#update በእስር ላይ የሚገኙት እነ አቶ በረከት ስምዖን #ኮምፒውተር፣ #ስልክ እና #የኢንተርኔት አገልግሎት ለማግኘት ያቀረቡትን ጥያቄ ፍርድ ቤት #ውድቅ አድርጎባቸዋል። ተጠርጣሪዎቹ አቶ በረከት ስምዖንና አቶ #ታደሰ_ካሳ ከዚህ በፊት ምስክሮችንና የሕግ ባለሞያዎችን ምክር ለማገኘት እንዲረዳቸው የኮምፒውተር፣ የኢንተርኔትና የስልክ አገልግሎቶች በባህር ዳር ማረሚያ ቤት እንዲሟላላቸው ጠይቀው ነበር፡፡ ሆኖም ለአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት ኮምፒዩተሮችና የስልክ አገልግሎት በማረሚያ ቤቱ ስለሚገኙ ተጠርጣሪዎቹም በዛው እንዲገለገሉ በማለት የባሕር ዳር እና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥያቄውን ዛሬ ወድቅ ማድረጉን የጀርመን ራድዮ ዘግቧል። ፍርድ ቤቱ ግለሰቦቹ እንደሌሎች ጠጠርጣሪዎች ማረሚያ ቤቱ የሚያቀርበውን ማንኛውንም ቁሳቁስ እንዲጠቀሙ በማለት ትዕዛዝ ሰጥቷል። ፍርድ ቤቱ ባለፈው አርብ እለት የአማራ ክልል የስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የጠየቀውን የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ በመፍቀድ #ተጠርጣሪዎቹ ለመጋቢት 2 ቀን 2011 ዓ.ም እንዲቀርቡ አዟል።
Via የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ብሄራዊ ቤተ መንግስት❓
የብሄራዊ ቤተ መንግስት የማያቀው ከ300 በላይ #የስልክና #የኢንተርኔት መስመሮችን ጨምሮ ለግለሰቦች በሚውሉ መስተንግዶዎች ምክንያት በየዓመቱ #ከ11_ሚሊየን ብር በላይ ለግል ጥቅም ሲውል መቆየቱ ተገለፀ።
በአሰራር ክፍተት #ሲመዘበሩ የነበረ በርካታ ሚሊየን ብሮች ግምት ያላቸው ወጪዎችን ማስቀረት መቻሉንም የብሄራዊ ቤተ መንግስት አስተዳደር አስታውቋል።።
በችግሮቹ ተሳታፊ ናቸው የተባሉ 31 ግለሰቦች ላይ #እገዳ የተጣለ ሲሆን፥ ቤተ መንግስቱ አሰራሩን በአዲስ መልክ በማደራጀት ክፍተቶቹን የማስተካከል ስራ እየሰራሁ ነው ብሏል።
በስሩ ከአስር በላይ በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ ቤተ መንግስቶችን የሚያስተዳድረው የብሄራዊ ቤተ መንግስት አስተዳደር በዋነኝነት ሶስት ዋና ዋና ተግባራትን ይፈጽማል።
ከቤተ መንግስት ጋር ተያይዞ የሚገኙ ቅርሶችን መጠበቅና መከባከብ፣ ትላልቅ መስተንግዶዎችን ማከናወን እና ቤተ መንግስቱ ገቢውን በማሳደግ ራሱን በተሻለ ደረጃ እንዲያስተዳደር የሚሉ ናቸው።
የሀገሪቱ ርእሰ ብሄር መቀመጫ የሆነው የብሄራዊ ቤተ መንግስት አስተዳደሩ የተሰጠውን ሀላፊነት ሲወጣ ቢቆይም ለረጅም ጊዜያት ከመመሪያና አሰራር ውጪ የሆኑ ተግባራት ሲፈጸሙበት መቆየቱን በጥናት ማረጋገጥ ተችሏል።
ባለፉት 9 ወራት በተሰራው የማጣራት ስራ ቤተ መንግስቱ በአስተዳደር ሂደት ውስጥ የሚያቀርባቸውን የመስተንግዶ አገልግሎቶች ለግለሰቦች ፍላጎት ማስፈጸሚያነት እንዲውል በማድረግ በየዓመቱ ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ሲደረግ ቆይቷል።
ከስልክ፣ ኢንተርኔትና ኢ ቪድዮ አገልግሎት ጋር ተያይዞ ብሄራዊ ቤተ መንግስት የማያገቃቸው ከ300 በላይ አካውንቶች በስሙ በየዓመቱ ከ5 ሚሊየን ብር በላይ ሲከፈል መቆየቱም ተደርሶበታል።
እነዚህ በማሳያነት የተነሱት ችግሮችና የተመዘበረ የገንዘብ መጠን ለማሳያነት የቀረቡ እንጂ በገንዘብ ያልተተመነና በአገልግሎት የሚገለጹ ሌሎች ጉድለቶችም እንደነበሩ ማረጋገጥ ተችሏል።
