TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ትምህርት_ሚኒስቴር || በየትኛውም መማርያ መጽሀፍት ላይ የኢትዮጵያ ካርታ ስራዎች መስሪያ ቤት ከሚሠጠው ካርታ ውጭ ለማስተማሪያነት እንደማይውል የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል። በተለያዩ የክፍል ደረጃዎች የሚገኙ ካርታዎች ለተማሪዎች ትክክለኛውንና ማወቅ የሚገባቸውን ካርታ በማሣየት ረገድ ችግሮች መታየታቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጥላዬ ጌቴ ተናግረዋል። በመሆኑም በሁሉም የትምህርት ዘርፍ የሚሠሩ አካላት በኢትዮጵያ ካርታ ሥራዎች የሚዘጋጁ #ካርታዎችን ብቻ ለማስተማሪያነት መጠቀም እንዳለባቸው ሚኒስትሩ አሳስበዋል፡፡ 29ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

Via #AMN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ትምህርት ሚኒስቴር ፦ በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለአንድ ሳምንት ይዘጋሉ። ዝግ የሚሆኑት ከህዳር 27 እስከ ታህሳስ 3 ቀን 2014 ዓ/ም ድረስ ነው። #ምክንያት ፦ መምህራን ፣ ተማሪዎች፣ ሰራተኞች ለሀገራዊ ትግል እንደየአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ነው። ት/ቤቶች ዝግ ሆነው በሚቆዩባቸው ቀናት ያልተሰበሰቡ የዘመች ሰብል መሰብሰብ እና ቤተሰብን የመርዳት…
#ትምህርት_ሚኒስቴር

በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከነገ ህዳር 27 ጀምሮ እስከ ታህሳስ 3 ድረስ ለአንድ ሳምንት ይዘጋሉ።

እንደ ትምህርት ሚኒስቴር መረጃ መምህራን ፣ ተማሪዎች፣ ሰራተኞች ለሀገራዊ ትግል እንደየአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ አስተዋጽኦ ያድረጋሉ።

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ዝግ ሆነው በሚቆዩባቸው ቀናት ያልተሰበሰቡ የዘመች ሰብል መሰብሰብ እና ቤተሰብን የመርዳት ዘመቻዎች በስፋት ይካሄዳል።

@tikvahethiopia
#ትምህርት_ሚኒስቴር

ከዛሮ ጀምሮ መረጃችሁን ሙሉ ፦

👉በመቐለ፣
👉በዓዲግራት፣
👉በኣክሱም፣
👉በራያ እንዲሁም ወልዲያ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን በሁለተኛ እና ሶስተኛ ዲግሪ በመደበኛ ፕሮግራም ሲከታተሉ ለነበሩ ተማሪዎች ምደባ ለመስጠት ተማሪዎች መረጃቸውን እንዲሞሉ የትምህርት ሚኒስቴር ጠይቋል።

ከዚህ ቀደም የተሰበሰበ መረጃ መሰረት በማድረግ ተማሪዎቹ ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች በጊዜያዊነት ለመመደብ ሲሰራ መቆየቱን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ይሁን እንጂ ተማሪዎችን ለመመደብ ተጨማሪ መረጃዎችን መሰብሰብ አስፈላጊ መሆኑን ሚኒስቴሩ ጠቁሟል።

በመሆኑም ተማሪዎቹ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥር 21/2014 ዓ.ም ድረስ ከዚህ በታች ባለው ቅጽ መሰረት መረጃቸውን እንዲሞሉ አሳስቧል።

መመዝገቢያ አድራሻ👇
forms.gle/Ksfm9kPCJunAx2xR6

@tikvahuniversity @tikvahethiopia
#ትምህርት_ሚኒስቴር

" በሁሉም ክልሎች በችሎታቸው የተመረጡ ተማሪዎች የሚማሩባቸው 50 ትምህርት ቤቶች ይገነባሉ " - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

ትምህርት ሚኒስቴር በሁሉም ክልሎች በችሎታቸው የተመረጡ ተማሪዎች የሚማሩባቸው 50 ትምህርት ቤቶች እንደሚገነቡ አሳወቀ።

ትምህርት ቤቶቹ የ8ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱና በችሎታቸው የተመረጡ ተማሪዎች የሚማሩባቸው ናቸው ተብሏል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) በሁሉም ክልሎች በዓይነታቸው ልዩ የሆኑና የልህቀት ማዕከል የሚሆኑ 50 ትምህርት ቤቶች ይገነባሉ ብለዋል።

ት/ ቤቶቹ ቀጣይ የአገር መሪ የሚሆኑ ብቁና ተወዳዳሪ ተማሪዎች የሚፈልቁበት በችሎታቸው ብቻ የሚመረጡ ተማሪዎች የሚማሩባቸው መሆናቸውን ተናግረዋል።

በትምህርት ቤቶቹ የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት መሠረት ባደረገና የትምህርት ሚኒስቴር በሚያወጣውን መመዘኛ የሚያሟሉ ተማሪዎች የሚማሩባቸው መሆናቸው ተገልጿል።

በሁሉም ክልሎች በሚገነቡት እነዚህ የልህቀት ማዕከላት ከሁሉም የአገሪቱ ክልሎች የሚመለመሉ ተማሪዎችን ተቀብለው የሚያስተምሩ ይሆናሉ።

ይህንን መረጃ ያጋራው የትምህርት ሚኒስቴር የማህበራዊ ትስስር ገፅ ሚኒስትሩ የትምህርት ቤቶቹ ግንባታ መቼ ተጀምሮ መቼ ለማጠናቀቅ እቅድ እንደተያዘ የተናገሩት ነገር ስለመኖሩ ያለው ነገር የለም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert ትምህርት ሚኒስቴር በጦርነት እና ግጭት ውስጥ ሆነው ተፈትነዋል ተብለው የተለዩ እና የ12ኛ ክፍል " የማለፊያ ውጤት ያላመጡ " ተማሪዎች በዚህ ዓመት በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና እንደ መደበኛ ተማሪ ሆነው መፈተን እንደሚችሉ አስታወቀ፡፡ ከዩኒቨርስቲዎች ጋር ውይይት በማድረግ ተጨማሪ የቅበላ አቅም እንዲኖር ከስምምነት ላይ መደረሱን እና ተጨማሪ የቅበላ አቅም በፍትሀዊነት በጦርነቱ…
የትምህርት ሚኒስቴርና የሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች !

ከብሄራዊ ፈተና አስተዳደር ጋር በተያያዘ ባለፉት አመታት የታዩ ችግሮች ለመቅረፍ ከፈተና ዝግጅት ጀምሮ እስከ ውጤት ማሳወቅ ያሉትን ተግባራት በጥቃቄ እንዲከናወኑ ፦

1ኛ. ፈተናዎችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ተደግፎ መስጠት የሚቻልበትን ሁኔታ ለማረጋገጥ የሚደረጉ ጥረቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ፤ ይህ እውን እስኪሆን ድረስ የሚሰጡ ፈተናዎች በየክልል ትምህርት ቤቶች መሆኑ ቀርቶ የፈተና ጣቢያዎች በፌዴራን ተቋማት ውስጥ ብቻ ሊሆኑ የሚችሉበትን መንገድ ከአሁኑ እንዲመቻች፤

2ኛ. ማህበረሰቡ ለረጅም ጊዜያት ሲጠይቅ የነበረውን እና መንግስት ግልፅ አቋም የያዘበትን የትምህርት ስርዓቱን የጊዜያዊ የፖለቲካ ጥቅም ማሳኪያ መሳሪያ አድርጎ መጠቀም፣ ማንንም የማይጠቅም በተለይ የልጆቻችን ትምህርት የሚጎዳ መሆኑ ታውቆ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ከእንዲህ አይነት ጎጂ አሉታዊ እንቅስቃሴ እራሱን እንዲያቅብ፤

