TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በአዲስ ዓመት አብሳሪዋ አደይ አበባ የተሰየመችው ተናፋቂዋ አደይ አበባ የሞባይል ጥቅል ይበልጥ ፈክታና ደምቃ፤
ከወትሮው ለየት ብላ የዳታ ጥቅሎቿ ላይ ፌስቡክ፣ ዩቲዩብ እና ቴሌግራም የሚያስጠቅም ስጦታን ይዛ ቀረበች!!!

ከአይነተ ብዙ ሰፊው ገበታችን አደይ አበባ ጥቅልን በቴሌብር ሱፐርአፕ እና ማይ ኢትዮቴል እንዲሁም በ*999# ለራስዎ እየገዙ ለሚወዷቸው በስጦታ እያበረከቱ የበዓል መልካም ምኞትዎን ያድርሱ!

ወዳጅ ዘመድን የምታቀላቅል… አደይ አበባ ጥቅል

መልካም አዲስ ዓመት!!
TIKVAH-ETHIOPIA
#G20 አፍሪካ ህብረት G20ን እንዲቀላቀል ጥሪ ቀረበለት። የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የ " አፍሪካ ህብረት " የቡድን 20 አባል እንዲሆን በዛሬው ዕለት ጥሪ ማቅረባቸውን ቪኦኤ ዘግቧል። በሚቀጥለው ወር በሕንድ ፤ ኒው ዴሊ የቡድኑ መሪዎች ጉባኤ ይካሄዳል። ሞዲ ለአፍሪካ ህብረት ጥሪውን ያቀረቡት " ቢ20 የተሰኘው በቢዝነስ ፎረም እና የመስከረም ወሩ ጉባዔ መዳረሻ መድረክ ላይ ማደረጉት…
አፍሪካ ኅብረት የቡድን 20 አባል ሆነ።

ቡድን 20 " ታሪካዊ ነው " በተባለ ውሳኔ የአፍሪካ ኅብረትን አባል አድርጎ ተቀበለ።

በኢንዱስትሪ የበለጸጉ እና ከአዳጊ አገራት የላቀ የምጣኔ ኃብት ዕመርታ ያስመዘገቡት አገራት ስብስብ የሆነው ቡድን ሃያ አባላት ውሳኔ ታሪካዊ ተሰኝቷል።

55 አባላት ያሉት የአፍሪካ ኅብረት የቡድን 20 (G20) አባል አገራትን ተቀላቅሏል።

የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ንሬንድራ ሞዲ የአፍሪካ ኅብረትን አዲስ የቡድን 20 ቋሚ አባል አድርገው ሲያስተዋውቁ አንደኛው ምክንያት ተብሎ የተጠቀሰው አፍሪካን በአንድ ድምጽ በዓለም አቀፍ መድረክ ማካተት ነው።

ሕንድ የቡድን 20 መሪነቷ የዓለምን ደቡባዊ አገራት ተሳትፎ ከማሳደግ ጋር የተያያዘ መሆኑን በተደጋጋሚ ገልጻለች። የዚህ ዕቅድ ትልቁ አካል ደግሞ የአፍሪካ ኅብረትን የቡድኑ አባል ማድረግ ነው።

ሞዲ የአፍሪካ ኅብረትን በቡድኑ መቀላቀል ሲገልጹ አጠገባቸው የነበሩ የአፍሪካ ተወካዮች ደስታቸውን ገልጸዋል።

የአፍሪካ ኅብረት ፕሬዝዳንት አዚል አሶሚኒ በቡድን 20 የፓርላማ አባላት መቀመጫ እንዲወስዱም በሞዲ ተጋብዘዋል።

ሁለቱ መሪዎች ይህ ይፋ ከተደረገ በኋላ ተቃቅፈው ታይተዋል። ተወካዮቹ “ታሪክ ተሠርቷል” ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል።

የአፍሪካ ኅብረት በቡድን 20 መቀላቀል ቡድኑን የተሻለ አካታች እንደሚያደርገው ተገልጿል።

ሕንድ በጉባኤው እንዲነሳ ከምትፈልገው ርዕሰ ጉዳይ አንዱ የታዳጊ አገራት ምጣኔ ሀብት ነው።

በርካታ ታዳጊ አገራት ከቻይና፣ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) የተበደሩትን ገንዘብ ለመክፈል ስለሚከብዳቸው ሕንድ ሃብታም አገራት እንዲያግዙ ትሻለች።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

