TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#G20

አፍሪካ ህብረት G20ን እንዲቀላቀል ጥሪ ቀረበለት።

የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የ " አፍሪካ ህብረት " የቡድን 20 አባል እንዲሆን በዛሬው ዕለት ጥሪ ማቅረባቸውን ቪኦኤ ዘግቧል።

በሚቀጥለው ወር በሕንድ ፤ ኒው ዴሊ የቡድኑ መሪዎች ጉባኤ ይካሄዳል።

ሞዲ ለአፍሪካ ህብረት ጥሪውን ያቀረቡት " ቢ20 የተሰኘው በቢዝነስ ፎረም እና የመስከረም ወሩ ጉባዔ መዳረሻ መድረክ ላይ ማደረጉት ንግግር ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ የዓለም አቀፉ የአቅርቦት ሰንሰለት ችግሮችን ለመቅረፍ ሀገራቸውን እንደመፍትሔ አቅርበዋል።

የ20 ግዙፍ ኢኮኖሚዎች ስሪት የሆነው ቡድን 19 አገሮችን እና የአውሮፓ ህብረትን በአባልነት ያቀፈ ሲሆን ፣85 በመቶውን ዓለም አቀፉ ጥቅል የሀገራት ምርት መጠን እና ከዓለም ህዝብ መካከል ደግሞ ሁለት ሶስተኛውን ይሸፍናል።

ይሁንና ከአፍሪካ የህብረቱ ብቸኛ አባል ደቡብ አፍሪካ ናት።

በታህሳስ ወር የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የአፍሪካ ህብረት የቡድን 20 ሀገራት G20 ቡድንን በቋሚ አባልነት እንዲቀላቀል እንደሚፈልጉ ተናግረው ነበር።

በዛሬው ዕለት የወቅቱ የቡድኑ ጉባዔ አስተናጋጅ ሀገር ሕንድ መሪ ሞዲ ባለፈው አመት በአጠቃላይ 3 ትሪሊዮን ዶላር አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት ያስመዘገበው ፓን- አፍሪካዊ ህብረት በቡድኑ አባልነት እንዲካተት ጥሪ አቅርበዋል።

" ቋሚ አባልነት በመስጠት ራዕይ ውስጥ ለአፍሪካ ህብረት ግብዣ አቅርበናል " ሲሉ ተናግረዋል ።

መቀመጫውን በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ ያደረገው የአፍሪካ ህብረት 55 አባላት ያሉት ሲሆን በወታደራዊ አስተዳደር ስር የሚገኙ አምስት ሀገራት ግን በአሁኑ ጊዜ ከአባልነት ታግደዋል ሲል ቪኦኤ በዘገባው አስታውሷል።

የቡድን 20 አባላት እነማን ናቸው ?

🇦🇷 አርጀንቲና
🇧🇷 ብራዚል
🇨🇦 ካናዳ
🇨🇳 ቻይና
🇫🇷 ፈረንሳይ
🇩🇪 ጀርመን
🇮🇳 ህንድ
🇮🇩 ኢንዶኔዥያ
🇮🇹 ጣልያን
🇯🇵 ጃፓን
🇰🇷 ደቡብ ኮሪያ
🇲🇽 ሜክሲኮ
🇷🇺 ሩስያ
🇸🇦 ሱዑዲ አረቢያ
🇿🇦 ደቡብ አፍሪካ
🇹🇷 ቱርክ
🇦🇺 አውስትራሊያ
🇬🇧 ዩናይትድ ኪንግደም
🇺🇸 አሜሪካ
🇪🇺 አውሮፓ ሕብረት ናቸው።

@tikvahethiopia