3ኛ. በየደረጃው ያለው የፖለቲካ እና ከመንግስት አመራር ፤ የትምህርት ባለድርሻ አካላት ፤መላው ህብረተሰብን ጨምሮ በጉዳዩ ዙሪያ ማነጋገርና ለመፍትሄው በከፍተኛ ደረጃ ተሳትፎ እንዲደረግ ለማስቻል ርብርብ እንዲደረግ ከወዲሁ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

(ተጨማሪ ከላይ ያንብቡ)

#ትምህርት_ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
#MoE

በቻይና ሀገር ትምህርታቸው ሲከታተሉ የነበሩ ተማሪዎች ያቋረጡትን ትምህርት እንዲከታተሉ ተፈቅዷል።

ትምህርት ሚኒስቴር በዓለም አቀፍ ደረጃ በተከሰተው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና ይሄንን ተከትሎ የቻይና መንግስት ባወጣው የኮቪድ- 19 ፕሮቶኮል ምክንያት በአጋጣሚ ወደሀገራቸው መጥተው መመለስ ያልቻሉ ተማሪዎች የኢትዮጵያ መንግስት እና በቻይና ሀገር የሚገኘው ኤምባሲ ባደረጉት ጥረት የቻይና መንግስት ተማሪዎች ተመልሰው ያቋረጡትን ትምህርት እንዲከታተሉ መፍቀዱን አሳውቋል።

ስለሆነም ከዚህ ጋር በተያያዘው ፎርም መሰረት ተማሪዎች አስፈላጊ መረጃዎችን በመሙላት እጅግ ቢዘገይ እ.ኤ.አ. እስከ June 20/2022 ብቻ በሚከተለዉ ማስፈንጠሪያ በመግባት ፎርሙን ሞልተው በተከታዩ ኢሜይል አድራሻ እንዲልኩ ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።

Link- https://moe.gov.et/AddReso

Email፡ [email protected],
[email protected]

#ትምህርት_ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
#ትምህርት_ሚኒስቴር

" ፈተናው የሚቀር አይደለም " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

* ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች ተማሪዎቻችሁን አዘጋጁ !

የመውጫ ፈተና በ2015 ዓ/ም መሰጠት ይጀምራል። ይህን በተመለከተ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለኢፕድ ከሰጡት ማብራሪያ ፦

" ... በሙሉ አቅማችን እየተዘጋጀን ነው። የሚቀር ነገር አይደለም ፤ 2015 ትምህርት ዘመን ማብቂያ ላይ ፤ ከዚህ በፊት እንደነበረው ዝም ብሎ ዲግሪ የሚሰጥበት ነገር ሀገሪቱን በጣም ክፉኛ ጎድቷታል የሚል እምነት አለን።

ይሄንንም ከዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንቶች ጋር፣ ከግል ኮሌጆች ፕሬዜዳንቶች እና ኃላፊዎች ባለቤቶች ጋር ፣ ከዩኒቨርሲቲ መምህራን እና ተማሪዎች ጋር ሰፊ ውይይት ያደረግንበት ነው።

ይሄ አዲስ ሀሳብ አይደለም አተገባበሩ ነው አዲስ የሆነው። ከዚህ በፊት ተሞክሮ ተቃውሞ ስለንበር ነው የተተወው።

የህግና የህክምና ትምህርቶችን ብቻ እንዲሰጡት አድርጎ አሁንም እየተሰጡ ሌሎች በሙሉ ተትተው ነበር።

አሁን ግን በአጠቃላይ ከከፍተኛ ትምህርት ጥራት ችግር ጋር በተገናኘ ምንም ልንወጣው የማንችለው እና ያን ጥራት ለማስተካከል ዩኒቨርሲቲዎቹ በራሳቸው ባስተማሩበት እና እራሳቸው በሰጡት ፈተና ብቻ የሚለኩበት ሁኔታ ከጀርባው ያለ ጠንካራ የሞራል መሰረት ይጠይቃል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ እራሳቸው ድግሪ ስንሰጥ ለማህበረሰቡ ይሄ ሰው እንዲህ እንዲህ አይነት ትምህርቶችን፣ እውቀቶችና ክህሎቶች አሉት ብለን ነው እየነገርን ያለነው።

