TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ሱዳን ውስጥ የነበሩ የግብፅ ወታደሮች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደረገ።

የሱዳን ጦር 177 የግብፅ የአየር ኃይል ወታደሮች ወደ ግብፅ መወሰዳቸውን አስታውቋል።

የሱዳን ጦር ባወጣው መግለጫ የግብፅ ወታደሮቹ በአራት የግብፅ ወታደራዊ አውሮፕላኖች ከሰሜናዊቷ ዶንጎላ ከተማ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደርገዋል።

ጦሩ ፤ ግብፃውያኑ ሱዳን የነበሩት የጋራ የአየር ሃይል ልምምድ ለማድረግ እንደነበር አመልክቷል።

የግብፅ ጦር የሰራዊት አባላቱ ሱዳንን  ለቀው ስለመውጣታቸውን እስካሁን በይፋ ባያሳውቅም ሱዳን ያሉ ወታደሮቹን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ከሱዳን ባለስልጣናት ጋር በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገልጾ ነበር።

የሱዳን ጦር አሁን መመለሳቸውን የገለፃቸው የግብፅ ወታደሮች ከቀናት በፊት በRSF የተያዙትን እንዳልሆነና በRSF ስር ያሉት 28 ወታደሮች መሆናቸውንና አሁንም በነሱ እጅ እንደሚገኙ ገልጿል።

ትላንት ምሽት ግን የሱዳን ጦር ወደ ግብፅ የተወሰዱት በRSF የተያዙት / የታሰሩ ወታደሮች መሆናቸውን ገልጾ መግለጫ አውጥቶ ነበር ፤ ይህንን መግለጫም ዋቢ በማድረግ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘገባዎችን ሰርተው ነበር።

ጦሩ ዛሬ ባወጣው መግለጫ የትላንቱ መግለጫው ትክክለኛ እንዳልሆነ አመልክታል። የተያዙት / የታሰሩት በሚል የገባው ቃል ሳይታወቅ በስህተት ነው ብሏል።

አሁን ወደ ግብፅ እንዲመለሱ የተደረጉት ወታደሮች ግጭቱ በተቀሰቀሰበት ወቅት ማራዊ ውስጥ የነበሩ ነገር ግን ከኤርፖርት ውጭ ስለነበሩ በRSF ያልተያዙ ናቸው ሲል አስረድቷል።

የሱዳን ውጊያ በተጀመረበት ወቅት በጄነራል መሐመድ ሃምዳን ደጋሎ (ሄሜቲ) የሚመራው የሱዳን ፈጥኖ ደራሻ (RSF) ሜሮዌ ላይ የግብፅ ወታደሮችን #መማረኩን ማሳወቁ ይታወሳል።

ከቀናት በፊት የግብፁ ፕሬዜዳንት አብድል ፈታህ አል ሲሲ ሱዳን ውስጥ የተያዙት የግብጽ ወታደሮች፣ በዚያ የተገኙት ከሱዳን አቻዎቻቸው ጋራ ወታደራዊ ልምምድ ለማድረግ እንጂ ፤ የትኛውንም ወገን ለመደገፍ አለመኾኑን ገልጸዋል።

ይህንን የገለፁት ከግብጽ ከፍተኛ ወታደራዊ ም/ቤት ጋር ስብሰባ በተቀመጡበት ወቅት ሲሆን የወታደሮቹን ደህንነት በተመለከተ ከRSF ጋር እየተነጋገሩ መሆኑን አስታውቀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የሱዳን ውጊያ 6ኛ ቀኑን ይዟል።

በተዋጊዎቹ ኃይሎች መካከል ለ2ኛ ጊዜ ትላንት የ24 ሰዓታት ለሰብዓዊት ተኩስ ለማቆም ሙከራ ተደርጎ የነበር ቢሆንም ሳይሳካ ቀርቶ ውጊያው ቀጥሎ እንደነበር ተሰምቷል።

የተኩስ አቁም እንዲደረግ የተሞከረው ዜጎቻቸውን ከሱዳን ለማስወጣት እየጣሩ ባሉ ሀገራት ግፊት መሆኑን አልጀዚራ ዘግቧል።

ዛሬም በሱዳን የተለያዩ ከተሞች ውጊያ መኖሩ በተለይ በካርቱም የፕሬዜዳንቱ ቤተመንግስት እና የሱዳን ጦር ዋና መስሪያ ቤት አካባቢ ወታደራዊ ግጭት መኖሩ ተመላክቷል።

በርካቶች ያለምግብ፣ውሃ፣ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በቤታቸው ውስጥ ዘግተው እንደተቀመጡ ይገኛሉ።

በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ቤታቸውን ጥለው ከካርቱም እየሸሹ እንደሚገኙ ተነግሯል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የሱዳን ውጊያ 6ኛ ቀኑን ይዟል። በተዋጊዎቹ ኃይሎች መካከል ለ2ኛ ጊዜ ትላንት የ24 ሰዓታት ለሰብዓዊት ተኩስ ለማቆም ሙከራ ተደርጎ የነበር ቢሆንም ሳይሳካ ቀርቶ ውጊያው ቀጥሎ እንደነበር ተሰምቷል። የተኩስ አቁም እንዲደረግ የተሞከረው ዜጎቻቸውን ከሱዳን ለማስወጣት እየጣሩ ባሉ ሀገራት ግፊት መሆኑን አልጀዚራ ዘግቧል። ዛሬም በሱዳን የተለያዩ ከተሞች ውጊያ መኖሩ በተለይ በካርቱም የፕሬዜዳንቱ ቤተመንግስት…
#ሱዳን

" ቤተሰቦቻችን ስላሉበት ሁኔታ ለማወቅ አልቻልንም ፤ጭንቀት ላይ ነን "

በሱዳን እየተካሄደ ያለው ውጊያ ዛሬ 6ኛ ቀኑን መያዙ ይታወቃል።

በሱዳን ያሉ ቤተሰቦቻችን ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅ ካርቱም ወዳለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ስልክ ብንደውልም ምላሽ አላገኘንም ሲሉ እዚህ ኢትዮጵያ የሚገኙ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት መልዕክት ልከዋል።

በሱዳን ያሉ ቤተሰቦቻቸውን ለማግኘት ባለመቻላቸው እንደተጨነቁ የገለፁት እንዚሁ አባላት ፤ ማንን መጠየቅ እንዳለብን ግራ ገብቶናል ይህ ጉዳይ የሚመለከተው አካል ምላሽ ሊሰጠን ይገባል ብለዋል።

ለበርካታ ኢትዮጵያውያን ሁለተኛ ቤት በሆነችው ሱዳን ውስጥ ኢትዮጵያውያን ለስራ እና በቋሚነት ለኑሮ እንደሚገኙ ይታወቃል።

የሰሞኑ የሱዳን ውጊያ ደግሞ እዛ ያሉትን ብቻ ሳይሆን እዚህ ያሉ ቤተሰቦችንም ጭምር ጭንቀት ውስጥ ጥሏል።

ከትላንት በስቲያ በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፤ በሱዳን እየተካሄደ ባለው ውጊያ በርካታ ሲቪሎች ለጉዳት መዳረጋቸውና ህይወትም እየተቀጠፈ መሆኑን በመግለፅ ከእነዚህ መካከል #ኢትዮጵያውያን እንደሚገኙበት መረጃዎች እንደደረሱት አሳውቋል።

ኤምባሲው ምን ያህል ኢትዮጵያውያን እንደሞቱ እና እንደተጎዱ በዝርዝር ባይገልፅም ይህን አስቸጋሪ ጊዜ ለማለፍ ኢትዮጵያዊን የተቻላቸውን ሁሉ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል።

መረጃ ለመለዋወጥ እና ለምክክር የኤምባሲው ባልደረባ የሆኑትን አቶ ነጅብ አብደላ በስልክ ቁጥር +249911646547 ማነጋገር እንደሚቻልም ገልጿል።

@tikvahethiopia
የዒድ አልፈጥር በዓል መቼ ነው ?

የፌዴራል ጠቅላይ ሼሪዓ ፍርድ ቤት ፥ የዒድ አልፈጥር በዓል ጨረቃ ዛሬ ሀሙስ ማታ ከታየች ነገ አርብ ፣ ካልታየች ደግሞ ቅዳሜ ይከበራል ሲል አሳውቋል።

ይህን ያሳወቀው ዛሬ በሰጠው መግለጫ ነው።

1 ሺህ 444ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል ፤ ለኢትዮጵያና ለመላው ዓለም ህብረተሰብ የሰላም፣ የደስታና የፍቅር እንዲሆን መልካም ምኞቱን የገለፀው ሼሪዓ ፍርድ ቤቱ ሙስሊሙ ህብረተሰብ በዓሉን ሲያከብር ያጡና የተቸገሩ ወገኖችን በማሰብና በመርዳት እንዲሆን ጥሪ አቅርቧል።

#ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
ሀሰተኛ መረጃና የጥላቻ ንግግር ሲመለከቱ ምን ያደርጋሉ?

