#Mekelle
የኢፌዴሪ የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን የባለድርሻ እና አጋር አካላት የውይይት መድረክ #በመቐለ ለመጀመርያ ጊዜ ይካሄዳል።
ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫ የባለድርሻ እና አጋር አካላት መድረክ ለመጀመርያ ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን በመቐለ እንዲደረግ የተወሰነበት ምክንያት ከሰላም ስምምነቱ ብኋላ ክልሉ ላይ አንፃራዊ መረጋጋት መፈጠሩ እና በሁለቱም ተስማሚ ወገኖች የመተማመን ጉዳዩ መጎልበቱን ማሰያ ነው ብሏል።
በመድረኩ ለመሳተፍ የተለያዮ ባለድርሻ እና አጋር አካላት ከፌዴራል መንግስት የተላከ የልኡኳን ቡድን በአምባሳደር ተሾመ ቶጋ መሪነት ዛሬ መቐለ ገብቷል።
የፌደራል መንግስቱ ልኡኳን ብድኑ ከጠቅላይ ሚኒስተር ፅህፈት ቤት፣ የሰላም ሚኒስቴር ፣ የመከላከያ ሰራዊት፣ የሰቪክ ማህበራት፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲሁም ከንግድ ሚኒስቴር እና የተለያዮ ክልሎች ተወካዮች ያካተተ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
#ድምፂወያነ
@tikvahethiopia

በዶ/ር ሊያ ታደሰ የተመራ ልዑክ መቐለ ገባ።
በጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የተመራው የጤና ሚኒስቴር ልዑካን ቡድን ዛሬ መቐለ ገብቷል።
ልዑኩ ከክልሉ አስተዳደር ጋር በተለያዩ የጤና ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚነጋገር ይጠበቃል።
ፎቶ ፦ ድምፂ ወያነ

የመቐለ ወደብና ተርሚናል አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አስታውቋል።
በጦርነት ተቋርጦ የቆየው የመቐለ ወደብና ተርሚናል ወደ መደበኛ አገልግሎት መመለሱ ተገልጿል።
በዚህም መዳረሻቸው መቐለ ወደብና ተርሚናል ለሆኑ ገቢ ጭነቶችን ከዛሬ ሚያዝያ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ከመነሻ የባሕር ወደብ ለመቐለ ኦፕሬሽን መክፈት የሚቻል መሆኑ ተነግሯል።

TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዛሬ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና የሰላም ልኡካኑ መቐለ ትግራይ ሲደርሱ በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ካብኔ ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ አማኑኤል አሰፋ እና ሌሎች የክልሉ አመራሮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ልዑኩ በመቐለ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ…
#Mekelle
በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የተመራው የሰላም ልኡክ ዛሬ ከሰአት በተለምዶ " መቐለ 70 ካሬ " ተብሎ በሚጠራው የተፈናቃዮች መጠለያ ጉብኝት አድርጓል።
በጉብኝቱ ተፈናቃዮች " ቅዱስ ሲኖዶሱ ለበዳዮች ወግንዋል " በማለት በድምፅና በፅሁፍ ተቋውሞ ማሰማታቸውን በስፍራው የነበሩ የመቐለ ቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ገልጸዋል።
ቅዱስ ፓትሪያርኩ ፤ " በውስጣችሁ የሚሰማችሁን እንኳን ተናገራችሁ " ካሉ በኋላ ፤ " ሰሚ ከተገኘ ወደ ቀያችሁ እንድትመለሱ ለሚመለከተው እንናገራለን " ብለዋል።

" በመቐለ ከተማ ከ184 ሄክታር በላይ የመንግስትና የህዝብ መሬት መጭበርበሩ በጥናት ተረጋግጧል " - የከተማዋ ከንቲባ ይትባረክ ኣምሃ
በትግራይ የነበረውን ጦርነት ተከትሎ በክልሉ ከተሞች ህገ ወጥነት ተንሰራፍቶ በርካታ ወንጀሎች መፈፀማቸው የመቐለ ከንቲባ ይትባረክ ኣማሃ ገለፁ።
ከንቲባው ፤ የመንግስትና የህዝብ መሬት ዘረፋና የፀጥታ መደፍረስ ዋነኛ ተጠቃሽ ችግሮች እንደሆኑ ጠቁመዋል።
የመሬት ወረራው የተካሄደው ለምቶ ወደ ተጠቃሚዎች ለመተላለፈ በተዘጋጀ ፤ በእርሻና በመንግስት ክፍት ቦታ ፤ ከገጠር ወደ ከተማ በተካለለና በተቀሙ የኢንቨስትመንት መሬቶች መሆኑ የገለፁት አቶ ይትባረክ ፤ " በህገወጥ ተግባሩ 3337 ሰዎች ተሳትፈዋል " ብለዋል።
" በመሬት ወረራው የተሳተፉ ህገወጦች በህግ እንዲጠየቁ የህዝቡ ጥያቄ ጭምር ነው " ያሉት ከንቲባ ይትባረክ " ከእርምጃው በፊት የተወረረው መሬት ማጥናት ፣ ቦታዎቹ የሰነዱ ፋይሎች ድህንነት ማረጋገጥ ተጠናቅቆ ወደ ተግባር ተገብቷል " ሲሉ ገልጸዋል።
አሳሳቢ የሆነውን የከተማዋ የፀጥታ ጉዳይ ለመፍታት እየተሰራ መሆኑ የገለፁት አቶ ይትባረክ በተካሄደው ጥናትና ክትትል በቡድን የሚዘርፉ ፣ ህገ-ወጥ ሕትመት የሚያካሂዱ ፣ የመሬት ፕላን ሰርተው የሚሸጡ ፣ አደንዛዥ ዕፅ የሚያዘዋውሩ የፎርጅድ ገንዘብ ማተምያ ማሽንና የተለያዩ ህገ ወጥ ገንዘቦች እጅ በፈንጅ ተይዘዋል ብለዋል።
የመሬት ወረራ ሆነ የሚፈፀሙ ህገወጥ ተግባራት ለመቆጣጠር እየተሰራ መሆኑ ያብራሩት ከንቲባው ህዝቡ መረጃና ሰነዶች ከመስጠት እስከ መመስከር ንቁና ተባባሪ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።
መረጃውን የመቐለ ቲክቫህ አባል የተላከ ነው።