TIKVAH-ETHIOPIA
#ትግራይ " የሚቋረጥ የትራንስፓርት አገልግሎት የለም ፤ ባንኮች ግን ለሁለት ቀን ዝግ ይሆናሉ " - የትግራይ አርበኞች ኮሚሽን ምክር ቤት የትግራይ የአርበኞች ኮሚሽን ም/ቤቱ በትግራይ ክልል ደረጃ የታወጀው " የሰማእታት የሃዘንና የክብር ቀን " ስነ-ሰርአት አስመልክቶ መስከረም 29/2016 ዓ.ም ባካሄደው ሁለተኛ ስብሰባው የህክምናና የትራንስፓርት አገልግሎት የማይቋረጥ ሲሆን የባንከ አገልግሎት ግን…
#ትግራይ
" በጦርነቱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ፣ መምህራን ፣ አምራች አርሶ አደሮች፣ ሃኪሞችን ጨምሮ ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች ተሰውተዋል " - ጊዜያዊ አስተዳደሩ
በተለያዩ የማህበራዊ የትስስር ገፆች በትግራዩ ደም አፋሳሽ ጦርነት ስለ ተሰው ታጋዮች " እንደ ተራ ነገር የሚነገረው ቁጥር የሃቅ መሰረት ስለሌለው ትርጉም አንሰጠውም " አሉ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት ጌታቸው ረዳ።
ፕረዚደንቱ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ሰማእታት የሃዘንና የክብር ቀን ስነ-ሰርአት በይፋ መታወጅ አስመልክተው ጥቅምት 2/2016 ዓ.ም ለክልሉ የመንግስት ፣ የግልና የውጭ ሚድያዎች ሰፊ ቃለ-መጠይቅና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ፕረዚደንት ጌታቸው ረዳ ፤ በክልሉ በተካሄደው ደም አፋሳሽና እልህ አስጨራሽ ጦርነት የተሰው ታጋዮች ቁጥር እንዲገልፁ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት መልስ " ... በትግሉ ስለተሰውት ታጋዮች ቁጥር ብዙ ተረት ነው የሚወራው ፤ የተሰውት ታጋዮች ቁጠር እንገልፃለን። ለጊዜው ግን መግለፁ አስፈላጊ ሆኖ ስላልታየን እናቆየዋለን " ብለዋል።
" ... ለትግራይ ህልውና የተከፈለ ዋጋ የሚመጥነው ደረጃና ዋጋ መስጠት አለብን ሲባል ለያንዳንዱ የተሰዋ ታጋይ ፤ ለያንዳንዱ የተሰዋበት ቤተሰብ የክብር የምስክር ወረቀት ልከናል " ያሉት አቶ ጌታቸው ፤ " የተሰውት ታጋዮች ቁጥር በእጃችን ይገኛል። ከቁጥሩ ባሻገር ግን እጅግ ከባድና ውድ ዋጋ ከፍለናል። ለህልውናችን የተከፈለ በመሆኑም ግን የሚያስቆጨን አይሆንም ሊባል ይችላል " ሲሉ አክለዋል።
አቶ ጌታቸው ፤ " ብዙ ልጆቻችን ከፍለናል። ጠላቶች (ፕሬዜዳንቱ ጠላቶች ያሏቸውን በስም አልገለጿቸውም) የኛ የመስዋእት ኪሳራ በማብዛት የነሱ ለማሳነስ እንደማነፃፀሪያ በማቅረብ ብዙ ይናገራሉ። በበኩሌ አሁን ካለው የተሰዋ ታጋይ ቁጥር ሩብ ፤ ከሩብ በታች ፤ አንድ መቶኛው እንኳን ብንከፍል ዋጋው ከባድ ነው የሚል እምነት አለኝ። " ብለዋል።
" አልተሳካልንም እንጂ ያለ አንድ ታጋይና ያለ አንድ ወጣት መስዋእት ፣ ራሳችን በራሳችን የማስተዳደር መብታችን የምናረጋግጥበት ዕድል ቢኖር እመርጥ ነበር " ሲሉ አክለዋል።
ፕሬዜዳንቱ በስም ያልጠሯቸውና " ጠላቶች " ሲሉ የጠሯቸው ኃይሎች " አሁን ላይ መጥራት በጀመሩት የተዛባና የተጋነነ ቁጥር በመደናገር ሌላው ያልሆነ ቁጥር ሲጠራ ቢውል ለኔ 20 ሺህ ተባለ ፣ 10 ሺህ ተባለ ፣ ህልውናችን ለማረጋገጥ አንድ ሰው ይሰዋ 20 ሺህ ዋጋው እጅግ ከባድ ነው " ብለዋል።
" በተሰውት ታጋዮች ዝርዝር ፦
- የዩኒቨርስቲ መምህራንና ተማሪዎች ፣
- ጥሩ አምራች አርሶ አደሮች
