TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኪም_ጆንግ_ኡን

" የወንበዴ አለቆች " - ኪም ጆንግ ኡን

" በጣም ጸያፍ ቋንቋ በመጠቀማቸው እናዝናለን " - የደቡብ ኮሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን የሀገሪቱን የባህር ኃይል ቀንን ምክንያት በማድረግ የባህር ኃይል ማዘዣን መጎብኘታቸው ተነግሯል።

በዕለቱ አሰምተዋል በተባለ ንግግር ኪም ፤ የሀገሪቱን የባህር ኃይል እንዲጠናከር ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

አሜሪካ በኮሪያ ልሳነ ምድር አቅራቢያ የሚገኘውን ውሃ " የኑክሌር ጦርነት አደጋ " ወደደቀነ ከፍተኛ አለመረጋጋት ቀይራለች ሲሉ ከሰዋል።

አሜሪካ፣ ደቡብ ኮሪያ እና ጃፓን  ፤ የሰሜን ኮሪያን የኒውክሌር ስጋት ለመቋቋም በሚል የባህር ኃይል ልምምድ እንቅስቃሴ ጨምሮ በቅርቡ የጋር ስብሰባ አድርገው ነበር።

የሶስቱ ሀገራት እንቅስቃሴ ኪምን ያስቆጣ ሲሆን አገራቸውን ለመውረር ያሴሩትን ሴራ ለማክሸፍ ወታደራዊ ኃይላቸው ያለማቋረጥ ዝግጁ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።

ኪም ጆንግ ኡን የሶስቱ ሀገራት መሪዎችን (ጆ ባይደን፣ ዩን ሱክ ዮል እና ፉሚዮ ኪሺዳ) " የወንበዴ አለቆች " ሲሉ ኃይለቃል ተጠቅመው ተናግረዋቸዋል።

የደቡብ ኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኪም ፤ የደቡብ ኮሪያን ፣ የአሜሪካ ፣ እና የጃፓን መሪዎችን ስም ለማጥላላት " በጣም ጸያፍ ቋንቋ " በመጠቀማቸው እንዳዘነ ገልጿል።

ሚኒስቴሩ ፤ " ሰሜን ኮሪያ ውጥረት የሚፈጥሩ ድርጊቶችን በግድ የለሽነት የትነዛቸውን ዛቻዎች እና ቅስቀሳዎች  " ማቆም አለባት ብሏል።

ፎቶ ፦ ኪም ጆንግ ኡን ከልጃቸው ጋር - የሰሜን ኮሪያ ሚዲያ KCNA

@tikvahethiopia
#Mekelle

በጦርነት የተጎዱ የትግራይ ኃይል አባላት በዛሬው ዕለት በመቐለ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል።

ሰልፈኞቹ
የ 85ቱ፣ 93 ቱ በ2015 ደገሙት፤
ድምፃችን ይሰማ ፤
ለህዝብ እንጂ ለግለሰብ አልታገልንም፤
ተጠቅመው ጥለውናል፤
መንግሰት ያየ ፍትህ ያየ ፤

የሚሉና ሌሎች መፈክሮች እያሰሙ በመቐለ ዋና ዋና መንገዶች ድምፃቸው አሰምተዋል።

ይህንን ዘገባ እስከተጠናከረበት ድረስ ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት የተሰጣቸው መልስ የለም።

ሰላማዊ ሰልፉ ላይ ፓሊስ ስነ-ስርዓት በማስከበር መሳተፉ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ከቦታው ዘግቧል።

Via @tikvahethiopiatigrigna (መቐለ)

@tikvahethiopia
⛽️ነዳጅ ቀድተው ለክፍያ ቴሌብር ሲሆን ምርጫዎ...

🛒ሁልጊዜ ኪስ አይሞላምና ለግብይት ክፍያ የጎደለን የሚሞላው ቴሌብር  እንደኪሴ እስከ 2000 ብር
🫰እንዲሁም እስከ 6,000 ብር የቴሌብር መላ የብድር ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ በደስታ እንገልጻለን!

