TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ይዞ መገኘት የሚቻለው የፌዴራል እና የቤተ ክርስቲያን አርማ ያለበትን ሰንደቅ ዓላማ ብቻ ነው " - ብፁዕ አቡነ አብርሃም

ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በመስቀል አደባባይ የሚከበረውን የደመራ በዓልን አስመልክቶ መልእክት አስተላለፉ።

ብፁዕነታቸው " በበዓሉ ላይ የሚፈትኑ ጉዳዮች ሊገጥሙን ስለሚችሉ በትዕግስት ማለፍ አለብን " ብለዋል።

በዕለቱ በይበልጥ ሰዓትን ማክበር ከፍተኛ ትኩረት እንደሚሰጠው አሳስበዋል።

ብፁዕነታቸው የመግቢያ ባጅ እደላው በሕግና በሥርዓት ትኩረት ተሰጥቶት የሚከናወን መሆኑን ገልጸዋል።

ሰንደቅ ዓላማን በተመለከተም የፌዴራል እና የቤተ ክርስቲያን አርማ ብቻ ያለበት መሆን እንደሚገባውና ርችት መተኮስ የቤተ ክርስቲያን ሥርዐት ባለመሆኑ እንደማይፈቀድ ገልጸዋል።

የቲሸርት አለባበስ በተመለከተም " ተንኳሽ መልእክት መጠቀም አይገባም " ያሉት ብፁዕነታቸው በየመንደሩና በየአጥቢያው በሚከበሩ በዓላት ላይም ጥንቃቄ ያስፈልጋል ብለዋል።

በበዓሉ ላይ የተፈቀደለት አስተናባሪ ብቻ የሚያስተናግድ ሲሆን ያልተፈቀደለት አካል ሲንቀሳቀስ ቢገኝ በወንጀል ያስጠይቃል ሲሉ ተናግረዋል።

ከዚህ ባለፈ በመርሐ ግብሩ ላይ መሪዎች እና ተናጋሪዎች በተፈቀደላቸው ሰዓት እንዲጠቀሙ አሳስበዋል።

በመጨረሻም ለመርሐ ግብሩ መሳካት ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ አባታዊ ጥሪ አስተላልፈዋል።

በዕለቱ የሙስሊም ወገኖቻችን የሚያከብሩት በዓል ስላላቸው በመከባበር እና በመተባበር በዓላቱን ማክበር ይገባል ሲሉም ጨምረው አሳስበዋል።

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በዓሉን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት ፤ በዓሉ መንፈሳዊ ስለሆን በመንፈሳዊነት ልናከብረው ይገባል እንደዚሁም በታዛዥነት እና በእምነት በበዓሉ ላይ ልንታደም ይገባል ብለዋል።

#EOTCTV

@tikvahethiopia
መስራት፣ ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን፣ ገበያ እና ተባባሪ አጋሮቹ መካከል ባለው ስምምነት የተደራጀ ሲሆን ለመስራት የስራ ፈጠራ ፕሮግራም ማመልከቻዎች መከፈቱን ያስታውቃል። መርሃ ግብሩ በመላው ኢትዮጵያ 100 ሁለገብ የጊግ ስራዎች እና ፕሮፌሽናል የገበያ ቦታዎችን ይደግፋል።

መስራት ለሥራ ፈጣሪዎች ብጁ የምርት ስም ያለው የገበያ ቦታ ቴክኖሎጂን በማቅረብ፣ የብቃት ማጣሪያ አገልግሎቶችን በመስጠት፣ ሥልጠናዎችን በማዘጋጀት፣ የምስክር ወረቀቶችን በመሸለም እና የጊግ ሠራተኞችን ለሥራ በማቅረብ ለእነዚህ ሥራ ፈጣሪዎች  የሚያስፈልጋችውን ድጋፍ ይሰጣል።