የገንዘቡም መጠን ሆነ የአገልግሎቱ ጉድለት ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ የቆየ ሲሆን፥ ይህም ወደ ገንዘብ ሲለወጥ በ100 ሚሊየን ብር የሚቆጠር ገንዘብ ሲመዘበር ቆይቷል ማለት ነው።
የብሄራዊ ቤተ መንግስት ችግሮቹን ከመለየት ባለፈ ድርጊት ፈጻሚዎች የሚባለኩት በአመራር ላይ የነበሩና ከአመራር የተሰናበቱ 31 ግለሰቦችን ለይቶ አግዷቸዋል።
ድርጊቱን በማስቆም ለተጠያቂነቱ ኮሚቴ በማዋቀር የማጣራት ስራን እየሰራ መሆኑንም አስታውቋል።
ሌላው በብሄራዊ ቤተ የግዢ ስርአት ውስጥ የነበሩ ክፍተቶች በርካታ ግዢዎች እየተፈጸሙ ለአገልግሎት ከማዋል ይልቅ በመመጋዘን የማከማቸት ችግር ይታይ ነበር።
የተገዛው እቃ በመከማቸቱ እየተበላሸ ሌሎች በተለይም የውጪ ግዢዎችን በተከታታይ እየፈጸሙ መጠን እየቀናነሱ ማስገባትም ሌላኛው ችግር ነበር።
የበርካታ ታሪካዊ ቅርሶች ባለቤት መየሆነው የብሄራዊ ቤተ መንግስት የንብረት አያያገዝ ችግሩም ሀብቶቹ እንዲባክኑ እየሆነ ነው።
ባለፉት ስድስት ወራት እነዚህን ችግሮች ለመፍታት የተለያዩ ስራዎች ሲሰሩ መቆታቸውን ያስታወቀው የብሄራዊ ቤተ መንግስቱ አስተዳደር፥ አሁን ላይ ወደ መፍትሄው እርምጃ መግባቱንም አስታውቋል።
በሂደቱ ተጨማሪና የተሻሉ አሰራሮችን መዘርጋትና ወደ ተግባር ማስገባነት የሚሉት ተጠቃሽ ናቸው።
የብሄራዊ ቤተ መንግስት በቅርቡ ለህዝብ ክፈት እንዲሆን ለማድረግ የሚያስፈልጉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩም መሆኑን ሰምተናል።
ቤተ መንግስቱ ያሉትን ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ ሀብቶች በአግባቡ በመጠቀምና እድሳት የሚያስፈልጋቸውንም በማደስ በአጭር ጊዜ ለህዝብ ክፍት እንደሚሆን ይጠበቃል።
ምንጭ፦ fbc

#NewsAlert በሱዳን ለሳምንታት ተቋርጦ የነበረው የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት ተለቋል። ኢንተርኔቱ የተዘጋው በአገሪቱ ዋና ከተማ ካርቱም ለበርካቶች ሞት እና ጉዳት ምክንያት የሆነውን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ጁን 3 በፀጥታ ሃይሎች እና ተቃዋሚዎች የተከሰተው ግጭት ተከትሎ ነበር፡፡
ኢንተርኔት በመዘጋቱ #ክሱን ያቀረቡት የህግ ባለሙያው አብደል አዚም ሃሰን እንዳሉት የካርቱም አከባቢ ፍ / ቤት ዛየን ለተባለው ኩባንያ የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲለቅ ትዕዛዝ ማስተላለፉን ገልጸዋል፡፡ ይህን ተከትሎ ለ37 ቀናት ተቋርጦ የቆየውን የኢንተንኔት አገልግሎት በከተማው መስራት መጀመሩን ተገልጿል፡፡ ፍርድቤቱ በተመሳሳይ ኤምትኤን እና ሱዳኒ ለተባሉ ተቋማትም ኢንትርኔት አገልግሎቱን እንዲለቁ ወስኗል፡፡
ወታደራዊ የሽግግር መንግስቱ ከዓለም አቀፍ ተቋማት #የኢንተርኔት አገልግለቱን ክፍት እንዲያደርግ ግፊት ሲደረግበትም ቆይቷል፡፡ ወታደራዊ የሽግግር መንግስቱ ከተቃዋሚዎች ከስምምነት መድረሱን ተከትሎ የኢንተርኔት አገልግሎት ለመጀመር ከስምምነት ደርሶ እነደነበርም ተገልጿል፡፡
ምንጭ፦ ዘ ኢስት አፍሪካ ኒውስ/ሱዳን ትሪቡን/#ENA/
🗞ቀን ሃምሌ 4/2011 ዓ/ም

#ሀዋሳ #የኢንተርኔት_አገልግሎት_መስራት_ጀምሯል
ከሳምንት በላይ ለሚሆን ጊዜ በሀዋሳ ከተማና ዙሪያዋ ተቋርጦ የነበረው የኢንተርኔት አገልግሎት ዛሬ መስራት ጀምሯል።

የሟቾች ቁጥር 100 ደርሷል፤ ኢንተርኔት በበርካታ የሀገሪቱ ከተሞችም ተዘግቷል!