በቴሌብር ሱፐርአፕ  https://onelink.to/fpgu4m ወይም *127#  የፋይናንሺያል አገልግሎት ስር እንደኪሴ እና መላ አገልግሎቶችን ያስጀምሩ
#Bank_of_Abyssinia

አቢሲንያ ባንክ ለዕድሮች ባዘጋጀው ዕድል ለመጠቀም አሁኑኑ ወደ ቅርንጫፎች ጎራ ይበሉ።

ለበለጠ መረጃ ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ፡፡ https://www.bankofabyssinia.com/saving-account/

#Edir #BankofAbyssinia  #BankingService  #DigitalEthiopia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
" ካለፈው ሃምሌ ወር አንስቶ በትንሹ 183 ሰዎች ተገድለዋል " - ተመድ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ቢሮ ዛሬ ማክሰኞ መግለጫ አውጥቷል።

ምን አለ ?

- በአንዳንድ የኢትዮጵያ ክልሎች ያለው የሰብአዊ መብት ሁኔታ መባባሱ በጣም ያሳስበናል ብሏል።

- ከሀምሌ ወር አስቶ በአማራ ክልል በተቀሰቀሰ ግጭት በትንሹ 183 ሰዎች መገደላቸውን ካሰባሰብነው መረጃ መረዳት ችለናል ሲል ገልጿል።

- አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀ በኃላ በመላው ኢትዮጵያ ከ1,000 በላይ ሰዎች መታሰራቸው መረጃ ደርሶናል ፤ ከታሰሩት መካከል ብዙዎቹ የፋኖ ደጋፊዎች ተብለው የተጠረጠሩ የአማራ ብሄር ተወላጅ ወጣቶች ናቸው ብሏል። ከነሃሴ መጀመሪያ አንስቶ የቤት ለቤት ፍተሻ ሲደረግ እንደነበር ፤ በአማራ ክልል ስላለው ሁኔታ ሲዘግቡ የነበሩ 3 ጋዜጠኞችም መታሰራቸውን ገልጿል።

- እስረኞቹ መሰረታዊ ነገሮች በሌላቸውና ምቹ ባልሆኑ የማቆያ ማዕከላት ውስጥ እንዲቀመጡ መደረጉ አመልክቷል።

- ባለሥልጣናት የጅምላ እስራት እንዲያቆሙ፣ ማንኛውም የነፃነት መነፈግ ድርጊት በፍርድ ቤት እንዲታይ እና በዘፈቀደ የታሰሩ እንዲፈቱ ጠይቋል።

- ባለሥልጣናት የታሰሩ ሰዎች ሁኔታ ዓለም አቀፍ ደንቦችን እና ደረጃዎችን የሚያከብሩ መሆናቸውን ማረጋገጥ እንዳለባቸው እንዲሁም የተመድ የሰብአዊ መብት ጽ/ቤት እና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ተቆጣጣሪ አካላት ሁሉንም የእስር ቦታዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲያዩ እንዲፈቅዱ ጠይቋል።

- በተወሰኑ የአማራ ክልል ከተሞች የፌደራል ሃይሎች መኖራቸውን ተከትሎ የፋኖ ታጣቂዎች ወደ ገጠራማ አካባቢዎች ማፈግፈጋቸውን የገለፀው ተመድ ሁሉም ተዋናዮች ግድያ፣ ጥቃትና ሌሎች ጥሰቶች እንዲያቆሙ ጠይቋል። ቅሬታዎች በውይይት እና በፖለቲካ ሂደት መፍታት አለባቸውም ብሏል።

- በምዕራብ ትግራይ አወዛጋቢ ቦታዎች ከ250 የማያንሱ የትግራይ ተወላጆች በአማራ ፖሊስ፣ በአካባቢው ባለስልጣናት እንዲሁም በአካባቢው ታጣቂዎችና በታጠቁ የወልቃይት ተወላጆች ባካሄዱት ዘመቻ መታሰራቸውን ገልጿል። በኃላም ወደ ትግራይ ጊዜው አስተዳደር ስር ወዳለ አካባቢ በታጠቁ የወልቃይት ወጣቶች እየተወሰዱ ሳለ በመከላከያ ሰራዊት እጅ መግባታቸውና በኃላም መከላከያ ልየታ አደርጎ የትግራይ ተወላጆቹ ወደ ምዕራብ ትግራይ እንዲመለሱ ወይም እዛው በጊዜዊ አስተዳደሩ ስር ባለ አካባቢ እንዲሆኑ የሚል ምርጫ እንደሰጣቸው ገልጿል።