ቪድዮ ፦ የደ/አፍሪካ ፕሬዜዳንት ፅ/ቤት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
 #Mekelle " መንግስት ያልፈቀደው ሰልፍ የቀሰቀሱና የተሳተፉ ከ49 በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል " - ፓሊስ " ከሰላማዊ የተቋውሞ ሰልፉ ጋር በተያያዘ ከ150 በላይ ሰዎች በፓሊስ ተደብድበው ታስሯል" - የተፎካካሪ የፓለቲካ ፓርቲ አመራር የመቐለ ከተማ ፓሊስ አዛዥ ኮማንደር ወልዳይ መውጫ ጳጉሜን 2 / 2015 ዓ.ም በከተማው ሮማናት አደባባይ በተፎካካሪ ፓርቲዎች ሊካሄድ የተጠራው…
#Tigray

" መሰረታዊ ሰብአዊና ህገ-መንግስታዊ መብቶች መከበር አለባቸው " ሲል የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ትእዛዝ አውጥቷል።

ፍትሕ ቢሮ ፤ ለትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ እና ለትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፓሊስ ኮሚሽን ደብዳቤ ፅፏል።

በፃፈው ደብዳቤም ፤ ሰብአዊና ህገ-መንግስታዊ መብቶች እንዲከበሩ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

በዚህ ሳምንት ተፎካካሪ የፓለቲካ ፓርቲዎች ከጠሩት ሰላማዊ ሰልፍ ጋር ተያይዞ የፓርቲዎቹ መሪዎችና አባላት የሚገኙባቸው በርካታ ሰዎች በቁጥጥር ስር እንደሚገኙ ለማወቅ ችለናል ያለው ቢሮው  በዚሁ ሂደት በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች መሰረታዊ ሰብአዊ መብታቸው እየተከበረ አይደለም የሚል ስሞታ ቀርቦልናል ብሏል።

በመሆኑም ፦

1. በህጉ መሰረት በ48 ሰአታት ወደ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ፤

2. ከቤተሰብም ሆነ ሌላ ጠያቂ እንዲገናኙና ምግብና ልብስ እንዲገባላቸው፤

3. የተጎዱ ህክምናና መድሃኒት እንደዲያገኙ፤ 

እንዲሁም ሌሎች ተዘማጅ መብቶቻቸው ሳይሸራረፉ ያለ ቅድመ ሁኔታ እንዲከበሩላቸው ሲል ትእዛዝ ሰጥቷል።

ትእዛዙ በአግባቡ መፈፀሙን ፤ በቁጥጥር ስር የዋሉ የሚገኙባቸው ማረፍያ ማእከላት በአካል ተገኝቶ የሚያረጋግጥ የሰብአዊ መብት ክትትል ቡድን ከቢሮው የተመደበ መሆኑን አሳስውቋል።

መረጃው የመቐለ ቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አፍሪካ ኅብረት የቡድን 20 አባል ሆነ። ቡድን 20 " ታሪካዊ ነው " በተባለ ውሳኔ የአፍሪካ ኅብረትን አባል አድርጎ ተቀበለ። በኢንዱስትሪ የበለጸጉ እና ከአዳጊ አገራት የላቀ የምጣኔ ኃብት ዕመርታ ያስመዘገቡት አገራት ስብስብ የሆነው ቡድን ሃያ አባላት ውሳኔ ታሪካዊ ተሰኝቷል። 55 አባላት ያሉት የአፍሪካ ኅብረት የቡድን 20 (G20) አባል አገራትን ተቀላቅሏል። የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ንሬንድራ…
#G20

አፍሪካ ህብረት " ቡድን 20 " ን በቋሚ አባልነት መቀለቀሉን ተከትሎ የቡድኑ ዝርዝር ይህን ይመስላል።

🇦🇷 አርጀንቲና
🇧🇷 ብራዚል
🇨🇦 ካናዳ
🇨🇳 ቻይና
🇫🇷 ፈረንሳይ
🇩🇪 ጀርመን
🇮🇳 ህንድ
🇮🇩 ኢንዶኔዥያ
🇮🇹 ጣልያን
🇯🇵 ጃፓን
🇰🇷 ደቡብ ኮሪያ
🇲🇽 ሜክሲኮ
🇷🇺 ሩስያ
🇸🇦 ሱዑዲ አረቢያ
🇿🇦 ደቡብ አፍሪካ
🇹🇷 ቱርክ
🇦🇺 አውስትራሊያ
🇬🇧 ዩናይትድ ኪንግደም
🇺🇸 አሜሪካ
🇪🇺 አውሮፓ ሕብረት
🌍 #አፍሪካ_ሕብረት

@tikvahethiopia
ከ5 ብር ጀምሮ ስንሞላ ከሳፋሪኮም ወደ ሳፋሪኮም ዕለታዊ እና ሳምንታዊ ጥሪ ማድረግ እንችላለን። ያለሃሳብ ከምንወዳቸው ጋር አብሮነታችንን እናጠንክር!

