#Amhara #Afar #Tigray #ICRC #ERCS
በአማራ እና በአፋር ክልሎች ውስጥ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የተፈናቀሉ ዜጎች ህይወታቸውን ለማዳን ቤታቸውን ጥለው በመሠደዳቸው በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ።
ተፈናቃዮቹ ምቹ ማረፊያ ባለማግኘታቸው በተጨናነቁ መጠለያዎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ እንዲሁም በማንኛውም ክፍት ቦታ ላይ ለመተኛት ተገደዋል፡፡
ተፈናቃዮቹ በተሰደዱበት አካባቢ በሚኑሩ ማህበረሰቦች ቢደገፉም፣ በቂ የውሀና የምግብ አቅርቦት ይሻሉ።
የጤና ተደራሽነት በአሁኑ ወቅት ዋነኛው የሰብአዊ ጉዳይ ሆኗል።
በቅርቡ በአማራ እና በአፋር ክልሎች የተካሄደውን ግጭት ተከትሎ ፣ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ወደ ጤና ተቋማት የሚመጡ የቆሰሉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው።
የአለምአቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ጋር በመተባበር በአማራና አፋር ክልሎች የመጠለያ፣ የንጽህና መጠበቂያ፣ የጤና አገልግሎትና ሌሎች የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፎችን እያደረገ ነው፡፡
ከነሐሴ ወር መጀመሪያ እስካሁን ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በትግራይ፣ አማራና አፋር ክልሎች ለ100,600 ሰዎች ፦
- ብርድልብሶች፣
- የማብሰያ ዕቃዎች
- የፋኖስ መብራቶች የመሳሰሉትን ቁሳቁሶች ስርጭት አድርጓል፡፡
በትግራይ ክልል በሚገኙ 18 ሆስፒታሎች ለ145,000 ህሙማንና የህክምና ባለሙያዎች የምግብ ድጋፍ የተደረገ ሲሆን በአማራ ክልል ለሚገኙ 13 ሆስፒታሎች ደግሞ 2000 ቁስለኞችን ለማከም የሚበቃ መድሐኒት ተሠራጭቷል፡፡
በተጨማሪም በአፋር ለሚገኘው የዱፕቲ ጠቅላላ ሆስፒታልና በትራይ የሱሁልና ሽራሮ ሆስፒታሎችን ጨምሮ በትግራይ ክልል የሚገኙ 14 የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ጣቢያዎችን መሠረተ ልማት መልሶ የመገንባት ስራም ተሠርቷል፡፡
ያንብቡ : telegra.ph/ERC-09-12
@tikvahethiopia

#ERCS
• የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የአምቡላንስ ሹፌር በታጣቂዎች ተገደለ።
• ማኅበሩ በባልደረባው ሞት የጥልቅ ሐዘን እንደተሰማው ገልጾ ግድያውን አውግዟል። ታጣቂ ሃይሎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም ማህበሩ ተማፅኗል።
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የሰሜን ጎንደር ቅርንጫፍ #የአምቡላስ_ሾፌር የነበረው አቶ መንግስት ምንይል ታጣቂ ሃይሎች በፈፀሙት ጥቃት ተገድለዋል።
ማህበሩ፤ ግድያውን በአፅንዖት አውግዟል።
አቶ መንግስት ምኒል በምዕራብ ደንቢያ ሰብዓዊ አገልግሎት በመስጠት ላይ የነበረና በሰብዓዊ ህይወት የማዳን ስራ ወልቃይት አዲ ረመፅ ሆስፒታል ተመድቦ አገልግሎት በመስጠት ላይ ነበር።
አቶ መንግስት አድዋ፣ ትግራይ ተሰማርተው በግጭት የተጎዱ ወገኖችን በማገዝ ላይ ከነበሩ 2 አምቡላንሶች አንዱን በማሽከርከር ከአድዋ ወደ ወልቃይት አዲ ረመፅ ሆስፒታል ቁስለኞችን ለማድረስ በተንቀሳቀሰበት ወቅት ቁስለኞቹን ጨምሮ በታጣቂ ሃይሎች በተፈፀመባቸው ጥቃት መገደላቸውን የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ገልጿል።
የአምቡላንስ ሹፌሩ አቶ መንግስት ምኒል የ40 ዓመት ጎልማሳ እና የሁለት ሴት ልጆች አባት ነበር።
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ አምቡላንስ በማሽከርከር ሰብኣዊ አገልግሎት በመስጠት ላይ በነበረው ባደረባው ግድያ ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማው ገልጿል።
በመላ ሀገሪቱ በሰብዓዊ አገልግሎት የተሰማሩ የቀይ መስቀል ማኅበር ሠራተኞችና በጎ ፈቃደኞችን ሰብዓዊ ተግባራቸውን በገለልተኝነት እና በአለማዳላት መንፈስ በነፃነት ተንቀሳቅሰው መስራት እንዲችሉ፣ እንዲሁም ደህንነታቸው እንዲጠበቅ፣ ታጣቂ ሃይሎች ከእንደዚህ አይነት ጥቃት እንዲቆጠቡ ተማፅኗል።