TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አብን

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ በዛሬው ዕለት በአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ላይ መግለጫ አውጥቶ ነበር።

አብን በዚህ መግለጫው ፤ በየትኛውም አሰላለፍ እና አግባብ ስለአማራ ህዝብ የተሰለፉ ሀይሎች #ጦርነት ዘላቂ ጥቅምን ለማረጋገጥ አስቻይ እንዳልሆነ ሊገነዘቡት ይገባል ብሏል።

ይልቁን ጦርነት ህዝብን ለተደራራቢ የማህበራዊ ፣ ሰብአዊና ኢኮኖሚያዊ ድቀት ስለሚዳርግ ለሰላማዊ የፖለቲካ መፍትሄዎች ተገቢውን ስፍራ ሰጥተው ለክልሉ ሰላም መመለስ  ድርሻቸውን እንዲወጡ ሲል ጥሪ አቅርቧል።

" የአማራ ህዝብ ከሌላው የሀገሪቱ ህዝብ ጋር ያለውን የወንድማማችነት እሴቶች ከሚንዱ ቅስቀሳዎች ፣ በራሱ እና በልጆቹ የተመሰረቱ ተቋማትን በተለይም የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከሚያጠለሹ መልዕክቶች እንዲሁም የአማራ ህዝብ ማህበራዊ ረፍት እንዲያጣ ከሚመኙ አካላት በስልት የሚሰጡትን አጀንዳዎች በመጸየፍ ወደ ሰላም መድረክ የሚያመሩ መንገዶችን ሁሉ ለመጥረግ አቅሙ የፈቀደውን ርብርብ እንዲያደርግ " ሲል አብን አሳስቧል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#አብን

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ምክትል ሊቀመንበር ከኃላፊነታቸው ለቀቁ።

የአብን ምክትል ሊቀመንበር መልካሙ ሹምዬ በገዛ ፍቃዳቸው ከድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበርነት እና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነት መልቀቃቸውን ለፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ በፃፉት ደብዳቤ አሳውቀዋል።

ለምን እዚህ ውሳኔ ላይ ደረሱ ?

መልካሙ ሹምዬ ፤ በእስካሁኑ ቆይታቸው በግል እና በድርጅት ሥራዎች ያጋጠሙ ፈተናዎችን ለመቋቋም የበኩላቸውን ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸውን ገልጸዋል።

ነገር ግን ከአብላጫው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ጋር ያላቸው የአቋም ልዩነት እየሰፋ መሆዱን ጠቁመዋል።

የሃሳብ እና የአቋም ልዩነቱ ከሕዝቡን መብት ፣ ጥቅም እና ኅልውና መከበር አንጻር ያለው ትርጉም እና ውጤት ከፍ ያለ መሆኑን እንዳመኑበት ፤ በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ውስጥ አሁን ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር በኃላፊትነት መቀጠል የድርጅቱንና የሕዝቡን ጥቅም የሚያስከብር ሆኖ ባለማግኘታቸው ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን አሳውቀዋል።

መልካሙ ሹምዬ ምንም እንኳን ከኃላፊነት በገዛ ፍቃዳቸው ቢለቁም የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ #አባልነታቸውን ይዘው የሚቀጥሉ መሆኑን ገልጻዋል።

@tikvahethiopia
የጀነራል ተፈራ ማሞ ባለቤት ወ/ሮ መነን ኃይሌ ዛሬ ማምሻውን በፌደራል ፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር መዋሏን ባለቤታቸው ጀነራል ተፈራ ማሞ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ምሽት 12:00 አከባቢ ፖሊሶች ወደ ቤታቸው መምጣታቸውን የገለጹት ጀነራሉ፥ እስከ ምሽት 3:30 ድረስ ፍተሻ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

የእስሩ ምክንያትም " ከዚህ ቀደም በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ባስተላለፈችው መልዕክት ጋር ተያይዞ እንደሆነ ነው የነገሩን " ሲሉ ጀነራሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።

ፖሊስ ፍተሻውን የጎረቤት ታዛቢዎች ባሉበት ማከናወኑን ገልጸው በፍተሻው ወቅትም ከህግ የወጣ ድርጊት አለመፈጸሙን ገልጸዋል።

ከፍተሻው በኋላ " የእኔ የነበረ ክላሽ፤ የተወሰኑ ጥይቶች፤ የእርሷን ፖስፖርትና የባንክ ቡክ አብረው ወስደዋል" ሲሉ ነው የተናገሩት።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ተጨማሪ

የባህር ዳር ፣ ጎንደርና ሸዋሮቢት ነዋሪዎች ምን አሉ ?

የባህር ዳር ፣ ጎንደር ፣ ሸዋሮቢት ከተማ ነዋሪዎች ከተማቸው በመከላከያ ሰራዊት ስር እንደሚገኝና ዛሬ ተኩስ እንዳልነበር ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

#ባህርዳር

ነዋሪ 1

" ከትለንት ከግማሽ ለሊት በኃላ መከላከያው ተቆጣጥሮታል።

ተኩስም የለም፤ መከላከያው ተቆጣጥሮታል። አንፃራዊ ሰላም አለ።

መከላከያው ነው እየተንቀሳቀሰ ያለው። ሰውም እንደ ሰሞኑን ሳይሆን መንቀሳቀስ ጀምሯል። ግን አገልግሎት መስጫ ተቋማት ዝግ ናቸው በተረፈ ቁስለኛ እየተነሳ ሃኪም ቤት እየሄደ ነው ፣ የሞተውም እየተቀበረ ነው።

ዘንዘልማ አካባቢ ብዙ ሰው ስለሞት እነሱ እየተነሱ እየተቀበሩ ነው። ከሟቾች ወደ ሆስፒታል የተወሰዱ የተወሰኑ ናቸው እንጂ በቤተሰብ አማካኝነት እዛው እየተቀበረ ነው። ብዛት ያለው ሰው ደግሞ ከመኮድ ይወረወር የነበረ ከባድ ተወዋሪ መሳሪያ እሱ ነው ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰው። መኖሪያ ቤት ላይ እየወደቀ፤ ህፃናቶችም ሞተዋል።

ቁጥሩን ባልገልፅም ብዙ ሰላማዊ ሰው ሞቷል፣ በተለይ ቀበሌ 14 ላይ ከፍተኛ ውጊያ ነበር፤ በጣም ብዙ ሰው ሞቷል። ዛሬ ብዛት ያለው ሰው ቀብር ነው የዋለው። ህዝቡ እየወጣ መቅበር ጀምሯል። "

ነዋሪ 2

" እኛ ኤርፖርት አካባቢ ነን። ዛሬ ሰላም ነው። ተኩስም የለም። የተረጋጋ ነው። ግን ብዙ ሰው ፍራቻ ስላለው ወደ ከተማ አይሄድም። በጣም ብዙ የሞተ ሰው ስላለ ፍራቻ አለ። ነገር ግን ከንጋት ጀምሮ ምንም ድምፅ የለም።

በአብዛኛው ሲቪልያን ነው የሚሞቱት ካለመሳሪያ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ፣ የሚታኮሱት አይደለም የሚሞቱት በብዛት። ጀሌው አለ አይደል በአጋጣሚ መንገድ ለመዝጋት የሚሄደው ነው። "

#ጎንደር

ነዋሪ 1

" ጎነደር ከትላንት ማታ ጀምሮ ማለት ይቻላል ተኩሱ ቆሟል። መከላከያው ከተማው ውስጥ ያሉትን መንገዶች የማፅዳት ስራ እየሰራ ነው ያለው። መንገዶች በድንጋይም፣ በእንጨትም ተዘጋግተው ስለነበር።

ሌሎች እንቅስቃሴዎች ገና ናቸው። የሰው እንቅስቃሴም የለም። ቤት ውሥጥ ቁጭ ብለን ነው የሰነበትን ዛሬ ሳምንታችን ነው። የሚቀጥለው ምን እንደሚሆን እየጠበቅን ነው።

በትክክል ስለደረሰው ጉዳት ይህ ነው ማለት ባልችልም፤ ሰው ግን ለሳምንት ከገበያ ከሌሎችም አገልግሎቶች ተገልሎ መቆየቱ ብዙ ሰው አላሰበውም እሮብ ማታ ድረስ ጤናማ ስራውን እየሰራ ከዚያ ምሽት በኃላ ግን መውጣት መግባት  የማይቻልበት፣ የጥይት ድምፅ የከባድ መሳሪያ ሲስተናገድ ነበር ወደ ህክምና ለመሄድም ትራንስፖርት የለም ጉዳቱ ቀላል አይሆንም። "

