TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን‼️

የከተራና የጥምቀት በዓላት #በሰላም ተከብረው መጠናቀቃቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

በሀገራችን በርከታ ህዝብ ወደ አደባባይ በመውጣት ከሚያከብራቸው ሃይማኖታዊ በዓላት መካከል የከተራና የጥምቀት በዓላት ይገኙበታል፡፡

እጅግ በርካታ ቁጥር ያላቸው የሃይማኖቱ ተከታዮች ፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ፣ መቀመጫቸውን ኢትዮጵያ ውስጥ ያደረጉ የውጭ ሀገራት ዲፕሎማቶች እና የተለያዩ ሀገራት ቱሪስቶች የታደሙበት በአዲስ አበባ ልዩ ልዩ ስፍራዎች በተለይም በጃን ሜዳ የተከበሩት የከተራና የጥምቀት በዓላት በሰላም መከበራቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

በዓላቱ  በሰላም እንዲከበሩ ህብረተሰቡ እና በዋናነት የከተማ  ወጣቶች ላደረጉት ቀና ትብብር ኮሚሽኑ ምስጋና አቅርቧል፡፡

በተጨማሪም  በነገው ዕለት  በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ  የሚከበረው የቃና ዘገሊላ በዓል በሰላም እንዲከበር ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩን #አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ መቅረቡን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ ፦ ነሲሓ የበጎ አድራጎትና የልማት ድርጅት (NCDO) በደብረ ብርሃን መጠለያ ካምፕ ውስጥ ለሚገኙ የወለጋ ተፈናቃዮች ድጋፍ አደረገ።

ድርጅቱ ፤ የዒደ አል አድሐ በዓልን በማስመልከት በሁለት ዙር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ፤ በመጀመሪያው ዙር 19 በሬዎችን ፣ በሁለተኛ ዙር 10 በሬዎችንና 100 በጎችን በደምሩ 1.8 ሚሊዮን ብር ገደማ የሚገመት ድጋፍ አድርጓል።

ድርጅቱ ለወደፊቱም በሚችለው ሁሉ እገዛውን ለሚሹ የማኅበረሰብ ክፍሎች የሚያደርገውን ድጋፍ #አጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳውቋል።

Credit : NCDO

@tikvahethiopia