#SafaricomEthiopia #FurtherAheadTogether
" አርሶ አደሩ መሬት የመሸጥና የመለወጥ መብት እንዲኖረው " ለማድረግ ማቀዱን ትንሣኤ 70 እንደርታ ፓርቲ ገለጸ።

የምሥረታ ጉባኤውን ጳጉሜ 3 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ  በቂርቆስ ክፍለ ከተማ መሰብሰቢያ አዳራሽ ያካሄደው የ " ትንሣኤ 70 እንደርታ " ፓርቲ (ትሰእፓ) ሊቀ መንበር ሆነው የተሾሙት አቶ ከበደ አሰፋ ፤ " አርሶ አደሩ መሬቱን የመሸጥና የመለወጥ መብት እንዲኖረው ይደረጋል " ብለዋል።

ሊቀ መንበሩ፤ "መሬት የሕዝብ እንጂ የመንግሥት መሆን የለበትም " ያሉ ሲሆን፣ ትሰእፓ " በመሆኑም መንግሥት ይህንን ታላቅ ሀብት በወጉና በሥርዓቱ እንዲሁም ሕዝብንና አገርን ጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ ጥቅም ላይ እንዲውል የሚያስችል ፓሊሲ ያዘጋጃል " ሲሉ አስረድተዋል።

አቶ ከበደ አክለውም፣ "መንግሥት አርሶ አደሩን የማይረባ ዋጋ እየሰጠ በማፈናቀል፣ መንግሥት ራሱ መሬቱን በከፍተኛ ዋጋ በመሸጥ የሚነግድበት ሥርዓት መወገድ አለበት" ብለዋል።

" እስከ  ዛሬ ድረስ 'መሬት የሕዝብም የመንግሥትም ነው' ተብሎ ግን መንግሥት በካሬ 40 ሺህ እና 50 ሺህ በሊዝ ስም የሚሽጥበት እውነታ ስለሆነ ያለው፣ መሸጥም ካለበት መንግሥት ሳይሆን ራሱ ሕብረተሰቡ ይሽጠው " ሲሉ ተናግረዋል።

ፓርቲው በተጨማሪም፣ "ታላላቅ ኢንዱስትሪዎች ሲቋቋሙ አገሬውን ተጠቃሚ በሚያደርግና በማያፈናቅል መንገድ፣ ለኢንቨስትመንት የሚውሉ ሰፋፊ መሬቶች አርሶ አደሩን በማማከር እና የልማቱን ባለድርሻ በማድረግ ይከናወናል " ብሏል።

በምስረታ ጉባኤው የታደሙ የፓርቲው ደጋፊዎች በበኩላቸው የፓርቲውን የእንደርታ ሕዝብ በሕወሓት አመራሮች ጫና፣ መገለል እንደተፈጸመበት በምሬት ተናግረዋል።

አክለውም ትሰእፓ ከሕወሓት ጋር ምንም አይነት ቁርኝት እንዳይኖረው ጠይቀዋል።

የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ከበደ በበኩላቸው ፓርቲው ከሕወሓት ጋር ቁርኝት ሊኖረው እንደማይችል አስረድተዋል።

ትሰእፓ የምስረታ ጉባኤውን ጳጉሜን 3 ቀን 2015 ዓ/ም ያካሄደ ሲሆን፣ በጉባኤው የተሳተፉ አባላቱ የማዕከላዊ ኮሚቴዎች፣ የኦዲትና ሥራ አስፈጻሚዎችን መርጠዋል።

አቶ ከበደ አሰፋ ለቲክቫህ በሰጡት ማብራሪያ ፤ " 15 የማዕከላዊ ኮሚቴ፣ ሦስት የኦዲትና ቁጥጥር ኮሚሽን ተመርጠዋል። እኔ አቶ ከበደ አሰፋ ሊቀመንበር ሆኘ ተመርጫለሁ " ሲሉ አስረድተዋል።

አክለውም 15ቱ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላቶችም ባከናወኑት ምርጫ 14 የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላቶችን መርጠዋል፤ አቶ ጊደና መድህን ምክትል ሊቀመንበር ሆነዋል" ብለዋል።

ትሰእፓ በትግራይ ክልል “የተንሰራፋውን ጭቆና እና የአንድ ፓርቲ ስርዓት” መታገል ዋነኛ አላማው መሆኑን አስታውቋል።

መረጃውን ያዘጋጀው የአዲስ አበባ ቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
#5G_AddisAbaba

