TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የፌደራል እና የአማራ ክልል የጸጥታ አስከባሪ ተቋማት #እርምጃ እንዲወስዱ ታዘዙ‼️

በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር እና በሰሜን ሸዋ ዞን አዋሳኝ አካባቢዎች ያለውን የጸጥታ መደፍረስ ለማረጋጋት የፌደራል እና የክልል የጸጥታ አስከባሪ ተቋማት እርምጃ እንዲወስዱ ታዘዙ። የጸጥታ ኃይሎቹ “አስፈላጊውን ህጋዊ እና #ተመጣጣኝ እርምጃ እንዲወስዱ” ትዕዛዝ መተላለፉን ያስታወቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የጸጥታ ምክር ቤት ነው።

ምክር ቤቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በአማራ ክልል “ከሚሴ እና በአጎራባች አካባቢዎች የተከሰተው የሰው ሕይወት መጥፋት እና የንብረት ውድመት በምንም አግባብ ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው” ብሏል። የምክር ቤቱ መግለጫ በአካባቢዎቹ በተፈጸመው ጥቃት ስለሞቱ ሰዎች ብዛት ከመጥቀስ ተቆጥቧል።

በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን እና የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን አጣዬ፣ ማጀቴ እና ካራቆሬ በተባሉ ከተሞች በተፈጸመ ጥቃት የሰው ሕይወት መጥፋቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። በሰሜን ሸዋ ዞን የኤፍራታና ግድም ወረዳ መንግስት ኮሚዩንኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት “የኦነግ ታጣቂዎች” ሲል የጠራቸው ጥቃት ፈጻሚዎች በከፈቱት ተኩስ አራት ሰዎች መሞታቸውን በትላትናው ዕለት አስታውቆ ነበር። ህይወታቸው ካለፈው መካከል ሶስቱ “የከተማይቱን ሰላም ለማስጠበቅ የተሰማሩ የፀጥታ አባላት” መሆናቸውን የገለጸው የወረዳው የመንግስት ኮሚዩንኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አንደኛው በተባራሪ ጥይት ተመትቶ መሞቱን ገልጿል።

በአካባቢዎቹ የተከሰተውን ጥቃት “ብጥብጥ” ሲል የጠራው የብሔራዊ ጸጥታ ምክር ቤት “ችግሮች የሚከሰቱት የራሳቸው አጀንዳ ባላቸው ውስን የጥፋት ሃይሎች ነው” ብሏል። ምክር ቤቱ “በአካባቢዎቹ በተከሰተው ብጥብጥ ላይ “እጁ ያለበት ማንኛውም አካል በህግ ተጠያቂ እንደሚሆኑ” ገልጿል። ብጥብጡን ያቀናበሩት፣ ያነሳሱትና የፈጸሙ አካላትን ለህግ ለማቅረብ እንዲቻል ጥናት የሚያደርግ፣ ከአማራ ክልል እና ከፌደራል ተቋማት የተውጣጣ ቡድን ወደ አካባቢዎቹ መሰማራቱንም አስታውቋል።

መንግስት ህግን ለማስከበርና የዜጎችን ሰላም ለማስጠበቅ ከመቼውም ጊዜ በላይ ቁርጠኛ እንደሆነ የገለጸው የብሔራዊ ጸጥታ ምክር ቤት “በሕገወጥ ተግባራት ላይ የሚሳተፉ አካላት ከድርጊታቸው የማይቆጠቡ ከሆነ መንግስት ሕግን ከማስከበር ወደ ኋላ እንደማይል በድጋሚ ያረጋግጣል” ሲል አስጠንቅቋል።

ምንጭ-የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia