TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
በመቐለ ከተማ በተወረወረ የእጅ ቦምብ የ5 ሰዎች ህይወት አለፈ። ቦምብ ተወርውሮ የሞት አደጋው ያጋጠመው ነሃሴ 18 /2015 ዓ.ም ከሌሊቱ 8:00 ሰአት ነው። የአይን እማኞች ለቲክቫህ የመቐለ ቤተሰብ እንደገለፁት ፤ የቦምብ አደጋው ያጋጠመው በከተማው ቀዳማይ ወያነ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 15 " ዳዕሮ " ተብሎ በሚጠራው መጠጥ ቤት ነው።  የአይን እማኞቹ አክለው እንደገለፁት ፤ በመጠጥ ቤቱ ሰዎች በብዛት…
#Mekelle

የመቐለ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ትላንት ለሊት 8 ሰዓት ላይ ቀበሌ 15 " ዳዕሮ " በሚባለው መጥጥ ቤት ቦንብ የተወረወረው " በቀድሞ ተሰናባች ታጋይ " በነበረ ግለሰብ መሆኑን ታውቋል።

እንደ ፖሊስ መረጃ ተጠርጣሪው እስካሁን አልተያዘም።

የመቐለ ከተማ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊው ኮማንደር ወልዳይ ማውጫ ፤ " ከአሸንዳ በዓል ጋር በተያያዘ በከተማዋ ከፍተኛ የፀጥታ ቁጥጥር ሲደረግ ቆይቷል " ብለዋል።

" በበዓሉ መዝጊያ ቀን ትናንት ግን በከተማዋ ቀዳማይ ወያነ ክፍለከተማ አሳዛኙ የቦንብ ጥቃት ተፈፅሞ ለበርካቶች ሞት እና ጉዳት ምክንያት ሆኗል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ጥቃቱን የፈፀመው ግለሰብ ማንነቱ ተለይቷል " ያሉት ኮማንደር ወልዳይ የተሰናበተ የቀድሞ ታጋይ መሆኑንና በቁጥጥር ስር ለማዋል ክትትል እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

የተወረወረው ኤፍዋን የተባለ የእጅ ቦንብ መሆኑን ፖሊስ አረግጧል። የጥቃቱ አላማም " የግለሰቦች ጠብ " መሆኑን አስረድቷል።

ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል በበኩሉ 20 በቦንብ ጥቃት የቆሰሉ ሰዎች ከሌሊቱ 8 ሰዓት ጀምሮ መቀበሉን ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ በሰጠው ቃል ገልጿል።

ትላንት ለሊት በተወረወረው ቦንብ 5 ሰዎች መሞታቸውንና በርካቶችም መቁሰላቸውን የመቐለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የሆስፒታል ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Mekelle

በመቐለ ቀዳማይ ወያነ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 15 " ትላንት ለሊት " ዳዕሮ " ተብሎ በሚጠራ መጠጥ ቤት ቦንብ ወርውሮ የሰዎችን ህይወት የቀጠፈውና ለጉዳት የዳረገው ተጠርጣሪ ግለሰብ ስሙ ሙሉጌታ እንደሚባል ታውቋል።

ፖሊስ ግለሰቡ የተሰናበተ የቀድሞ ታጋይ መሆኑንና " በቁጥጥር ስር ለማዋል " ክትትል እየተደረገ መሆኑን ገልጾ ህዝቡ ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበር ጥሪ አቅርቧል።

ተጠርጣሪው በመቐለ ከተማ በተለይ ቀበሌ 14 ፣ 15 ፣ 16፣ 17 በደንብ ይታወቃል ያሉን የመቐለ ቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ፤  የቀድሞ ታጋይና የኮሌኔልነት መአርግ ያለው ጭምር ነው በማህበረ ረድኤት ትግራይ /ማረት/  ሹፌር ሆኖም ሲሰራ ነበር ብለዋል።

ተጠርጣሪው በ2013 ዓ.ም መልሶ ወደ ትጥቅ ትግል መግባቱን በኃላም ከትግል መሰናበቱን የመቐለ ቲክቫህ ቤተሰብ አባላት አመልክተዋል።

ፖሊስ ተሰናባቹን የቀድሞ ታጋይና ቦንብ ወርውሮ የሰዎችን ህይወት ያጠፋውን እንዲሁም መከፍተኛ የአካል ጉዳት የዳረገውም " ሙልጌታ "ን በቁጥጥር ስር ለማዋል ሁሉም እንዲተባበር ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
#Mekelle

በጦርነት የተጎዱ የትግራይ ኃይል አባላት በዛሬው ዕለት በመቐለ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል።

ሰልፈኞቹ
የ 85ቱ፣ 93 ቱ በ2015 ደገሙት፤
ድምፃችን ይሰማ ፤
ለህዝብ እንጂ ለግለሰብ አልታገልንም፤
ተጠቅመው ጥለውናል፤
መንግሰት ያየ ፍትህ ያየ ፤

የሚሉና ሌሎች መፈክሮች እያሰሙ በመቐለ ዋና ዋና መንገዶች ድምፃቸው አሰምተዋል።

ይህንን ዘገባ እስከተጠናከረበት ድረስ ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት የተሰጣቸው መልስ የለም።

ሰላማዊ ሰልፉ ላይ ፓሊስ ስነ-ስርዓት በማስከበር መሳተፉ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ከቦታው ዘግቧል።

Via @tikvahethiopiatigrigna (መቐለ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
 #Mekelle

" መንግስት ያልፈቀደው ሰልፍ የቀሰቀሱና የተሳተፉ ከ49 በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል " - ፓሊስ

" ከሰላማዊ የተቋውሞ ሰልፉ ጋር በተያያዘ ከ150 በላይ ሰዎች በፓሊስ ተደብድበው ታስሯል" - የተፎካካሪ የፓለቲካ ፓርቲ አመራር

የመቐለ ከተማ ፓሊስ አዛዥ ኮማንደር ወልዳይ መውጫ ጳጉሜን 2 / 2015 ዓ.ም በከተማው ሮማናት አደባባይ በተፎካካሪ ፓርቲዎች ሊካሄድ የተጠራው ሰላማዊ የተቋውሞ ሰልፍ በማስመልከት ዛሬ ጳጉሜን 3 ለክልሉ ሚድያዎች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ፤ መንግስት ያልፈቀድው ሰልፍ የቀሰቀሱና የተሳተፉ ከ49 በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር አውለናል ብለዋል።

" ሁሉም ሰው ከህግ በታች እንጂ ከህግ በላይ አይደለም " ያሉት የፓሊስ አዛዡ " ፖሊስ መንግሥት ያልፈቀደውን ሰልፍ ማድረግ አትችሉም ብሎ ቢያስጠነቅቅም ፤ ለ20 ደቂቃ ያህል በአምቢተኝነት ከፓሊስ ጋር ለመጋጨት የሞከሩ ነበሩ " ብለዋል።

ፓሊስ ከጳጉሜን 1 /2015 ዓ.ም ረፋድ ጀምሮ  በመንግስት ያልተፈቀደው ሰልፍ እንዳይቀሰቅሱና እንዳይመሩ ለተፎካካሪ ፓለቲካ ፓርቲ አመራሮች ምክር መሰጡትንና ፤ ምክሩ ችላ ብለው ከሰዓት በኋላ 10:30 አከባቢ አመራሮቹ ሰልፉ እንዲካሄድ የሚቀሰቅስ ወረቀት ሲለጥፉ እጅ በፈንጅ  ተይዘው በቁጥጥር ስር ውለዋል ፤ በተጨማሪ ጳጉሜን 2 / 2015 ዓ.ም ጠዋት ሰልፉ ለማስተባበርና ለመሳተፍ የተገኙ ቀሪ አመራሮች መያዛቸው ገልፀዋል።   

ፓሊስ የተሰጠው ህግ የማስከበር ሃላፊነት መሰረት በማድረግ ግርግር ለመፍጠር የሞከሩ በደቂቃዎች በመቆጣጠር የመቐለ ከተማ እንቅስቃሴ ከወትሮ የተለየ የፀጥታ ስጋት እንዳይታይባት ማድረግ መቻሉንና ፤ ህዝቡ ያልተፈቀደውን ሰልፍ ለማደረግ የመኮሩ ጥቂቶች ሰርአት እንዲይዙ የማድረግ ሚናው በመወጣቱ አመስግነዋል። 

የውድብ ናፅነት ትግራይ (ውናት ) ምክትል ሊቀመንበር አቶ አለምሰገድ አረጋይ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃለምልልስ በበኩላቸው " ፓሊስ ሰልፉ ለመታደም በመጡ ድብድባ ፤ ማንገላታትና ባጠቃላይ ኢ-ሰብአዊ የሆነ ግፍ ፈፅመዋል " ብለዋል።

" ፓሊስ 50 ሊቀመናብርትና የማእከላይ ኮሚቴ አመራሮች የሚገኙባቸው ከ150 በላይ ሰዎች አስረዋል " ያሉት አቶ አለምሰገድ ፤ የዓረና ሉአላውነትና ለዴሞክራሲ ሊቀመንበር ዓምዶም ገ/ስላሴ ፣ የባይቶና ግዚያዊ አስተዳዳሪ ኪዳነ አመነ ከታሳሪዎች መካከል ናቸው ብለዋል። 

" ይህን መሰል አፈና ሊቆም የሚችለው ገዢው ፓርቲ ህወሓት ከስልጣኑ ሲነሳ ነው " ያሉት አመራሩ ህዝቡ ትግሉ አጠናክሮ እንዲቀጥል መልእክት አስተላልፈዋል። 

የግዚያው አስተዳደሩ ፕረዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ጳጉሜን 1/2015 ዓ.ም ለሚድያዎች በሰጡት ሰፊ ቃለመጠይቅ "... ሰልፍ ማድረግ መብት ነው : ቢሆንም በክልሉ ካለው ከባድ የፀጥታ ስጋት አንፃር ስልፉ ማካሄድ አስቸጋሪ ነው " ማለታቸው ይታወሳል።  
                
መረጃውን የመቐለ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነው ያደረሰን።

@tikvahethiopia