞ የተገኙ ውጤቶችና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን የተመለከቱ ጉዳዮችን የሚያመላክቱ መረጃዎች በአግባቡ ሲቀርቡ አለመመልከታችን፤
🔹በተለያየ ጊዜ የሕወሓት አመራሮች በተለያዩ መድረኮች ላይ የሚያሰሙት ግጭት ቆስቋሽ እና ተጨማሪ ውጥረቶችን የሚያጭሩ ገለፃዎችን መንግሥት ዐይቶ እንዳላየ በዝምታ ማለፉንና ማብራሪያ አለመስጠቱ ስንመለከት ሥምምነቱ በተባለው መልኩ ከመፈጸም ይልቅ ' በተቃራኒው እየሄደ ይሆን? ' የሚያስብል ስጋት ውስጥ ይጥላል " ብሏል ፓርቲው።
" ይህ የመንግሥት ቸልተኝነት እና በተለያየ ጊዜ የሚሰጡ ምክረ ሀሳቦችን አልሰማ ባይነት ለሌሎች ችግሮችም ሆነ አሁን በአማራ ክልል ለተፈጠረው የሰላም መደፍረስ ድርሻው ቀላል የሚባል ካለመሆኑ በተጨማሪ በክልሉ ላይ ለተፈጠረው ችግር ምክንያትነት ተብለው ከሚጠቀሱት ጉዳዮች መካከል ቀዳሚው ነው ቢባል ስህተት አይሆንም " ሲል ገልጿል።
ኢዜማ ከዚህ ቀደምም በተደጋጋሚ አሳስቢያለሁ እንዳለው መንግሥት ከስምምነቱ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን በተገቢው ወቅትና ሁኔታ ለሕዝብ የማድረስ ከፍተኛ ድክመቱን አርሞ የዚህን ሥምምነት የአፈጻጸም ሂደት ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ እና የገጠሙ ችግሮች ካሉም በይፋ ለሕዝብ እንዲያሳውቅ ጠይቋል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሄራዊ ቡድን ዛሬ አዲስ ዋና አሰልጣኝ ተሹሞለታል።
ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዋና አሰልጣኝነት የተሾሙት አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ እንደሆኑ ተገልጿል።
አዲሱ አሰልጣኝ የአንድ ዓመት ውል ፈርመዋል ነው የተባለው።
በሌላ በኩል አንድም ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሀገራችን አለመኖሩን ተከትሎ የኢትዮጵያን ህዝብ የሚወክለው ብሔራዊ ቡድን 2 የሜዳው ጨዋታዎችን ወደ ሞሮኮ ሀገር አቅንቶ እንደሚጫወት ተነግሯል።
ኢትዮጵያ ከሴራሊዮን (ህዳር 5) እንዲሁም ከቡርኪናፋሶ (ህዳር 11) በሀገሯ በሜዳዋ ላይ ልትዳርግ የሚገባቸው ጨዋታዎች በሞሮኮ አልጀዲዳ ከተማ እንደሚደረጉ ታውቋል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስቀድሞ ከሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በጋራ ለመስራት በተስማማው ስምምነት ቡድኑ በሞሮኮ በሚኖረው ቆይታ ሙሉ ወጪው በሞሮኮ እግር ፌዴሬሽን የሚሸፈን ይሆናል።
ኢትዮጵያ እጅግ ከፍተኛ የእግር ኳስ አፍቃሪ ህዝብ ያለባት ስትሆን ደረጃቸውን የጠበቁ የእግር ኳስ መጫወቻ ስታዲየሞች ስለሌላት ብሄራዊ ቡድኗ ከደጋፊው ህዝብ ርቆ ከሀገሩ እየወጣ ለመጫወት ተገዷል።
በየጊዜው በየክልሉ በመንግስት " ግንባታ ላይ ናቸው ፤ ይሄን ያህል ፐርሰንት ደርሰዋል ፣ የሚቀረው አንዳንድ እቃ ነው " እየተባለ የሚነገርላቸው ግዙፍ ስታዲየሞች አሁን ምን ላይ እንዳሉ አይታወቅም።
ዛሬም በከፍተኛ ገንዘብ ግንባታቸው የተጀመረ ግዙፍ ስታዲየሞች መቼ ተጠናቀው ኳስ እንደሚያስተናግዱ የሚታወቅ ነገር የለም።

#ምደባ ትምህርት ሚኒስቴር በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና ወስደው ያለፉ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ አሰራርን አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥቷል። ማብራሪያ ፦ - የምደባ ስርዓቱ በተፈጥሮም ሆነ በማህበራዊ ሳይንስ መስኮች 1000 ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን በመጀመሪያ የዩኒቨርስቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫቸው ምደባ የሚካሄድ ይሆናል ተብሏል። - የምደባ ስርዓቱ እያንዳንዱ…
