TIKVAH-ETHIOPIA
በትግራይ ያሉ አባቶች የፊታችን ሐምሌ 9 ቀን 2015 ዓ/ም በቅድስት ከተማ አክሱም ፅዮን የኤጲስ ቆጾሳት ምርጫ ለማድረግ ዝግጅት ላይ መሆናቸው ተሰምቷል። በክልሉ ለሚገኙ ሚዲያዎችም በስነስርዓቱ ላይ እንዲገኙ ጥሪ መቅረቡን ለማወቅ ተችሏል። በትግራይ ያሉ አባቶች ከማዕከል በመነጠል " የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤቤተክርስቲያን የመንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ከፍተኛ ቤተ ክህነት " በሚል እየተንቀሳቀሱ…
#EOTC
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ሐምሌ 5 እና 6 ቀን 2015 ዓ/ም አስቸኳይ ስብሰባ ማካሄዱ የታወቀ ሲሆን ይህን ከስብሰባው መጠናቀቅ በኃላ መግለጫ ሰጥቷል።
ቅዱስ ሲኖዶስ በመግለጫው :-
በትግራይ በሚገኙ አህጉረ ስብከት የተመደቡ አባቶች የቅዱስ ሲኖዶስ የሰላም ጥሪን ቸል ከማለት ባሻገር ሐምሌ 9 እናደርገዋለን ያሉት የኤጲስ ቆጶስነት ምርጫ ሕገ ቤተክርስቲያንን ያልተከተለ መሆኑን ገልጾ የሚመለከታቸው አካላት ሂደቱን በማስቆም ከቤተክርስቲያን ጎን እንዲቆሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን አቅርቧል።
ይደረጋል የተባለው የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን አንጻር ተገቢ ያልሆነ የቤተ ክርስቲያንን ማዕከላዊነት የሚጥስ፣ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት የሚጎዳና በጦርነት የተጎዳውን ሀብት ንብረቱ የወደመበትን ገዳማቱና አብያተ ክርስቲያናቱ የተጎዱበትን ሕዝብ የማይጠቅም ተገቢነት የሌለው በመሆኑ እንዲቆም ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
በትግራይ ክልል ተከስቶ የነበረውን ችግር የፌዴራል መንግሥትና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ችግሩን በውይይት የፈቱት መሆኑ እየታወቀ የሰላም ባለቤት የሆነችው ቤተ ክርስቲያን እስካሁን ሰላም መፈለጓ ያልተቋረጠ ቢሆንም አለመሳካቱ የሚያሳዝን በመሆኑ ለሰላም የሚደረገው ጥረት ዘላቂ መፍትሔ እስከሚገኝ ድረስ የማይቋረጥ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ገልጿል።
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ክቡር አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት እንዲሁም የፌዴራልና የክልሉ መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እየተደረገ ያለውን ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ያልተከተለ የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ እንዲያስቆሙ ብሎም ሰላም ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት በመደገፍ ችግሮቹ በውይይት እንዲፈቱ መንግሥታዊ እገዛ በማድረግ የውይይት መድረክ እንዲያመቻቹ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥሪውን አቅርቧል።
ቅዱስ ሲኖዶስ፤ " በመላው ዓለም የምትገኙ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና ሕዝበ ክርስቲያን እናት ቤተ ክርስቲያናችሁ ያስተላለፈችውን የሰላም ጥሪ ተግባራዊ ሆኖ አንድነቷ ጸንቶ ይኖር ዘንድ በጸሎት ተግጋችሁ ከቤተ ክርስቲያናችሁ ጎን እንድትቆሙ " ሲል ጥሪ አስተላልፏል።
(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia

Photo
#EOTC
ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በክልል ትግራይ ጉዳይ ከተናገሩት ፦
" የኢፌዴሪ መንግሥት ትናንት ተፈጥሮ በነበረው የቀኖና ቤተ ክርስቲያን ጥሰት ችግር (ኦሮሚያ ላይ) በውይይትና በምክክር በከፍተኛ ኃላፊነት እንዲፈታ ማድረጉን ይታወሳል።
አሁንም በትግራይ ክልል ባሉ የአህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳትና ሊቃውንት እየተከተሉት ያለውን መፍትሔ የማይሆነውን ችግር በማስቆምና ሰላማዊ የውይይት መድረኮችን በማመቻቸት የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ እምነታችን ነው።
ይህ ካልሆነ ግን በታሪክ የቤተ ክርስቲያንን አንድነትን ማን ከፋፈለ ሲባል የፌደራልና የክልሉ መንግሥት የሚል የታሪክ ተወቃሽ ሆኖ በታሪክ የሚመዘገብ ይሆናል።
ስለሆነም ይህን በትግራይ ክልል ይፈጸማል የሚባለውን ከቀኖና ቤተ ክርስቲያንና ሕገወጥ የሆነ ሹመት እንዲቆም ብሎም ችግሮች በውይይት እንዲፈቱ በማመቻቸት ታሪካዊ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ ቤተ ክርስቲያን ታሳስባለች። "
(ብፅዕ አቡነ አብርሃም የሰጡት ቃል ከላይ ተያይዟል)
በትግራይ ያሉ ብፁአን አባቶች በትግራይ ከነበረው ጦርነት ጋር በተያያዘ ከማዕከል ተነጥለው " የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ከፍተኛ ቤተ ክህነት " በሚል እየተንቀሳቀሱ መሆኑ ይታወቃል።
በቅርቡ በኣክሱም በተካሄደው ስነስርዓት ለዛው ለትግራይ የሚመደቡ 5 እንዲሁም ለውጭ ሀገር 5 በድምሩ 10 የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ አካሂደው የነበረ ሲሆን በቀጣይ ሹመት ይሰጣሉ ተብሏል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ቅዱስ ሲኖዶስ በኣክሱም የተካሄደው ምርጫ አሁን እየተደረገው ያለው የሹመት እንቅስቃሴ ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን አንጻር ተገቢ ያልሆነ የቤተ ክርስቲያንን ማዕከላዊነት የሚጥስ፣ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት የሚጎዳና ሕገወጥ ድርጊት መሆኑን በመግለፅ #እንዲቆም እያሳሰበ ነው።
የፌዴራል መንግሥት እና የትግራይ አስተዳደር የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል።