TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AddisAbaba

የዛሬው የጁምዓ ሶላት ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም ተሰግዶ ህዝበ ሙስሊሙም ወደየቤቱ መግባቱ ተገልጿል።

ባለፉት ሁለት የጁምዓ ሶላት ወቅቶች ላይ በሸገር ከተማ ውስጥ ከተፈፀመው የመስጂድ ፈረሳ ጋር በተያያዝ የፀጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ የሰው ህይወት ማለፉና ጉዳት መድረሱ የሚዘነጋ አይደለም።

ይህንም ተከትሎ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት እንዲሁም ከፌዴራል ፖሊስና አዲስ አበባ ፖሊስ ጋር ተከታታይ ውይይቶች ማድረጉና መግባባት ላይ መደረሱ የሚታወቅ ነው።

በሸገር ከተማ ከመስጂድ ፈረሳ ጋር በተያያዘ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ያቀረበው ጥያቄ የመፍትሄ አቅጣጫ የተቀመጠለት በመሆኑም በሁሉም መስጂዶች ከቁኑት ዱዓ ውጪ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች አስፈላጊ ባለመሆናቸው ህዝበ ሙስሊሙ የተለመደ ታዣዥነቱን በማሳየት የጁምዓ ሰላቱን ሰግዶ ብቻ መመለስ እንዳለበት ትላንት ማሳሰቢያ መተላለፉት ይታወቃል።

በዚህም ዛሬ የነበረው የጁምዓ ሶላት በሰላም ተከናውኖ ህዝበ ሙስሊሙ ወደቤቱ ገብቷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba የዛሬው የጁምዓ ሶላት ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም ተሰግዶ ህዝበ ሙስሊሙም ወደየቤቱ መግባቱ ተገልጿል። ባለፉት ሁለት የጁምዓ ሶላት ወቅቶች ላይ በሸገር ከተማ ውስጥ ከተፈፀመው የመስጂድ ፈረሳ ጋር በተያያዝ የፀጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ የሰው ህይወት ማለፉና ጉዳት መድረሱ የሚዘነጋ አይደለም። ይህንም ተከትሎ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት…
" ህዝበ ሙስሊሙ ሁልጊዜም ሰላም ፈላጊ እና የሰላም ዘብ መሆኑን እንደወትሮ ሁሉ ዛሬም አስመስክሯል " - ኡስታዝ አቡበከር አህመድ

በታላቁ አንዋር መስጂድ ህዝበ ሙስሊሙ እንደወትሮ ሁሉ የጁምዓ ሰላቱን ሰግዶ በሰላም ወደ መጣበት መመለሱን ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ገልጸዋል።

" ባለፉት ሁለት ጁምዓዎች በተፈጠሩ ችግሮች በርካታ ሙስሊሞች ከህይወት መስዋትነት አንስቶ ብዙ ዋጋ ከፍለዋል " ያሉት ኡስታዝ አቡበከር " የነሱ መስዋትነት ሁልጊዜም በልባችን ውስጥ ሲታወስ የሚኖር ነው " ብለዋል።

" ህዝበ ሙስሊሙ ሁልጊዜም ሰላም ፈላጊ እና የሰላም ዘብ መሆኑን እንደወትሮ ሁሉ ዛሬም አስመስክሯል " ያሉት ኡስታዝ አቡበከር " ለህዝበ ሙስሊሙ ሰላም የእምነቱ መርህ እና መመሪያው በመሆኑ ሰላሙን ለመጠበቅ ሁሌም ዝግጁ እና ንቁ ነው " ሲሉ ገልጸዋል

በዛሬው ጁምዓ ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ የመንግስት የፀጥታ ኃይል በመስጂዱ ዙሪያ ለጥበቃ በመሰማራቱ በህዝበ ሙስሊሙ ዘንድ ስጋት ፈጥሮ የነበረ ሲሆን ከሚመለከተው የፀጥታ አመራሮች ጋር በመነጋገር ዙሪያውን ከቦ የነበረው የፀጥታ ኃይል ወደኃላ እንዲመለስ በማድረግ ህዝበ ሙስሊሙ ፀጥታውን በራሱ በምእመናን እና በአስተባባሪዎቹ እንደወትሮ በማስጠበቅ የጁምዓ ሰላቱ በሰላም ተሰግዶ ማጠናቀቅ መቻሉ ተገልጿል።

ኡስታዝ አቡበከር ፤ የዛሬው ጁምዓ በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተዋፅኦ ላበረበተው ህዝበ ሙስሊም እንዲሁም የፀጥታ መዋቅሩ በድርሻው ህዝበ ሙስሊሙ በራሱ ሰላሙን ማስጠበቅ እንደሚችል እምነት በማሳደር የበኩላቸውን በመወጣታቸው ምስጋና አቅርበዋል።

በቀጣይም የፀጥታ ኃይሉ በትብብር እና በመናበብ ከህዝበ ሙስሊሙ እና ከአመራሩ ጋር ተቀራርቦ በመስራት የጋራ ሰላማችንን ማስጠበቅ እንደሚቻል ከዛሬው ጁምዓ ትምህርት መውሰድ ይቻላል ብለዋል።

@tikvahethiopia
ያልተገደቡ የድምጽ ጥቅሎች እስከ 30% ቅናሽ ተደርጎባቸው ቀረቡ!