ኢትዮ ቴሌኮም የ5ኛውን ትውልድ (5G) የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት በአዲስ አበባ ከተማ መጀመሩን ዛሬ ቅዳሜ ጳጉሜ 4 ቀን 2015 ዓ.ም ከሰዓታት በኋላ በይፋ ያበስራል፡፡

በዚህ ላይ ተጨማሪ መረጃዎች ይኖረናል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#5G_AddisAbaba ኢትዮ ቴሌኮም የ5ኛውን ትውልድ (5G) የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት በአዲስ አበባ ከተማ መጀመሩን ዛሬ ቅዳሜ ጳጉሜ 4 ቀን 2015 ዓ.ም ከሰዓታት በኋላ በይፋ ያበስራል፡፡ በዚህ ላይ ተጨማሪ መረጃዎች ይኖረናል። @tikvahethiopia
#Update

ኢትዮ ቴሌኮም 630 ሺ ደንበኞቹ ዛሬ ይፋ ያደረገውን የ5G ኔትወርኩን መጠቀም ይችላሉ ብሏል።

ኢትዮ ቴሌኮም የ5ኛውን ትውልድ (5G) የሞባይል ኔትወርክ በሙከራ ደረጃ በአዲስ አበባ እንዲሁም በአዳማ ከተሞ በሙከራ ደረጃ ሲያቀርብ ቆይቶ ዛሬ በይፋ በአዲስ አበባ አገልግሎት ማስጀመሩን አስታውቋል።

ኢትዮ ቴሌኮም የ5ኛውን ትውልድ (5G) የሞባይል ኔትወርክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሞከው በአዲስ አበባ ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ ነበር። በቀጣይም በሙከራ ደረጃ በአዳማ ከተማ አገልግሎቱን ሲሰጥ ቆይቷል።

ይህ የ5G ኔትዎርክ አገልግሎት በአዲስ አበባ ተደራሽነቱን አስፍቶ ለተጠቃሚዎች መቅረቡን የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ ዛሬ በነበረው ይፋዊ የማብሰሪያ መድረክ ላይ ተናግረዋል።

እንደ ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ገለጻ በኢትዮጵያ ይህንን አገልግሎት በአዲስ አበባ 145 ሳይቶች ላይ የ5G ኔትዎርክ ማስፋፊያ የተደረገ ሲሆን 630 ሺ ደንበኞቹ ይህንን አገልግሎት ለመጠቀም የሚያስችል ቀፎ (Device) መኖሩን አስታውቀዋል።

ይህ አገልግሎት ከተዘረጋባቸው ቦታዎች መካከል ከመስቀል አደባባይ እስከ ቦሌ ኤርፖርት፤ ከመስቀል አደባባይ መገናኛ CMC እንዲሁም ወደ ሰሚት የሚወስደው መንገድ፤ ከመስቀል አራት ኪሎና ስድስት ኪሎ ድረስ፤ ከመስቀል አደባባይ ሜክሲኮ ሳር ቤት እንዲሁም ልደታ ከመስቀል አደባባይ ለገሀር ቸርቸል ጎዳና ይህ መሰረተ ልማት የተዘረጋላቸው አከባቢዎች ናቸው ተብሏል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ በመግለጫቸው ተቋሙ በቀን በአማካይ ወደ 2,087 GB የዳታ ትራፊክ መኖሩን የገለጹ ሲሆን ከዚህ ውስጥም የ4G አገልግሎቱ ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚይዝ ጠቁመዋል።

በአለማችን ወደ 110  ሀገረት በአፍሪካ ደግሞ 16 ሀገራት ይህንን አገልግሎት የጀመሩ ሲሆን አሁን ላይ 1.3 ቢሊዮን ተጠቃሚዎችን የ5G ኔትዎርክ ተጠቃሚ መሆናቸው በመድረኩ ተገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ኢትዮ ቴሌኮም 630 ሺ ደንበኞቹ ዛሬ ይፋ ያደረገውን የ5G ኔትወርኩን መጠቀም ይችላሉ ብሏል። ኢትዮ ቴሌኮም የ5ኛውን ትውልድ (5G) የሞባይል ኔትወርክ በሙከራ ደረጃ በአዲስ አበባ እንዲሁም በአዳማ ከተሞ በሙከራ ደረጃ ሲያቀርብ ቆይቶ ዛሬ በይፋ በአዲስ አበባ አገልግሎት ማስጀመሩን አስታውቋል። ኢትዮ ቴሌኮም የ5ኛውን ትውልድ (5G) የሞባይል ኔትወርክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሞከው በአዲስ አበባ…
የ5G ያልተገደበ የኢንተርኔት አገልግሎት ዋጋ ስንት ነው ?

