TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#OLF50

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር የ50ኛ ዓመቱን ለማክበር ዝግጅት ላይ ይገኛል።

ኦነግ ፤ እኤአ 1973 ሐምሌ 01 የተመሰረተ ሲሆን ከኢትዮጵያ የፖለቲካ ድርጅቶች በአንጋፋነቱ ይጠቀሳል።

ድርጅቱ 50ኛ ዓመቱን በአገር ውስጥና በተለያዩ አገራት በድምቀት ለማክበር ማቀዱን አሳውቋል።

ይህንን የ50ኛ ዓመት ክብረ በዓል አስመልክቶ ከቀናት በፊት ሊቀመንበሩ አቶ ዳውድ ኢብሳ ለመገናኛ ብዙሃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህ ወቅት አቶ ዳውድ ኢብሳ ፤ በፓርቲው የትግል ሂደት ውስጥ የተሰው ጓዶቻቸውን አስታውሰው አመስግነውአቸዋል፡፡

ስለወቅታዊ አገራዊ ፖለቲካ እና የፓርቲያቸው ይዞታ ማብራሪያም ሰጥተዋል። ለአሁናዊው በተለይም የኦሮሚያ አለመረጋጋት መነሻ ያሉትንም ሃሳብ አስቀምጠዋል፡፡

አቶ ዳውድ ምን አሉ ?

" በኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) እና የኢትዮጵያ መንግስት መካከል በእኤአ ነሐሴ 07 ቀን 2018 ሰምምነት ተደርሶ ነበር፡፡

በዚህ ስምምነት መሰረት ጦርነት ቆሞ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (ኦነግ) በህዝቡ መሃል ሆኖ በነጻነት የፖለቲካ እንቅስቃሴውን እንዲያከናውን፤ ለዚህም ሙሉ መብት አለው የሚል ነበር፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ደግሞ ለኦሮሞ ነጻነት ግንባር  (ኦነግ) ብቻ ሳይሆን ለሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች ተመሳሳይ ነገር እንደሚፈቅድ ነው የተስማማው፡፡ የስምምነታችን አስኳሉ ይህ ነው፡፡

ከዚህ ጋር የተያያዙ የሰራዊታችንና ሰላም ጉዳይም በስምምነቱ ውስጥ ነበር፡፡

አሁን ላይ ይህ መከዳቱ ነው ላለፉት አምስት (5) ዓመታት በኦሮሚያ የቀጠለውን ጦርነት ያስከተለው፡፡  ለትግራይ ጦርነት እና አሁን በአማራ ክልል እየተስፋፋ ላለውም ቀውስ መሰረት የሆነው።

ስምምነቱ ላይ ተግዳሮት መግጠሙን ተከትሎ ፓርቲያችን ላይ ከፍተኛ የሆነ ወከባ ደርሷል።

...ስምምነታችንን በመሻር ነው መንግስት በደቡብ እና ምዕራብ እንዲሁም በመሃከለኛው አከባቢ ያሉ የኦነግ ሰራዊት ላይ ትጥቅ ለማስፈታት በሚል ተኩስ የከፈተው፡፡

ይህን በማድረግ ሂደት ውስጥ ሽማግሌዎችም በመሃል ገብተው ፤ የቴክኒክ ኮሚቴ በሚባልም ጥረቶች ሲደረጉ የነበረው፡፡ ያም አልሆነም ጦርነቱ ቀጠለ፡፡  መንግስት በተለያዩ ጊዜያት ይህን ሰራዊት አጠፋዋለው በሚል በተደጋጋሚ መግለጫ ሲያወጣ ነበር፡፡ ያ እንዳልሆነ ሁላችንም እናውቃለን፡፡

ያ ጦርነት ጫካ ብቻ ሳይሆን እዚህ ከተማ ውስጥ የኦነግ ጽ/ቤቶችን በመዝጋትና አመራሮቹን በማሰር የፓርቲውን እንቅስቃሴ በመግታትም ጭምር የተደረገ ነበር፡፡

አሁንም እንደ እኛ እምነት በኦሮሚያ ሰላም የሚሰፍነው መንግስት ከዋናው ባለጉዳይ ከእኛ ጋር ተቀምጦ ያ ስምምነታችን ሲከበር ነው ብለን እናምናለን፡፡ "

Credit : ዶቼ ቨለ

@tikvahethiopia