TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" የአማራ እና የትግራይን ህዝብ ወንድማማችነት ለማስቀጠል በቁርጠኝነት እንሰራለን " - ዶ/ር ይልቃል ከፋለ

የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ፤ የሚያጋጥሙንን የፖለቲካ ልዩነቶችን በውይይት በመፍታት የአማራ እና የትግራይን ህዝብ ወንድማማችነት ለማስቀጠል በቁርጠኝነት እንሰራለን አሉ።

ይህን ያሉት ለክልሉ ሚዲያ አሚኮ በሠጡት ቃለ ምልልስ ነው።

ዶ/ር ይልቃል ፥ የተፈጠረውን የሰላም ስምምነት ወደ ህዝብ ለህዝብ ግንኙነት በማሳደግ ተደጋግፈን ከችግራችን የምንወጣበትን መንገድ ማመቻቸት አለብን ብለዋል።

" የፖለቲካ ልዩነትን በውይይት ከመፍታት ይልቅ ጦርነትን አማራጭ ማድረግ መፍትሄ አልባ ኪሳራ እንደሚያደርስ አስተምሮናል " ያሉት ዶ/ር ይልቃል ቀድሞውኑ ችግሮች በሰላማዊ መንገድ ተፈተው ቢሆን ፣ በውይይት እና ድርድር ተፈተው ቢሆን ፣ በሽምግልናና በሰለጠነ አግባብ ተፈተው ቢሆን ይህ ሁሉ ችግር እና ምስቅልቅል በሀገሪቱ ላይደርስ ይችል ነበር ሲሉ ገልጸዋል።

ዶ/ር ይልቃል ፤ ጦርነት ከሰብዓዊ እና ቁሳዊ ጉዳት ባለፈ ስነልቦናዊ ስብራትን እንደሚያስከትል የአማራ እና ትግራይ ህዝብ በተግባር አይተዋል ያሉ ሲሆን " የአማራ ክልል ህዝብ የትግራይ ህዝብ ወንድሙ እንደሆነ ድሮም አብሮ ይኖር ነበር ወደፊትም ቢሆን አብሮ ለመኖር የተዘጋጀ ህዝብ ነው ፤ ከወንድሙ ጋር የሚያጋጥመውን ችግር በሰላም እና በድርድር ለመፍታት ነው የሚዘጋጀው የሚያስበው። የትግራይ ክልል ከኛ የሚጠይቀው ጉዳይ ካለ በሰላም በውይይት ፣ ከዚያም ባለፈ በህግ መፍታት እንችላለን ይሄን የሰለጠነ መንገድ ሁላችንም ተቀብለን መፈፀም አለብን " ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ ጦርነቱ የፈጠረውን ቁስል በሚያክም መንገድ መግባባት ፣ መገናኘት እንደ አንድ ሀገር ዜጋ እንደ ወንድም እና እህት ማህበረስብ መተሳሰብ ይገባናል ብለዋል።

" በዚህም ረገድ የአማራ መንግስትም ሆነ የአማራ ህዝብ የትግራይ ህዝብ የኔ ወንድም እና እህት ነው ብሎ የሚያስብ በችግሩ ጊዜ የሚደርስ በመሆኑ በዚያ መንፈስ ነው የምናየው ፤ ሰላም አብሮነትን የሚያፀና ፣ የሚያጠናክር ይሆናል ብለን እምነት እናደርጋለን " ሲሉ አክለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
36 የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ተፈተዋል።

በወንጀል ተጠርጥረው ክሥ ቀርቦባቸው የነበሩ የህወሓት ሲቪል እና ወታደራዊ አመራሮችን ክሥ ማቋረጡን የፍትሕ ሚኒስቴር ከአስታወቀ በኋላ እነ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፣ ዶ/ር አዲስአለም ባሌማ፣ ዶ/ር አብርሃም ተከስተን ጨምሮ 36 ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ ሃሙስ መጋቢት 21 ቀን 2015 ዓ.ም ከእስር ተለቀዋል።