👁‍🗨 ምስላዊ መረጃውን እንደ ዋቢ ይመልከቱ!

#ግራ_ቀኝ
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

RSF የግብፅ ወታደሮችን ለቀይ መስቀል አስረከበ።

የሱዳን ጦርነት በጀመረበት ወቅት በጄነራል መሐመድ ሃምዳን ደጋሎ የሚመራው የሱዳን ፋጥኖ ደራሽ (RSF) ኃይል እንደማረካቸው የገለፃቸውን የግብፅ ወታደሮችን ዛሬ ጥዋት ለዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ማስረከቡን አሳውቋል።

RSF ለቀይ መስቀል ያስረከባቸው የግብፅ ወታደሮች በማራዊ ጦር ሰፈር የነበሩና ላለፉት 5 ቀናት ይዞ ያቆያቸው ናቸው ፤ በቁጥርም 27 እንደሆኑ ተነግሯል።

የሱዳን ጦር በማራዊ ከኤርፖርት ውጭ የነበሩና በRSF ያልተያዙ በቁጥር 177 የግብፅ አየር ኃይል አባላትን ወደ ግብፅ እንዲመለሱ ማደረጉን ማሳወቁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#ሱዳን #ኢትዮጵያ

የሱዳን ጋዜጦች የኢትዮጵያን ጦር የተመለከተ ሀሰተኛ ዜናዎች ሲያሳራጩ ነበር።

የተሰራጨው ዜና ምን ነበር ?

ከትላንት ምሽት ጀምሮ የሱዳን ሚዲያዎች በተለይም በ " አልሱዳኒ ጋዜጣ " የኢትዮጵያ ጦር በሱዳን ላይ ጥቃት ከፍተ የሚሉ ሀሰተኛ መረጃዎች ሲያሰራጩ ነበር።

አል ሱዳኒ ፤ በትናንትናው እለት የኢትዮጵያ ጦር በታንክ፣ በታጠቁ ተሽከርካሪዎች እና በብዙ እግረኛ ወታደሮች በመታገዝ በ " አልፋሽቃ አል-ሱግራ " ላይ ወረራ እና ጥቃት ፈጽሟል ፤ የሱዳን ጦርም ጥቃቱን በመመከተ ከፍተኛ ኪሳራ አድርሷል ሲል ነው ሀሰተኛ መረጃ ያሰራጨው።

ይህንን ዜናም በርካቶች ወዲያውኑ ሲቀባበሉት እና ለብዙሃኑ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ ሲያዳርሱ ነበር።

ይህ መሰል ዜና እንዲሰራጭ ያደረገው የ " አልሱዳኒ " ጋዜጠኛ በትክክለኛ የፌስቡክ ገፁ የተሰራጨው ዜና ትክክል እንዳልሆነ በመግለፅ አንባቢውን ይቅርታ ጠይቋል።

" ዜናው እውነት አይደለም " ያለው ይኸው ጋዜጠኛ " ወረራም አልነበረም ፣ በሱዳንና በኢትዮጵያ ጦር መካከልም ግጭት አልነበረም " ብሏል።

የሰራው ሀሰተኛ ዜና በተፈጠረው ግራ መጋባትና መደናገር እንዳዘነ ይኸው ጋዜጠኛ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ፅፏል።

ሱዳን እጅግ በጣም ሰፊ የኢትዮጵያ መሬትን በኃይል ተቆጣጥራው እንደምትገኝ ይታወቃል። ይህን ያደረገችውም በትግራይ ክልል ጦርነት መነሳቱን እንደ አጋጣሚ በመጠቀም ነበር።

ከዚህ በኃላም ኢትዮጵያ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የድንበር ውዝግብ በጠረጴዛ ዙሪያ በሰላም እና በንግግር መፈታት እንዳለበት በተደጋጋሚ አቋሟን ስትገልፅ ቆይታለች።

ከሰሞኑን በሱዳን የውስጥ ኃይሎች መካከል በተፈጠረው ጦርነት ሳቢያ ሱዳን ከገባችበት ከፍተኛ ትርምስ እንድትወጣ ለማድረግ ኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንደምታደርግ አሳውቃለች።

ግጭት ውስጥ ያሉት የሱዳን ኃይሎችም ግጭት እንዲያረግቡ የሰላም ጥሪ ያቀረበችው ኢትዮጵያ ላለው ችግር አፍሪካዊ መፍትሄ ለመስጠት አዲስ አበባ በሯ ሁሌም ክፍት መሆኑን አቋሟን ገልጻለች።

@tikvahethiopia