- ሃኪሞች ሁሉም አይነት የህብረተሰብ ክፍሎች አሉ። በአጠቃላይ ትግራይን በሰላም ጊዜ ወደ ተሻለ የእድገት ደረጃ የማሸጋገር አቅም የነበራቸው በመስዋእትነት አጥተናል " ያሉት አቶ ጌታቸው ፤ " ይህንን መስዋእትነት ዋጋ መስጠት እንዳለ ሆኖ ፤ ቁጥሩ ጠላት በሚለው ደረጃ እንዳልሆነ መረዳቱ ስጋታችን ቀንሶ ያረጋጋናል " ማለታቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።
የትግራይ ሰማእታት የሃዘንና የክብር ቀን ሰነ-ሰርዓት ከጥቅምት 3 አስከ 5 በተለያዩ ዝግጅቶች ታጅቦ በመካሄድ ፤ ጥቅምት 6/2016 ዓ.ም " በሃዘን አንገታችን እንደፋም " በሚል መሪ ቃል በሚካሄድ የህዝብ ሰልፍ እንደሚጠቃለል ከወጣው መርሃ ግብር ለመረዳት ተችሏል።
መረጃው በቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የተዘጋጀ ነው።
@tikvahethiopia

Don't miss out! You have 3 days to submit your application for the Jasiri Talent Investor program. If you're considering applying, now is the time to go to jasiri.org/application and get your application in before the deadline. #Jasiri4Africa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#CARD: ይህን የ4 ደቂቃ መረጃ ዳሰሳ ጥናት በመሙላት የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመግታት የምንሰራው የግንዛቤ ማስጨበጫ መመርያ ያግዙ።
👉 https://09u34jhg43098.typeform.com/to/nToapX9c
(የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል)

#ወልቂጤ
- " በሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል። ቤቶች ተቃጥለዋል " - የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር
- " በቦታው አድማ የመበተን ሥራ እየተሰራ ነው " - የጉራጌ ዞን ፓሊስ ኮሚሽን
- " ግጭቱ እንዲባባስ በሚፈልጉ አካላት ንብረት ወድሟል፣ በሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል " - የጉራጌ ዞን ኮማንድ ፓስት
አዲስ በተዋቀረው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወልቂጤ ከተማና ቀቤና ልዩ ወረዳ መከከል በተቀሰቀሰ ግጭት በንጹሐን ላይ አካላዊ ጉዳት መድረሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።
ነዋሪዎቹ በገለጹት መሠረት፣ ከጥቅምት 2 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በተቀሰቀሰው ግጭት በንጹሐን ላይ ጉዳት ደርሷል፣ ቤት ተቃጥሏል ብለዋል።
ምን ያህል ሰዎች እንደሞቱ፣ እንደቆሰሉ፣ ተኩስ እንደቆመና እንዳልቆመ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረቡላቸው አንድ የአካባቢው ነዋሪ፣ " አንድ የፌደራል ፖሊስ አባል በጥይት ተመቶ ሞቷል። እኔ ባለኝ መረጃ መሠረት 25 በላይ ሲቭል ሰዎች ቆስለዋል። ከትላንት 7 ጀምሮ ዛሬ ጥዋት 2 ሰዓት ድረስ ተኩስ ነበር አሁን ቆማል " ብለዋል።
