TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ማዳበሪያ . . . አርሶ አደሮች የአፈር ማዳበሪያ ባለማግኘታቸው ያዘጋጁትን የእርሻ መሬት በዘር ለመሸፈን መቸገራቸውን እያሳወቁ ይገኛሉ። ለአብነት ቃላቸውን የሰጡ በምዕራብ ጎጃም ዞን ፤ ጎንጅ ቆለላ ወረዳ የሚገኙ አርሶ አደሮች በቂ የአፈር ማዳበሪያ ባለማግኘታቸው ያዘጋጁትን የእርሻ መሬት በዘር ለመሸፈን ተቸግረዋል። ቄስ ተበባል መኮነን ፤ 2 ነጥብ 5 ሄክታር የእርሻ መሬታቸውን በበቆሎ ፣ በስንዴ…
ማዳበሪያ . . .

" ማዳበሪያ በወቅቱ ስላልቀረበልን የዘር ስራችን እየተደናቀፈብን ነው " - በደብረ ብረሀን ከተማ ዙሪያ የሚገኙ አርሶ አደሮች

" የማዳበሪያ አቅርቦት ችግር  ከአቅሜ በላይ ነው " - የደብረብርሃን ከተማ ግብርና መምሪያ

በደብረብርሃን ከተማ ዙሪያ በጫጫ ክፍለ ከተማ የጨፋንን ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ካሳየ ሄየ ፦

" በበጋ መስኖ ስንዴ ስናለማ መንግስት ሰው ሰራሽ ማዳበሪያና ምርጥ ዘር ድጋፍ ስላደረገልን ጥሩ  ውጤት አይተናል።

በ2015/16 ከመኸር ሰብል የበለጠ ምርት ለማግኘት አቅጄ ማሳዬን ደጋግሜ አርሼ ለዘር ባዘጋጅም እስካሁን እጄ ላይ የገባ ግብዓት ባለመኖሩ የዘር ስራው እየተደናቀፈ ነው።

በጨፋንን አካባቢ በደረቅ የሚዘራ ቢሆንም የወቅቱ ዝናብ  ተጽዕኖ ቀላል አይደለም።

ዝናቡን ተቋቁመው የተዘጋጀውን መሬት በዘር ለመሸፈን እስከ ግንቦት 10 የሚመለከተው አካል ማዳበሪያ ሊያቀርብልን ይገባል።

ዘግይቶ የሚመጣ ከሆነ ግን ዋጋ የለውም። "

አርሶ አደር ፅጌ ኃይለማሪያም ፦

" የራሴን እና በኮንትራት የያዝኩትን መሬት ደጋግሜ አርሼ ባዘጋጅም የማዳበሪያ አቅርቦት ችግር የዘር ስራውን አስተጓጉሎብኛል።

ባለፉት ዓመታት ማዳበሪያ እስከዚ ጊዜ ድረስ እንቀበል ነበር። በዚህ ዓመት ግን የቀረበልን ግብዓት የለም።

በፍጥነት ካልቀረበ የሚደርሰው ጉዳት ቀላል አይደለም። "

የደብረብርሃን ከተማ ግብርና መምሪያ ምን ምላሽ ሰጠ ? 

የመምሪያው ኃላፊ ኃላፊ አቶ መርሻ አይሳነው ፦

" አርሶ አደሮቹ ያቀረቡት ቅሬታ ትክክል ነው።

የማዳበሪያ አቅርቦት ችግሩ  ከመምሪያው አቅም በላይ ነው።

በ2015/16 የምርት ዘመን ከ21 ሺህ ሄክታር  መሬት በላይ በመኸር ሰብል በመሸፈንና በ11 በመቶ መርትን በማሳደግ ከ768 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት ታቅዶ እየተሰራ ነው።

ይህም ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃጸር የ75 ሺህ ኩንታል ምርት ብልጫ ያለው ነው።

