#update በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 105 #ክላሽንኮቭ የጦር መሳሪያ #በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡ ህገወጥ የጦር መሳሪያው በቁጥጥር ስር የዋለው ትናንት ለሊት #በቡራዩ_ከተማ ነው፡፡ የጦር መሳሪያው በአይሱዙ ተሽከርካሪ ውስጥ ተጭኖ #ከጋምቤላ ወደ #አማራ_ክልል ሊጓጓዙ የነበረ ነው ተብሏል፡፡ የተያዘው የጦር መሳሪያ 42 ታጣፊና 63 ባለሰደፍ በድምሩ 105 ክላሽንኮቮች፣ 95 #የክላሽንኮቭ_መጋዝኖች እና 5 ጥይት ነው፡፡ ከአይሱዙ ኤፍ.ኤስ.አር የጭነት #ተሽከርካሪው ፊት በመሄድ ሁኔታዎችን #ሲያመቻች የነበረ አንድ ዶልፊን ሚኒባስም ተይዟል፡፡
Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Amhara የትግራይ ክልል ጦርነት ወደ አፋር እና አማራ ክልሎች ከሰፋ በኃላ ህወሓት የተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎችን ፣ በርካታ ህዝብ የሚኖርባቸውን ከተሞች እንደተቆጣጠረ ይገኛል። መንግስት አካባቢዎቹን ከቡድኑ ለማስለቀቅ አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ እየተዘጋጀ መሆኑንም ከዚህ ቀደም ሲገልፅ ነበር። ከሰሞኑ የህወሓት ቡድን ታጣቂዎች ይዘዋቸዋል በተባሉ ቦታዎች ላይ የአየር ድብደባ እየተፈፀመ…
የህወሓት በ #አማራ_ክልል በያዛቸው አካባቢዎች የኢትዮጵያ ጦር ከዛሬ ጥዋት ጀምሮ "ሙሉ የማጥቃት" እርምጃ እየወሰደ መሆኑ ዛሬ በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ሲዘገብ ውሏል።
ህወሓት ዛሬ ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ ጦር ተከፈተብኝ ያለውን ጥቃት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እንዲያወግዝ ጥሪ አቅርቧል።
ህወሓት የኢትዮጵያ ሠራዊት የተቀናጀ ጥቃት ከፍቶብኛል ያለ ሲሆን ዓለም አቀፉ ማኅረሰብ ይህንን እርምጃ እንዲያወግዝ ጠይቋል።
ህወሓት በኢትዮጵያ ሰራዊት እየተሰነዘረበት ያለው ጥቃት "በከባድ ጦር መሳሪያ፣ በታንክ፣ በሮኬቶች፣ በድሮኖች እና በተዋጊ ጀቶች" የታገዘ እንደሆነ ገልጿል።
ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ ጦር በህወሓት ታጣቂዎች በተያዙ ቦታዎች ላይ "ከባድ" የተባለ ጥቃት መፈፀም እንደጀመረ መገለፁ አይዘነጋም።
ካለፉት ቀናት አንስቶ በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ሲዘዋወሩ ለነበሩ መረጃዎች ቃሉን ያልሰጠው የመከላከያ ሰራዊት በይፋዊ ገፁ ላይ ዛሬ ምሽር መግለጫ አውጥቷል።
ሰራዊቱ ፥ "ህወሓት ውሸት ቀለቡ ነው ያለ ሲሆን ፤ በአንድ በኩል "ተጠቃሁ" ድረሱልኝ ፤ በሌላ በኩል ደግሞ "የትግራይ ሰራዊት የኢትዮጵያን ሰራዊት ባለበት ተኮማትሮ እንዲቀመጥ አድርገነዋል" ሲል ይገልጻል ብሏል።
አክሎ ፥ የዛሬው ፈሊጥ ለጋላቢዎቹ "መጠነ ሰፊ ጥቃት" ተሰነዘረብኝ እባካችሁ አድኑኝ እያለ ሲማፀን ለሚጋልባቸው ደግሞ "አኮማትሬያለሁ" እያለ መዘላበድ ሆኗል ብሏል።
መከላከያ ሰራዊት በራሱ ዕቅድ ሙሉ ማጥቃት ከጀመረ " ተጠቃሁ " ብሎ ለመናገር እንኳን ጊዜ ሳያገኝ የሚፈፀም እንደሚሆን መታወቅ አለበት ያለ ሲሆን ህዝቡ በወሬ ሳይደናገር የቁርጥ ቀን ልጆቹ በመንግስት ትዕዛዝ አይቀሬውን ድል እስኪያበስሩ የተለመደውን ድጋፍ እንዲያደርግ ሲል ጠይቋል።
* መግለጫው ከመከላከያ ሰራዊቱ ገፅ ተነስቷል።
@tikvahethiopia

" ክትትል እየተደረገ ነው ፤ በወረርሽኝ ምክንያት ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች አሉ " - ወ/ሮ ሰላማዊት ግርማቸው (በኢሰመኮ የሰሜንና ማዕከላዊ ሪጅን የክትትልና ምርመራ ዳይሬክተር) በኦሮሚያ ክልል፣ ሸገር ከተማ በማቆያና በፓሊስ ጣቢያዎች የሚገኙ ወገኖች እንዳሉና በእነዚህ ወገኖች የሰብዓዊ መብት ሁኔታ ላይ ክትትል እያደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።…
#አማራ_ክልል
ከትጥቅ ግጭት ጋር በተያያዘ #አሳሳቢነታቸው የቀጠለ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የተላከልን መግለጫ ከላይ ተያይዟል።