ነዋሪ 2

" ዛሬ ተኩስ የለም። ከተማ ውስጥ ምንም እንቅስቃሴ የለም። ከመከላከያ ውጭ የሚንቀሳቀስ የለም። ሰው ከቤት አልወጣም።

ሰላማዊ ሰዎች ብዙ ተጎድተዋል።

ህክምና ለማግኘትም አልተቻለም። ጉዳቱ ከመብዛቱ አንፃር እንዲሁም አንስቶ የሚወስድም አልተገኘም።

የሞቱ ሰዎች ትላንት አልፎ አልፎ ተቀብረዋል። ከሟች ብዛት አንፃር ያልተቀበሩ አሉ። "

በተመሳሳይ በሸዋሮቢት ከተማ ሀገር መከላከያ የገባ ሲሆን ዛሬ የተረጋጋ ሁኔታ መኖሩን ነዋሪዎች ገልጸዋል።

በግጭቱ ሳቢያ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውና መቁሰላቸውን የገለፁት ነዋሪዎቹ የሞቱ ሰዎች እየተለቀሙ ተቀብረዋል።

አንድ ነዋሪ እሳቸው ብቻ ባረጋገጡት 13 ንፁሃን እንደሞቱ ገልፀው ሚካኤል ቤተክርስቲያን 10 ሰው፣ ማርያም 2 ሰው፣ ሙስሊም መቃብር 1 ሰው መቀበሩን መረጃ እንዳላቸው ተናግረዋል። በየገጠሩ ያለው ገና አልታወቀም ሲሉ አክለዋል።

ትራንስፖርት አለመኖሩ፣ መንቀሳቀስም አስፈሪ ስለነበር ተጎጂዎችን ወደሆስፒታል ለመውሰድ አስቸጋሪ እንደነበር ነዋሪዎች ለሬድዮ ጣቢያው ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
#ሰከላ_ስኩል_ሲስተም

የግልና የመንግስት የትምህርት ተቋማትን ሁለንተናዊ ክንውን የሚያዘምነውን የሰከላ ሲስተምን (SIMS) በአዲሱ የት/ት ዘመን ይተግብሩ!

ክፍያዎችን በኦንላይን ለመፈፀም፣ መረጃ አያያዝና አስተዳደርን ዲጂታል ለማድርግ ሁሉን በአንድ የያዘ አስተማማኝ መተግበርያ!

ይህንን https://sekela.app ወይንም https://sekela.app/school-registration ሊንክ በመከተልና በመመዝገብ ያለምንም ኢንስታሌሽንና ቅድመ ክፍያ ካሉበት ይጠቀሙ
#HamaqPLC
Car Hand Break And Gear Shift Lock -ለመኪናዎ የሚያገለግል አስተማማኝ መቆለፊያ  
-በአሁኑ ጊዜ እየተበራከተ ለመጣው የመኪና ስርቆት ሁነኛ መፍትሄ
-በኮንዶሚኒየም፣አፓርታማና በጋራ መኪና ማሳደሪያ ለሚጠቀሙ ተመራጭ
-የእጅ ፍሬንን ከማርሽ ጋር የሚቆልፍ    

ዋጋ =3000 ብር  ☎️ 0912917632 ከየማይቀረፅ ቁልፎች ጋር ያሉበት ቦታ በነፃ እናደርሳለን::👉Free delivery

አድራሻ:- አቢሲኒያ ፕላዛ
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ወደ ደሴ (ኮምቦልቻ) በረራ ነገ ይጀምራል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ደሴ (ኮምቦልቻ) በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን መደበኛ በረራ ነገ ነሐሴ 5 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚጀምር መሆኑን አሳውቋል።

መንገደኞች የአየር መንገዱን ድረ-ገጽ (www.ethiopianairlines.com) ወይም የሞባይል መተግበሪያውን (https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app) በመጠቀም ለጉዟቸው የሚያስፈልጉ ተግባራትን ካሉበት መከወን ይችላሉ ተብሏል።

