TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" ወደ ውድድር ከመግባታችን በፊት ተነጋግረን ወርቅ ፣ ብር እና ነሀስ እንዲመጣ እናደርጋለን " - አትሌት ለተሰንበት ግደይ በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሀገራችን በሴቶች 5000 እና 10,000 ሜትር ረጅም ርቀት ውድድር ሁለቱም የወርቅ ሜዳሊያ በአትሌት ለተሰንበት ግደይ (10,000 ሜትር) እና ጉዳፍ ፀጋይ (5000 ሜትር) መገኘት ችሎ ነበር። ሁለቱም አትሌቶች አምና ሀገራችን በርቀቱ ላስመዘገበችው…
ተጀመረ !

በከፍተኛ ጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የ10,000 ሜትር የሴቶች ፍፃሜ ውድድር ተጀምሯል።

ሀገራችን ፦

- በአትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ፣
- በአትሌት ለተሰንበት ግደይ ፣
- በአትሌት እጅጋየሁ ታዬ
- በአትሌት ለምለም ሀይሉ ተወክላለች።

ውድድሩን በብሔራዊ ቴሌቪዥን መዝናኛ ቻናል እንዲሁም በDSTV 226 ላይ መመልከት ይቻላል።

ድል ለሀገራችን !
ድል ለአትሌቶቻችን !

@tikvahethiopia
ኢትዮጵያ ወርቅ !
ኢትዮጵያ ብር !
ኢትዮጵያ ነሃስ !

@tikvahethiopia
ጉዳፍ ፀጋይ ወርቅ
ኢትዮጵያ

🥇ጉዳፍ - ወርቅ
🥈ለተሰንበት - ብር
🥉እጅጋየሁ - ነሃስ

የኔዘርላንዷ አትሌት ሲፋን ሀሰን ውድድሩን በአንደኝነት ለመጨረስ በተቃረበችበት ወቅት ወድቃ አሳዛኝ ተሸናፊ ሆናለች።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ኢትዮጵያ 🥇ጉዳፍ - ወርቅ 🥈ለተሰንበት - ብር 🥉እጅጋየሁ - ነሃስ የኔዘርላንዷ አትሌት ሲፋን ሀሰን ውድድሩን በአንደኝነት ለመጨረስ በተቃረበችበት ወቅት ወድቃ አሳዛኝ ተሸናፊ ሆናለች። @tikvahethiopia
ፎቶ ፦ ሀገራችን #ኢትዮጵያ ❤️ ዛሬ በተጀመረው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ10 ሺህ ሜትር የሴቶች ፍፃሜ የወርቅ ፣ ብር ፣ ነሃስ ሜዳሊያዎችን አስመዝግባለች።

በሀንጋሪ የሚገኘው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ የስፖርት ባልደረባ ከላይ የተያያዙትን ፎቶዎች አድርሶናል።

More 👇
https://t.iss.one/+VvwzStMNcNHmhK0x

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ ሀገራችን #ኢትዮጵያ ❤️ ዛሬ በተጀመረው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ10 ሺህ ሜትር የሴቶች ፍፃሜ የወርቅ ፣ ብር ፣ ነሃስ ሜዳሊያዎችን አስመዝግባለች። በሀንጋሪ የሚገኘው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ የስፖርት ባልደረባ ከላይ የተያያዙትን ፎቶዎች አድርሶናል። More 👇 https://t.iss.one/+VvwzStMNcNHmhK0x @tikvahethiopia
" የህዝባችን ፀሎት ሰምሯል " - ጉዳፍ ፀጋይ

የወርቅ አሸናፊዋ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ከድሏ በኃላ ስለ ቡድን ስራ እንዲሁም ደግሞ አጠቃላይ የተሰማትን ስሜት ተጠይቃ ተከታዩን ብላለች።

ጉዳፍ ፀጋይ ፦

" ተነጋግረን ነበር የገባነው።

ዋናው ነገር #ወርቁን ማምጣት ስለሆነ ተነጋግረን እኔ 16 እና 17 ፤ ከዛ ሁለት ዙር ሲቀር በራሳችንን አቅም መሄድ ነበርና ወርቁ ከራሳችን እንዳይወጣ ነበር ጥረት ስናደርግ የነበረው።

እግዚአብሔርም ሲጨመርበት ነውና ውጤት የሚያምረው የህዝባችን ፀሎት ሰምሯል። "

ጉዳፍ ውድድሩን በበላይነት ያጠናቀቀችው እግሯ እየደማ ሲሆን ይህ እንዴት እንደተፈጠረ ተጠይቃ መልሳለች።

" ሩጫ ላይ እንዲህ ያለው ነገር ያጋጥማል። በሩጫው መሃል ላይ ተነክቼ ነው እንደዛ የሆነው። 17 ወይም 18 ላልፍ አካባቢ ነው እግሬ የደማው " ብላለች።

