TIKVAH-ETHIOPIA
#Oromia " የልዩ ኃይል ስምሪት አቁመናል ፤ ... በክልሉ ያለውን የፀጥታ ማስከበር ሥራ የአገር መከላከያ ሠራዊት ተረክቧል " - የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የኦሮሚያ ክልል መንግሥት የልዩ ኃይል አደረጃጀት ስምሪት ማቆሙን አስታወቀ። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ ከዶይቼ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ ነው ይህንን ያሳውቁት። ዋና ኮሚሽነሩ ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል ፤ የፌዴራሉ…
#Oromia
የክልል ልዩ ኃይሎችን መልሶ የማደራጀት ተግባር መጀመሩን ተከትሎ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የልዩ ኃይል ስምሪት #ማቆሙን ገልጿል።
በክልሉ ያለውን የፀጥታ ማስከበር ስራ የአገር መከላከያ ሰራዊት መረከቡንም አሳውቋል።
የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ጄነራል አራርሳ መርዳሳ ፤ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃለ ምልልስ ነው ይህን ያሉህ።
ኦሮሚያ የሚንቀሳቀሰው መንግሥት " ሸኔ " እያለ የሚጠራውና እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን የመንግሥትን ጥሪ በመቀበል እንቅስቃሴውን የሚያቆም ከሆነ በክልል ሌሎች የፀጥታ ሥራዎች #በመደበኛ_ፖሊስ እንደሚከወኑ ያሳወቁት ጄነራል አራርሳ ለጊዜው ግን የዜጎች ደህንነት አደጋ ላይ እንዳይወድቅ የመከላከያ መከላከያ ሰራዊት ኃላፊነቱን ተረክቧል ብለዋል።
በኦሮሚያ ላይ አሁናዊ የፀጥታ ሁኔታው #አስተማማኝ_እንዳልሆነ ያልሸሸጉት ኮሚሽነሩ በተለያየ ስያሜ በመንቀሳቀስ ኅብረተሰቡን የሚያፈናቅሉ መኖራቸውን ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃለምልልስ ገልጸዋል።
@tikvahethiopia

#Amhara
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) መንግሥት የክልል ልዩ ኃይሎችን በፌዴራልና በክልል መደበኛ የጸጥታ ኃይሎች ውስጥ እንዲካተቱ በማድረግ መልሶ ለማደራጀት ያሳለፈውን ውሳኔና ትግበራ መጀመሩን ተከትሎ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የተነሱ ተቃውሞዎች፣ የጸጥታ መደፍረስ እና በአንዳንድ አካባቢዎች የደረሱ ግጭቶችንና ጉዳቶችን በተመለከተ ክትትል እያደረገ እንደሚገኝ ገልጿል።
በተለይም፦
- በቆቦ፣
- በባሕር ዳር፣
- በወረታ፣
- በኮምቦልቻ፣
- በደብረ ብርሃን እና በመራዊ የተቃውሞ ሰልፎች፣ መንገድ መዘጋት፣ የአገልግሎት መቋረጥ እንዲሁም በጸጥታ ኃይሎች መካከል ፍጥጫዎች የተከሰቱ ሲሆን፤ በአንዳንድ አካባቢዎች ግጭቶች በጸጥታ ኃይሎች በተወሰዱ እርምጃዎችና ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች የተፈጸሙ ጥቃቶች የሰብአዊ እርዳታ ድርጅቶች ሠራተኞችን ጨምሮ የሲቪል ሰዎች ሞት እና የአካል ጉዳት ማስከተሉን ኢሰመኮ አሳውቋል።