ተጨማሪ ዕገዛ የሚሹ መንገደኞች በአቅራቢያቸው የሚገኙትን የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሽያጭ ቢሮዎች ወይም ወደጥሪ ማዕከሉ (6787) በመደወል መስተናገድ እንደሚችሉ ተገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አፅድቀውታል ፤ ፈርመውበታል ! ዩጋንዳ የ " ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት " ን ወንጀል የሚያደርገውን ሕግ አፀደቀች። ዛሬ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ያፀደቁት / ፊርማቸውን ያኖሩበት የረቂቅ አዋጅ ሕግ ተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት የሚፈጽሙ ሰዎችን ሁሉ በዕድሜ ልክ እስራት የሚያስቀጣ ነው። በአንዳንድ ሁኔታዎች ዳግሞ #የሞት ቅጣትን የሚያስከትል ነዉ። ረቂቅ ሕጉ ባለፈው መጋቢት ወር ላይ በአገሪቱ…
" ኢፍትሃዊ እና ግብዝነት የተሞላበት ነው " - ኡጋንዳ

የዓለም ባንክ ለኡጋንዳ አዲስ ብድር አልሰጥም ብሏል።

ይህን ያለው ለምን የፀረ ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ህግን አውጥተሽ ተግባራዊ አደረግሽ በሚል ነው።

የዓለም ባንክ ኡጋንዳ ያወጣችው ሕግ " መሰረታዊ ከሆኑ እሴቶቼ ጋር ይቃረናል " ብሏል።

ተቋሙ ለሁሉም ኡጋንዳውያን ያለምንም ልዩነት " ከድህነት እንዲወጡ፣ መሰረታዊ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ እና ሕይወታቸውን እንዲያሻሽሉ ለመርዳት " ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል።

በኡጋንዳ ከዚህ ቀደምም የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነቶች ሕገ ወጥ የነበሩ ሲሆን ግንቦት ላይ በጸደቀው አዲሱ ሕግ መሰረት ደግሞ የዕድሜ ልክ እስራትን ጨምሮ #ሞት ያስቀጣል።

በኡጋንዳ ተግባራዊ በተደረገው የፀረ ተመሳሳይ ጾታ ሕግ ፤ ከ18 ዓመት በታች ከሆነ ሰው ጋር የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት የፈጸመና የኤችአይቪ ቫይረስ በደሙ ከሚገኝበት ሰው ጋር ግኝኑነት የፈጸመ ሰው እስከወዲያኛው ይሸኛል / የሞት ቅጣት ይፈረድበታል።

ዓለም ባንክ ይህ ሕግ ተግባራዊ ከተደረገ በኃላ አንድ ቡድን ወደ ኡጋንዳ አሰማርቶ የነበረ ሲሆን ሕጉ " በመሰረታዊነት የዓለም ባንክ ቡድን እሴቶችን ይቃረናል " ብሏል።

ራዕያችን " ዘር፣ ጾታ ወይንም ተመሳሳይ አፍቃሪነትን ሳይለይ ሁሉንም ያካተተ ነው " ሲል ገልጿል።

በሕጉ ውስጥ የተካተቱ አዳዲስ እርምጃዎች እስኪገመገሙ ድረስ " ለኡጋንዳ አዲስ ብድር እንዲጸድቅ ለሥራ አስፈጻሚ ቦርድ አይቀርብም " የሚል ውሳኔ አሳልፏል።

ኡጋንዳ ምን አለች ?

የዓለም ባንክ የወሰደው እርምጃ ኢፍትሃዊ እና ግብዝነት ነው ብላለች።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኡጋንዳ አምባሳደር አምባሳደር አዶኒያ አየባሬ ፥ " የገንዘብ ተቋሙን እርምጃ በጣም የከፋ ነው። የዓለም ባንክ የአሰራር ዘዴ እና የቦርዱን ውሳኔ እንደገና የማጤን ጊዜው አሁን ነው " ሲሉ ገልፀዋል።

የኡጋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዲኤታ ኦኬሎ በበኩላቸው ፤ እርምጃው ከሌሎች አገራት ጋር ሲወዳደር ወጥነት የለውም ብለዋል።

" የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን የማይታገሱ በርካታ የመካከለኛው ምስራቅ አገራት አሉ። ተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችንም የሚቀጡት በመስቀልና በመግደል ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

" በአሜሪካ ውስጥ በርካታ ግዛቶች የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን የሚቃወሙ ወይንም የሚገድቡ ሕጎችን አውጥተዋል። ታዲያ ለምን ኡጋንዳ ላይ አነጣጠራችሁ ? "ሲሉም ጠይቀዋል።

