TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በቅርቡ በሶስት የሀገራችን ከተሞች #ለመጀመሪያ ጊዜ #በአካል_ተገናኝተን በሰላም ጉዳይ እና በሌሎች ለሀገራችን እና ለህዝባችን ጠቃሚ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ውይይት እናደርጋለን።

የትኞቹ ከተሞች የሚለውን ሰሞኑን አሳውቃለሁ!!

ሰላም+ፍቅር+አንድነት=ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በፎቶሾፕ ከሚቀናበሩ የምርጫ ውጤቶች ተጠንቀቁ !

የምርጫ ጣቢያዎች ውጤት እያሳወቁ ይገኛሉ።

በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች ውጤት ናቸው የተባሉ ወረቀቶች እየተለጠፉ ነው።

ነገር ግን ወረቀቶቹ ላይ ያሉትን ቁጥሮች በፎቶሾፕ የመነካካት፣ የማስተካከል ምልክቶችን ታዝበናል።

በተለይ የቲክቫህ አባላት በሙሉ ፦

1ኛ. ዘመኑ የረቀቀ ነውና የምርጫ ውጤትን በተመለከተ ትክክለኛው ሪፖርት እስኪላክላችሁ ታገሱ

2ኛ. ድምፅ የሰጣችሁበት የምርጫ ጣቢያ #በአካል ተገኝታችሁ የተለጠፈውን ውጤት እንድትመለከቱ እናበረታታለን።

የውጤት ጉዳይ በጥንቃቄ ካልተያዘ እስካሁን የተመጣበትን #ሰላማዊ ሂደትን ሊያበላሽ ስለሚችል ከሀሰተኛ መረጃዎች/በይፋ በምርጫ ቦርድ ካልተረጋገጡ ሪፖርቶች ሁሉ እንድትርቁ አደራ እንላለን።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#WoldiaUniversity የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት የመጀመሪያ አመት መደበኛ ተማሪዎች ጥሪ እንዲደረግላቸው ውሳኔ አሳለፈ። የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አስተላልፏል። ሴኔቱ በዛሬው ዕለት ከስዓት በፊት በነበረው ስብሰባ ዋነኛ አጀንዳ ከነበሩት መካከል የመምህራን የደረጃ እድገት እና የመጀመሪያ አመት መደበኛ ተማሪዎች የጥሪ ሁኔታን የሚመለከቱ ነበሩ።…
#Update

ከቀናት በፊት የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት የመጀመሪያ አመት መደበኛ ተማሪዎች ጥሪ እንዲተላለፍላቸው ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል።

ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ለአንደኛ ዓመትና አራተኛ ዓመት የፔዳጎጅካል ሳይንስ መደበኛ ተማሪዎች ጥሪ አስተላልፏል።

ተማሪዎች ከየካቲት 30/2014ዓ.ም እስከ መጋቢት 1/2014ዓ.ም #በአካል ተገኝተው እንዲመዘገቡ ጥሪ ተላልፏል።

ሌሎች ተማሪዎች በሌላ ማስታወቂያ ጥሪ እስኪተላለፍ ድረስ በትዕግስት እንዲጠባበቁ ዩኒቨርሲቲው መልዕክት አስተላልፏል።

More @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
" ውጤታችሁን በየት/ቤታችሁ ማየት እና መወሰድ ትችላላችሁ " - ትምህርት ቢሮ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የ8ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤታቸድን በየትምህርት ቤታቸው ማየት እና መውሰድ ይችላሉ ብሏል። ቢሮው " ይፋ በተደረገው የውጤት መመልከቻ ሊንክ #በኔትዎርክ_መጨናነቅ ምክንያት ውጤታችሁን ያላያችሁ ተማሪዎች በየት/ቤታችሁ ማየት እና መውሰድ ትችላላችሁ " ብሏል። ተማሪዎች ውጤታቸውን እንዲያዩ…
" ከውጤት ጋር ተያይዞ ቅሬታ ያላችሁ ተማሪዎች ቅሬታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ " - አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ

ከ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ጋር ተያይዞ ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎች ቅሬታቸውን ማቅረብ እንደሚችሉ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

ተማሪዎች ቅሬታቸውን ወደ ከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ #በአካል በመሄድ ማቅረብ እንደሚችሉ የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አበበ ቸርነት ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል።

የተማሪዎቹ ውጤት ወደየትምህርት ቤቶች መላኩን የገለጹት ኃላፊው፤ በተፈጠረው የኔትወርክ መጨናነቅ ምክንያት ውጤታቸውን ማየት ያልቻሉ ተማሪዎች ወደትምህርት ቤታቸው በመሄድ ማየት እና መውሰድ ይችላሉ ብለዋል፡፡

@tikvahuniversity @tikvahethiopia
#ተመዝገቡ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን የሃይማኖት የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን በመመዝገብ ላይ ይገኛል።

የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ፤ የሃይማኖት ድርጅቶች አስተምህሮታቸውን በመገናኛ ብዙኃን እንዲያደርሱ የብሮድካስት አገልግሎት ፈቃድ ማግኘት እንዳለባቸው ይደነግጋል፡፡

በዚህም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ከሰኔ 27/ 2014 ዓ.ም ጀምሮ የሃይማኖት የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን በመመዝገብ ላይ እንደሚገኝ አሳውቋል።

ማንኛውም የሃይማኖት የቴሌቪዥን ጣቢያ እስከ #ነሐሴ_13_ቀን_2014 ዓ.ም ድረስ https://www.eservices.gov.et/ በሚለው ፖርታል ውስጥ በመግባት ወይም #በአካል_በመቅረብ ማመልከትና ፈቃድ መውስድ እንዳለበት ባለሥልጣኑ አሳስቧል።

Via @EthMediaAuth