በሌላ በኩል በእነዚህ ከተሞችና ሌሎችም አካባቢዎች በተፈጠረው ውጥረት፣ አለመረጋጋት፣ የአገልግሎት መቋረጥ እና የእንቅስቃሴ እገዳዎች ምክንያት በነዋሪዎች የዕለት ተዕለት ኑሮ እና ሥራ ላይ እንቅፋት መፈጠሩን አመልክቷል።
አጠቃላይ ችግሩና የጸጥታው ሁኔታ አስቸኳይ እልባት ካላገኘ ለከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ሥጋት በመሆኑ ፦
➤ ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት ጉዳዩን በምክክርና በመግባባት እንዲፈቱ፣
➤ በተለይም አጠቃላይ የፖለቲካ ነባራዊ ሁኔታው የፈጠረውን ሥጋትና የአለመተማመን ስሜት ከግምት በማስገባት መንግሥት የፖሊሲ ውሳኔውን አስፈላጊነትና ጠቀሜታ ለሚመለከታቸው ሁሉ በትዕግሥትና በጽሞና የሚያስረዳበትን ሁኔታ እንዲያመቻች፣
➤ የጸጥታ አካላት ያልተመጣጠነ እና ሕይወት የሚያጠፋ ኃይል ከመጠቀም እንዲቆጠቡ፣
➤ መንግሥት ስለደረሰው ጉዳት ሁሉ አስፈላጊውን ምርመራ በማድረግ ተጠያቂነት እንዲያረጋግጥ እንዲሁም ሁሉም ሰው ሐሳቡን በሕጋዊና ሰላማዊ መንገድ ብቻ እንዲገልጽ ኢሰመኮ ጥሪውን አቅርቧል።
ኢሰመኮ ከመደበኛው የክትትል እና ምርመራ ሥራው ጎን ለጎን ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት በሙሉ በማነጋገር እና ምክረ ሐሳቦችን በመስጠት የተፈጠረው ችግር በውይይት እንዲፈታ ጥረት በማድረግ ላይ የሚገኝ መሆኑን ገልጿል።
ምንጭ፦ ኢሰመኮ

" የተከሰተው ችግር #በውይይት_ተፈቷል ፤... የሰላም #ስምምነትም ተደርጓል " - የሰ/ ወሎ ዞን አስተዳደር
የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር ፤ ከሰሞኑን ከክልል ልዩ ሀይል መልሶ ማደራጀት ጋር ተያይዞ ተከስቶ የነበረው የፀጥታ ችግር በውይይት መፈታቱን ዛሬ ምሽት አሳውቋል።
የፀጥታ ችግሩን ለመፍታት በሐይማኖት አባቶች፣ በአገር ሽማግሌዎችና በዘወልድ ሽምግልና ስርዓት የሠላም ስምምነት ተደረጓል ብሏል።
በሰላም ስምምነት ስነስርዓቱ ላይ ፦
- የአገር መከላከያ ሠራዊት ፣
- የክልል ፣ የዞን ፣ አመራሮች
- የምስራቅ አማራ ፋኖ አመራሮች
- የአገር ሽማግሌዎች የሰላም ስምምነቱን አስመልክተው መግለጫ መስጠታቸውንም የዞን አስተዳደሩ አመልክቷል።
ስምምነቱን በተመለከተ የሰ/ወሎ ዞን አስተዳደር ለህዝብ ያሰራጨው መረጃ #ከላይ ተያይዟል።
NB. ውድ ቤተሰቦቻችን በዚህ የሰ/ወሎ ዞን አስተዳደር መግለጫ ዙሪያና ስምምነቱ ዙሪያ ከፋኖ አደረጃጀት አመራሮች ዘንድ የሚሰጥ አስተያየት ካለ ተከታትለን የምናሳውቅ ይሆናል።

Photo
#Update
የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር ፤ ከሰሞኑን ከክልል ልዩ ሀይል መልሶ ማደራጀት ጋር ተያይዞ ተከስቶ የነበረው የፀጥታ ችግር በውይይት፣ በመግባባት መፈታቱን አሳውቋል።
ከዚህ ስምምነት በኃላ የፋኖ አባላቱ ምንድነው ያሉት ?