ኢትዮ ቴሌኮም አሁን ላይ 81.8 ሚሊዮን ከኔትዎርክ የተገናኙ መሳሪያዎች መኖራቸውን ያሳወቀ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 42 በመቶ የሚሆነው ስማርት ስልኮች (Smart Phones) መሆናቸውን ገልጿል።

በተጠቃሚዎች ቁጥር ደግሞ 34.4 ሚሊዮን ሰዎች የኢንተርኔት ዳታ ተጠቃሚ ናቸው ያለው ተቋሙ፥ እነዚህ ደንበኞቹ በአማካይ በቀን 2,087 GB ዳታ ዝውውር (Average Daily data traffic) የሚፈጽሙ ሲሆን ከዚህ ውስጥ የ4G ተጠቃሚዎቹ 66 በመቶ የሚሆነውን እንደሚሸፍኑ አስታውቋል።

አዲሱ የኢትዮ ቴሌኮም የ5G ኔትዎርክ በአዲስ አበባ ከተማ በተወሰነ ክልል ለተጠቃሚዎች የቀረበ ሲሆን የራሱ የክፍያ ፖኬጆችም ተዘጋጅተውለታል።

ይህ የክፍያ ፖኬጅ ከዚህ በፊት ከነበሩት የኔትወርክ አገልግሎቶች (4G, 3G, 2G) የዋጋ #ጭማሪ ያለው ነው።

በዚህም ኢትዮ ቴሌኮም ወርኃዊ ያልተገደበ የ5G አገልግሎቱን በ1,199 ብር እና በ300 GB ፍትሃዊ የአጠቃቀም ፖሊሲ ባለው (FUP) እንዲሁም ፕሪሚየም የተሰኘውን ወርኃዊ ያልተገደበ ጥቅሉን በ1,299 ብር በ400 GB ፍትሃዊ የአጠቃቀም ፖሊሲ ባለው (FUP) ለተጠቃሚዎች አድርሷል።

ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮ ቴሌኮም ያልተገደበ 150 GB የ5G ኢንተርኔት በ929 ብር እንዲሁም 250 GB ደግሞ 979 በር ለተጠቃሚዎች አቅርቧል።

ኢትዮ ቴሌኮም ከዚህ ቀደም በነበረው ኔትዎርክ ወርኃዊ ያልተገደበ የኢንተርኔት አገልግሎት በ999 ብር ለተጠቃሚዎች እንደሚያቀርብ ይታወሳል።

የ5G ኔትዎርክ አገልግሎት ለመጠቀም ምን ላድርግ ?

ኢትዮ ቴሌኮም አሁን ላይ 5G ኔትዎርክ መቀበል የሚችሉ መሳሪያዎችን የያዙ ደንበኞችን ልየታ አጠናቆ ወደ ኔቶርኩ እያስገባ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የገለጸ ሲሆን በቀጣዮቹ ቀናት ይህ ሥራ እንደሚጠናቀቅም አሳውቋል።

በመሆኑም ደንበኞች ወደ ኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ ማዕከላት ሳይሄዱ አገልግሎቱን መጠቀም የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ የጹሑፍ መልዕክት የሚደርሳቸው ይሆናል ተብሏል።

ደንበኞች በራሳቸው ይህንን አገልግሎት ለመጠቀም መጀመሪያ የያዙት ስልክ ወይም ኢንተርኔት ማስጠቀም የሚችል ቁስ (Device) የ5G ኔትዎርክ መቀበል እንደሚችል መሆኑን ማረጋገጥ ይችላሉ።

NB : የፍትሃዊ አጠቃቀም ፖሊሲ (FUP) ማለት ኢንተርኔት አቅራቢዎች ያልተገደበ የኢንተርኔት አገልግሎቶችን አላግባብ የመጠቀምን ወይም የመተላለፊያ ይዘትን (Bandwidth) ከመጠን በላይ መጠቀምን ለመከላከል የሚያስችላቸውና ፍጥነትን የሚቀንሱበት አሰራር ነው። ኢትዮ ቴሌኮም ይህንን ፖሊሲ ከዚህ ቀደም የሰዓት እና የቀን ያልተገደበ የኢንተርኔት አገልግሎቶች ላይ ተግባራዊ አድርጓል።

ፎቶ 1 ፦ ለተጠቃሚዎች የቀረበውን የዳታ ጥቅል የሚያሳይ

ፎቶ 2፦ የ5G አገልግሎት የተዘረጋባቸው አከባቢዎች የሚያሳይ

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethiopia