#BekeleGerba #USA🇺🇸
አቶ በቀለ ገርባ በአሜሪካ ሀገር #ጥገኝነት መጠየቃቸውን አሳወቁ።
ለረዥም ዓመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ በግል እና በፓርቲ ደረጃ ተሳታፊ የነበሩት የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ ፓርቲ ተቀዳመ ምክትል ፕሬዜዳንት አቶ በቀለ ገርባ በፓርቲያቸው የነበራቸውን ተሳትፎ አብቅተው በአሜሪካ ጥገኝነት መጠየቃቸውን ለቢቢሲ አማርኛ ክፍል ተናገሩ።
አቶ በቀለ ፤ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ያለው ፖለቲካዊ ሁኔታ " በሰላማዊ መንገድ ለመታገልም ሆነ በግል በነጻነት መኖር " አሳሳቢ በመሆኑ በሄዱበት አሜሪካ ጥገኝነት መጠየቃቸውን ገልጸዋል።
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ተቀዳሚ ምክትል የሆኑት አቶ በቀለ፣ በውጭ አገር ሆነው ሥልጣኑን ይዘው መቀጠጣለቸው ጠቃሚ ስላልሆነ እራሳቸውን ከፓርቲው ለማግለል መወሰናቸውን ተናግረዋል።
አቶ በቀለ ገርባ ፤ ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ ተፈጥሮ የነበረውን ሁከት ተከትሎ በቁጥጥር ሥር ውለው ለ18 ወራት በእስር ላይ ቆይተው ከተለቀቁ በኋላ ወደ አሜሪካ ተጉዘዋል። አሜሪካ ከሄዱ 1 ዓመት ከሶስት ወር ሆኗቸዋል።
አቶ በቀለ ከእስር ከወጡ በኋላ ወደ አሜሪካ ሲጓዙ ዓላማቸው የእርሳቸውን ከእስር መለቀቅ ሲጠይቅ ለነበረው የዳያስፖራ ማኅብረሰብ ምስጋና ለማቅረብ ነበር።
ነገር ግን አሜሪካ በቆዩባቸው ያለፉት 15 ወራት በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ በመቀየሩ " ወደዚያ አገር መመለሱ አስፈላጊ መስሎ አልታየኝም " በማለት እዛው ጥገኝነት መጠየቃቸውን እና ከፓርቲው ኃላፊነትም እራሳቸውን ማግለላቸውን ለቢቢ አማርኛ አገልግሎት በሰጡት ቃል ገልጸዋል።
More - https://telegra.ph/BBC-08-28-2
@tikvahethiopia

#USA
የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ማይክ ሐመር ከነሐሴ 22 እስከ ጳጉሜ 3 ድረስ በኬንያ እና በኢትዮጵያ ቆይታ እንደሚያደርጉ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል።
በናይኖቢ እንዲሁም በአዲስ አበባ ቆይታቸው ከሀገራቱ ባለስልጣናት፣ ከአፍሪካ ህብረት፣ ከልማት ድርጅት ባለስልጣን እና ሌሎች ዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር ይነጋገራሉ ተብሏል።
ሐመር በአዲስ አበባ በሚያደርጉት ቆይታ፣ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ያሉትን ግጭቶች በድርድር እንዲቋጩ እና ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት እንዳይደርስ እና ከለላ እንዲያገኙ ግፊት ያደርጋሉ ተብሏል።
ሐመር፣ በሱዳን ቀውስ እና ጦርነቱን ለማስቆም እየተደረጉ በሚገኙ ቀጠናዊና ዓለማቀፋዊ ጥረቶች ላይም ከአካባቢዉ አገራት፤ ከአፍሪቃ ኅብረትና ከኢጋድ መሪዎች ጋር እንደሚመክሩ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ገልጿል።
የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመድ ከዚህ ቀደም በተለይም በትግራይ ከነስቶ ወደ አፋር እና አማራ ክልል የተስፋፋውን የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ሰላማዊ መፍትሄ እንዲበጅለት በተደጋጋሚ ወደ ኢትዮጵያ እና ጎረቤት ሀገራት መምጣታቸው የሚዘነጋ አይደለም።

#ETHIOPIA #USA
ዓለም አቀፍ ለጋሾች ያቆሙት የምግብ ርዳታ ይቀጥል ዘንድ በጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና በአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን መካከል የስልክ ውይይት ተደረገ።
የሚኒስቴር መ/ቤቱ ቃል አቀባይ ማት ሚለር እንዳሳወቁት ብሊንከን ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር የስልክ ውይይት አድርገዋል።
በዚህ ውይይት ወቅትም ፤ ዓለም አቀፍ ለጋሾች ያቆሙት የምግብ ርዳታ ይቀጥል ዘንድ ፣ የሰብአዊ ሁኔታ ቁጥጥር ተሻሽሎ ስለሚቀጥልበት አሠራር ላይ ተወያይተዋል።
በተጨማሪ አንተኒ ብሊንከን፣ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል ያለው ሁኔታ " አሳስቦኛል " ሲሉ ተናግረዋል።
በሁለቱ ክልሎቹ ያሉትን ችግሮች #በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት፣ የፖለቲካ ውይይትንና የሰብአዊ መብቶች መከበር አስፈላጊነትን አጽንዖት ሰጥተውበታል።
እውነተኛ ፣ ታማኝ እና ሁሉን አካታች የሽግግር ፍትሕ ሒደትን ለመፍጠር እየተከናወነ ያለውን ሥራ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመልካም እንደተቀበሉት ተጠቁሟል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከንና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ፣ በአፍሪካ ቀንድ ስለሚታየው የጸጥታ ተግዳሮት፣ እንዲሁም አንዲት፣ ሰላማዊት እና የበለጸገች ኢትዮጵያን ለማየት ያላቸውን የጋራ ግብ አስመልክቶም እንደተወያዩ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መ/ቤትን ዋቢ በማድረግ ቪኦኤ ዘግቧል።