TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Wolaita
ነገ ሰኞ ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ/ም በዎላይታ ዞን የድጋሜ ሕዝበ ውሳኔ ምርጫ (ሪፈረንደም) ድምፅ አሰጣጥ ይካሄዳል።
ስለ ሪፈረንደሙ ምን እናውቃለን ?
- የመራጮች ምዝገባ እና የድምፅ መስጠት ሂደት በአንድ ቀን የሚደረግ ይሆናል።
- የቀረቡት ሁለት አማራጮች ናቸው። እነሱም ፦
ነጭ እርግብ ፦ የ6ቱ ዞኖች (ኮንሶ፣ ዎላይታ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋሞ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና የ5ቱ ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ደራሼ) በአንድ የጋራ ክልል መደራጀትን #እንደግፋለሁ።
ጎጆ ቤት ፦ የ6ቱ ዞኖች (ኮንሶ፣ ዎላይታ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋሞ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና የ5ቱ ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ደራሼ) በአንድ የጋራ ክልል መደራጀትን #አልደግፍም።
- ድምፅ መስጠት የሚጀመረው ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ ነው።
- በ1,812 የድምፅ መስጫ ጣቢያዎች ድምፅ ይሰጣል ፤ ለዚህም ዝግጅት ተደርጓል።
- ከአዲስ አበባ 5,215 ፤ ከዎላይታ ዞን 3,845 ተመልምለው በቦርዱ የሰለጠኑ አስፈፃሚዎች በምድብ ጣቢያዎቻቸው ላይ ይገኛሉ።
- ከነገ ድምፅ የመስጫ ቀን ጋር በተያያዘ በዞኑ በሚገኙ የፌዴራል እና የክልል መንግስታዊ ተቋማት ስራ አይኖርም።
- ማንኛውም መንግሥታዊ ያልሆኑና የግል ተቋማት #ዝግ ሆነው ይውላሉ።
- የአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ሆስፒታሎችን ጨምሮ የዕለት ተዕለት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት (ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ የትራንስፓርት አገልግሎት …ወ. ዘ. ተ) በዝግ ቀናት የሚያደርጉትን አገልግሎት በተመሳሳይ ማከናወን ይችላሉ። እንዲዘጉ አይገደዱም።
- የትራንስፓርት አገልግሎት በተለመደው መንገድ ይቀጥላል።
@tikvahethiopia

#ኮፔይ
የነዳጅ ክፍያን ለመፈፀም፣ ኮፔይ ኢብር ፈጣን እና ቀላል አማራጭ መሆኑን ስንገልጽልዎ በታላቅ ደስታ ነው።
የኮፔይ ኢብር መተግበሪያን አውርደው በመጠቀም፣ ጊዜ ሳያባክኑ ወደ ጉዞዎ ይመለሱ !
መተግበሪያውን ለማውረድ ይህንን ማስፈጠሪያ ይጠቀሙ ፦ https://bit.ly/45f71CP
#Coopbank #DigitalPayment #Banking

#ኤክሶደስ
በኤክሶደስ የፊዚዮቴራፒ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ የምንሰጣቸው የህክምና አገልግሎቶች ፦
- ለአንገት፣ ለትክሻ፣ ለወገብ ህመም ፣ ከዲስክ መንሸራተት ጋር በተያያዘ ለሚመጣ ችግር
- ለማዞር ወይንም ሚዛን የመጠበቅ ችግር፣ ለፊት መጣመም፣ ከስትሮክ በኋላ ለሚመጣ ግማሽ የሰውነት ክፍል መዛል
- ለስፖርታዊ ጉዳቶች፣ ከህፃናት የእድገት ውስንነት ጋር በተያያዘ ለሚከሰቱ የእንቅስቃሴ ችግሮች
- በአጠቃላይ ከነርቭ፣ ከጡንቻ፣ ከመገጣጠሚያ ጋር በተገናኘ ለሚከሰቱ ችግሮች መፍትሄ ያግኙ ይዳኑ!
የስራ ሰዓት ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:30 እስከ #ምሽት 1:00 ሰዓት፤ አድራሻችን 22 ከመክሊት ህንፃ ፊት ለፊት ባሮ ህንፃ ላይ እንገኛለን። ስልክ ቁጥር 0979099909/ 0911039377
√በቴሌግራም ቻናላችን ጠቃሚ መረጃ ያግኙ
https://t.iss.one/ExodPhysioClinic

