" ዕድሜ አጭበርብረዋል " የተባሉት አትሌቶች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለፀ።
ከጥር 23 -28/2015 ዓ.ም በአሰላ አረንጓዴው ስቴድዮም ከ #ሃያ (20) ዓመት በታች የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና እየተካሄደ ይገኛል።
በዚሁ ውድድር ላይ ከእድሜ ተገቢነት ጋር በተያያዘ ከፍተኛ መነጋገሪያ ጉዳዮች ተፈጥረዋል፤ በማህበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወሩ የነበሩ ፎቶዎችም በርካቶችን " እንዴት እኚህን የሚያክሉ አትሌቶች ከ20 ዓመት በታች ይወዳደራሉ " በሚል አስገርመዋል።
ይህን በተመለከተ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከደቂቃዎች በፊት ባሰራጨው መልዕክት ፤ ከእድሜ በላይ ሆነው የተገኙ አትሌቶችን በሠነድ እና በአካላዊ ምርመራ ከውድድር ውጭ መሆናቸውን ይፋ አድርጓል።
ፌዴሬሽኑ ቁጥራቸው ከ80 የሚልቁ አትሌቶችም ስማቸውን ይፋ አድርጓል።
ተግባሩን በፈፀሙ ቡድኖች አሰልጣኞች ላይም እርምጃ እንዲወሰድ ለየክልላቸው፣ ከተማ አስተዳደራቸው፣ ክለባቸውና ተቋሞቻቸው ፌዴሬሽኑ ማስጠንቀቂያ አዘል ደብዳቤ እንደሚልክ አሳውቋል።
ማጣራቱ እስከ ውድድሩ ማብቂያ ድረስ የሚቀጥል እንደሆነ የገለፀው አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከዚህ ሲያልፍ ከሳምንትም ሆነ ከወር በኋላም ቢሆን ተጨማሪ መረጃ ከተገኘ አትሌቱ የተሸለመው ሜዳልያም ሆነ የገንዘብ ሽልማት ተመላሽ እንደሚደረግ በጥብቅ አሳስቧል።
የእድሜ ተገቢነት ችግር ውስጥ የተገኙ አትሌቶችን ዝርዝር ከሥር ከላይ ተያይዟል።
@tikvahethiopia