ያልተገደቡ የሞባይል የድምጽ ጥቅሎችን አቅምን ባገናዘበ ዋጋ እስከ 30% ቅናሽ አድርገን ስናቀርብ በልዩ ደስታ ነው !!

ዕለታዊ ድምፅ 35 ብር የነበረው 25 ብር
ወርሃዊ ድምፅ 999 ብር የነበረው 699 ብር
ወርሃዊ ድምፅ እና ዳታ 1700 ብር የነበረው 1399 ብር

እንደፍላጎትዎ በዕለታዊ ሳምንታዊ እና ወርሃዊ አማራጮች የቀረቡትን ያልተገደቡ ጥቅሎች በቴሌብር ሱፐርአፕ https://onelink.to/fpgu4m ማይ ኢትዮቴል ወይም *999# የራስዎ ያድርጉ።

(ኢትዮ ቴሌኮም)
TIKVAH-ETHIOPIA
አሜሪካ በኢትዮጵያ የምታደርገው የምግብ እርዳታ እንዲቋረጥ ወሰነች። የአሜሪካ መንግሥት የዓለም አቀፍ ልማት ተራድኦ ድርጅት (USAID) በኢትዮጵያ የሚያቀርበው የምግብ እርዳታ " ለተረጂዎች ሳይደረስ ሌላ ጥቅም ውሏል " በሚል እንዲቋረጥ መወሰኑን አስታውቋል። USAID እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው " ለኢትዮጵያ ሕዝብ መቅረብ የነበረበት የምግብ እርዳታ በከፍተኛ መጠን እና በተቀናጀ ሁኔታ ከታቀደለት አላማ…
የዓለም ምግብ ፕሮግራም የምግብ ርዳታ ስርጭት አቆመ።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) የኢትዮጵያ የርዳታ ምግብ ሥርጭቱን ማቆሙን አስታውቋል።

የተባበሩት መንግሥታት የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) ለኢትዮጵያ ተጎጂዎች ሲያሠራጭ የቆየውን የምግብ ርዳታ፣ " #ስርቆት_በመንሰራፋቱ " ምክንያት ለጊዜው ማቆሙን ዛሬ ገልጿል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም፣ የርዳታ ምግብ የማቆም ውሳኔውን ይፋ ያደረገው፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ተመሳሳይ ርምጃ መውሰዷን፣ በዩኤስኤአይዲ በኩል ካሳወቀች ከአንድ ቀን በኋላ መሆኑን ቪኦኤ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

በሕጋዊ እና ሰላማዊ አማራጮች ላይ ያለው ገደብ ዜጎች እና የፖለቲካ ፓርቲዎች መብቶቻቸውን ለማስከበር ሌሎች አማራጮችን እንዲጠቀሙ ሊያደርግ ስለሚችል ችግሩ እንዲቀረፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ጠየቀ፡፡

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ ቤት ባለፈው ግንቦት 24 ቀን 2014 ዓ.ም. ባካሔደው አስቸኳይ ስብሰባ በሕጋዊ እና ሰላማዊ አማራጮች ላይ ያለው ገደብ፣ ዜጎች እና የፖለቲካ ፓርቲዎች መብቶቻቸውን ለማስከበር ሌሎች አማራጮችን እንዲጠቀሙ የሚያስገድድ እየኾነ እንዳለ አጽንዖት የሰጠ ሲሆን በፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ እየተደረገ ነው ያለው ጫና እንዲቆም ጠይቋል፡፡

ምንም እንኳን መንግሥት የፖለቲካ ምኅዳሩ ስለ መስፋቱ ቢገልጽም የጋራ ምክር ቤቱ ነገሩ የተገላቢጦሽ እንደኾነ እንደሚያምን ምክትል ሰብሳቢው ዶክተር አብዱልቃድር አደም ተናግረዋል፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤቱ በዚሁ አስቸኳይ ስብሰባው በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ያሉ ግጭቶች እና የፖለቲካ አለመረጋጋቶች በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ አስተዳደር እየተፈጸመ ያለውን የቤቶች፣ የአብያተ እምነቶች እና ሌሎች ግንባታዎች ፈረሳ፣ የኑሮ ውድነት፣ የሙስና መንሰራፋት እና ሌሎችንም ልዩ ልዩ ወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች በተመለከተ ውይይት ማድረጉን አስታውቋል፡፡

ገዢውን የብልጽግና ፓርቲን ጨምሮ 61 ሀገር አቀፍ እና ክልላዊ ፓርቲዎችን በሥሩ ማቀፉን የገለጸው ምክር ቤቱ በሰጠው መግለጫ ኢትዮጵያ በዘርፈ ብዙ የጸጥታ፣ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና ማኅበራዊ ችግሮች ውስጥ እንደምትገኝ ገልጾ ባለ12 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቷል፡፡


ግጭቶችን በሰላም ከመፍታት አንጻር፣ በትግራይ ክልል አንጻራዊ ለውጥ እንደታየ የጠቀሰው መግለጫ፣ " በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በጋምቤላ ክልሎች ያለው የሰላም ኹኔታ ግን፣ እጅግ አሳሳቢ ነው " ብሏል፡፡

በመሆኑም በአገሪቱ ያሉ ግጭቶች ሁሉ፣ በድርድር እና በውይይት እንዲፈቱ ጠይቋል፡፡

ሌላው መግለጫ ከዳሰሳቸው ጉዳዮች መካከል ዜጎችን በኃይል የመሰወር ድርጊት አሳሳቢነት ይገኝበታል፡፡

እጅግ አሳሳቢ ሆኗል ያለው፣ የአፈና እና አስገድዶ የመሰወር ድርጊት እንዲቆም፣ የጋራ ምክር ቤቱ አሳስቧል፡፡

ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣው የመሠረታዊ ሸቀጦች የዋጋ ንረትም፣ ዜጎችን ለከፋ ጉዳት መዳረጉን ያብራራው የአቋም መግለጫው፣ ለዚህም ዋና ምክንያት አድርጎ ያስቀመጣቸው፣ የፖሊሲ ችግር እና ሙስና አስቸኳይ እልባት እንዲሰጣቸው ጠይቋል።

በሸገር ከተማ ያለው የቤቶች እና የእምነት ተቋማት ፈረሳ ድርጊት ቆሞ፣ ሕጋዊ መንገድን እንዲከተል የጋራ ምክር ቤቱ በአቋም መግለጫው አሳስቧል፡፡

ለሀገሪቱ ውስብስብ ችግሮች መፍትሔ ያመጣል ያለው ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ ውይይት ግልጽ እና አሳታፊ በሆነ መንገድ እንዲካሔድም ጠይቋል፡፡

(ሙሉ የአቋም መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

Credit : የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች ምክር ቤት / ቪኤኤ

@tikvahethiopia
We Are Hiring!
Berhan Bank seeks to hire applicants for the positions of
 Junior Customer Service Officer
Use the link below to apply for the vacancy
https://t.iss.one/berhanbanksc
በትላንትናው ዕለት ከአዲስ አበባ ወደ ደምቢ ዶሎ በሚያቀና አምቡላንስ ላይ በተፈፀመ ጥቃት / ተኩስ የሰው ህይወት አለፈ።

የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ይፋ ባደረገው መረጃ ከአድስ አበባ ወደ ደምቢ ዶሎ በመመለስ  ላይ እያለ በነበረ አምቡላንስ ላይ በተፈፀመ ጥቃት / ተኩስ የተቋሙ ሰራተኛ ህይወት አልፏል።

በተኩሱ የተገደሉት ፤ አቶ ገመቹ ጀቤሣ የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ  ሆስፒታል ጤና በለሙያ መሆናቸውን ተገልጿል።

ተኩሱ  በአምቡላንሱ ላይ በድንገት የተከፈተ ሲሆን ተኩሱ የተፈፀመው " እናንጎ " አከባቢ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ጥቃት አድራሾቹን በተመለከተ ተቋሙ በዝርዝር ያለው ነገር የለም።

ደምቢ ዶሎ ዩኒቭርስቲ በሰራተኛው ሕልፈተ ሕይወት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገልጾ ለቤተሰቦቹ፥ ለወዳጅ ዘመዶቹ፥ ለሥራ ባልደርቦቹ እና ለደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በሙሉ መጽናናትን ተመኝቷል።

@tikvahethiopia
" ... ለመንገዶች ደህንነት የተለየ ጥበቃ ቢደረግም ታጣቂዎች ሸማቂ መሆናቸው ችግሩን ከመሰረቱ የማስወገድ ስራን አስቸጋሪ አድርጎታል " - አቶ ገዳ ጎዳና

በዚህ ሳምንት በኦሮሚያ ክልል፣ ምዕራብ ጉጂ ዞን በታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት ሁለት ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች አራት ቆስለዋል።

ጥቃቱ የተፈፀመው ማክሰኞ እኩለ ቀን በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪ ላይ ሲሆን ቦታው ለቡሌ ሆራ አቅራቢያ በሆነችው " ባዳ መጋዳ " በተባለ ስፍራ ነው ተብሏል።

ጥቃቱን በማድረስም ከአደጋው የተረፉ የዓይን እማኞች እና የመንግስት ባለስልጣናት እራሱን " የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት " ያለውና መንግስት " ሸኔ " ያለውን ሸማቂ ቡድን ከሰዋል፡፡

በታጣቂ ቡድኑ በኩል ግን ስለዚህ ጥቃት የተሰጠ ማረጋገጫም ሆነ ማስተባበያ አልተሰማም፡፡

የምዕራብ ጉጂ ዞን ፀጥታ አስተዳደር ኃላፊ አቶ ገዳ ጎዳና ለዶቼ ቨለ ሬድዮ በሰጡት ቃል ይህ ጥቃት ከመፈጸሙ ከደቂቃዎች አስቀድሞ በመንግስት ጦር እና " ኦነግ ሸኔ " ባሉት ታጣቂ ቡድን መካከል የተውክስ ልውውጥ እንደነበር ገልጸዋል፡፡

ኃላፊው " ጠላት " ያሉት ሸማቂው ቡድን ንጹኃን ላይ ተውክስ ከፍተው ሁለት ሰዎች ገለዉ፤ አራት ሰዎች ቢያቆስሉም፤ በአከባቢው የነበረ የመንግስት የፀጥታ ኃይል ደርሶ ሊደርስ የነበረዉን ተጨማሪ ጥቃት አስጥሏል ብለዋል፡፡

የፀጥታ ችግሩ በዚህ አከባቢ ለዓመታት መቀጠሉን ነዋሪዎች በምሪት ያነሳሉ፡፡

የዞኑ ፀጥታ አስተዳደር ኃላፊው ግን ለመንገዶች ደህንነት የተለየ ጥበቃ ቢደረግም ታጣቂዎች ሸማቂ መሆናቸው ችግሩን ከመሰረቱ የማስወገድ ስራን አስቸጋሪ አድርጎታል ብለዋል፡፡

መረጃው የዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ኢትዮጵያ

" በአንድ አገር የመድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲ ባህል እንዲጎለብት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች የማይተካ ሚና ይጫወታሉ፡፡

ከዚህ አንጻር በእንጭጭ የሚገኘው የሀገራችን የዴሞክራሲ ስርአት እንዲያብብ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሚና እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡

ህጋዊ እና ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴን #መገደብ እና የፖለቲካ ምህዳሩን #ማጥበብ በሀገራችን ያለውን የፖለቲካ አለመረጋጋት ይበልጥ ከማባባስ በተጨማሪ ዜጎች እና ልዩ ልዩ የፖለቲካ ኃይሎች መብቶቻቸውን ለማስከበር ሌሎች አማራጮችን እንዲያስቡ እና እንዲጠቀሙ ይገፋል።

ይህንን በመገንዘብ በተለያየ ደረጃ የሚገኙ #የመንግስት_አካላት በተቃዋሚ የፖለቲካ ኃይሎች ላይ የሚያደርጉትን ህገ ወጥ ጫና በአስቸኳይ እንዲያቆሙ፣ በተለይም #በታችኛዉ የአስተዳደር እርከኖች የሚገኙ የገዢዉ ፓርቲ አመራሮች የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ላይ እያደረጉ ያሉትን ከፍተኛ ጫና፣ እስር እና ማዋከብ በአስቸኳይ እንዲያቆሙ ም/ቤቱ በአጽንኦት ያሳስባል "

(የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት)

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
DEVELON (ዲቬሎን) የሚለው አዲሱ የዱሳን ስያሜ የ Develop (“ማደግ”) እና Onward (“ወደፊት”) ቃላቶች ውህድ ሲሆን፤ በኮንስትራክሽን ማሽነሪ ዘርፍ ያሳረፍነዉን ትልቅ አሻራ በማጎልበት በጎ ነገሮችን ይዘን “ወደፊት ለማደግ” ያለንን ምኞት ያንፀባርቃል።

• ከአዲሱ የብራንድ ስያሜ ለዉጥ ውጭ ምንም አይነት ውጫዊ ገፅታም ሆነ ውስጣዊ የማሽኑ አካላት ላይ ለውጥ አልተደረገም።
 
• ኦርጅናል መለዋወጫ፣ አስተማማኝ፣ ቀልጣፋና እና ተደራሽነት ያለው የጥገና አገልግሎት መለያችን ናቸው።

ማይ ዊሽ ኢንተርፕራይዝ ኃላ/የተ/የግ/ማ ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ https://t.iss.one/MYWISHENT 
+251-913-356384  +251-912-710661  +251-910-626917  +251-928-414395
+251-911-606068  +251-922-475851  +251-935-409319  +251-911-602664