- በኦሮሚያ ክልልም የሰብአዊ መብት ረገጣ እና ወንጀሎች መቀጠላቸውን በማመልከትም በአሁኑ ወቅት በክልሉ ያለው ሁኔታ አሳሳቢ ነው ብሏል።

(የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ከነዳጅ ዋጋ 📈

ቤንዚን እና ናፍጣ ላይ በሊትር ከ5 ብር በላይ ጭማሪ ተደረገ።

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ጭማሪ ተደርጓል።

ከዛሬ ጀምሮ ለአንድ ወር የሚቆይ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ይፋ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ገልጿል።

ሚኒስቴሩ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ የዓለም ነዳጅ ዋጋ ከሚያዝያ ወር 2015 ጀምሮ እስከሰኔ ወር መጨረሻ ድረስ አንጻራዊ መረጋጋት እንደታየበት ገልጿል፡፡

በዚህም ፥ ላለፉት አራት ወራት በችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ለውጥ ሳይደረግ መቆየቱን አስታውሷል፡፡

ሆኖም ግን የዓለም ነዳጅ ዋጋ ከሐምሌ ጀምሮ የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ እያሳየ በመምጣቱ ዋጋውን ማሻሻያ ማድረግ ማስፈለጉ ተገልጿል፡፡

በዚሁ መሰረት ፦

1. ቤንዚን 👉 74 ብር ከ85 ሳንቲም በሊትር

2. ነጭ ናፍጣ 👉 76 ብር ከ34 ሳንቲም በሊትር

3. ኬሮሲን ብር 👉 76 ብር ከ34 ሳንቲም በሊትር

4. የአውሮፕላን ነዳጅ 👉 68 ብር ከ58 ሳንቲም በሊትር

5. ቀላል ጥቁር ናፍጣ 👉 62 ብር ከ22 ሳንቲም በሊትር

6. ከባድ ጥቁር ናፍጣ 👉 61 ብር ከ07 ሳንቲም በሊትር መሆኑ ተገልጿል።

ምንጭ፦ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ከነዳጅ ዋጋ 📈 ቤንዚን እና ናፍጣ ላይ በሊትር ከ5 ብር በላይ ጭማሪ ተደረገ። የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ጭማሪ ተደርጓል። ከዛሬ ጀምሮ ለአንድ ወር የሚቆይ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ይፋ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ገልጿል። ሚኒስቴሩ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ የዓለም ነዳጅ ዋጋ ከሚያዝያ ወር 2015 ጀምሮ እስከሰኔ ወር መጨረሻ ድረስ አንጻራዊ መረጋጋት እንደታየበት ገልጿል፡፡ በዚህም…
በነዳጅ ምርቶች ላይ የተደረገው ጭማሪ ምን ያህል ነው ?

ላለፉት አራት ወራት ማለትም እስከ ትላንት ድረስ ቤንዚን በሊትር 69 ብር ከ52 ሳንቲም ሲሸጥ የነበረ ሲሆን ከዛሬ ጀምሮ ግን በሊትር 74 ብር ከ85 ሳንቲም እንዲሸጥ ተወስኗል።

ነጭ ናፍጣ በሊትር 71 ብር ከ15 ሳንቲም ሲሸጥ የነበረ ሲሆን ወደ 76 ብር ከ34 ሳንቲም ከፍ ብሏል።

የቤንዚን እንዲሁም የነጭ ናፍጣ ላይ የደረገው የዋጋ ጭማሪ ከ5 ብር በላይ ነው።

ኬሮሲን በሊትር 71 ብር ከ15 ሳንቲም ሲሸጥ የነበረ ሲሆን ከ5 ብር በላይ ጭማሪ ተደርጎ በሊትር 76 ብር ከ34 ሳንቲም ገብቷል።

የአውሮፕላን ነዳጅ በሊትር 65 ብር ከ35 ሳንቲም የነበረው ከ3 ብር በላይ ጭማሪ ተደርጎ አሁን 68 ብር ከ58 ሳንቲም በሊትር ገብቷል።

ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 57 ብር ከ97 ሳንቲም የነበረው ከ4 ብር በላይ ጭማሪ ረደርጎ 62 ብር ከ22 ሳንቲም በሊትር ገብቷል።

ከባድ ጥቁር ናፍጣ ደግሞ በሊትር 56 ብር ከ63 ሳንቲም የነበረው 61 ብር ከ07 ሳንቲም ገብቷል።

ሚያዚያ ወር 2015 ላይ ጭማሪ ከተደረገ በኃላ እስከ ትላንት ድረስ የነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ሳይደረግ ባለበት እንዲቀጥል ተወስኖ የነበረ ሲሆን የዓለም የነዳጅ ዋጋ በመጨመሩ ምክንያት አሁን ላይ የነዳጅ ዋጋ መጨመር እንዳስፈለገ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#Amhara

በአማራ ክልል ፤ ምንም እንኳን የትጥቅ ግጭቶች ከከተማ ወጣ ባሉ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ቀጥለው የነበር ቢሆንም ከሰሞኑን ግን እንደ ደብረ ታቦር እና ደብረ ማርቆስ ባሉ ትልልቅ ከተሞች ዳግመኛ የከተማ ውስጥ ግጭት ተደርጎ በርካታ ሰዎች መሞታቸው ታውቋል።

በደብረ ታቦር ካለፈው ቅዳሜ እስከ ሰኞ ድረስ በከተማ ውስጥ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ በርካታ ሲቪል ሰዎች መጎዳታቸውን ፣ ተቋማትም መጎዳታቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል።

በተለይ ባለፈው ቅዳሜ እና እሁድ፣ ሰኞም በነበረ ግጭት የንፁሃን ዜጎች ህይወት አልፎ እንደነበር በርካቶችም ቆስለው ወደብረ ታቦር ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ገብተው እንደነበር ታውቋል።

አንድ ስማቸው እንዲነገር ያልፈለጉ የሆስፒታሉ ምንጭ፤ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሆስፒታሉ በከባድ መሳሪያ ተመታ እየተባለ የሚሰራጨው ወሬ ሀሰት ነው ሲሉ ለቪኦኤ ተናግረዋል።

" ሆስፒታሉ ምንም አልተመታም ውሸት ነው ፤ የተወሰነ ተኩስ ሲለዋወጡ አንድ አስታማሚ በአጋጣሚ ሲያልፍ ተመቶ ቆስሎ እየታከመ ነው። ከዛ ውጭ ሆስፒታሉ አልተመታም ሌላውም ደህና ነው። አሉባልታ ነው በጣም ብዙ ሰው ይሄን ጠይቆኝ ነበር " ብለዋል።

በደብረ ታቦር የሚኖሩ አንድ ነዋሪ በከተማው በተደረገው የተኩስ ልውውጥ የሁለት ልጆች አባት የሆኑ መምህር ጓደኛቸው መገደላቸውን ገልጸው ቀብራቸው ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን መፈፀሙን ገልጸዋል።

እስካሁን ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ንፁሃን መገደላቸውን ተናግረዋል።

ትላንት ማክሰኞ ባለፉት ቀናት በነበረው ግጭት የተገደሉ ሰዎችን አንስቶ የመቅበር ስራ ሲሰራ እንደነበር ፣ ተኩስም እንደቆመ፣ እንቅስቃሴ ቆሞ ከተማው ጭር እንዳለ እኚሁ ነዋሪ ጠቁመዋል።

በደብረ ማርቆስ በተመሳሳይ ካለፈው ቅዳሜ አንስቶ ግጭት አገርሽቶ የከተማ ውስጥ የተኩስ ልውውጥ ሲደረግ እንደነበር ነዋሪዎች የገለፁ ሲሆን ትላንት አንስቶ ግን ከከተማው ውጭ ከሚደረግ የተኩስ ልውውጥ ውጭ ከተማው ፀጥ እንዳለች መሆኑን ገልጸዋል።

በከተማው ከሰሞኑን በነበረው ግጭት የሰዎች ህይወት መጥፋቱን አመልክተዋል።

መረጃው የቪኦኤ ነው።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia