TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA ከትላንት ምሽት አንስቶ በኢትዮጵያ ቴሌግራም ፣ ፌስቡክ  እንዲሁም ሌሎች የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች እንዲገደቡ መደረጉ ታውቋል። አገልግሎቶቹ በሁለቱም የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢዎች ማለትም በኢትዮ ቴሌኮም እንዲሁም በሳፋሪኮም በኩል እየሰሩ እንዳልሆነ ለመረዳት ችለናል። ከማህበራዊ መገናኛዎቹ አገልግሎት መገደብ ጋር በተያያዘ በሌሎች ለአብነት በጎረቤት ሀገራት ውስጥ እስካሁን የታየ መቆራረጥ…
#Ethiopia

ከጥቂት ቀናት በፊት አገልግሎታቸው እንዲገደብ የተደረጉት የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ዛሬም አገልግሎታቸው ወደ ቦታው እንዳልተመለሰ ለመረዳት ታችሏል።

#ቴሌግራም ጨምሮ ሌሎች የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አገልግሎታቸው እንዲገደብ ከተደረገ ቀናት ያለፉ ሲሆን ጉዳዩን በተመለከተ ያብራራ/ያሳወቀ የለም።

የአገልግሎት ገደቡ በሁለቱም የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢዎች (ኢትዮ ቴሌኮም እና ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ) ተፈፃሚ እየሆነ ይገኛል።

የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ከኢትዮጵያ ውጭ ባሉ ለአብነት በጎረቤት ሀገራት ያለ አንዳች ገደብ እየሰሩ ሲሆን በኢትዮጵያ አገልግሎት የመገደብ እርምጃ ከምን በመነሳት እንደተወሰደ እና እስከመቼ ድረስስ እንደሚቆይ ያብራራ አካል የለም።

ምንም እንኳን አገልግሎቶች ላይ ገደብ ቢደረግም የማህበራዊ መገናኛ ተጠቃሚዎች በ #VPN ገደቡን በማለፈ አገልግሎት እየተጠቀሙ ይገኘሉ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#MoE

በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የRemedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምርጫቸውን በየትምህርት ቤታቸው በተወከሉ መምህራን አማካይነት ማስተካከል ይችላሉ ሲል ትምህርት ሚኒስቴር አሳስውቋል።

ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምርጫ ማስተካከል የሚችሉት እስከ የካቲት 10/2015 ዓ.ም ድረስ መሆኑ ተመላክቷል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በዚህ ፕሮግራም የማይካተቱ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

More : @tikvahuniversity

@tikvahethiopia
#EOTC

በእሥር ላይ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያንን በተመለከተ #በጥቂት_ቀናት ጉዳያቸው ታይቶ እንደሚፈቱ ከመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር መግባባት ላይ መደረሱን ብፁዕ አቡነ አብርሃም ማሳወቃቸውን የኢ/ኦ/ተ/ቤ መገናኛ ብዙሀን አገልግሎት ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሦስቱ አባቶች መመለስ ታላቅ ደስታ ተሰምቷታል " - ቅዱስ ሲኖዶስ

ከቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ውስጥ የተወሰደ ፦

" ... በዛሬው ዕለት የቤተ ክርስቲያን ጸሎቷ፣ ሐዘኗና ጩኸቷ ተሰምቶ ወደ ነበረችበት ልዕልናዋና አንድነቷ ተመልሳለች፡፡ ይህ አንድነቷና ልዕልናዋ እስከ ዓለም ፍጻሜ ተጠብቆ ይኖራል፡፡

በቅርቡ በቤተ ክርስቲያናችን ተከስቶ የነበረው ችግርም በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት ተፈትቷል፡፡

... በችግሩ አፈታት ወቅት መንግሥት በተለይም ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ፖለቲካዊ ችግሩን በፖለቲካዊ መንገድ ከመፍታታቸውም ባሻገር የቤተ ክርስቲያን ችግር በቀኖናና በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን መሠረት እንዲፈታ ታላቁን አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡

ክቡር የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ቀደም ሲል ሁለቱን ሲኖዶስ አንድ በማድረግ ያደረጉትን አስተዋጽኦ አሁንም የቤተ ክርስቲያን አንድነት ተጠብቆ እንዲኖር ላደረጉት መልካም ተግባር ቤተ ክርስቲያን ከልብ ታመሰግናለች፡፡

... ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሦስቱ አባቶች መመለስ ታላቅ ደስታ ተሰምቷታል፡፡ ካህናት፣ ምእመናን በሀዘናችን ተካፋይ የነበራችሁ በሙሉ የዚህ ደስታ ተካፋዮች በመሆናችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ በማለት ቅድስት ቤ ክርስቲያን ደስታዋን ትገልጻለች፡፡ "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ስምምነት

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ያጋጠመውን ፈተና ለመፍታት የተደረሰው ስምምነት ዝርዝር ፦

1. በኦሮሚያ ክልል በኦሮምኛ ቋንቋ ትምህርት፤ ቅዳሴ እና ሌሎችም አገልግሎቶች እንዲሰጡ የተጀመረው ሥራ የሕዝቡን ጥያቄ በሚመልስ መልኩ እንዲጠናከር። ለዚህም ከዚህ በፊት ከተደረገው በተጨማሪ አስፈላጊው በጀትና የሰው ኃይል እንዲመደብ።

2. በኦሮሚያና በሌሎች አካባቢዎች የተዳከሙ አብያተ ክርስቲያናት ቋንቋውን በሚያውቁ አገልጋዮችና በአገልግሎት እንዲጠናከሩ አስፈላጊው ዕቅድ ተዘጋጅቶ ከበፊቱ በበለጠ ተገቢው በጀትና የሰው ኃይል እንዲመደብ።

3. በኦሮሚያ እና በሌሎች አካባቢዎች የሚያገለግሉ ቋንቋውን የሚያውቁ አገልጋዮችን የሚያሠለጥኑ ተጨማሪ ኮሌጆች እና ማሠልጠኛዎች እንዲከፈቱ፣ የተከፈቱትም እንዲጠናከሩ እንዲደረግ።

4. ለኦሮሚያ አህጉረ ስብከት በቂ የሆነ የኦሮምኛ ቋንቋን የሚያውቁና በቋንቋው የሚያገለግሉ ኤጲስቆጶሳት በቀጣይ የግንቦት ርክበ ካህናት ተወስኖ እንዲሾሙ፡፡

5. ሦስቱ ሊቃነ ጳጳሳት ብጹዕ አቡነ ሳዊሮስ፣ ብጹዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ እና ብጹዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ወደ ቀደመ ሀገረ ስብክታቸውና የክነት ማዕረጋቸው እንዲመለሱ።

6. በሦስቱ አባቶች የተሾሙት አባቶች ቀድሞ ወደነበሩበት የክነት ማዕረግ ይመለሳሉ፡፡ ከእነርሱ ውስጥ በቤተ ክርስቲያን ሕግና ሥርዓት ተመዝነው የሚያሟሉት እንደገና በቅዱስ ሲኖዶስ እንዲሾሙ ይደረጋል።

7. በአስተዳደራዊ ጉዳዮች፣ በፋይናንስ ፣ በምደባ፣ በቅጥር የሚታዩ ክፍተቶችን በጥናት የወንጌል አገልግሎትን በሚያጠናክር መልኩ እናሻሽላለን።

8. የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት የበለጠ ለማጠናከርና ለትውልድ አርአያ የሚሆን ቤተ ክህነት እንዲኖረን ለማድረግ አሠራራችንን በጥናት አሻሽለን ቤተ ክርስቲያንን ለትውልድ እናሻግራለን፡፡

9. ጥላቻን የሚያባብሱ ጉዳዮችን ከማድረግ መቆጠብ ይገባል። ሚዲያዎች፣ አክቲቪስቶች፣ መምህራን እና አባቶች ፍቅርን ከሚያጠፋ፣ ጥላቻን ከሚያበዛና መለያየትን ከሚያሰፋ ነገር ሁሉ እንዲቆጠቡ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን። ይሄንን ተግባር ሆን ብለው የሚያደርጉትንም እናወግዛለን።

10. የገጠመን ፈተና ይበልጥ ውስጣችንን ለመፈተሽ፤ አንድነታችንን ለማጠናከር፤ ወንጌልን የበለጠ ለመስበክና የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ለማስፋፋት ለበጎ እንጠቀምበታለን።

በመጨረሻም #ፍቅር#ይቅርታ እና #አንድነት እንዲመጣ የደከማችሁትን ሁሉ በቤተ ክርስቲያን ስም እናመስግናለን። ዋጋችሁንም እግዚአብሔር እንዲከፍላችሁ እንጸልያለን።

@tikvahethiopia