ፎቶ ፦ ዛሬ ከንጋት 12 ሰዓት ጀምሮ በዎላይታ ዞን የድጋሜ የሕዝበ ውሳኔ ድምፅ አሰጣጥ እየተካሄደ ይገኛል።
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ በዎላይታ ሶዶ ምርጫ ጣቢያዎች የሕዝበ ውሳኔ ድምጽ አሰጣጥ ሒደትን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
Photo Credit : NEBE & FBC
@tikvahethiopia
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ በዎላይታ ሶዶ ምርጫ ጣቢያዎች የሕዝበ ውሳኔ ድምጽ አሰጣጥ ሒደትን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
Photo Credit : NEBE & FBC
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Hawassa በሀዋሳ ከተማ በሚገኝ ትምህርት ቤት የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ሜላት መሀመድ ትላንት ሰኔ 5/2015 ዓ.ም ቀትር ላይ በሁለት ተሽከርካሪ በመጡ ግለሰቦች 'መጠለፏን' ቤተሰቧቿ ተናግረዋል። የ14 ዓመት ከ 8 ወር ታዳጊዋ ሜላት ከትምህርት ቤት ወደ ወደ መኖሪያ ቤቷ በመመለስ ላይ እያለች በሀዋሳ ከተማ ሞኖፖል ተብሎ በሚጠራው አከባቢ " ቤት ልትደርስ ጥቂት ሜትሮች ሲቀራት " በሃይል ታግታ…
" የጠለፋ ወንጀሉ ሰለባ የሆነችው ታዳጊ ለህክምና ወደ ሆስፒታል ተወስዳለች " - የሐዋሳ ከተማ ፖሊስ
ሐዋሳ ከተማ ውስጥ ታዳጊ ሜላት መሐመድን በመጥለፍ የተጠረጠረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የሐዋሳ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል።
ፖሊስ ተጠርጣሪውን ግለሰብ ትናንት እሁድ ምሽት 5: 30 አካባቢ ይርጋለም ከተማ ዉሃ ልማት ቀበሌ በአንድ ግለሰብ ቤት ውስጥ ተሸሽጎ መገኘቱን ረዳት ኢንስፔክተር መልካሙ አየለ ለዶይቼ ቬለ ሬድዮ ተናግረዋል።
በጠለፋ ወንጀል የተጠረጠረው ሳምሶን ሸኑ የተለው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ የወንጀል ማጣራት ስራ እየተከናወ እንደሚገኝ ረዳት ኢንስፔክተር መልካሙ ገልጸዋል።
የጠለፋ ወንጀሉ ሰለባ የሆነችው ታዳጊ ለህክምና ወደ ሆስፒታል መወሰዷን በማከል።
ታዳጊዋ ከጠለፋ መለቋቋን ታላቅ ወንድሟ እንዳልካቸው አስራትም አረጋግጧል። ታዳጊዋ በሐዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና አገልግሎት እያገኘች እንደምትገኝም ገልጿል።
ታዳጊ ሜላት መሐመድ ፤ ከቀናት በፊት በሐዋሳ ከተማ #በኃይል ወደ ተሽከርካሪ እንድትገባ ተደርጋ መወሰዷን ቤተሰቦቿ መግለፃቸው ይወሳል።
በወቅቱ የአካቢው ሰው ሊታደጋት መሞከሩን፤ ሜላት ስትጮህም ይዟት የጠፋውን መኪና የፊትለፊቱን መስታወት የአከባቢው ሰው መሰባበሩን ፤ ከዛ በኋላ እየበረረ ማመለጡን የታዳጊዋ ቤተሰቦች ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት መግለፃቸው አይዘነጋም።

#ትኩረት ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም መስመር በሚያቀኑ የጭነት የተሽከርካሪ ሾፌሮች እና ረዳቶች ላይ " እገታ ተፈፅሟል " ሲሉ የታጋች ቤተሰቦች ገለፁ። ድርጊቱ ዛሬ ንጋት 12 ሰዓት " አሊዶሮ " በሚባለው አካባቢ ስለመፈፀሙ አንድ ወንድሜ ታግቷል ያለ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ጠቁሟል። የታጠቁ አካላት " እስከ ሰላሳ / 30 የሚሆኑ ሰዎችን ከመኪናቸው አስወርደው አግተዋቸዋል ከነሱ ውስጥ ደግሞ አንዱ…
" ለማን ነው አቤት የምንለው ? "
በታጣቂዎች የታጋቱ ሹፌሮች እና ረዳቶች ገንዘብ እየተጠየቀባቸው መሆኑን ቤተሰቦቻቸው ገለፁ።
ከቀናት በፊት ሹፌሮች እና ረዳቶች ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም መስመር እና በተቃራኒው ጉዞ ላይ የነበሩ አዳራቸውን " አሊዶሮ " ላይ ካደረጉ በኃለ በታጣቂዎች መታገታቸውን ቤተሰቦች መግለፃቸው ይታወሳል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ድርጊቱ በተፈፀመበት ዕለት መልዕክት ካደረሱት ተጨማሪ የታጋች ወዳጆችን ፣የሚያውቋቸውን እንዲሁም በዕለቱ ጉዞ ላይ ከነበሩ አባላት መልዕክት ተቀብሏል።
አንድ በዕለቱ ከባህርዳር ወደ አዲስ አበባ እየመጣ የነበረ የቤተሰባችን አባል ፤ ገብርጎራቻ 2 ሰዓት በደረሱበት ወቅት " አሊዶሮ " ላይ ወደ 14 መኪና ሹፌርና እርዳት መወሰዳቸውን እንደሰሙ ገልጿል። " ለ4 ሰዓታት ያህል ቁመን መከላከያ መጥቶ ነው መንገዱ ተከፍቶ ወደ አ/አ የሄድነው " ሲል አስረድቷል።
አንድ የቤተሰባችን አባል " የኔም ጓደኝዬ ከታገቱት አንዱ ነው " ሲል ቃሉ ሰጥቶ ትላንት ለቤተሰቡ ተደውሎ " አንድ ሚሊዮን ብር ላኩ " መባሉንና ቤተሰብም ከፍተኛ ጭንቀት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።
" ለማን ነው አቤት ምንለው ? " ሲልም አክሏል።
እንዲሁ ሌላ የቤተሰባችን አባል ፤ " አሊደሮ " ላይ ከታገቱት መካከል ሁለቱ የቻግኒ ልጆች እንደሆኑና ለእያንዳንዳቸው 1 ሚሊየን ብር መጠየቁን እንደሚያቅ ፤ ለቤተሰቦችም ይህንን ብር ካላመጡ " እንገላቸዋለን " የሚል ማስፈራሪያ መላኩን አስረድቷል። በዚህም ምክንያት ቤተሰቦቻቸው በጭንቅ ላይ እንደሚገኙ ገልጿል።
እገታው በተፈፀመበት ዕለት መልዕክቱን የላከልን አንድ ወንድሙ መታገቱን ያመለከተ የቤተሰባችን አባልም፤ አጋቾቹ ደውለው " 1 ሚሊዮን ብር አምጡ እኛ እነሱን አንፈልግም " ማለታቸውን ገልጿል።
ሹፌሮች እና ረዳቶች መታገታቸው ከተነገረ ቀናት ቢያልፍም ከሚመላከታቸው የመንግሥት አካላት በኩል አንድም የተሰጠ ማብራሪያ የለም።
Via @tikvah_eth_BOT

#Tigray
ቻይና ፤ ትግራይን #መልሶ_ለመገንባት ድጋፍ እንደምታደርግ አስታወቀች።
በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር የተመራ የልኡኳን ቡድን በትግራይ ክልል የስራ ጉብኝት እያደረገ ይገኛል።
ልዑኩ በጉብኝቱ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደት ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ መወያየቱ ተነግሯል።
በውይይቱ ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ የቻይና መንግስት የሰብአዊ ድጋፍ እና ትግራይን መልሶ በመገንባት ረገድ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።
ልኡኩም ፤ የቻይና መንግስት ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ እና ትግራይን መልሶ ለመገንባት ድጋፍ እንደሚያደርግ መግለፁን ድምፂ ወያነ ዘግቧል።

#ሻሸመኔ
ዛሬ በሻሸመኔ ከተማ ቆሻሻ ውስጥ ተጥሎ የነበረ ቦምብ ፈንድቶ ያገለገሉ ፕላስቲኮችን እየለቀሙ የሚተዳደሩ አራት ልጆች ህይወታቸው አለፈ፡፡
ልጆቹ ያገለገሉ ፕላስቲኮችን እየለቀሙ ባለበት ሰዓት ከተጠራቀመ ቆሻሻ ውስጥ ቦምቡ መፈንዳቱን ፖሊስ ገልጿል።
በዚህም የአራት ልጆች ህይወታቸው ሲያልፍ፥ ሁለት ህፃናት ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
Via OBN / FBC