... ከዚህ በፊት አንዱ የነበረው ችግር ማሳለፍ የሚባል ነገር አለ። ዝም ብሎ ማሳለፍ ምክንያቱም ተማሪዎች ከወደቁ የትምህርት ክፍሉን ድክመት ያሳያል እየተባለ ሲሳራበት የነበረው ነገር ምን ያህል ሀገሪቱን እንደጎዳት አሁን ለውይይትም የሚቀርብ አይደለም።

እኔ በዚህ ጉዳይ ባለፉት ሰባት (7) ወራት በትምህርት ዘርፍ ከሚሰሩ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንቶች የግል ኮሌጆች ባለቤቶች እንደዚህ አይን ያወጣ የለም መሆን የለበትም የሚል ክርክር አልሰማሁም። ሁሌ የሚሰማው ለምን በኛ ጊዜ ? ለምን ባንተ ጊዜ ለምን በሌላውስ ሰው ጊዜ የሚለውን ልትመልስ አትችልም ይሄ ዝም ብሎ ደረቅ ክርክር ነው።

በአንድ በሆነ ጊዜ መጀመር አለበት ምክንያቱም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጥራት ላይ እየደረሳ ያለው ጉዳት ሀገሪቱን ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈላት ነው። ይሄንን ዝም ብለን ማለፍ አንችልም ብለን እየሄድንበት ነው።

ለተማሪዎችም ፣ ለወላጆችም፣ ለቤተሰብም አንድ (1) ዓመት የመዘጋጃ ጊዜ ሰጥተናል። ለኮሌጆችም ተማሪዎቻቸውን እንዲያዘጋጁበት ጊዜ ሰጥተናል ይሄን ጊዜ በደንብ ተጠቅመው ስራቸውን መስራት አለባቸው።

ይሄ የመውጫ ፈተና የተማሪዎች ፈተና ብቻ አይደለም። ከተማሪዎች በላይ የትምህርት ክፍሎች፣ የኮሌጆች ፣ የዩኒቨርሲቲዎች ፈተና ነው። ምን እያደረጉ ነው ዩኒቨርሲቲዎቹ የሚለውን እንደትምህርት ሚኒስቴር ከዚህ የምናገኘው ፤ እነዚህ ኮሌጆች ፣ ዩኒቨርሲቲዎች በእርግጥም ተማሪዎችን እያበቁ ነው ? ወይስ የዲግሪ ወፍጮ ቤት እንደሚሏቸው ዝም ብሎ ጊዜ እያስቆጠሩ ድግሪ የሚሰጡ ናቸው የሚለውን የምንለይበት ነው።

ስለዚህ የሚቀር አይደለም። ሁሉም እንደማይቀር አውቆ የተሰጠውን የመዘጋጃ ጊዜ በደንብ ተጠቅሞ ትምህርትን በደንብ አስተምሮ በደንብ አስጠንቶ ቢያዘጋጅ ነው የሚሻለው "

@tikvahethiopia
#ትምህርት_ሚኒስቴር

የ2014 12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን በ12 ኮድ (በጥያቄ አቀማመጥ ስብጥር) ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው።

የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከዚህ በፊት እንደነበረው በ4 ኮድ (4 የተለያዩ ፈተናዎች/በጥያቄ አቀማመጥ) ሳይሆን እስከ 12 እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

ይህ የፈተና ኩረጃን ለመከላከል ከሚሰሩት ስራዎች መካከል አንዱ መሆኑን የሚገልፁት ፕ/ር ብርሃኑ ጎን ለጎን ያሉ ተማሪዎች እርስ በእርስ የሚፈተኑት ፈተና የጥያቄው ዝርዝር (order) በፍፁም የተገናኘ እንዳይሆን እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