ከጠበቆቻቸው አንዱ የሆኑት አቶ ሀፍቶም ከሠተ ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃል ፤ ከእስር ተፈቺዎቹ፣ በማረሚያ ቤት መኪኖች፥ ሳሪስ፣ ፒያሳ እንዲሁም ሲኤምሲ ወደሚገኙ ቤተሰቦቻቸው እንደተሸኙና ቤተሰቦቻቸውም አቀባበል እንዳደረጉላቸው ገልጸዋል፡፡

በዛሬው ዕለት ከእስር የተፈቱት 16ቱ የህወሓት የሲቪል እና ወታደራዊ ባለሥልጣናት፣ ላለፉት ሁለት ዓመታት በዶ/ር ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል የክሥ መዝገብ ሥር እንደነበሩ ጠበቃው ገልጸዋል።

በሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ የክሥ መዝገብ ሥር ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ሲታይ የቆየው 20 ተከሣሾች እንደሆኑም ጠበቃው ለሬድዮ ጣቢያው ጠቅሰዋል።

Photo : File

@tikvahethiopia
አቶ ዶሪ አስገደሞ ከእስር ተፈተዋል።

የዓሲምባ ዴምክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ዶሪ አሰገዶም ዛሬ መጋቢት 21 ቀን 2015 ዓ/ም ከእስር መለቀቃቸውን ለማወቅ ተችሏል።

አቶ ዶሪ አስገዶም ለሁለት ዓመት ያህል ከቆዩበት እስር ነው የተፈቱት።

@tikvahethiopia
#ExodusPhysiotherapy

በኤክሶደስ የፊዚዮቴራፒ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ የምንሰጣቸው የህክምና አገልግሎቶች ፦ ለአንገት ፣ ለትክሻ ፣ ለወገብ ህመም ፣ ከዲስክ መንሸራተት ጋር በተያያዘ ለሚመጣ ችግር ፣ ለማዞር ወይንም ሚዛን የመጠበቅ ችግር ፣ ለፊት መጣመም፣ ከስትሮክ በኋላ ለሚመጣ ግማሽ የሰውነት ክፍል መዛል ፣ ለስፖርታዊ ጉዳቶች፣  ከህፃናት የእድገት ውስንነት ጋር በተያያዘ ለሚከሰቱ የእንቅስቃሴ ችግሮች ፣ በአጠቃላይ ከነርቭ ፣ ከጡንቻ ፣ ከመገጣጠሚያ ጋር በተገናኘ ለሚከሰቱ ችግሮች መፍትሄ ያግኙ ይዳኑ !

የስራ ሰዓት ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ     #ከጠዋቱ 2:30 እስከ #ምሽት 1:00 ሰዓት

አድራሻችን ፦ 22 ከመክሊት ህንፃ ፊት ለፊት ባሮ ህንፃ ላይ እንገኛለን፤ ስልክ 0979099909/ 0911039377

በቴሌግራም ቻናላችን ጠቃሚ መረጃ ያግኙ
https://t.iss.one/ExodPhysioClinic
TIKVAH-ETHIOPIA
የቀጠለው የቤት ማፍረስ ዘመቻ ... በአዲስ አበባ ዙሪያ ከሚደረግ የቤት ማፍረስ ዘመቻ ጋር በተገናኘ ቤት የፈረሰባቸው ዜጎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የተናገሩት ፦ • " ... #ቤት_ለመፈለግ እንኳን በቂ ጊዜ አልተሰጠም በዚህም እቃችንን ወደ ምናውቃቸው ሰዎች አሽሽተናል ፤ መጠለያ አጥተው ሜዳ ላይ የወደቁም ጎረቤቶችም አሉ። ቤት ለመከራየት እንኳን የቤት ኪራይ በዚህ ምክንያት ጨምሯል።" • " የዚህኛው…
የቤት ማፍረስ ዘመቻው ቀጥሏል።

አዲስ በተመሰረተው ሸገር ከተማ አሁንም የቤት ፈረሳ ዘመቻው መቀጠሉን የየአካባቢው ነዋሪዎች እየገለፁ ይገኛሉ።

መንግሥት ቤቶችን እያፈረሰ የሚገኘው " ህገወጥ ነው " በሚል እንደሆነ ከዚህ ቀደም ገልጿል።

ቤት እየፈረሰባቸው ያሉ ወገኖች ስለጉዳዩ ምን ይላሉ ?

⮕ በርካታ ቤቶች ናቸው እየፈረሱ ያሉት፤ እነዚህ ቤቶች ከገበሬ የተገዙ እና ረጅም ዓመታት ጭምር ሰዎች ሲኖሩባቸው የነበሩ ናቸው።

⮕ ከፈረሱት ቤቶች ውስጥ ዜጎች ለዓመታት ለፍተው የሰሯቸው ይገኙበታል።

⮕ ምትክ ቦታ/ ማረፊ ሳይመቻች ነው ሜዳ ላይ የተጣልነው።

⮕ መንግስት ዛሬ ላይ ህገወጥ ነው እያለ የሚያፈርሰው ቤቶቹ ሲገነቡና ይህን ሁሉ ዓመት ሲኖርባቸው የት ነበር ?

⮕ በአንዳንድ ቦታዎች ቤት የሚፈርሰው በለሊት ጭምር ነው፤ ሰዎች በተኙበት ምንም ሳይዘጋጁ እንዲፈርስባቸው ይደረጋል።

⮕ እየፈረሱ ካሉት ቤቶች መካከል አንዳንዶቹ የመብራት የውሃ ክፍያ፣ የአፈር ግብርም የፈፀሙ ናቸው።

⮕ ከቤት ማፍረስ ዘመቻው ጋር በተያያዘ አንዳንድ ቤቶችን ማንነትን/ ብሔርን ለይቶ ማፍረስም ይስተዋል።

⮕ የሰብዓዊነት ጉዳይ ጭራሽ ከምንም የማይቆጠርበት ሁኔታ ነው እየተፈጠረ ያለው ፤ ነፍሰ ጡር እና በእድሜ የገፉ እናቶች እንዲሁም ህፃናትን ጨምሮ በርካቶች #ሜዳ ላይ ወድቀዋል። እቃ እንኳን እንዳይወጣ ላያቸው ላይ ቤታቸው ፈርሷል።

ስለሚፈርሱ ቤቶች ከዚህ ቀደም የከተማው ከንቲባ ዶ/ር ተሾመ አዱኛ ምን ምላሽ ሰጥተው ነበር (አንከር ለተሰኘ ሚዲያ)?

➣ የሚፈርሱት ለአንድ ከተማ ፀር የሆኑ ህገወጥ ግንባታዎች ናቸው።

➣ ህገወጥ ግንባታዎችን እናፈርሳለን ህጋዊ ከተማ መልክ እንዲይዝ እናደርጋለን።

➣ በአስተዳደር ችግር ፣ ጠንካራ የሆነ አስተዳደር በፊት አለመኖር ምክንያት የግንባታ እና የመሬት ባለቤትነት፣ የግንባታ ፍቃድ ሳይኖር መብራት ማውጣት ይሄ ስራ አሁን ከሚፈለገው የከተማ ሂደት ጋር የማይሆኑ ነገሮች ነው የተፈጠሩት እነሱ በመኖራቸው አይፈርሱም የሚል ሳይንስ የለም። አንድ ሰው በስርዓት ካርታ መውሰድ አለበት፣ በስርዓት የግንባታ ፍቃድ ማግኘት አለበት፣ የክልሉ ህግና ስርዓት ጠብቆ መሄድ አለበት እነዚህ ሳይሟሉ በራሳችን መዋቅር ድክመት / አሰራር መብራት ስላልስገባ / ውሃ ስላስገባ የማይፈርስ የለም። ያ እንደጥፋት የምናየው ከአሁን በኃላ መደገም የለበትም።

➣ ሰብዓዊነት እኛም ይሰማናል መታየት ያለበት ግን ህግ መከበር አለበት፤ እኛ ይሄንን ከጨረስን በኃላ በክልል ደረጃም ይሁን በከተማ ደረጃ አንድ ሰው ቤት ማግኘት ሰብዓዊ መብቱ ስለሆነ እኛ በምናወጣቸው ፕሮግራሞች አካተን ያለውን ችግር መፍታት እንችላለን።