የዩኒቨርስቲ ምደባ ይፋ ሆነ።
በ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ እና ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) ትምህርታቸውን ለሚከታተሉ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
Website: https://result.ethernet.edu.et/
Telegram bot: @moestudentbot

የሬሜዲያል መቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ።
የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የሚያስችል የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደርጓል፡፡
በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያላስመዘገቡ ነገር ግን ትምህርት ሚኒስቴር ያወጣቸውን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተማሪዎች የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የሚያስችላቸው የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደርጓል፡፡
በዚህም መሰረት በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 30 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማለትም (210 ከ 700፣ 180 ከ 600 እና 150 ከ500) የተቆረጠ መሆኑ ተመላክቷል።
ከላይ በተራ የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግስት ተቋማት (ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) የRemedial ፕሮግራም የሚከታተሉት የሚከተሉትን መቁረጫ ነጥብ ያሟሉ ብቻ እንደሚሆኑ ተጠቁሟል፡፡
☑ የተፈጥሮ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች 255 ከ700 ያመጡ
☑ የተፈጥሮ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ሴት ተማሪዎች 234 ከ700 ያመጡ
☑ የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች 218 ከ600 ያመጡ
☑ የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛና የማታ ሴት ተማሪዎች 200 ከ600 ያመጡ
☑ ታዳጊ ክልል የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 224 ከ700 ያመጡ
☑ ታዳጊ ክልል የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 210 ከ700 ያመጡ
☑ ታዳጊ ክልል የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 192 ከ600 ያመጡ
☑ ታዳጊ ክልል የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 180 ከ600 ያመጡ
☑ አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 210 ከ700 ያመጡ
☑ አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 210 ከ700 ያመጡ
☑ አርብቶ አደር አካባቢ የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 180 ከ600 ያመጡ
☑ አርብቶ አደር አካባቢ የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 180 ከ600 ያመጡ
☑ ዓይነ ስውራን ማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 150 ከ500 ያመጡ
☑ ዓይነ ስውራን ማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 150 ከ500 ያመጡ መሆን አለባቸው ተብሏል።
መረጃውን ትምህርት ሚኒስቴርን ዋቢ በማድረግ ያሰራጨው ኤፍ ቢ ሲ ነው።

#SafricomEthiopia
ዛሬ በ25 ብር ብቻ ለአስደሳች ጊዜ እንዘጋጅ! ጥቅሉን ለመግዛት *777# እንደውል፤
ጨዋታውን ባልተገደበ የኢንተርኔት ፍጥነት እንመልከት።
ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/SafaricomET
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/safaricomet/
ትዊተር- https://twitter.com/SafaricomET
ሊንክዲን- https://www.linkedin.com/company/safaricom-ethiopia/
ቴሌግራም- https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC
#SafaricomEthiopia #FurtherAheadTogether

#AddisAbaba
አዲስ አበባ ውስጥ በዘላቂነት መቋቋም የሚሹ የድሃ ድሃ ተብለው የተለዩ ከ300,000 በላይ ሰዎች መኖራቸውን የሴቶችና ሕፃናት ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።
የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ወይንእሸት ዘሪሁን እንደገለጹት፣ ፦
- ጎዳና ላይ የወደቁ፣
- በጸጥታ ችግር ከተለያዬ ክልሎች ወደ አዲስ አበባ የመጡ፣
- በአጠቃላይ የድሃ ድሃ ተብለው የተለዩ ሰዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም ታቅዷል።
በዘላቂነት ማቋቋም የሚሹ ምን ያህል ሰዎች እንደሆኑ እንዲገልጹ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ " በዘላቂነት መቋቋም የሚሹ የድሃ ድሃ ተብለው የተለዩ ከ300,000 በላይ ሰዎች አሉ " ብለዋል ኃላፊዋ።
ሰዎቹን በዘላቂነት ለማቋቋም ምን ያህል ገንዘብ እንደሚያስፈልግ ሲጠየቁም፣ " ከፍተኛ የሆነ በጀት ይጠይቃል። በጀት ብቻም ሳይሆን ዝግጅትም ይጠይቃል " ነው ያሉት።
እነዚህን ሰዎች ለማቋቋምም የአዲስ አበባ አስተዳደር ሴቶችና ሕፃናት፣ የሴቶችና የፌደራሉ ሴቶች፣ ሕፃናትና ማኅበራዊ ጉዳዮች ቢሮዎች ከሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ጋር ተቀናጅቶ ለመስራት በቅርቡ ውይይት ተደርጓል።
ጎዳና ላይ የሚገኙን በዘላቂነት መቋቋም የሚሹ አዛኛዎቹ ሰዎች ከየክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ሥራ ፍለጋ፣ አንዳንዶቹ ደግሞ በአቻ ግፊት፣ በጸጥታ መደፍረስና በሌሎች መሰል ምክንያቶች ወደ አዲስ አበባ ከተማ የመጡ መሆቸው ተነግሯል።
በተለያዩ ምክንያቶች ወደ መዲናዋ የመጡ ሰዎችን እጣ ፈንታ በተመለከተ ማብራሪያ ሲሰጡም ወ/ሮ ወይንሸት፣ " ከሚመለከታቸው ከጤና ሙያተኞች ጋራ ሆነን ወደዬ አካባቢያቸው ሊመለሱ የሚችሉበትን ሁኔታ ነው የምንፈጥረው። ከዚህ ውጭ ያሉትን ግን የሥራ ዕድል ሊያገኙ የሚችሉበትን ሁኔታ ከተለያዩ የግል ድርጅቶች፣ መግሥታዊ የሆኑና ያልሆኑ ተቋማት ጋራ በመነጋገር በመግባባት፣ በማሳመንም ጭምር ወደ ሥራ እዲቀላቀሉ ስልጠና እንዲያገኙ ካደረግን በኋላ ወደሥራ የሚገቡበትን ሁኔታ እንፈጥራለን " ብለዋል።
" ሴቶችን በተመለከተ በተመሳሳይ
አሁንም እየሰሩ ያሉ ድርጅቶች አሉ " ያሉት ኃላፊዋ፣ " የአረጋዊ ማቋቋሚያ ተብሎ ከሰንሻይን ጋራ በጋራ የተሰራ አለ። እስከ 750 አረጋውንን በቋሚነት የያዘ ትልቅ ማእከል ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
" ሁልግዜ ተረጂ ሁነው ቀጥታ ድጋፍ ከማድረግ ይልቅ እራሳቸውን ችለው ሰልጥነው ሥራ ይዘው ቤተሰቦቻቸውን የሚመሩበት ደረጃ ላይ ለማድረስም በእንጀራ መጋገር ሥራ (በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ከ3ሺ 280 እስከ 4000 ይይዛል፣ ጉለሌ ላይ ጨምረናል ሌሎችም ሪሀቭቴሽን ሴንተር እያቋቋምን ነው " ብለዋል።
" ወሲብ ንግድ የተሰማሩ ሴቶችን ለማቋቋም መግሥት በጀት መድቦ ኦረዲ ስራውላይ ናቸው። የእዚህን ጉድለትና ክፍተት ግን ማኅበረሰቡ ሊደግፈን ይገባል " ሲሉ አክለዋል።
ወ/ሮ ወይንሸት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ " አብዛኛዎቹ የድሃ ድሃ ተብሎ የተለዩ ናቸው። ግን በምገባ ስርአት ውስጥ የገቡ በቀን አድግዜ መመገብ የሚችሉ ሰዎች ናቸው። በተጨማሪ በሰፍቲነት ቀጥታ ድጋፍ ውስጥ የተካተቱ አሉ የተለያዩ ስራላይ እዲካተቱ ይደረጋል ባለኝ ዳታ 330, 000 ገደማ የተለዩ እዳሉ አውቃለሁ፣ ግን ቁጥር ሊቀንስም ሊጨምርም ይችላል" ሲሉ አብራርተዋል።
መረጃው በአ/አ ቲክቫል ኢትዮጵያ ቤተሰብ ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

Photo
" የሬሜዲያል ተማሪዎች ምደባ በቀጣይ ይካሄዳል " - ትምህርት ሚኒስቴር
ትላንት ይፋ በተደረገው የማካካሻ ትምህርት / ሬሜዲያል መቁረጫ ነጥብ መሰረት ወደ መንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ገብተው ለሚማሩ ተማሪዎች በቀጣይ የዩኒቨርሲቲ ምደባ እንደሚካሄድ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።
የመቁረጫ ነጥብ ያመጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ከተደረገላቸው በኃላ ለ4 ወራት የማካካሻ ትምህርት የሚወስዱ ሲሆን ይህንን ተከታትለው በተቋማቸው እና በማዕከል የሚሰጣቸውን ፈተና ማለፍ ሲችሉ በቀጣይ መደበኛ ተማሪ ሆነው ወደ ፌሽማን ይቀላቀላሉ።
ትምህርት ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው የመቁረጫ ነጥብ በሁሉም አማራጮች ማለትም #በግል እና #በመንግስት ተቋማት የሬሜዲያል ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 30 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል፤ ይህም ማለት 210 ከ700፣ 180 ከ600 እና 150 ከ500 ማስመዝገብ አለባቸው።
በመንግስት ተቋማት (ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) በዩኒቨርሲቲ ተመድበው የሬሜዲያል ፕሮግራም የሚከታተሉ በ #ተፈጥሮ_ሳይንስ የመደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች መቁረጫው 255 ከ700 ነው። የሴት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች መቁረጫው ደግሞ 234 ከ700 ነው።
በዩኒቨርሲቲ ተመድበው ለሚማሩ የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥቡ 218 ከ600 ሲሆን ፤ የሴት ተማሪዎች መቁረጫው 200 ከ600 ነው።
እንደ ትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ከሆነ ዘንድሮ 164,242 የሬሜዲያል ተማሪዎች በግል እና በመንግሥት ተቋማት ገብተው ይማራሉ።
#ማስታወሻ ፦ የሬሜዲያል መቁረጫ ነጥብ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።
በሌላ በኩል ፤ በ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈትነው የማለፊያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ምደባ ከትላንት ጀምሮ ይፋ የተደረገ ሲሆን የምደባ መመልከቻው ፦በድረገፅ https://result.ethernet.edu.et/
የቴሌግራም ቦት @moestudentbot መሆኑን ለማስታወስ እንወዳለን።
#TikvahEthiopia

አሁን ባሉበት ይችላሉ!!
ባንክ መሄድ ሳይጠበቅብዎ ባሉበት ሆነው ለክፍያ እና ሌሎች አገልግሎት አማራጭዎ በግሎባል ሞባይል ባንኪንግ ቀላል ሆኗል፡፡
መተግበሪያውን ከጎግል ፕሌይ ስቶር በማውረድ በአቅራቢያዎ በሚገኝ ቅርንጫፎቻችን ማስጀመር ይችላሉ፡፡ መተግበሪያውን በቴሌግራም ቻናላችን ያገኙታል፡፡
ቴሌግራም ቻናላችንን ለማግኘት
https://t.iss.one/Globalbankethiopia123
#GBEmobile #Digitalbanking #Finance #Globalbankethiopia