ድጋፋችን የንግድ ልማትን፣ የፋይናንስ አቅርቦትን እና የገበያ ትስስርን ያካትታል። በተጨማሪም፣ ለጊግ ኢኮኖሚ እና ለጊግ ሰራተኞች ፖሊሲ፣ ስትራቴጂ እና መመሪያ ልማት እናበረታታለን እና ከህዝብ ሴክተር ተዋናዮች ጋር አንድ ላይ እንሰራለን።

ፍላጎት ያላቸው አመልካቾች፡ በእዚህ ያመልክቱ
https://mesirat.org/apply

የማመልከቻ ገደብ፡ መስከረም 19, 2016 ሲሆን ለማንኛዉም አይነት ጥያቄዎች [email protected] ላይ ማቅረብ ይቻላል።
" የዓለም ሪከርድን መስበር እፈልግ ነበር ፣ ሆኖም ግን በርሊን ላይ አደርግዋለሁ ብዬ አልጠበኩም ነበር " - አትሌት ትዕግስት አሰፋ

ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትግስት አሰፋ የሴቶች ማራቶን ሪከርድን ከሁለት ደቂቃ በላይ በማሻሻል በበርሊን ማራቶን በዛሬው ዕለት መስበር ችላለች።

አምና ይህንን ውድድር የግሏን ምርጥ ሰዓት በማስመዝገብ ያሸነፈችው ትግስት አሰፋ እ.ኤ.አ በ 2019 በኬንያዊቷ ብሪጅድ ኮስጊ የተያዘውን የዓለም ሪከርድ በ2:11:53 በመግባት የግሏ አድርጋለች።

" የዓለም ሪከርድን መስበር እፈልግ ነበር ፣ ሆኖም ግን በበርሊን ማራቶን አደርግዋለሁ ብዬ አልጠበኩም ነበር " ስትል የ26 ዓመቷ የቀድሞ የ800ሜ ሯጭ ትግስት ተናግራለች።

ይህ " የጠንካራ ስራ እና የልፋቴ ውጤት ነው " ስትል ድሉን ገልጻለች።

ትግስት በፓሪሱ ኦሎምፒክ በማራቶን ሀገራችንን የምትወክልበት እድል ሰፊ ሆኗል።

" ውጤቱን አስመዝግቤያለው ፣ ውሳኔው የእኔ ሳይሆን የኦሎምፒክ ኮሚቴው እና ሀላፊዎች ነው ፣ እኔን ለኦሎምፒክ መምረጥ የእነሱ ኃላፊነት ነው " ስትል ገልጻለች።

ትዕግስት በድንቅ አጨራረስ የዓለም ሪከርድ የሰበተችበትን ውድድር ይመልከቱ ፦ https://twitter.com/tikvahethiopia/status/1705895213145751869?t=xteY99id6gPrTBvLrawC6w&s=19

@tikvahethiopia
" ትምህርት ሚኒስቴር ስላለንበት ሁኔታ ከወዲሁ ያስብበት " - በአማራ ክልል ነዋሪ የሆኑ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች

ሰላም በራቃቸው የአማራ ክልል ቀጠናዎች  ነዋሪ የሆኑ በተለያዩ የመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚማሩ ተማሪዎች ወቅቱ ዩኒቨርሲቲዎች የመግቢያ ቀን እያሳወቁ የሚገኙበት ቢሆንም አሁን ላይ ያለው ሁኔታ በተባለው ቀን እንዲገኙ ላያደርጋቸው እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸው ትምህርት ሚኒስቴር ከወዲሁ በጉዳዩ ላይ እንዲያስብበት ጥይቀዋል።

ተማሪዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት የፅሁፍ መልዕክት " በክልላችን ያለው ሁኔታ ይታወቃል " ያሉ ሲሆን " መንገድ ዝግ ነው ፤ የተወሰኑ ቦታዎች ኔትዎርክ አይሰራም፣ የዳታ ኢንተርኔት ከተዘጋ በርካታ ሳምንታት አልፈዋል ፤ በዚህ ሁኔታ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ደግሞ እየጠሩ ነው " ብለዋል።

" አሁን ላይ ተማሪዎች ጉዞ እንዳያደርጉ መንገድ ዝግ የሆነባቸው እና ደህንነታቸው ያልተረጋገጠባቸው ቦታዎች አሉ፤ ይህንንም  በቦታው ያለ ሰው  ያውቀዋል ፤ ከጎጃም ጎንደር ወሎ ለመምጣት አዳጋች ነው ፤ በኤርፖርት እንኳን ለመምጣት ከገጠር በረራ ወዳለባቸው ቦታ ለመምጣት ከባድ ነው " ሲሉ አስረድተዋል።

እንዚሁ ተማሪዎች በክልሉ ባለው ጦርነት ምክንያት በተባራሪ ጥይት የሰዎች ህይወት ስለመቀጠፉ ጠቁመው ይህን እየሰሙና እያዩ ለመምጣት አደጋች እንደሚሆን ከወዲሁ ገልጸዋል።

አንድ መልዕክቱን የላከ ተማሪ " እኔን ጨምሮ  ጓደኞቼ የምንማርበት ተቋም በቅርቡ ነው የጠራው ፤ ነገር ግን ለመግባት አደጋች ነው ፤ ለምሳሌ እኛ  ክላስ  እንኳን ብንወስድ ከ33 ተማሪዎች 15  የምንሆነው የአማራ ክልል ተማሪዎች ነን ለመግባት ሁላችንም  አንችልም " ብሏል።

ይኸው ተማሪ ፤ እነሱ የሚማሩበትን ክፍል እንደ ምሳሌ አነሳው እንጂ በዚህ አይነት ብዙ ተማሪዶች ከትምህርት  ገበታ ሊስተጓጎሉ ስለሚችሉ ይህም በብዙ መልክ ኪሳራ አለው  በመሆኑ  ትምህርት ሚኒስቴር ከወዲሁ ቢያስብበት ብሏል።

በሌላ በኩል በአማራ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ የሌሎች ክልል ተማሪዎች በሰላም እጦት ምከንያት ከአቻ ባቻቸው ወደኃላ እንዳይቀሩ ከወዲሁ በክልሉ ያለው ሁኔታ ተፈትሾ ሰላሙ አስተማማኝ ከሆነ እንደሌሎች ተቋማት ጥሪ እንዲደረግ ካልሆነ ወደ ሌላ ተቋማት የሚመደቡበት ሁኔታ እንዲመቻች በላኳቸው የፅሁፍ መልዕክቶች ጠይቀዋል።

ከዚህ ቀደም በትግራይ ክልል በተቀሰቀሰው አስከፊ ጦርነት በክልሉ የሚገኙ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ርቀው ከእድሜ እኩዮቻቸው ወደኃላ መቅረታቸው ይታወሳል።

ጦርነቱ በትግራይ የሚገኙ ተማሪዎችን ብቻ ሳይሆን በክልሉ ባሉ ተቋማት በሚማሩ የሌሎች ክልሎች ተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ምስቅልቅል መፍጠሩ የሚዘነጋ አይደለም።

በሌላ በኩል ፤ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ተማሪዎች ዛሬ ንጋት ጀምሮ የከተማ ውስጥ የተኩስ ልውውጥ እንደነበር ጠቁመዋል።

በነበረው ሁኔታ የከባድ መሳሪያ ድምፅም ይሰማ እንደነበር ፤ በከተማይቱ መንገድ ተዘጋግቶ እንደነበርና ሁኔታ ለደህንነታቸው እንዳሰጋቸው አሳውቀዋል።

ከተማሪዎች በተጨማሪም ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሌሎች አባላት ባገኘው መረጃ ዛሬ ጎንደር በተኩስ ስትናጥ እንዳረፈደችና ከተማይቱ አለመረጋጋት ውስጥ እንዳለች ለመረዳት ተችሏል።