ፋኖ ምሬ ወዳጁ ፦
" ያላሰንብነው መከላከያ ጋራ የሆነ accident ተፈጠረብን፤ መከላከያ ማለት በዚህ ትግል ላይ ብዙ አስተዋጽኦ ያደረገ እጅግ የምንወደው የምናከብረው ወደፊትም ቢሆን አገር ነው ተቋም ነው።
ይሄ በተደረገው በዚህ ሰበብ በጠፋብን ህይወት በተለያየ ቦታ እጅግ አዝነናል እኛም ያጣናቸው ጓዶች አሉ የመከላከያም ተመሳሳይ ይሄን ባለው በሀገር ሽማግሌ፣ በሃይማኖት አባት በሁሉም ተደራድረን ፥ ይሄን ያደረግንበት ምክንያት ምንድነው ጠላት ሲደሰት ስላየሁት ነው ፤ አባት የሌለበት ሀገር ሽማግሌ የሌለበት ሀገር ሀገር አይደለም ብለን እናስባለን።
ስለዚህ የሃይማኖት አባቶች የሀገር ሽማግሌዎች ለሀገር ትልቅ ባለውለታ ናቸውና ደም ከመፋሰስ ከግጭት ሳይደረስ የሀገር ችግሮች በእነደዚህ አይነት አባቶች ይፈታሉ።
አሁን በሰላም ቦታ ውለናል ወደፊትም የእየተማከርን ነገሮችን እንድንፈታ መልዕክታችን ነው። "
ሌላ ቃሉን የሰጠ የፋኖ አባል አበበ ፈንታው ተከታዩን ተናግሯል ፦
" ድንገት በጊዜያዊ አለመግባባቶች የተፈጠሩ ሁኔታዎች ናቸው። ከግጭቱ ምንም የተተረፈ ነገር የለም።
ከዛ አንፃር የነበረውን የተፈጠረውን ችግር በሀገር ሽማግሌ ፣ በሃይማኖት አባቶች በታዋቂ ግለሰቦች አጠቃላይ እንደ ህዝብ በሽምግልና ጠንካራ የሆነ የሽምግልና ስርዓት ስላለ እኛንም ያለንበት ቦታ በየተራራው ድረስ መጥተው የሃገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች ባሉበት ሄደው ሽማግሌዎች አቀራርበውን የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ደርሰናል።
በዚህ አጋጣሚ የሀገር መከላከያ ሰራዊት የሁላችንም ዋስትና ጠበቃ ነው ከፈጣሪ በታች ፤ የሀገር መከላከያ ሰራዊታችን ላይ በተፈጠረው ድንገተኛ ችግር ብዙ ጓዶች በግራም በቀኝም በሁላችንም ጠፍተዋልና ለዚህ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን እንደተቋም ትልቅ ይቅርታ መጠየቅ እንፈልጋለን።
የአማራ ህዝብ ብዙ ጥያቄዎች ያሉት ህዝብ ነው ፤ ከዛ አንፃር ወደፊትም ግጭቶች ሊኖሩ ይችላሉ ብዬ አስባለሁ ግን እነዚህን ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ በውይይት ልክ አሁን እንደፈታነው በቀጣይ በዛ መንገድ መፈታት አለባቸው አሁንም በዘላቂነት ጥያቄዎችን መንግሥት መፍታት አለበት። "
ሊንክ ፦ https://www.youtube.com/live/r17AHZmGQa4?feature=share

#Update የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር ፤ ከሰሞኑን ከክልል ልዩ ሀይል መልሶ ማደራጀት ጋር ተያይዞ ተከስቶ የነበረው የፀጥታ ችግር በውይይት፣ በመግባባት መፈታቱን አሳውቋል። ከዚህ ስምምነት በኃላ የፋኖ አባላቱ ምንድነው ያሉት ? ፋኖ ምሬ ወዳጁ ፦ " ያላሰንብነው መከላከያ ጋራ የሆነ accident ተፈጠረብን፤ መከላከያ ማለት በዚህ ትግል ላይ ብዙ አስተዋጽኦ ያደረገ እጅግ የምንወደው የምናከብረው…
#ENDF
የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ም/አዛዥ ሜጄር ጄነራል ብርሃኑ ጥላሁን በሰሜን ወሎ ስለተደረሰው የሰላም ስምምነት ምን አሉ ?
" ይሄ ችግር መረገብ አለበት። ለማንም ለምንም አይጠቅምም ፤ አሁን ደግሞ ችግር በውይይት ነው መፍታት የምትችለው ወይስ በጠብመንጃ ነው በጠብመንጃ የፈቱ ሀገሮች የትም የሉም። ህይወት ጠፋ ስለዚህ ሌሎችም ቢሆን ረጋ ብለው ይዩ ሁኔታውን ትክክል አይደለም ፤ በስተጀርባ ያለውን በትክክል ማየት አለባቸው።
ይሄ ግጭት ፤ ይሄ ንትርክ፣ ይሄ በየመንገዱ የነበረውን ሁከት ያቆመው ማንም አይደለም የሀገር ሽማግሌ መሃል እየገባ ነው ያቆመው ነፍሥ እንዳይጠፋ፣ ህፃናት እንዳይጎዱ ፣ የመንግስት እና የግል ንብረት እንዳይወድም ፣ ቤት እንዳይቃጠል ፣ ወንጀለኛ ያለአግባብ ተፈቶ እንዳይወጣ ከፍተኛ ስራ የሰራው የሀገር ሽማግሌ ነው።
ሌላው እዛ ያለው የፀጥታ ኃይልም ከሀገር ሽማግሌ ጋር ሆኖ መስራት አለበት ፣ ችግሩን ማስረዳት አለበት።
ሀገርን የሚጠቅም፣ ህዝብን የሚጠቅም መመሪያ ነው የወረደው ስለዚህ ያልተረዱና በጀርባ ሌላ መልክ የሚሰጡ ሰዎች ግፊት የተፈጠረ ችግር አሁን ህብረተሰቡ በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ነው ያለው ስለዚህ ይሄንን ለመፍታት የመንግስትን መመሪያ ለማክብረ ተስማምተናል ከነሱ ጋር።
ሌላው በእነሱ ላይ ሲደርስ የነበረው ችግር፣ በእኛ ላይ አንዳንድ ነገሮች ይስተካከልልን የተባለው በሙሉ መንግሥት / የክልሉ መንግሥት ያደርጋል።
ስለዚህ ይሄን በተለየና በተጣመመ መንገድ የሚረዱ ሰዎች ትክክለኛ ባልሆነ መንገድ ነው እየቃኙ ያሉት ይሄ እንዲስተካከል ነው ጥረት ያደረግነው ፤ ችግሩን ለመፍታት በትዕግስት መከላከያ እየሞተም ቢሆን ለማስተካከል ጥረት አድርጓል ፣ ዛሬ ተሳክቶልናል። "

#ERC
" በባልደረቦቼ እና በአምቡላንስ ላይ የተፈፀመውን ጥቃት በፅኑ አወግዛለሁ፤ ታጣቂ ሃይሎች ከመሰል ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እማፀናለሁ " - የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የሰሜን ጎንደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አምቡላንስ ሾፌርና አዋላጅ ነርስ ላይ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂ ኃይሎች ጥቃት መፈፀሙን ገልጿል።
ማህበሩ ጥቃቱን በአፅኖት አውግዟል።
የማኅበሩ አምቡላንስ ሾፌር እንዲሁም አዋላጅ ነርስ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ በለሳ ወረዳ አይባሽካ ቀበሌ ሚያዝያ 01 ቀን 2015 ዓ.ም ምሽት 2፡30 ሰዓት በምጥ የተያዘች እናትን ከመኖሪያ ቤቷ ወደ ጤና ተቋም ለማድረስ ወደ ቤቷ እያመሩ እያለ ነበር ጥቃቱ የተፈፀመባቸው፡፡
በተፈፀመው ጥቃት ከሠራተኞቹ በተጨማሪ በአምቡላንስ ተሸከርካሪው ላይም ጉዳት ደርሷል፡፡
የአምቡላንስ ሾፌሩና አዋላጅ ነርሱ በጥቃቱ በደረሰባቸው ጉዳት ምክንያት በአሁኑ ወቅት በጎንደር ሪፈራል ሆስፒታል እና በምስራቅ በለሳ ወረዳ ጓላ አንደኛ ደረጃ ሆስፒታል ህክምናቸውን በመከታተል ላይ እንደሚገኙ ማህበሩ አሳውቋል።
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በመላው ሀገራችን በሰብዓዊ አገልግሎት የተሰማሩ የቀይ መስቀል ሠራተኞችና በጎፈቃደኞች ሰብዓዊ ተግባራቸውን በገለልተኝነት እና በአለማዳላት መንፈስ በነፃነት ተንቀሳቅሰው መስራት እንዲችሉ፣ እንዲሁም ደህንነታቸው እንዲጠበቅ፣ ታጣቂ ሃይሎች ከእንደዚህ አይነት ጥቃት እንዲቆጠቡ ተማፅኗል።