መምሪያው ዕቅዱን ለማሳካት የባለሙያ ስልጠና መስጠቱንና በየደረጃው ከሚገኙ አመራሮች፣ አርሶ አደሮችና አጋር አካላት ጋር መግባባት ላይ ተደርሶ እየተሰራ ነው።

ምርታማነትን ለማሳደግ አርሶ አደሮች  182 ሺህ ሜትር ኪዩብ  የተፈጥሮ ማዳበሪያ አዘጋጅተው ማሳቸው ላይ እንዲበትኑ ተደርጓል።

52 ሺህ ኩንታል ሰው ሰራሽ ማዳበሪያ እንዲቀርብልን የበላይ አካል ጠይቀን  30 ሺህ ኩንታል ቢፈቀድም እስካሁን እጃችን የገባው የዕቅዱን 13 በመቶ ብቻ ነው።

በደብረብርሃን አካባቢ ቀድሞ የሚዘራ ቢሆንም ግብዓት ባለመቅረቡ የዘር ስራው እየተጓተተ ይገኛል።

የተሻለ ምርት ለማግኘት ተደጋግፎ መስራት ወሳኝ ነው።

... ጊዜው ሳያልፍ ግብዓት እንዲቀርብና የዘር ስራው እንዲቀጥል  ለችግሩ የመፍትሄው አካል በመሆን በየደረጃው የሚመለከታቸው ሁሉ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል። "

መረጃው ከቀናት በፊት ከደ/ብርሃን ኮሚኒኬሽን የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ማዳበሪያ . . . " ማዳበሪያ በወቅቱ ስላልቀረበልን የዘር ስራችን እየተደናቀፈብን ነው " - በደብረ ብረሀን ከተማ ዙሪያ የሚገኙ አርሶ አደሮች " የማዳበሪያ አቅርቦት ችግር  ከአቅሜ በላይ ነው " - የደብረብርሃን ከተማ ግብርና መምሪያ በደብረብርሃን ከተማ ዙሪያ በጫጫ ክፍለ ከተማ የጨፋንን ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ካሳየ ሄየ ፦ " በበጋ መስኖ ስንዴ ስናለማ መንግስት ሰው ሰራሽ ማዳበሪያና…
የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምን አለ ?

በአማራ ክልል በ2015/16 የመኸር የእርሻ ዘመን 5 ሚሊዮን ሔክታር ማሣ በዘር በመሸፈን 160 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማምረት ሰፊ የቅድመ ዝግጅትና የትግበራ ስራ እየተሰራ ነው ብሏል።

ነገር ግን የማዳበሪያ አቅርቦት እንዲሁም ስርጭቱ በሚፈለገው ፍላጎትና ቢሮው በአስቀመጠው የዕቅድ መጠን ልክ እንዳልሆነ አልሸሸገም።

ይህም ካለው የሀገሪቱ አጠቃላይ ወቅታዊ ችግርና ማዳበሪያ በሀገር ውስጥ የሚመረት እና እንደ ምርጥ ዘር በራሳችን የሚቀርብ አለመሆኑን ሁሉም መገንዘብ ይኖርበታል ብሏል።

ቢሮው  ፤ " ከፌደራል ግብርና ሚኒስቴር ጋር በቅርበትና በቅንጅት በመስራት ማንኛውንም የሚቻለንን ሁሉ እየሠራን ነው "  ሲል ገልጾ " ችግሩን ይበልጥ #ማጯጯህ ሳይሆን ይህም ችግር እንደማንኛውም ችግር የሚያጋጥምና ችግሩን መወጣትም አንዱ የትግል አካል በመሆኑ በመተባበርና በመቀናጀት መስራት ይገባል " ብሏል።

ቢሮው ፦

1ኛ. ቀድሞ የገባን ማዳበሪያ ቀድመው ለሚዘሩ ሰብልና አካባቢዎች በመተሳሰብ ማሰራጨት፤

2ኛ. ማንኛውም የሚቀርቡ ግብአቶች ከብልሹ አሰራርና ህገወጥ ድርጊት መከላከል፤

3ኛ. የተፈጥሮ ማዳበሪያ ኮምፓስት፣ ቨርሚ ኮምፓስትና ሌሎችንም ቢሮው ሲከታተለው የከረመ በመሆኑ በዞኖች በሪፓርት የተላከውን ኮምፓስት መጠቀም መቻል፤

4ኛ. የመረጃ ቅብብሎሽ በትክክለኛና በተመጠነ አኳኃንና እንዲሁም የአርሶአደሩን ሞራልና ስሜት የሚያበረታታና የሚያጠነክር መሆን አለበት ብሏል።

ቢሮው በአሁኑ ሰዓት በክልሉ በሁሉም የሰብል አይነትና መጠን የምርጥ ዘር ችግር በአንጻራዊነት ችግር እንደሌለ ገልጿል።

ከግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት አማራ ቅርንጫፍ በተገኘው መረጃ መሠረት አማራ ክልል በነዚህ በተዘረዘሩት ሰብሎች የሚከተለውን " #ሀገራዊ_ድርሻ " የያዘ ክልል ነው።

- ጤፍ  👉 40% ሀገራዊ ድርሻ አለው።

- ሰሊጥ 👉 80% ሀገራዊ ድርሻ አለው።

- ስንዴ 👉 32% ሀገራዊ ድርሻ አለው።

- አኩሪአተር 👉 85% ሀገራዊ ድርሻ አለው።

- ሩዝ 👉 63% ሀገራዊ ድርሻ አለው።

- በርበሬ 👉 45% ሀገራዊ ድርሻ አለው።

- እጣንና ሙጫ 👉 60% የማምረት ድርሻ አለው።

መረጃው ከአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት #ቤተመንግስት ግንባታ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሂዷል።

ግንባታው ቦሌ ላይ እንደሆነ ተነግሯል።

የፕሮጀክቱ ጠቅላላ ግንባታ በ 6.5 ሄክታር መሬት ላይ እንደሚያርፍ በመርሐ ግብሩ ላይ ተገልጿል።

የፕሮጀክቱ ዲዛይን የኦሮሞን ህዝብ ወግ ፣ ባህል ታሪክ ፣ የገዳ ስርዓት ለዘመናት እያበረከተ ያለውን ጠቀሜታ የሚገልጽ ነው ተብሏል።

የግንባታ ስራው በሁለት ዓመት ጊዜ ይጠናቀቃል የተባለ ሲሆን ግንባታውን የሚያከናውነው የቻይናው ሲቪል ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ነው።

Via OBN / Ato Addisu Arega

@tikvahethiopia
#big5construct

Join us for a thought-provoking discussion on challenges & opportunities in the Ethiopian real estate sector through the construction project management lens. Our esteemed moderator and panelists, including  Brook Tefera, Bruk Berhanu & Robel Tsegaye will share their insights and expertise on this topic. 

19 May 2023 | 11:00 AM - 12:00 PM

Register now: https://bit.ly/3oI8P6L
#MyWishEnterprise

DEVELON (ዲቬሎን) የሚለው አዲሱ የዱሳን ስያሜ የ Develop (“ማደግ”) እና Onward (“ወደፊት”) ቃላቶች ውህድ ሲሆን፤ በኮንስትራክሽን ማሽነሪ ዘርፍ ያሳረፍነዉን ትልቅ አሻራ በማጎልበት በጎ ነገሮችን ይዘን “ወደፊት ለማደግ” ያለንን ምኞት ያንፀባርቃል።

• ከአዲሱ የብራንድ ስያሜ ለዉጥ ውጭ ምንም አይነት ውጫዊ ገፅታም ሆነ ውስጣዊ የማሽኑ አካላት ላይ ለውጥ አልተደረገም።
 
• ኦርጅናል መለዋወጫ፣ አስተማማኝ፣ ቀልጣፋና እና ተደራሽነት ያለው የጥገና አገልግሎት መለያችን ናቸው።

ማይ ዊሽ ኢንተርፕራይዝ ኃላ/የተ/የግ/ማ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ https://t.iss.one/MYWISHENT 
0913356384 / 0912710661  0910626917 / 0928414395
0911606068 / 0922475851  0935409319 /0911602664
የትግራይ ተማሪዎች . . .

በትግራይ ጦርነት ምክንያት በክልሉ ያሉ ትምህርት ቤቶች ወድመዋል፣ ተዘርፈዋል፤ እንዳልነበሩ ሆነዋል።

ከምንም በላይ ደግሞ የትግራይ ልጆች ለከፍተኛ የስነ ልቦና እና የአካል ጉዳት ተዳርገዋል።

ከዓመታት በኃላ የመማር ማስተማር ሂደት በትግራይ ውስን አካባቢዎች ቢጀመርም የትግራይ ልጆች / ተማሪዎች የወደፊት ብሩህ ህልማቸው ለማሳካት ሲሉ በድንጋይ ላይ ፣ በዛፍ ግንድ ስር እና በወደሙ የመማሪያ ክፍሎች ውስጥ ቁጭ ብለው ለመማር እየታገሉ ይገኛሉ።

የትግራይ ልጆች / ተማሪዎች በድንጋይ ላይ ተቀምጠው የሚማሩበትን ጊዜ ለማሳጠር ብዙ ጥረት ይጠይቃል ተብሏል።

ይህን ችግር ለመፍታት ሁሉም ርብርብ እንዲያደርግ እየተጠየቀ ሲሆን ባለሃብቱ ዘርኡ ገብረሊባኖስ ፤ በሰለኽለኻ በድንጋይ ላይ ተቀምጠው ለሚማሩ ተማሪዎች ወንበር መግዣ ይሆን ዘንድ 1 ሚሊዮን ብር ማበርከታቸውን ከድምፂ ወያነ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

በሌላ በኩል ፤ ባለሃብቱ ዘርኡ በሰሜናዊ ምዕራብ ትግራይ ፅምብላ ወረዳ ለሚያስገነበቱ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዛሬ የመሰረት ድንጋይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተቀምጧል።

Photo Credit ፦ ድምፂ ወያነ / ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Voice message
#Update

ፖሊስ ስለ #ወለንጪቲ ምን አለ ?

በኦሮሚያ ክልል፣ ምስራቅ ሸዋ ዞን የቦሰት ወረዳ ፖሊስ ፤ ትላንት ማክሰኞ ታጣቂዎች በወለንጪቲ ከተማ ላይ ጥቃት ከፍተው እንደነበር በማረጋገጥ የታጣቂዎቹ የጥቃት ዓላማ " እስረኞችን ለማስፈታት ነበር " ብሏል።

ፖሊስ ይህን ያለው ለቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት በሰጠው ቃል ነው።

የቦሰት ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር መሐመድ ሱፋ ምን አሉ ?

- በወለንጪቲ ከተማ የተፈጸመው ጥቃት በኦነግ ሸኔ / እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እያለ በሚጠራ ኃይል ነው ብለዋል።

- ትላንት አመሻሽ ወደ 11 ሰዓት አካባቢ ወደ ወለንጪቲ ከተማ ዘልቀው ለመግባት ባደረጉት ሙከራ ፤ በንጹሃን ሰዎች ላይ ሞትና ጉዳት አደርሰዋል ሲሉ ገልጸዋል። በዚህም ሁለት ንፁሃን መገደላቸውን ፣ ሁለት ንፁሃን መጎዳታቸውን አመልክተዋል።

- " በዚህ በእኛ ቦሰት ወረዳ ውስጥ ኦነግ ሸኔ የሚባለው ኃይል በሰፊው ይንቀሳቀሳል። በአብዛኛው ጊዜ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ላይ ጉዳት ለማድረስ ይሞክራሉ። ከተማዋ ላይም ጥቃት ለማድረስ ሲጥሩ ነበር። " ብለዋል።

- ታጣቂ ቡድኑ ትላንት 11 ሰዓት አካባቢ በበርካታ ቁጥር ወደ ከተማዋ ለመግባት ሙከራ ያደረገ ሲሆን በአካበቢው የሚንቀሳቀሱ የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በጥምረት ጥቃቱን ለመከላከል እንደቻሉ አመልክተዋል።

- በከተማዋ ላይ ጥቃት ለመፈጸም ተሰማርተው ከነበሩት ታጣቂዎች ወገን 6 መሞታቸውን እና 4 ደግሞ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፖሊስ አዛዡ ተናግረዋል።

- በታጣቂዎች የተፈጸመው ጥቃት እና የተካሄደው የተኩስ ልውውጥ ከ30 ደቂቃ በላይ አልቆየም ፤ የታጣቂዎቹ የጥቃት ዓላማ " እስረኞችን ለማስፈታት ነበር " ብለዋል።

- " በፖሊስ ጽህፈት ቤት ውስጥ ልዩ ልዩ እስረኞች አሉ። ከእነርሱም ወገን ተይዘው የታሰሩ አሉ። " ያሉት አዛዡ " እነዚህን ለማስፈታት ነበር ወደ ፖሊስ ጣቢያው የመጡት " ብለዋል። ነገር ግን ታጣቂዎቹ ወደ ፖሊስ ጣቢያው መግባት እንዳልቻሉ እና በአቅራቢያው ያለው የአገር መከላከያ ሠራዊት ደርሶ እርምጃ በመውሰዱ " የተወሰኑት ሲገደሉ እና ሲቆስሉ የቀሩት ደግሞ የያዙትን በመጣል ወደ ጫካ ሸሽተዋል " ሲሉ ተናግረዋል።

- የወለንጪቱ ከተማ ዛሬ ረቡዕ በተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ መሆኗን ተናግረው፤ ወደ ምሥራቁ የአገሪቱ ክፍል የሚያቋርጠው ዋና መንገድ መደበኛ የትራንስፖርት አግልግሎት እየሰጠ መሆኑን አሳውቀዋል።

NB. የፖሊስ አዛዡ ቃላቸውን የሰጡት ለቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በትላንትናው ዕለት በወለንጪቲ ስለነበረው ሁኔታ ትላንት ከተቀበላቸው በተጨማሪ ከሌሎች ቤተሰቦቹ መልዕክቶችን ሲቀበል ነበር።

ቤተሰቦቻችን በከተማው ንፁሃን በተባራሪ ጥይት መገደላቸውን ፤ የቆሰሉም ሰዎች መኖራቸውን አሳውቀዋል።

አንድ የቤተሰባችን አባል ፤ ሁኔታው እጅግ በጣም አስከፊ እንደነበር በመግለፅ እራስሩ እራሱ በቅርብ የማያውቃቸው ሰዎች መገደላቸውን ጠቁሟል።

" የተገደሉት ምንም የማያወቁ ፤ እየተፈጠረ ስለነበረው ነገር መረጃ እንኳን የሌላቸው ንፁህ ሲቪል ሰዎች ናቸው " ብሏል።

በዚህ ቀጠና ያለው ነገር እጅግ በጣም አሳሳቢ ነው ያለው ይኸው የቤተሰባችን አባል ፤ ከዚህ በፊትም ተኩስ መስማት የተለመደ ነው ነገር ግን የትላንቱ እጅግ የከፋ ነበር ብሏል።

በዚህ የወለንጪቲ መስመር ላይ የታጣቂዎች እንቅስቃሴ መኖሩ ፣ ግድያን ጨምሮ ዝርፊያ እገታ እንደሚፈፀም በተደጋጋሚ መጠቆሙ ይታወቃል።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia @tikvah_eth_BOT