TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Wolaita

ነገ ሰኞ ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ/ም በዎላይታ ዞን የድጋሜ ሕዝበ ውሳኔ ምርጫ (ሪፈረንደም) ድምፅ አሰጣጥ ይካሄዳል።

ስለ ሪፈረንደሙ ምን እናውቃለን ?

- የመራጮች ምዝገባ እና የድምፅ መስጠት ሂደት በአንድ ቀን የሚደረግ ይሆናል።

- የቀረቡት ሁለት አማራጮች ናቸው። እነሱም ፦

ነጭ እርግብ ፦ የ6ቱ ዞኖች (ኮንሶ፣ ዎላይታ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋሞ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና የ5ቱ ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ደራሼ) በአንድ የጋራ ክልል መደራጀትን #እንደግፋለሁ

ጎጆ ቤት ፦ የ6ቱ ዞኖች (ኮንሶ፣ ዎላይታ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋሞ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና የ5ቱ ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ደራሼ) በአንድ የጋራ ክልል መደራጀትን #አልደግፍም

- ድምፅ መስጠት የሚጀመረው ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ ነው።

- በ1,812 የድምፅ መስጫ ጣቢያዎች ድምፅ ይሰጣል ፤ ለዚህም ዝግጅት ተደርጓል።

- ከአዲስ አበባ 5,215 ፤ ከዎላይታ ዞን 3,845 ተመልምለው በቦርዱ የሰለጠኑ አስፈፃሚዎች በምድብ ጣቢያዎቻቸው ላይ ይገኛሉ።

- ከነገ ድምፅ የመስጫ ቀን ጋር በተያያዘ በዞኑ በሚገኙ የፌዴራል እና የክልል መንግስታዊ ተቋማት ስራ አይኖርም።

- ማንኛውም መንግሥታዊ ያልሆኑና የግል ተቋማት #ዝግ ሆነው ይውላሉ።

- የአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ሆስፒታሎችን ጨምሮ የዕለት ተዕለት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት (ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ የትራንስፓርት አገልግሎት …ወ. ዘ. ተ) በዝግ ቀናት የሚያደርጉትን አገልግሎት በተመሳሳይ ማከናወን ይችላሉ። እንዲዘጉ አይገደዱም።

- የትራንስፓርት አገልግሎት በተለመደው መንገድ ይቀጥላል።

@tikvahethiopia