ፈተናው በዩኒቨርሲቲዎችና በፌዴራል ተቋማት እንደሚሰጥም ገልፀዋል።

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለኢፕድ የሰጡት ቃል፦

" ...የክልል ባለሟሎች፣ የክልል ኃላፊዎችን ከፈተና ጉዳይ ጋር እንለያቸው ፤ ፈተናው እራሱ የፌዴራል ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ስለሆነ በፌዴራል ተቋማት ውስጥ ብቻ እንስጥ ብለን አሁን በሙሉ ተማሪዎቹን አጓጉዘን ቢቻል ሁሉንም ከክልላቸው ውጭ በሆኑ ክልሎች ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች እና የፌዴራል ተቋማት ውስጥ ለመስጠት ነው እየተዘጋጀን ያለነው።

ያ የሚያደርገው ሁለት ነገር ነው። አንደኛ በመንገድ ላይ ሊኖር የሚችለውን የመሰረቅ አደጋ ይቀንሰዋል። ሁለተኛ ክፍል ውስጥ ከተገባ በኃላ ለመስረቅ የሚቻልበትን አደጋ ይቀንሰዋል።

ከዛም በላይ ፈተናዎቹን በማዘጋጀት ደረጃ በፊት በ4 የተለያዩ ፈተናዎች ነበር የምናዘጋጀው እስከ 12 አድርገን Completely scrambled እንዲሆኑና ማንም ጎኑ ያለው ተማሪ የሚፈተነው ፈተና አንተ ከምትፈተነው ፈተና order ጋር በፍፁም ያልተገናኘ እንዲሆን አድርገን እየሰራን ነው።

ይሄ በጣም በብዙ ደረጃ የፈተና ስርቆትን ይቀንሰዋል ብለን ነው ተስፋ የምናደርገው። "

@tikvahethiopia
#MoE

የትምህርት ሚኒስቴር የምርምርና ስነ ምግባር ስራ ክፍል የምርምር ስነ ምግባር ግምገማን የተቀላጠፈ እና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግ ያስችላል ያለድን ድረ-ገፅ አዘጋጅቶ ወደ ስራ ማስገባቱን በዛሬው ዕለት አሳውቋቃ።

ድረ-ገፁ ተመራማሪው ስራዎቹን ለማመልከት እንዲሁም ገምጋሚው ዶክመንቶቹን አይቶ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷታ።

የሚሰሩ የምርምር ስነ ምግባር ስራዎችን በተመለከተ ተገልጋዮች ባሉበት ቦታ ሆነው “NRERB Research Ethics Review Portal በመጠቀም በኦላይን : https://nrerb.ethernet.edu.et ላይ አገልግሎቱን በቀላሉ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

#ትምህርት_ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
#ትምህርት_ሚኒስቴር

የትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው ውጤታቸው ከግማሽ በታች የሆኑትን በቅድመ መደበኛ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ጉድለታቸውን እንዲሞሉ ኮርስ ይወስዳሉ ብሏል።

የትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታው ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ለኤፍ ቢ ሲ በሰጡት ቃል ፤ " እነኚህ ተማሪዎች ያለባቸውን ጉድለት የሚሞላው የሬሜዲያል ፕሮግራም ይከታተላሉ፤  ያ ማለት በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተማሯቸውን ከሞላ ጎደል እነኚህን ኮርሶችን እንዲማሩ እናደርጋለን " ብለዋል።

" ዋና ዋና ይዘቶች እና መታወቅ ያለባቸውን እስከ አራት ወር ወስደን ከየካቲት 15 እስከ ሰኔ መጫረሻ አካባቢ እነኚህን ትምህርቶችን እንዲማሩና እንዲከልሱ እናደርጋለን " ሲሉ ዶ/ር ሳሙኤል ተናግረዋል።

ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ፤ " ተማሪዎች ተከታታይ ምዘና ይመዘኑና ከመቶ ይያዝላቸዋል ፤ እሱን ወደ 30% ቀይረን ከማዕከል ተመሳሳይ ፈተና በግል ተቋማትም ዕጩ ለሆኖ ፍሬሽ ተማሪዎች በመንግስት ተቋማት ላሉ እጩ ፍሬሽ ማን ተማሪዎች ተመሳሳይ ፈተና እንሰጣለን። ይሄንን አድርገን 50 % እና ከዛ በላይ ያመጡትን ወደ መደበኛ ፌሽ ማን ፕሮግራም እንዲገቡ ይደረጋል። መደበኛ ፍሬሽማን ፕሮግራም ተከታትለው የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ይሆናሉ " ብለዋል።

ተማሪዎች የሚማሩት በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ላይ ያሳዩት ጉድለት ሲሆን ፦

- ቋንቋ፣
-  ሂሳብ፣
- የተፈጥሮ ሳይንስ (ኬሚስትሪ፣ ባዮሎጂ፣ ፊዚክስ) አስፈላጊ ከሆነ ዩኒቨርሲቲዎች ተጨማሪ ይዘት ይጨምሩላዋል ተብሏል።

በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ ፦

- ጂዮግራፊ፣
- ታሪክ፣
- ቋንቋ እና ሂሳብ የሚማሩ ሲሆን ዩኒቨርሲቲዎች እንደፍላጎታቸው ተጨማሪ ይዘት ሊጨምሩላቸው እንደሚችሉ ተገልጿል።

መንግስት ለ100 ሺህ ተማሪዎች የቅድመ ፍሬሽማን ኮርስ እድል የሚያማቻች ሲሆን ለዚህም ቁርጥ ያለ ነጥብ እንደሚያስቀምጥ ይጠበቃል በራሳቸው ወጪ ሸፍነው ኮርስ ለሚወስዱ መንግስት ዝቅተኛ የመቁረጫ ነጥብ እንደሚያስቀምጥ ተነግሯል።

ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ፦

" ወጪውን ችሎ ወደ መንግስት ተቋማት የሚሄደው የግል ውሳኔ ስለሆነ አነስተኛውን መቁረጫ ነጥብ ብቻ መንገር ነው የኛ ኃላፊነት።

በመንግስት የሚሄደውን መለየት ስላለብን በዝርዝር ለሴቶች፣ ለወንዶች፣ ለተፈጥሮ ሳይንስ ፣ ለማህበራዊ ሳይንስ ፣ አካል ጉዳት ላለባቸው፣ ከታዳጊ ክልል ለመጡ፣ ለአርብቶ አደር አካባቢዎች በዝርዝር ማስቀመጥ ስላለብን 100 ሺ ለመቀበል ስንት ተማሪ ምንያክል መቁረጫ ነጥብ አድርገን ነው የምናገኘው የሚለው የመንግስት ውሳኔ ነው የሚሆነው።

እኚህ መንግስት ወጪያቸውን ችሎ፣ ዶርም አስገብቶ፣ አብልቶ ፣ አስተኝቶ ሬሚዲያል ፕሮግራም ለሚሰጣቸው ነው።

በራስ ለሚወሰን አነስተኛውን ነው መንገር ያለብን በራስ ውሳኔ የሚለው የግድ ወደ ግል ተቋማት ይሄዳሉ ማለት አይደለም በመንግስት ተቋማትም ሊማሩ ይችላሉ ወጪያቸውን ሸፍነው " ብለዋል።

ይኸው እድል ለአንድ አመት ብቻ እንደሆነ ተገልጿል።

በ2014 ዓ/ም ፈተና ያለፉ #ተማሪዎችን_ምደባ እስከ #እሁድ ለማሳወቅ ፤ የቅድመ ፍሬሽማን ተማሪዎችን መቀበያ ነጥብ እስከ #ሰኞ ይፋ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ለፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት ተናግሯል።

@tikvahethiopia