TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የትግራይ አካባቢዎች ከፍተኛ የሃዘን ድባብ ውስጥ ናቸው።
ጥቅምት 2 በይፋ የታወጀው የትግራይ ሰማእታት የሃዘንና የክብር ቀን ስነ-ሰርአት ተከትሎ የክልሉ ከተሞችና ገጠሮች በከፍተኛ የሃዘን ድባብ ውስጥ ይገኛሉ።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ በትግራይ ያለው የሃዘንና የመርዶ ስነ-ሰርአትና ተዛማጅ ጉዳዮች አፈፃፀም በሚከተለው ሪፓርታዥ አጋርቶናል።
ዓርብ ጥቅምት 2/2016 ዓ.ም ከሰዓት በኃላ በክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት ጌታቸው ረዳ የሃዘንና የክብር ስነ-ሰርአቱ መታወጅ ተከትሎ ከ1:00 ሰዓት አመሻሽ ጀምሮ ከማይጨው እስከ ሸራሮ በ500 ኪሎ ሜትር ርቀት አከባቢ የሚገኙ ከተሞች ሰማእታት የሚዘክር ሻማ ያበሩ ሲሆን ፤ በሌሊቱ በቤተከርስትያንና በመስጊዶች ቅዳሴና ፀሎት እንዲሁም ዱዓ ሲያደርጉ አድረዋል።
ጥቅምት 3 ጠዋት 12:00 ሰዓት የክልሉ ባንዴራ ዝቅ ብሎ ሲውለበለብ ፤ በመቐለ ጥቅምት 3 ከምሽቱ 1:00 ሰማእታትዋ ለማሰብ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕረዚደንትና ካቤኔያቸው ፣ የህወሓት ሊቀመንበርና የከተማው ነዋሪ በተገኘበት ጥዋፍ አብርታለች።
የሃዘንና የክብር ስነ-ሰርአቱ ለማስፈፀም የወጣ መመሪያ የሚከለክላቸው ነገሮች ተፈፃሚነታቸው ከጥቅምት 3 ጀምሮ መሆኑ በመመሪያ የተቀመጠ ቢሆንም እንደ መጠጥ ቤት የመሳሰሉ አገልግሎት ሰጪዎች በራሳቸው ፍላጎት ጥቅምት 2 ከሰአት በኃላ ጀምሮ ዘግተዋል።
ጥቅምት 2 ከሌሊቱ 8:00 ሰዓት ጀምሮ በተሰው ቤተሰቦች መኖሪያ ይፋዊ የመርዶ ስነ-ሰርአት የተካሄደ ሲሆን የመርዶ ስነ-ሰርአቱ የሚያከናውኑት ፦
- የአገር ሽማግሌ
- የሃይማኖት አባቶች
- ታጋዩ ሲሰዋ በአጠገቡ የነበረ የአይን ምስክር
- ከነባር ታጋይ የተወጣጡ ኮሚቴ ሲሆኑ ቤተሰቡ ሲያረዱ ከመንግስት የተላከ የክብር መግለጫ የምስክር ወረቀትና የትግራይ ባንዴራ በመስጠት ነው።
መርዶ ከተነገረ በኃላ የተሰዋ ታጋይ ቤተሰብ ኮሚቴው አረጋግቶ በማጀብ እና በመምራት መርዶ ወደ ተነገሩ ሌሎች ቤተሰቦች ጋር በማቀላቀል ወደ መሰባሰብያ ቦታ ወስደዋቸዋል።
ከጥዋቱ 12:30 በየአከባቢው መርዶ የተነገረው ሁሉም ወደየ መገናኛ ቦታ ተሰባሰበ። በቦታው ደርሶ ልክ 1:00 ሰአት ከጠዋቱ በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ የሚኖር ትግራዋይ በሚድያ የሚመራ የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት ተደርጓል።
ከህሊና ፀሎት በኋላ የተሰዋ ቤተሰብ አባል እንደየ እምነቱ ወደ ሚመለከተው የማምለክያ ቦታ በህዝብ ታጅቦ ተጓዘ።
በእምነት ማስፈፀምያ ቦታ እንደየ እምነቱ የሚሰጠው ፀሎተ ፍትሃት፣ ዱዓና መፅናኛ የሃይማኖት አስተምህሮ ከተሰጠ በኃላ ከጊዚያዊ አስተዳደሩ የተላከ መልእክት በንባብ ቀርቧል።
በቤተ እምነት የተካሄደው ፍፃሜ ከተጠቃለለ በኃላ የሰማእታት ቤተሰብ በህዝቡ በመታጀብ ወደየ ቤታቸው ተመልሰዋል።
በየሃይማኖት ማምለኪያ ቦታዎቹ ከሚፈፀም ስነ-ሰርአት ጎን ለጎን በትግራይና ድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን በቀጥታ ስርጭት የተላለፈ በሰማእታት የመታሰብያ ሃወልት በክብር መዝገብ ፅሁፍ የማኖርና የአበባ ጉንጉን የማስቀመጥ ስነ-ሰርአት ተከናውኗል።
መቐለ ጨምሮ ማይጨው፣ መኾኒ፣ ዓዲጉዶም፣ ውቕሮ፣ ዓብዪ ዓዲ፣ ዓዲግራት፣ ዓድዋ፣ አክሱም፣ ሽረ፣ ሸራሮና ሌሎች ከተሞች በከፍተኛ የሃዘን ድባብ ውስጥ ሲሆኑ እንደ ባንክ የመሳሰሉ አገልግሎት ሰጪዎች የሃዘንና የክብር ቀን ስነ-ሰርአቱ ለማስፈፀም አስመልክቶ በወጣ መመሪያ መስረት ዝግ ሆነው ውለዋል።
የትግራይ ሰማእታት የሃዘንና የክብር ቀን ስነ-ሰርአት በተለያዩ ፕሮግራሞች በመቀጠል ጥቅምት 6 በህዝባዊ ሰልፍ እንደሚጠቃለል የወጣው መርሃ ግብር ያስረዳል።
መረጃው ተዘጋጅቶ የተላከው ከመቐለ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነው።
ፎቶ፦ ከላይ ተያይዟል
@tikvahethiopia

ትክክለኛ የማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይከተሉ!
=====================
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ስምና አርማ በመጠቀም በሚከፈቱ ሀሰተኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች የተለያዩ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት የሌብነት ተግባር የሚፈፅሙ አጭበርባሪዎች አሉ፡፡
በመሆኑም የባንኩን ትክክለኛ የማኅበራዊ ትስስር ገፆች ብቻ በመከተል ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ ያግኙ፤ ከአጭበርባሪዎች ይጠበቁ!
የባንኩ ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች፡
• Facebook፡- https://www.facebook.com/combanketh
• YouTube፡- https://www.youtube.com/commercialbankofethiopia
• LinkedIn፡- https://www.linkedin.com/company/commercialbankofethiopia
• Twitter፡- https://twitter.com/combankethiopia
• Telegram፡- https://t.iss.one/combankethofficial
• Instagram፡- https://www.instagram.com/commercialbankofethiopia/
• tiktok:- https://www.tiktok.com/@commercialbankofethiopia

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#CARD: ይህን የ4 ደቂቃ መረጃ ዳሰሳ ጥናት በመሙላት የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመግታት የምንሰራው የግንዛቤ ማስጨበጫ መመርያ ያግዙ።
👉 https://09u34jhg43098.typeform.com/to/nToapX9c
(የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል)

ነዳጅ ከ5% በላይ ጨመረ።
የዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ ከፍተኛ ጭማሪ እያሳየ ይገኛል።
የአንድ በርሜል ብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በ5.69% መጨመሩ ተነግሯል።
በዚህም በበርሜል 90.89 የአሜሪካ ዶላር ገብቷል።
በአሜሪካ ነዳጅ ገበያ እንደመለኪያ በሚታየው ዌስት ቴክሳስ ኢንተርሚዴትም አንድ በርሜል ነዳጅ ከቀናት በፊት ከነበረው በ5.77 % ጨምሯል።
ከሳምንት በፊት የጀመረው የእስራኤል እና ሃማስ ጦርነት በተለይ በነዳጅ ዋጋ ላይ ከፍተኛ የሆነ ተፅእኖ እንደሚያሳድር መነገሩ አይዘነጋም።
ግጭቱ ከቀን ወደ ቀን እየባሰበት በመሆኑ ከፍተኛ የነዳጅ አምራች የሆነው የመካከለኛ ምስራቅ ቀጠና ላይ አለመረጋጋት ፈጥሮ የነዳጅ ዋጋ አሁን ካለውንም እንዲንር ያደርገዋል ተብሎ ተሰግቷል።

ሚንስትሩ ለትግራይ ህዝብ የመፅናኛ መልእክት አስተላለፉ።
የአገር መከላከያ ሚንስትር ሚኒስቴር ዶ/ር አብራሃም በላይ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው " ብርታትና መፅናናት ለትግራይ ህዝብ እመኛለሁ " ብለዋል።
" በአሁኑ ወቅት ህዝባችን በተለይ ደግሞ የትግራይ እናት በማለፍ ላይ ያለሸው ሁኔታ ከባድና መራር ነው " ያሉት ዶ/ር አብራሃም " ፅናቱ ይስጥሽ !! ህዝቤ ፅናቱ ይስጥህ " ሲሉ አክለዋል።
ዶ/ር አብራሃም በላይ በመልእክታቸው ማጠቃለያ " ፀንተን ለትግራይ መልሶ ግንባታ እና ትግራይ እንድታገግም እንረባረብ " ብለዋል።
በትግራይ ከጥቅምት 3 አስከ 5/2016 ለሶስት ቀናት የሚቆይ የሃዘንና የክብር ቀን ስነ-ሰርአት ታውጆ መላው ክልሉ በከፍተኛ የሃዘን ድባብ ውስጥ እንደሚገኝ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተከታታይ ዘገባዎች በማቅረብ ላይ ይገኛል።

#DrTedrosAdhanom
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሓኖም የትግራይ ሰማእታት የሃዘንና የክብር ቀን ስነ-ሰርዓት በማስመልከት የማፅናኛ መልእክት አስተላለፉ።
ዶ/ር ቴድሮስ አድሓኖም በመፅናኛ መልእክታቸው " ትግራይ ፅናቱ ይስጥሽ። አይዞን " ብለዋል።

#ብሔራዊ_ፈተና
ባለፉት ሁለት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናዎች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተማሪዎች ተፈትነው ያለፉት ግን እጅግ በጣም ጥቂት ናቸው።
ምን የተቀረ ነገር ኖሮ ነው ? የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ከሰሞኑን በብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው ማብራሪያ ሰጥታዋል።
ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፦
" የፈተናው ክብደ እና ቅለት ከሆነ ምንም የተቀየረ ነገር የለም።
የፈተና አሰጣጥ እና ዝግጅት ሂደት አለ፤ እራሱን የቻለ ሳይንስ አለው በጣም እንዳይከብድም በጣም እንዳይቀልም።
እስከ ዛሬ ሲሰራ ከነበረው ምንም የተለየ ነገር የለም። የተለየው ፈተና አሰጣጡ ነው።
ፈተና አሰጣጡ ያመጣው ለውጥ ምንድነው ከተባለ ፤ ከዚህ በፊት ፈተናዎች በየትምህርት ቤት ነው የሚሰጡት ፈተና መታተም ከጀመረ ጊዜ ጀምሮ ፣ ከወጣ ጊዜ ጀምሮ ፈተናዎቹ ይሰረቃሉ።
ፈተና ሲሰረቅ የነበረው በተደራጀ መልክ ነው በክልሎች ፈታኞች በየክልሉ ሲሄዱ ትልቅ ግብዣ ተደርጎ ጉቦ ተሰጥቷቸው ተማሪዎቹ እንዲኮራረጁ ይደረጋል። ውጤቱ ትርጉም ያለው አልነበረም።
እኔ ትምህርት ሚኒስቴር የመጣሁ ጊዜ በሁለተኛው ሳምንት ፈተና ሰጥተን ነበር በድሮው አሰጣት ፎርማት ያኔ ነው የማለፊያ ውጤት 50 በመቶ ነው ብለን ፖሊሲ ያደረግነው ፣በወቅቱ ፈተና አሰጣጡን አልቀየርንም ነበር ያኔ ያለፈው 48% ነው። አንዳንድ ክልሎች 70-80 በመቶ አሳልፈዋል።
በምንም አይነት የተማሪዎቹ ችሎታና ብቃት አይደለም። ... መሰረቅ መኮረጁን ለማወቅ ዳታውን ከተታትሎ ማግኘት ይቻላል፤ ግልፅ ነው።
ፈተናው እራሱ የተማሪዎች ችሎታና ብቃት መለኪያ አልነበረም። ያንን ነው የቀየርነው። ከምንም በፊት የሰራነው በተማሪዎች ጭንቅላት ውስጥ በስርቆት፣ በማጭበርበር ፣ ሌላ ሰው በማስፈተን ፣ በመኮረጅ የሚገኝ ትምህርት የለም የሚል ነው። ይሄን አውቀው እንደ ችሎታቸው እንዲያጠኑ ነው ያደረግነው።
የዛ ውጤት፣ እንደ ሀገር ያለንበትን ልክ ነው ያሳወቀን። በዚህም ይሄ ነው የትምህርት ስርዓቱ ካልን በኃላ ሪፎርሞችን በተግባር አውለን አንድ ትውልድ ቢበላሽብን ቀጣዩን እንዴት እናድናለን ብለን ነው እየሰራን ያለነው። "
እንደ ትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ፤ በ2014 እና በ2015 በድምሩ 1,741,619 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውስደዋል። ከነዚህ ውስጥ ያለፉት በድምሩ 57,301 ተፈታኞች ናቸው።
በዚህ ልክ ተፈታኝ ተማሪዎች መውደቃቸው ዜጎችን ያስደነገጠ ቢሆንም ከነዚህ ተማሪዎች በፊትም ፈተናው አሰጣጡ በዚህ መንገድ ቢሆን ውጤቱ ከዚህ እንደማይለይና የትምህርት ስርዓቱ ውድቀት ከታች ጀምሮ የመጣ እንደሆነ የሚገልጹ በርካቶች ናቸው።
ለዚህ ውድቀት ደግሞ ሁሉም ባለድርሻ ኃላፊነት እንዳለበትና ተማሪዎቹን ከሚያስተምሯቸው መምህራን ብቃት አንስቶ ፣ የትምህርት ቤቶች የጥራት ጉዳይ፣ የግብዓት አቅርቦት ሁሉ ሊፈተሽ የሚገባው እንደሆነ የሚያመላክት መሆኑ ይነሳል።

#SafaricomEthiopia
በሁለት አማራጮች የቀረቡልንን የYoutube ጥቅሎች በመግዛት ማርሻችንን ወደ ላቀ መዝናናት እንቀይር ፤ ፈታ ዘና እያለን እንዋል!
#SafaricomEthiopia
#FurtherAheadTogether