TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ድርድር

መንግሥት " ኦነግ ሸኔ " እያለ የሚጠራው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አዛዥ መሮ ዲሪባ ፥ የታጠቂ ቡድኑን ከፌደራል መንግሥቱ ጋር የሚያደራድር ሦስተኛ አካል መኖሩን ለቢቢሲ በሰጡት ቃል አረጋግጠዋል።

ጃል መሮ አደራዳሪዎቹ እነማን እንደሆኑ በስም ከጥቀስ ተቆጥበዋል።

መሮ ዲሪባ ታጣቂ ቡድኑን ወክለው ከመንግሥት ጋር የሚደራደሩ የልዑክ ቡድን አባላት ወደ #ታንዛኒያ ጉዞ እያደረጉ ስለመሆኑ አሳውቀዋል።

መሮ ዲሪባ ይህ ንግግር በታንዛኒያዋ ራስ ገዝ ግዛት በሆነችው #ዛንዚባር ደሴት ላይ እንደሚከናወን ገልጸው፤ " የጥይት ድምጽ ሳይሰማ የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ መልስ የሚያገኝ ከሆነ በራችን ሁሌም ክፍት ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

መሮ ፥ በቅርቡ ኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና መንግሥት ሦስተኛ ወገን ባለበት በኬንያ ለመነጋገር ቀጠሮ ይዘው የታጣቂ ቡድኑ ተወካዮች በቦታው ቢገኙም የመንግሥት ተወካዮች ግን ሳይገኙ ቀርተዋል ብለዋል።

" በሌሎች አገራት ግብዣ በኬንያ ለመገናኘት ቀጠሮ ነበር። ነገር ግን መንግሥት ሳይገኝ ቀረ "  ያሉት መሮ " በአሁኑ ድርድር ስኬት ላይ ጥርጣሬዎች ቢኖረንም የንግግር ሂደቱ ሰላም ሊያመጣ ይችላል የሚል ተስፋ አለኝ " ሲሉ ተናግረዋል።

" ንግግር መጀመሩ ጥሩ ነው። መነጋገር እና መፍታት ያለብን ብዙ ነገሮች ስላሉ ጉዳዩ በአንድ ጊዜ የሚጠናቀቅ አይሆንም " ሲሉ አክለዋል።

ከዚሁ ድርድር ጋር በተያያዘ ቢቢሲ የኢትዮጵያ መንግሥት ከታጣቂ ቡድኑ ጋር በሚደረገው ንግግር ፦
- የስዊድን፣
- የኖርዌይ፣
- የኬንያ፣
- የአውሮፓ ኅብረት እና የአሜሪካ ዲፕሎማቶች እንደሚገኙ ሁለት ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ ምንጮች እንደገለፁለት ዘግቧል።

@tikvahethiopia