ከዓለም ባንክ በተጨማሪ አሜሪካ በጸረ ተመሳሳይ አፍቃሪ ሕግ ምክንያት በኡጋንዳ ላይ ማዕቀብ ጥላለች። (ሮይተርስ/ቢቢሲ)

ኡጋንዳ ፤ ሕጉን ከማፅደቋ በፊት ከምዕራባውያን ሀገራት እና ተቋማት ብዙ ማስጠንቀቂያዎች ቢደርሳትም ሕጉ ለሀገሬ አስፈላጊ ነው በማለቷ ፕሬዜዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ፈርመውት አፅድቀውታል፤ ተግባራዊም ሆኗል።

ከዚህ ቀደም የኡጋንዳ ፕሬዜዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ፤ #ምዕራባውያን አገራት የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን መብቶች #በአፍሪካ አገራት ላይ #በኃይል ለመጫን እየጣሩ ነው ሲሉ ተናግረው ነበር።

ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ  " እንግዳ የሆነ ባህል / ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት እንድንፈቅድ ምዕራባዊያኑ #ማዕቀብ በመጣል ጫና ያሳድራሉ " ሲሉ ነበር የገለፁት።

ስለ ኡጋንዳ አዲሱ ሕግ ለማወቅ ፡ https://t.iss.one/tikvahethiopia/78787

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ግብረሰዶማዊነት በሀገራችን ህግ ፍፅሙ የተከለከና በህግ የሚያስጠይቅ ተግባር ነው " - ፖሊስ የአዲስ አበባ ከተማ ባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ወግ እና ባህል ያፈነገጡ ድርጊቶችን አስመልክተው መግለጫ አውጥተዋል። " ሀገራችን በህብረ ብሄራዊነቷ የምትታወቅና የተለያዩ ባህሎችና ወጎች ያሏት ሀገር ነች፡ " ያሉ ሲሆን ፤ " ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከማህበረሰቡ ወግና ባህል ያፈነገጡ…
#Update

በአዲስ አባባ የግብረ-ሰዶም ተግባር በሚፈጸምባቸው ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰድ እንደተጀመረ ተገለፀ።

እርምጃውን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በመተባበር እየወሰዱ ነው ተብሏል።

እርምጃ እየተወሰደባቸው ያሉት ሆቴሎች፣ ባሮችና ሬስቶራንቶች መሆናቸው ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ፤ ከነባሩ የሀገሪቷ ባህል፣ ወግ፣ የአኗኗር ስርዓት እና ኃይማኖቶች ባፈነገጠ መልኩ የግብረ-ሰዶም ተግባር በሚያስፈጽሙ ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ ፔንሲዮኖችና መሰል የመዝናኛ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ላይ ከህብረተሰቡ በሚደርስ ጥቆማ መሰረት አስተማሪ እርምጃ እየተወሰደ ነው ብሏል።

ቢሮው ፤ የግብረ-ሰዶም ተግባር መፈጸምና ማስፈጸም በኢትዮጵያ በሥራ ላይ ባሉ ሕጎች የተከለከለ መሆኑ ገልጾ " ይህንን አስጸያፊ በሰውም በአምላክም ዘንድ የተጠላ ደርጊት በሚፈጽሙና በሚያስፈጽሙ የመዝናኛ አገልግሎት መስጫ ተቆማት ላይ ካለ አንዳች ርህራሄ ከህብረተሰቡ በሚደርሰን ጥቆማ መሰረት ከፖሊስ ጋር በመተባበር እርምጃ መውሰዳችንን አጠናክረን እንቀጥላልን " ሲል አሳውቋል።

በዚህም ፤ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አስተዳደር ውስጥ በሚገኝ " አበባ ገስት ሐውስ " በሚባል የመዝናኛ አገልግሎት መስጫ ተቋም ላይ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሰረት እርምጃ እንደተወሰደበት አሳውቋል።

የተቋሙ ኃላፊም በከተማው ፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውል በማድረግ ምርመራ እየተከናወነ ይገኛል ተብሏል።

ከግብረሰዶም ፀያፍ ተግባር ጋር የተገናኘ መረጃ እና ጥቆማ ያለው ማንኛውም ሰው በአቅራቢያው በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ በግንባር በመቅረብ እንዲሁም በነፃ የስልክ መስመር 991 እና 987 እንዲሁም በ011-1- 11-01-11 እና 011-5-52-63-02 በመጠቀም መረጃና ጥቆማ መስጠት ይችላል።

@tikvahethiopia