ጉዳዩን በተመለከተ ማብራሪያ እንዲሰጡ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸውና ለደኅንነታቸው ሲባል ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ባለስልጣን፣ " በሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል። ቤቶች ተቃጥለዋል " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
ግጭቱ በቀቤና ልዩ ወረዳና በወልቂጤ ከተማ የወሰን ይገባኛል ጥያቄን መሠረት በማድረጉ ከዚህ በፊትም አለመረጋጋት እንደነበር ገልጸው፣ አሁንም እንዳይባባስ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ በጥምረት እየሰሩ ነው ብለዋል።
ተመሳሳይ ጥያቄ የቀረበላቸው የጉራጌ ዞን ፓሊስ ኮሚሽን ዋና ኢኒስፔክተር ገና በበኩላቹው፣ " በቦታው አድማ የመበተን ሥራ እየተሰራ ነው " ብለዋል።
የጉራጌ ዞን ኮማንድ ፖስት ጥቅምት 03 ቀን 2016 ዓ.ም ጉዳያ አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ፣ " በቀን 02 ቀን 2016 ዓ.ም በወልቂጤ ከተማ የተቀሰቀሰው አመጽ እንዲበርድ የጸጥታ ኃይላት በሆደ ሰፊነት ግጭቱ እንዲበርድ እና የሚደርሰው ቁሳዊና ሰብዓዊ ጉዳት ለመቀነስ በኃላፊነት ሲሰራ እንደነበር ይታወቃል " ብሏል።
አክሎም ፣ " ይህን እንጅ ግጭቱ እንዲባባስ በሚፈልጉ አካላት ንብረት ወድሟል፣ በሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል " ሲል አስታውቋል።
" በዜጎች ላይ የሚደርሰው አካላዊና ስነልቦናዊ ጉዳት ለመቀነስ የዞኑ ኮማንድ የሰዓት እላፊ ገደብ እንዲጣል ወስኗል " ያለው መግለጫው፣ " በመሆኑም ከዛሬ ጥቅምት 03/2016 ጀምሮ በተሽከርካሪዎች እና በሰዎች እንቅስቃሴ ላይ የሰዓት ገደብ ተጥሏል " ሲል አስገንዝቧል።
" በዚህ መሰረት የትኛውም ተሽከርካሪ ማለትም ፦
- ሞተር ሳይክል፣
- ባለሶስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ)፣
- አነስተኛም ሆነ ከፍተኛ የህዝብ አመላላሽ ተሽከርካሪዎች እንዲሁም ሰዎች ላይ ከ11:00 እስከ ጠዋት 1:00 ድረስ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሏል " ብሏል።
መረጃው በአዲስ አበባ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

#ትግራይ " በጦርነቱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ፣ መምህራን ፣ አምራች አርሶ አደሮች፣ ሃኪሞችን ጨምሮ ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች ተሰውተዋል " - ጊዜያዊ አስተዳደሩ በተለያዩ የማህበራዊ የትስስር ገፆች በትግራዩ ደም አፋሳሽ ጦርነት ስለ ተሰው ታጋዮች " እንደ ተራ ነገር የሚነገረው ቁጥር የሃቅ መሰረት ስለሌለው ትርጉም አንሰጠውም " አሉ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት ጌታቸው ረዳ።…
" ሽበት እና ክህነት የማይከበርበት ዘመን ላይ ደርሰን ለዚህ ኀዘን በቅተናል " - ቅዱስነታቸው
ብፁዕ ወቅዱስ #አቡነ_ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በትግራይ ክልል በተካሔደው ጦርነት ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች እየተከናወነ ያለውን የኀዘን ሥነ ሥርዓት በማስመለክት አባታዊ የማጽናኛ መልእክት አስተላለፉ።
