TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.1K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ቲክቶክ

ካናዳ ከዛሬ ጀምሮ መንግሥት በገዛው ‘ኤሌክትሮኒክስ’ ቁሳቁስ #ቲክቶክ መጠቀም ክልል መሆኑን አሳውቃለች።

በዚህ ሳምንት መንግሥት ገዝቶ ለሠራተኞች ካደላቸው ተንቀሳቃሽ ስልኮች ውስጥ ቲክቶክ ይጠፋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ፤ መተግበሪያው ለመረጃ ደኅንነት አስጊ እንደሆነ ጠቋሚ ፍንጮች ስላሉ ነው ውሳኔው የተላለፈው ብለዋል።

የቲክቶክ ቃለ አቀባይ በካናዳ መንግሥት ውሳኔ ኩባንያው እንደተከፋ ገልጠዋል።

ቲክቶክ ይህን ውሳኔ ተከትሎ ባወጣው መግለጫ የካናዳ መንግሥት ኩባንያውን ሳያማክር አሊያም በቂ ማስረጃ ሳይኖረው ይህን ማድረጉ አሳዛኝ መሆኑን ገልጧል።

* የአውሮፓ ኮሚሽን

ከቀናት በፊት የአውሮፓ ኮሚሽን ተመሳሳይ ውሳኔ አሳልፏል። የአውሮፓ ሕብረት ኮሚሽን ሠራተኞች ከመጋቢት 15 ጀምሮ ቲክቶክን በኮሚሽኑ ንብረት መጠቀም አይችሉም ሲል ነው ውሳኔ ያሳለፈው።

* አሜሪካ

ባለፈው የፈረጆቹ ዓመት የአሜሪካ የፌዴራሉ መንግሥት ሠራተኞች ቲክቶክን እንዳይጠቀሙ ተከልክለዋል።

ትላንት ዋይት ሐውስ የመንግሥት መ/ቤቶች በሚቀጥሉት 30 ቀናት ከኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎቻቸው ቲክቶክን #እንዲያስወግዱ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

በርካታ የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች መተግበሪያውን ከኔትዎርኮቻቸው ላይ አስወግደውታል።

* ሕንድ

ሕንድን ጨምሮ በሌሎች የእስያ ሃገራት የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በቲክቶክ ላይ ተመሳሳይ እርምጃ እየወሰዱ ነው።

#ቲክቶክ

ቲክቶክ ባይትዳንስ የተሰኘው ኩባንያ ንብረት ነው።

መተግበሪያው ግላዊ መረጃን በመበዝበዝ ከፍተኛ ወቀሳ የሚደርስበት ሲሆን ከቻይና መንግሥት ጋር ግንኙነት አለው በሚልም ስሙ ይነሳል።

ኩባንያው የቻይና መንግሥት መረጃውን እንደማያገኝበትና ቻይና ያለው ቲክቶክ ከሌላው ዓለም ፈፅሞ የተለየ መሆኑን ደጋግሞ አሳውቋል።

#ቢቢሲ

@tikvahethiopia