➣ የምናፈርሰው ግልፅ የሆነ አንድ ዘመናዊ ከተማ ላይ እንቅፋት ሊሆኑ የሚችሉ ሁኔታዎችን ታሳቢ በማድረግ ነው። ከእንቅፋቶቹ አንዱ ከቁጥጥር ውጭ የሆነ የመሬት ወረራ እና ህገወጥ ግንባታዎች ነው ይሄን መሰረት አድርገን ነው የምንሄደው (የግንባታ ፍቃድ የሌላቸው፣ በስርዓት መሬት ያልወሰዱ፣ ካርታ የሌላቸው) ይሄን ነው የምንከተለው ፈረሳው ብሄርን / ዘርን መሰረት ያደረገ አይደለም። ማንንም ዒላማ አድርገን አይደለም የምንሰራው።

➣ ቅደመ ማስጠንቀቂያ ይሰጣል ፣ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ብቻ ሳይሆን ማህበረሰቡን አወያይተን ፣ ህገወጥ እንዳሆኑ ነገረን ፣ ህገወጥ ያደረጋቸው ምን እንደሆነ አስረድተን፣ ምልክት አድርገን ነው የምናፈርሰው ፤ በእኛ ሀገር ' ቤት ሰባቴ ካልፈረሰ ቤት አይሆንም ' የሚል የማይሆን አመለካከት ስላለ በአንድ በኩል አያፈርሱም ብለው ያስባሉ ቢፈርስም ትንሽ ዞር ሲሉ መልሰን እንገባበታለን የሚል ነገር አለ ስለዚህ እየነገርን እየታወቀ ነው ፈረሳው የሚደረገው።

@tikvahethiopia
" ክስ መቋረጥን ተከትሎ ከእስር የመፍታት ስራ ተጀምሯል " - አቶ ጌታቸው ረዳ

በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራ የልዑካን ቡድን አዲስ አበባ ውስጥ ከፌዴራል መንግስት ጋር እየመከረ ይገኛል።

ቡድኑ ከፌዴራል መንግስት ጋር እየተወያየ የሚገኘው በትግራይ መልሶ ማቋቋም እና ሌሎች ወሳኝ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ስለመሆኑ ተነግሯል።

ከዚህ ባለፈ ልዑኩ በአዲስ አበባ ካሉ የትግራይ ተወላጅ የንግድ ማህበረሰብ ጋር የተወያየ ሲሆን የትግራይ ተወላጆች ትግራይን መልሶ ለመገንባት እና ሁለንተናዊ ችግሯን በመቅረፍ የበኩላቸውን ለማበርከት " ዝግጁ ነን " ብለዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ በዚሁ መድረክ ላይ የሲቪል እና ወታደራዊ አመራሮች ክስ መቋረጥን ተከትሎ ከእስር የመፍታት ስራ መጀመሩን አሳውቀዋል።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ልዑክ ከፌዴራል መንግሥት ጋር የሚያደርገው ምክክር መቀጠሉን የክልሉ ቴሌቪዥን / ትግራይ ቲቪ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
" ለመምህራንና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች የመጋቢት ጨምሮ የ4 ወራት ደምወዝ ተከፍሏል " - ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ

ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ስራ ለመጀመር የሚያስችለው የዩኒቨርሲቲ ካዉንስል ስብሰባ ትላንት በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ አከናውኖ ነበር።

በተለያየ ደረጃ የሚገኙ የዩኒቨርሲቲው አመራር አባላት ባካሄዱት ውይይት ስራ ለመጀመር የሚያስችል የሶስት ወራት እቅድ ስለማዘጋጀት አስፈላጊነት ስምምነት ተደርሶበታል።

በውይይቱ ወቅት በየደረጃው የተቀናጀ ጥረት በማድረግ ዩኒቨርሲቲው በአጭር ጊዜ ውስጥ ተማሪዎችን መልሶ ለመቀበል ወደሚችልበት ደረጃ ማድረስ እንደሚቻል ግንዛቤ ተወስዷል።

ለዚህም ይረዳ ዘንድ ሁሉም ኮሌጆች፣ ትምህርት ክፍሎች፣ ዳይሬክተሮችና ሌሎች ፅ/ቤቶች መደበኛ ስራቸው እንዲጀምሩ መመርያ ተሰጥታል።

ዩኒቨርሲቲው ለመምህራንና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች የመጋቢት ጨምሮ የአራት ወራት ደምወዝ የከፈለ መሆኑ ለማወቅ ተችሏል።

#AdigratUniversity

@tikvahethiopia