ምናልባት ሲፋን ሀሰን ባትወድቅ ኖሮ ውጤቱ ይቀየር ነበር ? ተብላ ተጠይቃም መልሳለች።

ጉዳፍ ፀጋይ ፥

" እኔ እስከመጨረሻው ድረስ በጭራሽ እጅ አልሰጥም ብዬ ነው የገባሁት። ምክንያቱም እኔ ህዝቤ ይደግፈኛል ከሚገባው በላይ ፤ ወርቅ ማምጣት ምን ያህል እንደሆነ የህዝቡን ስሜት አይቻለሁ ፤ ከጎኔ ሆነው የሚደግፉኝ የኢትዮጵያ ህዝብ አሉና እነሱን ለማስደሰት ፣ ለራሴም ታሪክ ስለሆነ እስከመጨረሻው ተስፋ አልቆረጥኩም " ብላለች።

ሲፋን ሀሰን ምን አለች ?

በመጨረሻ ጥቂት ሰደንዶች ላይ ወድቃ ተሸናፊ የሆነችው ሲፋን ሀሰን " ተገፍቼ ነበር " ስትል ቃሏል ለቢቢሲ ሰጥታለች።

" እሷ ወደ ውጭ እየሮጠች ነበር እናም ተዘግቶብኝ ነበር " ያለችው ሲፈን ፤ " ግን ምን ታደርጋለህ ስፖርት ነው፣ ሊከሰት ይችላል " ስትል ተናግራለች።

የመጨረሻውን ትንቅንቅ በዚህ ይመልከቱ ፦ https://t.iss.one/+rbdEU4UaEdQxYWFk

የቪድዮ ባለቤት ፦ አረጋ ከፈለው
ፎቶ ፦ @tikvahethsport

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የህዝባችን ፀሎት ሰምሯል " - ጉዳፍ ፀጋይ የወርቅ አሸናፊዋ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ከድሏ በኃላ ስለ ቡድን ስራ እንዲሁም ደግሞ አጠቃላይ የተሰማትን ስሜት ተጠይቃ ተከታዩን ብላለች። ጉዳፍ ፀጋይ ፦ " ተነጋግረን ነበር የገባነው። ዋናው ነገር #ወርቁን ማምጣት ስለሆነ ተነጋግረን እኔ 16 እና 17 ፤ ከዛ ሁለት ዙር ሲቀር በራሳችንን አቅም መሄድ ነበርና ወርቁ ከራሳችን እንዳይወጣ ነበር ጥረት ስናደርግ…
" ውጤት የሚያስቀይር ስህተት የለም "

ከ10,000 ሜትር ሴቶች ውድድር በኃላ በሲፋን ሀሰን ጉዳይ የሀገሯ ሆላንድ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ወደ ዓለም አትሌቲክስ የዳኞች ቡድን ስለተፈጠረው ነገር ማረጋገጫ ለማግኘት ሄደው የነበረ  ቢሆንም ፤ ውጤት ሊያስቀይር የሚችል ስህተት እንደሌለ ተነግሯቸው መመለሳቸው ተሰምቷል።

Credit ፦  ሀይለ እግዚአብሔር አድሀኖም

More 👇
https://t.iss.one/+VvwzStMNcNHmhK0x

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba ምክንያቱ በግልፅ ይፋ ባልተደረገበት " ላልተወሰነ ጊዜ " የታገዱ በሞተር ስራ የሚተዳደሩ ዜጎች ቅሬታቸውን ገለፁ። የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የሞተር ብስክሌት ማሽከርከርን መጀመሪያ እስከ ነሐሴ 3/2015 ዓ.ም ማገዱ ፤ ከዛም በኃላ እግዱ ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን ማሳወቁ ይታወሳል። በከተማዋ ሞተር ለምን እንደታገደ በቢሮው በኩል እስካሁን የተሰጠ ማብራሪያም ይሁን…
እገዳው ተነሳ።

የሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ላይ ተጥሎ የነበረው እግድ ተነሳ፡፡

በአዲስ አበባ የሚገኙ የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎችና ባለንብረቶች በሙሉ ከነገ ነሐሴ 15/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ ከአሽከርካሪው ውጪ ሌላ ተጨማሪ ተሳፋሪ ሳይጨምሩ የሞተር ብስክሌት ማሽከርከር እንደሚቻል የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አሳውቋል፡፡

ከተፈቀደው የሰው መጫን አቅም በላይ በሚጭኑ ማህበራትና አሽከርካሪዎች ላይ ቢሮው ጥብቅ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ገልጿል።

አሽከርካሪዎችም ለትራፊክ አደጋ መንስኤ ከሆኑ ከፍጥነት በላይ ማሽከርከር፣ የራስ ቆብ መከለያ (ሄልሜት) አለመጠቀም፣ ከወንጀል ድርጊት በመራቅና ወንጀል የሚፈጽሙ ሲያጋጥሙም ለጸጥታ አካላት ጥቆማ እንዲሰጡ ቢሮው አሳስቧል።

@tikvahethiopia