ከቅዱስነታቸው መልዕክት የተወሰደ ፦
" ዛሬ በትግራይ ክልል እየተዘከሩ ስላሉ ወገኖች በእጅጉ ማዘናችንን እንገልጣለን ።
ይህ እንዳይመጣ ብዙ ተማጽኖ ስናቀርብ የነበረ ቢሆንም ሽበት እና ክህነት የማይከበርበት ዘመን ላይ ደርሰን ለዚህ ኀዘን በቅተናል።
ዛሬ በትግራይ ክልል የማይለቀስበት ቤት የለም። የተሰዉት ልጆቻችን በሕይወተ ሥጋ ኖረው ቢሆን ብዙ ታሪክ መሥራት ይችሉ የነበረ ቢሆንም እነዚህ የቤተሰብና የቤተ ክርስቲያን እንዲሁም የሀገር ተስፋዎች በእሸት በመቅረታቸው በኀዘን በተሰበረ ልብ ሁነን ለነፍሳቸው ዕረፍተ መንግሥተ ሰማያትን እንዲሰጥልን እንጸልያለን።
በኀዘን የተጎዳችሁ አባቶችና እናቶችም ይህ ቢሆን ኖሮ እያላችሁ ራሳችሁን እንዳትጎዱ፤ የእናንተ መጎሳቆል የሞቱትን ቀና አያደርግምና ልባችሁን እንድታበረቱ እናሳስባለን ምክንያቱም መቃብር መጨረሻችን ያልሆነ የትንሣኤ ሕዝብ ነን፡፡
በምድር ላይ ስንኖር ማንም ለራሱ መከራን አያቅድምና የታቀዱ ቀኖችንም ለማለፍ ሕገ ተፈጥሮ አይፈቅድልንምና በሆነውና በሚሆነው ነገር ሁሉ ' እንደ ፈቃድህ ይሁን ' እያሉ ልብን ማሳረፍ ይገባል በማለት እንመክራለን፡፡ "
(ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል)

#Update
በትግራይ የተለያዩ ከተሞች በጦርነቱ ህይወታቸው ላለፈ ወገኖች የጥዋፍ ማብራት ስነስርዓት ተከናውኗል።
በተለይም በክልሉ መዲና መቐለ ሰማዕታት ሃውልት እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የመቐለ ነዋሪ በተገኘበት ነው ስነስርዓቱ የተከናወነው።
ፎቶ / ቪድዮ ፦ ከመቐለ፣ ዓዲግራት ፣ ማይጨው ፣ ሽረ እንዳስላሴ (በቴሌቪዥን ትግራይ)

አንጋፋዋ አርቲስት ሀሎ ዳዌ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች።
አርቲስት ሀሎ ዳዌ በኦሮሞ የኪነጥበብና የትግል ታሪክ ውስጥ አንጋፋ ከሆኑ አርቲስቶች አንዷ ናት።
አርቲስት ሀሎ ዳዌ ባደረባት ሕመም ምክንያት ለረጅም ጊዜ በህክምና ስትረዳ ብትቆይም ማገገም ባለመቻሏ ዛሬ በአዳማ በሚገኘው መኖሪያ ቤቷ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷን ከ #ኦቢኤን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
@tikvahethiopia
አርቲስት ሀሎ ዳዌ በኦሮሞ የኪነጥበብና የትግል ታሪክ ውስጥ አንጋፋ ከሆኑ አርቲስቶች አንዷ ናት።
አርቲስት ሀሎ ዳዌ ባደረባት ሕመም ምክንያት ለረጅም ጊዜ በህክምና ስትረዳ ብትቆይም ማገገም ባለመቻሏ ዛሬ በአዳማ በሚገኘው መኖሪያ ቤቷ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷን ከ #ኦቢኤን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የትግራይ አካባቢዎች ከፍተኛ የሃዘን ድባብ ውስጥ ናቸው።
ጥቅምት 2 በይፋ የታወጀው የትግራይ ሰማእታት የሃዘንና የክብር ቀን ስነ-ሰርአት ተከትሎ የክልሉ ከተሞችና ገጠሮች በከፍተኛ የሃዘን ድባብ ውስጥ ይገኛሉ።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ በትግራይ ያለው የሃዘንና የመርዶ ስነ-ሰርአትና ተዛማጅ ጉዳዮች አፈፃፀም በሚከተለው ሪፓርታዥ አጋርቶናል።
ዓርብ ጥቅምት 2/2016 ዓ.ም ከሰዓት በኃላ በክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት ጌታቸው ረዳ የሃዘንና የክብር ስነ-ሰርአቱ መታወጅ ተከትሎ ከ1:00 ሰዓት አመሻሽ ጀምሮ ከማይጨው እስከ ሸራሮ በ500 ኪሎ ሜትር ርቀት አከባቢ የሚገኙ ከተሞች ሰማእታት የሚዘክር ሻማ ያበሩ ሲሆን ፤ በሌሊቱ በቤተከርስትያንና በመስጊዶች ቅዳሴና ፀሎት እንዲሁም ዱዓ ሲያደርጉ አድረዋል።
ጥቅምት 3 ጠዋት 12:00 ሰዓት የክልሉ ባንዴራ ዝቅ ብሎ ሲውለበለብ ፤ በመቐለ ጥቅምት 3 ከምሽቱ 1:00 ሰማእታትዋ ለማሰብ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕረዚደንትና ካቤኔያቸው ፣ የህወሓት ሊቀመንበርና የከተማው ነዋሪ በተገኘበት ጥዋፍ አብርታለች።
የሃዘንና የክብር ስነ-ሰርአቱ ለማስፈፀም የወጣ መመሪያ የሚከለክላቸው ነገሮች ተፈፃሚነታቸው ከጥቅምት 3 ጀምሮ መሆኑ በመመሪያ የተቀመጠ ቢሆንም እንደ መጠጥ ቤት የመሳሰሉ አገልግሎት ሰጪዎች በራሳቸው ፍላጎት ጥቅምት 2 ከሰአት በኃላ ጀምሮ ዘግተዋል።
ጥቅምት 2 ከሌሊቱ 8:00 ሰዓት ጀምሮ በተሰው ቤተሰቦች መኖሪያ ይፋዊ የመርዶ ስነ-ሰርአት የተካሄደ ሲሆን የመርዶ ስነ-ሰርአቱ የሚያከናውኑት ፦
- የአገር ሽማግሌ
- የሃይማኖት አባቶች
- ታጋዩ ሲሰዋ በአጠገቡ የነበረ የአይን ምስክር
- ከነባር ታጋይ የተወጣጡ ኮሚቴ ሲሆኑ ቤተሰቡ ሲያረዱ ከመንግስት የተላከ የክብር መግለጫ የምስክር ወረቀትና የትግራይ ባንዴራ በመስጠት ነው።
መርዶ ከተነገረ በኃላ የተሰዋ ታጋይ ቤተሰብ ኮሚቴው አረጋግቶ በማጀብ እና በመምራት መርዶ ወደ ተነገሩ ሌሎች ቤተሰቦች ጋር በማቀላቀል ወደ መሰባሰብያ ቦታ ወስደዋቸዋል።
ከጥዋቱ 12:30 በየአከባቢው መርዶ የተነገረው ሁሉም ወደየ መገናኛ ቦታ ተሰባሰበ። በቦታው ደርሶ ልክ 1:00 ሰአት ከጠዋቱ በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ የሚኖር ትግራዋይ በሚድያ የሚመራ የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት ተደርጓል።
ከህሊና ፀሎት በኋላ የተሰዋ ቤተሰብ አባል እንደየ እምነቱ ወደ ሚመለከተው የማምለክያ ቦታ በህዝብ ታጅቦ ተጓዘ።
በእምነት ማስፈፀምያ ቦታ እንደየ እምነቱ የሚሰጠው ፀሎተ ፍትሃት፣ ዱዓና መፅናኛ የሃይማኖት አስተምህሮ ከተሰጠ በኃላ ከጊዚያዊ አስተዳደሩ የተላከ መልእክት በንባብ ቀርቧል።
በቤተ እምነት የተካሄደው ፍፃሜ ከተጠቃለለ በኃላ የሰማእታት ቤተሰብ በህዝቡ በመታጀብ ወደየ ቤታቸው ተመልሰዋል።
በየሃይማኖት ማምለኪያ ቦታዎቹ ከሚፈፀም ስነ-ሰርአት ጎን ለጎን በትግራይና ድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን በቀጥታ ስርጭት የተላለፈ በሰማእታት የመታሰብያ ሃወልት በክብር መዝገብ ፅሁፍ የማኖርና የአበባ ጉንጉን የማስቀመጥ ስነ-ሰርአት ተከናውኗል።
መቐለ ጨምሮ ማይጨው፣ መኾኒ፣ ዓዲጉዶም፣ ውቕሮ፣ ዓብዪ ዓዲ፣ ዓዲግራት፣ ዓድዋ፣ አክሱም፣ ሽረ፣ ሸራሮና ሌሎች ከተሞች በከፍተኛ የሃዘን ድባብ ውስጥ ሲሆኑ እንደ ባንክ የመሳሰሉ አገልግሎት ሰጪዎች የሃዘንና የክብር ቀን ስነ-ሰርአቱ ለማስፈፀም አስመልክቶ በወጣ መመሪያ መስረት ዝግ ሆነው ውለዋል።
የትግራይ ሰማእታት የሃዘንና የክብር ቀን ስነ-ሰርአት በተለያዩ ፕሮግራሞች በመቀጠል ጥቅምት 6 በህዝባዊ ሰልፍ እንደሚጠቃለል የወጣው መርሃ ግብር ያስረዳል።
መረጃው ተዘጋጅቶ የተላከው ከመቐለ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነው።
ፎቶ፦ ከላይ ተያይዟል