TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59K photos
1.5K videos
211 files
4.08K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray ንግድ ባንክ በትግራይ ክልል፣ መቐለ እና ዙሪያው #የተሟላ የባንክ አገልግሎት መስጠት ጀመረ። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ፤ በትግራይ ክልል በመቐለ እና በዙሪያው ባሉ ከተሞች  የሚገኙ 31 የባንኩ ቅርንጫፎች የተሟላ የባንክ አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን በትዊተር ገፃቸው ላይ አሳውቀዋል። ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ @tikvahethiopia
ፎቶ፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በትግራይ ክልል ተከስቶ በነበረው ጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የባንክ አገልግሎት ዛሬ አስጀምሯል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከብሄራዊ ባንክ ለክልሉ የተላከውን ብር ለቅርጫፎች በማከፋፈል በመቐለ ከተማ በሚገኙት ሁሉም ቅርንጫፎች እንዲሁም በዓብይ ዓዲ፤ ማይ ለሚን፤ ሳምረ፤ ግጀት፤ ሃይቂ መስሓል፤ወርቅ አምባ፤ አፅቢ እና አጉላዕ በሚገኙ በአጠቃላይ በ31 ቅርንጫፎች የተሟላ የባንክ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ገልጿል።

በተጨማሪም በዓዲግራት፣ ውቕሮ፣ ፍረወይኒ፣ ሓውዜን፣ ዓዲጉዶም፣ ሒዋነ፣ ዓዲሽሁ፣ መኾኒ፣ ማይጨውና አካባቢው በሚገኙ ቅርንጫፎች በቅርብ ሰዓታት ውስጥ ባንኩ የተሟላ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር የባንኩ መቐለ ዲስትሪክት አሳውቋል።

የኢትዮጰያ ንግድ ባንክ ሥራ የጀመረባቸው አካባቢዎች የቴሌ መሰረተ ልማት ዝርጋታዎች የተሟላባቸው ሲሆን፣ የተወሰኑ የቴሌ መሰረተ ልማት ጥገና ባልተጠናቀቀባቸው አካባቢዎች በቅርቡ ሙሉ በሙሉ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁ አሳውቋል።

Photo Credit : CBE

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አሁንም በብፁአን አባቶች እና ምእመናን ላይ እየደረሰ ያለው ስቃይና እንግልት መቀጠሉን ገለፀች።

ቤተክርስቲያኗ ከቀናት በፊት በሻሸመኔ ከተማ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በተፈፀመው ጥቃት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከፍ ማለቱን ገልጻለች።

ቤተክርስቲያኗ የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ቀሲስ ሐረገወይን ከመንግስት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው በሕክምና ሲረዱ ቢቆዩም ህይወታቸው ሊተርፍ እንዳልቻለ አሳውቃለች።

በተጨማሪ ቤተክርስቲያኗ ፤ በፓሊሶች ፊት በአጣና ጭንቅላቱን ተቀጥቅጦ በሀዋሳ በፅኑ ህሙማን ክፍል ሕክምና ሲደረግለት የነበረ አያሌው ተረፈ የተባለ ምዕመን በደረሰበት ጉዳት ህይወቱን ማትረፍ ሳይቻል ቀርቶ ማረፉን ገልጻለች።

በጽኑ ሕሙማን ክፍል ሌሎችም ተጎጂዎች እንደሚገኙ የገለፀችው ቤተክርስቲያን የጤናቸው ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን አስረድታለች።

ከሰሞኑ ሁኔታ ጋር በተያያዘ በሻሸመኔ ከተማ እስካሁን አጠቃላይ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎችን ቁጥር ቤተክርስቲያኗ ይፋ አላደረገችም።

ከዚህ ባለፈ ቤተክርስቲያኗ ፤ በሻሸመኔና አርሲ ነገሌ በሌሎችም ስፍራዎች የቤተክርስቲያን አባቶች፣ ምዕመናን ሰብአዊ ክብራቸው ተጥሶ ዛሬም በየእስር ቤቱ እንደሚገኙ አሁንም እየታሰሩ የሚገኙ መኖራቸውን አሳውቃለች።

መንግስታዊዎቹ የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋምና የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ዝምታን መምረጣቸው እጅግ እንዳሳዘናት ቤተክርስቲያኗ ገልጻለች።

በሌላ በኩል ቤተክርስቲያኗ ፤ ወደ ከፋ ሸካና  ቤንች ማጂ ሀገረ ስብከታቸው የተጓዙት የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል የኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ኃይሎች ክልሉን አቋርጠው ወደ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እንዳይሄዱ በማገዳቸው ወደ አዲስ አበባ እንደተመለሱ ገልጻለች።

@tikvahethiopia
#Update

የሣውላ ከተማ አስተዳደር ፤ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዕውቅና ውጭ የሚንቀሳቀሱ አካላትን " አላስተናግድም " አለ።

" የመንግሥት ተቀዳሚ ተግባር የአከባቢውንና የህዝቡን ሠላም ማስጠበቅ ነው " ያለው የከተማው አስተዳደር ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዕውቅና ውጭ የሚንቀሳቀሱ አካላትን ከተማዋ ተቀብላ አታስተናግድም ብሏል።

የሣውላ ከተማ ከንቲባ አቶ ሙሉቀን ጉጃ ፤ " የደንባ ጎፋ ወረዳ ቤተክህነት በህገወጥ መንገድ ጳጳሳት የሆኑ አካላት ወደ አካባቢያችን እየተንቀሳቀሱ መሆኑን መረጃው ደርሶኛል ሲል በፃፈው ደብዳቤ ገልፆልን መንግስትና የፀጥታ አካላት ቅድስት ቤተክርስቲያንና የአካባቢውን ሠላም በቅርበት እንዲከታተልና የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ጠይቀናል " ሲሉ ተናግረዋል።

ከንቲባው ፤ ህብረተሰቡ የሠላም ማስከበር ስራውን አጠናክሮ እንዲያስቀጥል፤ በአከባቢው እንግዳ ነገሮች ሲያጋጥሙ ጥቆማ እንዲሰጥና ከፀጥታ አካላት ጎን በመሆን የተለመደ ተግባሩን እንዲያከናውን ጥሪ አቅርበዋል።

በተጨማሪ ህዝበ ክርስቲያኑ ያለአንዳች የፀጥታ ስጋት በፆመ ነነዌ የጀመረውን ሱባኤ በአርምሞ እንዲያከናውን በመግለፅ የከተማው መንግሥት ከፖሊስ እንዲሁም ከሠላምና ፀጥታ መዋቅሮች ጋር በጋራ በመቀናጀት የአከባቢውን ደህንነት እንደሚያስጠብቁ አረጋግጠዋል።

በከተማዋ ላሉ አቢያተ ክርስቲያናት መንግሰት የተጠናከረ ጥበቃ እንደሚያደርግ ከንቲባው አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ቱርክ #ሶሪያ በቱርክ እና ሶሪያ ድንበር አቅራቢያ ባሉ ከተሞች በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የሞቱ ሰዎች ከ4,800 በላይ መድረሱን ቢቢሲ ዘግቧል። የሟቾች ቁጥር ከዚህ ሊበልጥ እንደሚችል እየተነገረ ነው። የነፍስ አድን ሠራተኞችም በፍርስ ራሾች ውስጥ ተቀብረው የሚገኙ ሰዎችን ለማትረፍ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ ተብሏል። በሌላ በኩል ፤ የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን በቱርክ የሰባት ቀናት…
#Update

በቱርክ እና ሶሪያ መሬት መንቀጥቀጥ የሞቱ ሰዎች ከ7,300 አልፈዋል።

በቱርክ እና ሶሪያ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ አሁን ላይ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ7,300 ማለፉን ባለስልጣናት አሳውቀዋል።

ሰዎችን ከፍርስራሽ ውስጥ ፈልጎ የማውጣቱ እንዱሁም የነፍስ አድን ስራው አሁንም መቀጠሉ የታወቀ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ከዚህም ሊጨምር እንደሚችል ተነግሯል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

የኢትዮጽያ የሚድያ ህግ ከሴቶችና ህጻናት መብቶች አንጻር በሚል ርዕስ ከሚድያ አካላት እና ከኪነጥበብ ባለሙያዎች ጋር የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

በአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ህጻናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በተዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ ላይ የኢትዮጵያ የሚድያ አዋጅና ድንጋጌዎቻቸው ከሴቶች እና ህጻናት ጥበቃ አንጻር የተቀመጡት ድንጋጌዎች የቀረቡ ሲሆን ቢሮው የሰራቸውንና በመስራት ላይ ያለው ስራ ቀርቧል።

ቢሮው ፦
👉 ለዓመታት ስትደፈር ስለቆየች ሴት፤

👉 በአባታቸው ስለተደፈሩ ልጆች፤

👉 ተገለው በመንገድ ስለተጣሉ ልጆች እና  ሌሎችም በመዲናዋ (አዲስ አበባ) የተከሰቱ ዘግናኝ ኬዞችን እየተከታተለ እንዳለ አሳውቋል።

#አንዳንድ ሀኪሞች፣ መምህራን፣ መንገደኞች ፣ ሚድያዎች እና ሌሎችም በሴቶችና ህጻናት ላይ ጥቃት ከሚያደርሱ መካከል እንደሚመደቡም ተነግሯል።

በመድረኩ በሀገሪቱ የሚሰሩ ፊልሞችና ማስታወቂያዎች ለአብነትም የዳይፐር፣ የሳሙና፣ የማድ ቤት እቃዎችና ሌሎች ማስታወቂያዎች ላይ የሚሰሩት ሴቶች መሆናቸውን በመጠቆም የማስታወቂያዎቹ አሰራርም የሴቶችን አቅም የሚያዳክምና መሰል ኃላፊነቶች የእነሱ ብቻ መሆናቸውን አመልካች በመሆኑ ሊስተካከል እንደሚገባ ተገልጿል።

በመጨረሻም የኪነጥበብ ስራዎች የሴቶችና ህጻናትን መብቶች የሚያከብሩ እና ክብራቸውን የሚጠብቁ ሊሆኑ እንደሚገባና ሚድያውም የራሱን ሚና እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia
#ኢንሹራንስ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በኢንሹራንስ ዘርፍ ላይ ቁጥጥርና ክትትል እንዲያደርግ በሕግ የተሰጠውን ሰልጣን በማሻሻል፣ የኢንሹራንስ ዘርፉ ከብሔራዊ ባንክ ውጪ ራሱን በቻለ ገለልተኛ ባለሥልጣን ቁጥጥር እንዲደረግበት ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን ሪፖርተር አስነብቧል።

በዚህም መሠረት የኢንሹራንስ ዘርፉን የሚቆጣጠርና የሚከታተል ገለልተኛ ተቋም ለማቋቋም አማካሪ ተቀጥሮ ሥራ መጀመሩን ለማወቅ ተችሏል።

ይህ ሥራ ተጠናቆ ተቋሙ ከተመሠረተ በኋላም የኢንሹራንስ ዘርፍ #ለውጭ ኩባንያዎች ውድድር ክፍት እንደሚሆን ታውቋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሰሞኑን እንዳስታወቀው የኢንሹራንስ ሪጉላቶሪ ኤጀንሲ ራሱን የቻለ ገለልተኛ ኤጀንሲ እንዲኖረው በመንግሥት በተሰጠው አቅጣጫ መሠረት ኤጀንሲውን ለማቋቋም የሚያስችሉ ሥራዎች ተጀምረዋል፡፡

ብሔራዊ ባንክ " የውጭ ባንኮች በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ እንዲገቡ እንደተፈቀደው ሁሉ ለኢንሹራንስ ዘርፉም ሊከፍት ይገባል " በሚል የሚቀርበው ተደጋጋሚ ጥያቄ አግባብ ቢሆን መጀመርያ ሊሠሩ የሚገባቸው ሥራዎች ስላሉ ይህ ከተጠናቀቀ በኋላ ቀጣዩ ዕርምጃ በዘርፉ የውጭ ኩባንያዎችን መጋበዝ ይሆናል ብሏል።

የኢንሹራንስ ተቆጣጣሪ ኤጀንሲው ሳይቋቋም የውጭ ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ የማይፈቀድ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መጠቆሙን ሪፖርተር ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

አዲስ አበባ ከተማ በምታስተናግደው የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ምክንያት ከዛሬ ጀምሮ የሞተር ብስክሌት እና የባጃጅ እንቅስቃሴ መከልከሉ ታውቋል።

የከተማው የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ፤ " 36ኛው የአፍሪካ ህብረት ስብሰባን ምክንያት በማድረግ ከዛሬ የካቲት 1/2015 ዓ.ም ከቀኑ 6:00 ሰዓት ጀምሮ በከተማችን ሞተር ብስክሌት እና የባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) ማሽከርከር የተከለከለ መሆኑን እናሳውቃለን " ብሏል።

የባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ ባጃጅ ክልከላው ከዛሬ የካቲት 1/2015 ዓ.ም ከዛሬ ጀምሮ እስከ የካቲት 5/2015 ዓ.ም አመሻሽ 12:00 ሰዓት ድረስ ፀንቶ ይቆያል ተብሏል።

ሞተር ብስክሌቶች ከዛሬ የካቲት 1/2015 ዓ.ም  ጀምሮ ስበስባድ እስኪጠናቅ የካቲት 13/2015 ዓ.ም አመሻሽ 12:00 ሰዓት ድረስ ሞተር ብስክሌትን ማሽከርከር ፍጹም የተከለከሉ መሆኑ ተገልጿል።

ክልከላ የሚመለከተው የፀጥታ እና የትራፊክ ቁጥጥር ስራ አካላት ከሚጠቀሙባቸው ውጪ ነው ተብሏል።

ክልከላድ በአዲስ አበባ ከተማ #በሁሉም አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ ባጃጆችን፣ ባለሁለት እግር ሞተር ብስክሌቶችን በኤሌክትሪክ የሚሰሩትን ጭምር በሙሉ የሚያካትት መሆኑ ተመላክቷል።

የባጃጅ ባለንብረቶችና አሽከርካሪዎች፣ የሞተር ብስክሌት ባለንብረቶችም ሆኑ አሽከርካሪዎች ይሄንኑ ክልከላ መሰረት በማድረግ እስከ ተጠቀሰው ቀን ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ ኤጀንሲው አሳስቧል።

ክልከላድን በሚተላለፉ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ ይወሰዳል ሲል ኤጀንሲው አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በቱርክ እና ሶሪያ መሬት መንቀጥቀጥ የሞቱ ሰዎች ከ7,300 አልፈዋል። በቱርክ እና ሶሪያ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ አሁን ላይ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ7,300 ማለፉን ባለስልጣናት አሳውቀዋል። ሰዎችን ከፍርስራሽ ውስጥ ፈልጎ የማውጣቱ እንዱሁም የነፍስ አድን ስራው አሁንም መቀጠሉ የታወቀ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ከዚህም ሊጨምር እንደሚችል ተነግሯል። @tikvahethiopia
#Update

በቱርክ እና ሶሪያ የሟቾች ቁጥር 11,000 ደረሰ።

ሰኞ በቱርክና ሶሪያ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 11,000 መድረሱን አልጀዚራ ዘግቧል።

ከ11 ሺህ ሟቾች መካከል በትንሹ ከቱርክ 8,574 ሲሆኑ ከሶሪያ ደግሞ 2,530 ሆነው መመዝገባቸው ተመላክቷል።

ሰዎችን ከህንፃ ፍርስራሾች ውስጥ ፈልጎ የማውጣቱ እንዱሁም የነፍስ አድን ስራው አሁንም መቀጠሉ የታወቀ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ከዚህም ሊጨምር እንደሚችል ተነግሯል።

#አልጀዚራ

@tikvahethiopia
#ብርሃን_ባንክ
እንደ ስማችን ብርሃን ነው ስራችን!
አዳዲስ እና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ !
Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://t.iss.one/berhanbanksc
Instagram: https://www.instagram.com/berhanbanksc/
Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/76151001
YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCvOxWe439dzMSvNnMrjcYVQ
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ክስ በመመስረት ሂደት ላይ መሆኗን አሳወቀች። ቤተክርስቲያኗ ይህን ያሳወቀችው ዛሬ ከህግ ባለሙያዎች ጋር በመሆን በሰጠችው መግለጫ ነው። ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ለመመስረት ጥያቄ የቀርበ ሲሆን ክስ የመመስረት ሂደት ጊዜ ስለሚፈልግ ጊዜያዊ እግድ እንዲሰጥ ጥያቄ መቅርቡ ታውቋል። ክሱ / እግዱ የቀረበው በልደታ ምድብ ሁለተኛ መሰረታዊ…
" ቤተ ክርስቲያኗ ቡድኑ ለጊዜው በአመልካች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ንብረቶች ፣ቅጥር፣ቅርስና ዐብያተ ክርስቲያናት እና ገዳማት እንዳይደርስ እግድ እንዲሰጥ ነው የጠየቀችው " - ጠበቃ አንዷለም በእውቀቱ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የክስ ሂደት መጀመሯ ይታወቃል።

ቤተክርስቲያኗ አውግዛ የለየቻቸው ፣ኤጲስ ቆጶሳትን የሾሙት የቀድሞ ሥስት ሊቃነ ጳጳሳት እንዲሁም ሹመቱን የተቀበሉ አካላት ወደ አብያተ ክርስቲያናት ከመግባት እንዲታገዱ ያቀረበችው ጥያቄ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።

ተለዋጭ ቀጠሮውን የሰጠው ጉዳዩን የሚከታተለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለተኛ መሠረታዊ መብቶች እና ነጻነቶች ምድብ ችሎት ነው።

የቤተክርስቲያኗ የጠበቆች ቡድን አባላት ዛሬ ብይን ለመስማት ቢቀርቡም እገዳ እንዲጣልበት ጥያቄ የቀረበበት ቡድን ጠበቃ መሆኔ አይቀርም ብለው በችሎቱ የቀረቡት ግለሰብ እግድ ከተጠየቀባቸው ወገኖች ሕጋዊ የጥብቅና ውክልና ይዘው የካቲት 3 ቀን 2015 ዓም ለክርክር ይቅረቡ ሲል ፍርድ ቤት መቅጠሩን የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ከቤተክርስቲያኗ ጠበቆች አንዱ የሆኑትን አቶ አንዷለም በእውቀቱ ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።

አቶ አንዷለም ፤ ቤተ ክርስቲያኗ ቡድኑ ለጊዜው በአመልካች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ንብረቶች ፣ቅጥር፣ቅርስና ዐብያተ ክርስቲያናት እና ገዳማት እንዳይደርስ እግድ እንዲሰጥ ነው የጠየቀችው ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

@tikvahethiopia