@tikvahethiopia
#AI

በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተሰሩ የታዳጊ ሴቶች የእርቃን ምስሎች ስፔን ውስጥ ከፍተኛ ድንጋጤ የፈጠሩ ሲሆን ፖሊስ ምርመራ ላይ ነው።

በደቡባዊ ስፔን ውስጥ የምትገኘው አልመንድራሌሆ ከተማ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተሰሩ የታዳጊ ሴቶች እርቃን ምስሎች ከእነርሱ እውቅና ውጭ በማኅበራዊ ሚዲያ ከተዘዋወሩ በኋላ ድንጋጤ ውስጥ ገብታለች ሲል ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

እርቃን ምስሎቹ የተሰሩት ሙሉ ልብስ ለብሰው የተነሱትን የታዳጊዎቹን ፎቶ በመጠቀም ነው።

በርካታ ምስሎቹ የተወሰዱትም ከታዳጊዎቹ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች ነው።

ምስሎቹ ከተወሰዱ በኋላም አንድ ግለሰብ እርቃኑን ምን እንደሚመስል የሚያሳይ ምናባዊ ምስል የሚፈጥር መተግበሪያ በመጠቀም የታዳጊዎቹ ምስል እርቃን እንዲቀር ተደርጓል።

እስካሁን ዕድሜያቸው በ11 እና በ17 ዓመት መካከል የሚገኙ 20 ታዳጊ ሴቶች፣ የዚህ ድርጊት ሰለባ መሆናቸውን በመግለጽ በደቡብ ምዕራብ ግዛቷ ባዳጆዝ ውስጥ በምትገኘው አልመንድራሌሆ ከተማ እና አቅራቢያው ሪፖርት አድርገዋል።

በማኅበራዊ ሚዲያ የተጋሩት ሐሰተኛ የእርቃን ምስሎች በታዳጊ ሴቶቹ ላይ የተለያዩ ተፅዕኖዎችን አሳድረዋል።

የተወሰኑ ታዳጊዎች ከቤታቸው ለመውጣት እንደተሳቀቁ ተነግሯል።

ይህ ጉዳይ ወደ አደባባይ የወጣው ከታዳጊዎቹ ሴቶች መካከል የአንዷ እናት በሆነችው የማሕጸን ሐኪም ማሪያም አል አዲብ ምክንያት ነው።

አዲብ ማኅበራዊ ሚዲያዋን በመጠቀም ባወጣችው መልዕክት ምክንያት ጉዳዩ የስፔን ሕዝብ መነጋጋሪያ መሆን ችሏል።

አዲብ ታዳጊ ሴቶችንና ወላጆችን ለማረጋጋት ስትል በማኅበራዊ ሚዲያ ባጋራችው ቪዲዮ " የወጡት የAI ምስሎች የተፈጠሩት በበጋ ወቅት ቢሆንም ጉዳዩ ወደ አደባባይ የወጣው በቅርብ ቀናት ነው " ብላለች።

" ምን ያህል ሕጻናት ምስሎቹ እንደነበራቸው አናውቅም። ምስሎቹ የወሲብ ፊልም በሚጫንባቸው ገጾች ላይ ተጭነው እንደሆነም አናውቅም ነበር። ይህ ሁሉ ስጋት ነበረብን " ብላለች።

በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተሰሩ የታዳጊ ሴቶች እርቃን ምስሎችን ባማውጣት የተጠረጠሩ ታዳጊዎች ዕድሜያቸው ከ12 እስከ 14 የሚደርስ ነው።

ፖሊስ ድርጊቱን እየመረመረ ሲሆን ምስሎቹን በመፍጠር ሒደት ውስጥ አሊያም በማኅበራዊ ሚዲያዎቹ #ዋትስአፕ እና #ቴሌግራም በማጋራት ተሳትፈዋል ያላቸውን ቢያንስ አስራ አንድ የአካባቢው ነዋሪ የሆኑ ታዳጊ ወንዶችን መለየቱን አስታውቋል።