በኢራቅ ዋና ከተማ ባግዳድና አከባቢዋ 6 ቀናትን ባስቆጠረው ታቀውሞ የሞቱት ሰዎች 100 ደርሰዋል። በኢራቅ የተለያዩ ክፍሎች የሀገሪቱን መንግስት በመቃውም ተቃውሞ ከተቀሳቀሰ ስድስት ቀናትን አስቆጥሯል። በዚህ ታቃውሞ በርከት ብለው በመሳተፍ ላይ የሚገኙት ወጣቶች ሲሆኑ ሙስናን ፣ ስራ አጥነትን እና ዝቅተኛ መንግስት አገልግሎትን በመቃወም ነው ተቃውሟቸውን እያሰሙ የሚገኙት፡፡
#የኢንተርኔት_አገልግሎት በበርካታ የሀገሪቱ ከተሞች ተቋርጧል። ዛሬ ጥዋት ለጥቂት ሰዓት ተከፍቶ የነበረ ቢሆንም የኢራቅ መንግስት ዳግም እንዲዘጋ አድርጎታል። ኢንተርኔት በተከፈተበት ወቅት የኢራቅ ዜጎች #VPN በመጠቀም በርካታ አሳዛኝና ለማየት የሚከብዱ ቪድዮዎችን ሲያጋሩ ነበር።
#IRAQ
•100 ሰዎች ሞተዋል
•4000 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል
•በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ታስረዋል
•ሙሉ በሙሉ በሚል ደረጃ ኢንተርኔት ተዘግቷል

#መልዕክት
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሁሉም አባላት ድምፅ የሚሰማባት ሰፊው ቤታችን ነው።
ትልቁ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስራም ከ1.1 ሚሊዮን በላይ አባላት መካከል የመረጃ ልውውጥ እንዲኖር ማድረግ ነው።
ቲክቫህ ፦
- የሚዲያ ባለቤቶች እና የሚዲያ ሰዎች፣
- የጋዜጠኞች፣
- የጤና ባለሞያዎች፣
- የገበሬዎች፣ የአርሶና አርብቶ አደሮች
- የመንግስት እና የግል ሰራተኞች ፣
- የገዢ ፓርቲ ደጋፊዎችና አመራሮች ፣
- የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎችና አመራሮች፣
- የተማሪዎች፣
- የንግድ ሰዎችና ባለሃብቶች የሌሎችም በርካታ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን መሰባሰቢያ ቤት ነው።
ቲክቫህ ከመነሻው የሃሳብ ብዝሃነት ለሀገር እድገት ያለውን ከፍተኛ ሚና የሚረዱ ፣ ለሀገር የሚያስቡ፣ በሶሻል ሚዲያ ላይ ለሚፅፉት እያንዳንዱ ቃል ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚያደርጉ አባላትን ባለፉት ዓመታት ማፍራት ችሏል።
የእውነተኞቹ የቲክቫህ አባላት መገለጫ ብስለት፣ እርጋታ፣ መረጃ ማመዛዘን፣ የነገን የአብሮነትና ጉዞ ማሰብ፣ ለወገን መቆርቆር ነው።
ያለፈውን አንድ ወር የሀገራችን ማህበራዊ ሚዲያ የለየለት የውሸት እንዲሁም የጥላቻ መድረክ ሆኖ ማለፉን ሁሉም የቲክቫህ አባላት የሚያውቀው ነው።
እንዲህ ያሉ ወቅቶች በተደጋጋሚ ስለገጠሙ እና በእንዲህ ያለ የውጥረት ሰዓት ላይ ማህበራዊ ሚዲያዎች እንዴት እንደሚዘወሩ ለቲክቫህ አባላት አዲስ አልነበረም።
ለዚህም ነው ከጥቂቶች / ከአዲስ አባላት ውጭ ሁሉም አባል በሚባል ደረጃ እያንዳንዱን ሁኔታ በፍፁም እርጋታ ሲከታተል የነበረው።
ያልሰሙትን ሰምተናል፣ ያላዩትን አይተናል ፣ ያልተደረገውን ተደርጓል እያሉ የተገኘውን ተባራሪ ወሬ ሁሉ በማህበራዊ ሚዲያዎች ሲያሰራጩ የነበሩ አካላት በጊዜ ሂደት ምን ምን ጉዳዮችን ሲዋሹ እንደነበር ሁሉም አባላት በትዝብት ተመልክቷል።
ምንም ያለተረገጠና ውቅቱን ያልጠበቀ እንዲሁም ተባራሪ ወሬዎችን ለህዝብ ሲያሰራጩ የከረሙት የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችም ብዙ የሀገራችን እናቶች ፣ ወላጆችን በሀሰት ዜና አስነብተዋል፣ ብዙ ቀናትንም ያለ እንቅልፍ በጭንቀት አሳድረዋል።
እውን እኛ ያለንባት #ኢትዮጵያ እንደ ማህበራዊ ሚዲያው ያለች ብትሆን ለአንድም ቀን እንኳን በሀገራችን ባላደርን ነበር።
ውድ አባላት የዛሬው መልዕክታችን ፦
• መረጃ ለቲክቫህ 1.1 ሚሊዮን አባላት ለማሳወቅ ስትልኩ ስለምታውቁት /ስላረጋገጣችሁት/ ጊዜውን እና ወቅቱ ስለመጠበቁ ገምግማችሁ እንዲሆን፤
• ሁሉም ወገን ወገን ፈጥሮ በሚሰራው ዘመቻ ተጠልፋችሁ እንዳትወድቁ በመጠንቀቅ፤
• የአእምሮ ጤናችሁን ከሚያቃውስ የስድድብ፣ የጥላቻ አካባቢዎች በመራቅ፤
• የምትናፍቋችሁን የቲክቫህ ትግራይ ክልል አባላት በትዕግስት የመልዕክት ልውውጥ ማድረግ እስኪጀምሩ በመታገስ፤
• ያላረጋገጣችሁትን ጉዳይ ባለመናገር ፣
• በየማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚነገረው ሁሉ እውነት ነው እያላችሁ ለሰው ከማጋራት በመቆጠብ ፣
• በተለመደው እርጋታችሁን ፣ ትዕግስታችሁን ፣ መከባበራችሁን ፣ የነገ አብሮነታችሁን እና ሀገራችሁን በማሰብ ወደፊት ትቀጥሉ ዘንድ መልዕክት እናስተላልፋለን።
ሌላው በትግራይ ክልል ያሉ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን የቲክቫህ አባላት ደህንነት ለማወቅ እየሰራን ነው፤ ስልክ የሚሰራባቸው አካባቢዎች ያሉ አባላቶችን እያገኘን ነው።
የትግራይ ክልል የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት #የኢንተርኔት ግንኙነት በሚያገኙበት ጊዜ ከዞን፣ ከወረዳ እስከ ቀበሌ ድረስ መረጃዎችን አዲስ በተዘረጋው የቲክቫህ አባላት የመረጃ ልውውጥ መድርክ www.tikvahethiopia.net ላይ ያሳውቃሉ ብለን እንጠብቃለን።
ሌሎችም የቲክቫህ አባላት www.tikvahethiopia.net በመመዝገብ ስለአካባቢያችሁ ጉዳይ ብቻ የምታውቁትን ማካፈል ትችላላችሁ። የአንድ ክልል፣ ዞን፣ ወረዳ መረጃ በሌሎች አባላት አይታይም!
Tikvah/Hope/ተስፋ
#TikvahFamily❤️
@tikvahethiopiaBOT