መርማሪዎች ታዳጊ ወንዶቹ ሐሰተኛ ምስሎችን በመጠቀም ታዳጊ ሴቶቹን #በማስፈራራት ማግኘት የፈለጉት ነገር ስለመኖሩ ለማወቅ ምርመራ እያካሄዱ ነው።

#BBC

@tikvahethiopia
በተራችን ልናገለግላችሁ ተዘጋጅተናል!
እንደባለውለታነታችሁ የተሻለ ጥቅም፣ ቅድሚያና ልዩ መስተንግዶ ይገባችኋል!
ጋሻ የቁጠባ ሒሳብ
=========
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እድሜያቸው 55 እና ከዛ በላይ ለሆኑ ዜጎች ጋሻ በሚል መጠሪያ አዲስ የቁጠባ ሒሳብ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡

• ከ250 ብር ጀምሮ የሚከፈት፤
• የተሻለ ወለድ የሚያስገኝ እና የቁጠባ መጠን ሲጨምር አብሮ የሚጨምር የወለድ መጠን የሚያስገኝ፤
• የቁጠባ ሒሳቡ ባለቤቶች እንደ ታላቅነታቸው ቅድሚያ የሚስተናግዱበት አሠራር የተመቻቸለት፤
• ህመም ቢያጋጥምዎ ባሉበት አገልግሎት የሚያገኙበት፤
• መስፈርቱን ለሚያሟሉ ደንበኞች የብድር አገልግሎት የሚሰጥበት፤ እና
ሌሎችንም ተጨማሪ ጥቅሞች የሚያስገኝ የቁጠባ አገልግሎት ነው፡፡

ይቆጥቡ፤ እንደባለውለታነትዎ የተሻለ ጥቅም ያግኙ!

https://t.iss.one/combankethofficial
#ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች አስጠልላቸው የሚገኙ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ስደተኞች የዕርዳታ እህል በመቋረጡ፣ ሕይወታቸው አደጋ ላይ መሆኑንና ለአገርም የደኅንነት ሥጋት መደቀኑ ተነገረ፡፡

ከጥቂት ወራት በፊት የዓለም የምግብ ፕሮግራምና የአሜሪካ መንግሥት ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (USAID) በኢትዮጵያ ተፈጸመ ባሉት የዕርዳታ እህል ዝርፊያ ምክንያት ለኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ዕርዳታ ማቆማቸው ይታወሳል፡፡

የምግብ አቅርቦቱ እንደገና እንዲጀመር የኢትዮጵያ መንግሥት እየተነጋገርኩበት ነው ቢልም፣ ዕርዳታው እየቀረበ ባለመሆኑ በኢትዮጵያ የተጠለሉ የውጭ አገሮች ስደተኞች በምግብ ዕጦት እየሞቱና ሕመም ላይ መውደቃቸውን፣ የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት አስታውቋል፡፡

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ምን አለ ?

- ኢትዮጵያ ስደተኞችን ተቀብላ ስታስተናግድ የዓለም አቀፉን ሕግ መሠረት በማድረግ ከለላና ጥበቃ የምታደርግ ቢሆንም፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለስደተኞች የሚቀርበው ዕርዳታ በመቆሙ ቀውስ ተፈጥሯል።

- በምግብ እጥረት ምክንያት የሚሞቱትና የሚታመሙት ወይም የሚቸገሩት ስደተኞች ብቻ ሳይሆኑ፣ ችግር ሲፈጠር በመሠረታዊነት የመጀመርያ ተጎጂ ሕፃናትና ሴቶች ናቸው።

- በመጠለያ ካምፕ የሚገኝን ሀብት አፈላልጎ ለመመገብ ጥረት በሚያደርግበት ወቅት፣ ስደተኞቹ ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር ግጭት ውስጥ ይገቡና ሰላማዊ የኑሮ ሁኔታን የሚያናጋ ነገር እየተፈጠረ ነው።

- በአሁኑ ወቅት ምግብ ነክ ድጋፎች እየቀረቡ ባለመሆናቸእ በቀጣይ አፋጣኝ ዕርምጃ ካልተወሰደ ችግሩ የከፋ ሊሆን ይቻላል። በሁሉም የአገሪቱ መጠለያ ካምፖች ችግሩ ተከቷል።

- በኢትዮጵያ የሚገኙ ስደተኞችን ለመታደግ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር ንግግር እየተደረገ ነው ፤ በአጭር ጊዜ ዕርዳታው እንደገና ይጀመራል የሚል እምነት አለ።

በስደተኛ ቁጥር ፦
👉 በጋምቤላ ወደ 400,000
👉 በቦሎ መልካዲዳ በሶማሌ ክልል 200,000፣
👉 በቤኒሻንጉል አሶሳ ወደ 90,000፣
👉 በአፋር 68,000፣
👉 በሶማሌ ጅግጅጋ ወደ 50,000፣
👉 አማራ ክልል ባባት 25,000፣ መተማ ወደ 40,000፣ እንዲሁም በአዲስ አበባ ወደ 80,000 ስደኞች ይገኛሉ።

ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ስደተኞች መካከል ከ900,000 በላይ የሚሆኑት በመጠለያ ካምፕ ውስጥ ናቸው።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከሰሞኑ ባወጣው መግለጫ፣ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ ዕርዳታ ለተረጂዎች እየቀረበ ባለመሆኑ ወደ 400,000 የሚጠጉ በጋምቤላ ክልል ውስጥ በካምፕ የሚገኙ ስደተኞች ሕይወት አደጋ ውስጥ መውደቁን ገልጾ አፋጣኝ ዕርምጃ እንዲወሰድ ጠይቋል፡፡

በጋምቤላ ክልል ከግንቦት 2015 ዓ.ም. ወር ጀምሮ ዕርዳታ ያላገኙ ስደተኞች (አብዛኞቹ ከደ/ሱዳን የተሰደዱ) በምግብ እጥረት የተነሳ በሚመጣ ረሃብ ለሞትና ለከፋ ሕመም እየተጋለጡ መሆናቸውን አረጋግጧል።

ኮሚሽኑ ከስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ተቋም አገኘሁት ባለው መረጃ በምግብ እጥረት ምክንያት በጋምቤላ ብቻ 30 ሰዎች መሞታቸውን፣ 5 ዓመት ያልሞላቸው ሕፃናት ለከፋ ሕመም መጋለጣቸውን አስታውቋል፡፡

በተከሰተው የምግብ እጥረት የተነሳ ከስደተኞች መጠለያ ካምፕ ወጥተው ወደ ማኅበረሰቡ በሚገቡበት ወቅት ለሰላም ችግር መንስዔ መሆናቸው በኮሚሽኑ ሪፖርት የተገለጸ ሲሆን፣ ከመጠለያ ወጥተው በምግብ ስርቆት በመሰማራታቸውና ከቆሻሻ ላይ ምግብ ለማንሳት ሲጥሩ ሕይወታቸው ያለፉ መኖራቸውንም አስታውቋል፡፡

አሁን ላይ በርካታ ስደተኞች አደጋ ላይ በመሆናቸው የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላትም ሆኑ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅቶች አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጡ ኢሰመኮ አሳስቧል።

#ሪፖርተር

@tikvahethiopia
መስራት፣ ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን፣ ገበያ እና ተባባሪ አጋሮቹ መካከል ባለው ስምምነት የተደራጀ ሲሆን ለመስራት የስራ ፈጠራ ፕሮግራም ማመልከቻዎች መከፈቱን ያስታውቃል። መርሃ ግብሩ በመላው ኢትዮጵያ 100 ሁለገብ የጊግ ስራዎች እና ፕሮፌሽናል የገበያ ቦታዎችን ይደግፋል።

መስራት ለሥራ ፈጣሪዎች ብጁ የምርት ስም ያለው የገበያ ቦታ ቴክኖሎጂን በማቅረብ፣ የብቃት ማጣሪያ አገልግሎቶችን በመስጠት፣ ሥልጠናዎችን በማዘጋጀት፣ የምስክር ወረቀቶችን በመሸለም እና የጊግ ሠራተኞችን ለሥራ በማቅረብ ለእነዚህ ሥራ ፈጣሪዎች  የሚያስፈልጋችውን ድጋፍ ይሰጣል።

ድጋፋችን የንግድ ልማትን፣ የፋይናንስ አቅርቦትን እና የገበያ ትስስርን ያካትታል። በተጨማሪም፣ ለጊግ ኢኮኖሚ እና ለጊግ ሰራተኞች ፖሊሲ፣ ስትራቴጂ እና መመሪያ ልማት እናበረታታለን እና ከህዝብ ሴክተር ተዋናዮች ጋር አንድ ላይ እንሰራለን።

ፍላጎት ያላቸው አመልካቾች፡ በእዚህ ያመልክቱ
https://mesirat.org/apply

የማመልከቻ ገደብ፡ መስከረም 19, 2016 ሲሆን ለማንኛዉም አይነት ጥያቄዎች [email protected] ላይ ማቅረብ ይቻላል።
#አማራ

ከፊታችን ያሉት ሃማኖታዊ በዓላት በአደባባይ እንዲከበሩ ተፈቀደ።

የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ መምሪያ ዕዝ በአማራ ክልል ለመውሊድ ፣ ደመራ እና መስቀል በዓላት መሰባሰብን ፈቀደ።

ዕዙ ፤ መስከረም 16 እና 17 /2016 የሚከበሩት የመውሊድ፣ የደመራና የመስቀል በዓላት በአማራ ክልል የሃይማኖቶቹ ሥርዓት በሚፈቅዱት መንገድ እንዲከበሩ እየሰራሁ ነው ብሏል።

ምንም እንኳን የሕዝብ ስብሰባዎች በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ቢከለከሉም መስከረም 16 እና 17 የሚከበሩት ሃይማኖታዊ በዓላት የአደባባይ በዓላት በመሆናቸው ለበዓላቱ ሥነ ሥርዓት ሲባል የአደባባይ መሰባሰብን መፍቀዱን ገልጿል።

ዕዙ ፤ እነዚህ መሰባሰቦች ለሃይማኖታዊ የበዓል አከባበር ሥነ ሥርዓት ብቻ  የሚውሉ እንደሆነ አሳውቋል።

የአደባባይ መሰባሰቦች የበዓላቱ አከባበር ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ብቻ የሚከናወኑ ገልጿል።

በእነዚህ አከባበሮች ወቅት ለሕዝብ ደኅንነት ሲባል ከጸጥታ አካላት ጋር መተባበር #ግዴታ እንደተጣለ አሳውቋል።

በአማራ ክልል የፀጥታ ሁኔታ ከክልሉ አስተዳደር አቅም በላይ በመሆኑ ክልሉ ለፌዴራል መንግሥት ባቀረበው ጥሪ መሰረት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁ ይታወሳል።

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከተቀመጡ ክልከላዎች አንዱ ደግሞ " መሰባሰብ " ነው። ከቀናት በኃላ በሚከበሩት ሃይማኖታዊ በዓላት ላይ ስነሥርዓቶቹ ተከናውነው እስኪያልቁ መሰባሰብ መፈቀዱ ይፋ ተደርጓል።

@tikvahethiopia
#ትግራይ

በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን የዛፍ አምበጣ መንጋ የታየ ሲሆን ይኸው መንጋ በዛፍና በደረሱ እህሎች ጉዳት እያደረሰ መሆኑ የክልሉ እርሻና ገጠር ልማት ቢሮ አስታውቋል።

የአምበጣ መንጋው ጉዳት ያደረሰባቸው የዞኑ ወረዳዎች ታሕታይ ኣድያቦ ፣ አስገደና ማእኸላይ ኣድያቦ የተባሉ ናቸው።

የአንበጣ መንጋው ከመስከረም 2/2016 ዓ.ም ጀምሮ መታየቱ የገለፀው ቢሮው ፤ በ471 ሄክታር መሬት በተካሄደው የኬሚካል መርጨት ስራ 17 በመቶ መከላከል መቻሉ በቢሮው የተባዮች መከላከል ከፍተኛ ባለሙያ አቶ መለስ ኣባዲ ገልፀዋል።

አሁን በክልሉ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን የተከሰተው የዛፍ አንበጣ መንጋ ወረራ ሙሉ በሙሉ ለመከላከል የሚያስችል የኬሚካል መርጫ መሳርያ እጥረት መኖሩንና አርሶ አደሩ በተቻለው ሁሉ በመጠቀም የመከላከል ስራው አጠናክሮ እንዲቀጥል ባለሙያው አሳስበዋል።

በዞኑ ማእኸላይ አድያቦ ወረዳ ደግሞ በ8 ቀበሌ ገበሬ ማህበራት 1950 ሄክታር አዝርእት የሸፈነ የበቆሎ ተባይ መታየቱ ተገልፀዋል።

በተያያዘ ዜና በትግራይ ደቡባዊ ዞን ራያ ዓዘቦ ወረዳ የአንበጣ መንጋ ወረራ በሁለት ቀበሌ ገበሬ ማህበራት መታየቱንና በባለሙያዎችና በህዝቡ የተቀናጀ ተሳትፎ የመከላከለ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ከክልሉ የእርሻና ገጠር ልማት ቢሮ የተገኘ መረጃ ያስረዳል ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።
                         
@tikvahethiopia
የመውሊድ በዓል ረቡዕ ይከበራል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት 1498ኛው የነቢዩ ሙሐመድ (ሰዓወ) የመውሊድ በዓል የፊታችን ረቡዕ መስከረም 16 ቀን 2016 ዓ.ም በታላቁ አንዋር መስጂድ እንደሚከበር አሳውቋል።

ለበዓሉ አከባበር ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከታላቁ አንዋር መስጂድ ጋር በቅንጅት ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ ተገልጿል።

በዓሉ ረቡዕ ከጠዋት አንስቶ እስከ ቀን 7:00 ሰዓት ድረስ በታላቁ አንዋር መስጂድ እንደሚከበር ተመላክቷል።

@tikvahethiopia
" የመስቀል ደመራ በዓል ላይ ርችት መተኮስ አይቻልም "- አዲስ አበባ ፖሊስ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ለ #ኤፍቢሲ በሰጠው ቃል ፤ የመስቀል ደመራ በዓል ላይ ርችት መተኮስ በፍጹም የተከለከለ መሆኑን አሳውቋል።

ፖሊስ ምን አለ ?

- ህብረተሰቡ በመስቀል ደመራ በዓል ላይ የተከለከሉ ነገሮችን በፍጹም መያዝ አይገባውም። ለሚኖሩ ፍተሻዎችም መተባበር አለበት።

- በየአካባቢው በሚደመሩ ደመራዎች አደጋ እንዳይከሰት ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል።

- ከዚህ በፊት ደመራ ተደምሮባቸው የማያውቁ ቦታዎች #የጸብ_መነሻ እንዳይሆኑ የድሮዎቹን መጠቀም ይገባል።

- ርችት መተኮስ በፍጹም ክልል ነው። ክልከላው የተደረገው ርችትን ሽፋን በማድረግ ህገወጦች ህገወጥ የጦር መሳሪያቸውን የሚሞክሩበት ጊዜ በመሆኑ ነው። ርችት ሲተኩስ የተገኘ ግለሰብ ሆነ ተቋም በህግ አግባብ እርምጃ ይወሰድበታል።

@tikvahethiopia