TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
208 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA ዛሬ የሀገራችን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የ49 አገራት መሪዎች እንዲሁም አፍሪካ ህብረት የሚሳተፉበት ሁለተኛው የአሜሪካ- አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ይጀመራል። ለዚሁ ጉባኤ ዶ/ር ዐቢይን ጨምሮ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች አሜሪካ ላይ ተሰባስበዋል። ለሦስት ቀናት የሚካሄደው ይኸው የመሪዎች ጉባኤ ዓለማችንን እየፈተኗት ያሉ ተግዳሮቶች ፦ - የአየር ንብረት ቀውስ፣ - መልካም አስተዳደር፣…
#USA #ETHIOPIA

በአሜሪካ ፤ የአሜሪካ-አፍሪካ መሪዎች ጉባኤ ትላንት መካሄድ ጀምሯል። ይኸው ሶስት ቀን እንደሚቆይ የተነገረው የመሪዎች ጉባኤ የሀገራችን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የበርካታ አፍሪካ ሀገራት መሪዎች እየተካፈሉ ይገኛሉ።

ከዚሁ ጉባኤ ጎን ለጎን ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከአሜሪካ ባለስልጣናት ጋር ምክክር አድርገዋል።

- ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ከአሜሪካ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ጃክ ሳሊቫን ጋር የተወያዩ ሲሆን ውይይቱ በጦርነቱ ማቆም አተገባበር፣ በመንግሥት ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያ ሥራዎች እንዲሁም የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ማደስ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር።

- ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጋር የተወያዩ ሲሆን ይህን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገፃቸው እንዲሁም የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በድረገፁ ውይይቱን በተመለከተ መረጃ አጋርተዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፦

ከብሊንከን ጋር ውጤታማ ውይይት ማካሄዳቸውን ገልፀዋል። ሰላምን ለማስፈን በሚደረገው ጥረት አሜሪካ  ላበረከተችው አስተዋፅዖ ምስጋና አቅርበዋል። ለበርካታ አስርት አመታት ኢትዮጵያ በአፍሪካ የአሜሪካ ቁልፍ አጋር ሆና ቆይታለች ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን አጋርነታችንን ማጠናከር በሚቻልበት መንገድ ላይ ተወያይተናል ብለዋል።

አንቶኒ ብሊንከን ፦

ዶ/ር ዐቢይ በጉባኤው ላይ እና በዋሽንግቶን በመገኘታቸው በጣም ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። የስምምነቱ ዜና ለመላው ሀገሪቱ ጥሩ ዜና መሆኑን ገልፀዋል። ከዚህ ቀደም ከጠ/ሚኒስትሩ ጋር ንግግር በማድረጋቸው (በስልክ) በጣም ደስተኛ እንደነበሩና አሁን ደግሞ በአካል መገናኘታቸው ጥሩ መሆኑን ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA #ETHIOPIA በአሜሪካ ፤ የአሜሪካ-አፍሪካ መሪዎች ጉባኤ ትላንት መካሄድ ጀምሯል። ይኸው ሶስት ቀን እንደሚቆይ የተነገረው የመሪዎች ጉባኤ የሀገራችን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የበርካታ አፍሪካ ሀገራት መሪዎች እየተካፈሉ ይገኛሉ። ከዚሁ ጉባኤ ጎን ለጎን ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከአሜሪካ ባለስልጣናት ጋር ምክክር አድርገዋል። - ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ከአሜሪካ የብሔራዊ ደኅንነት…
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ፦

• አንቶኒ ብሊንከን የሰላም ስምምነቱን አፈጻጸምን አድንቀዋል።

• የኢትዮጵያ መንግስት የሰብአዊ አቅርቦትን ለማሻሻል እና አስፈላጊ አገልግሎቶችን ወደነበረበት ለመመለስ የወሰደውን እርምጃ አድንቀዋል።

• ብሊንከን የስምምነቱ ተፈፃሚነት የተፋጠነ እንዲሆን አሳስበው ፤ ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ የሰብአዊ መብቶች ተቆጣጣሪዎች ግጭት በተከሰተባቸው ቦታዎች እንዲንቀሳቀሱ ጠይቀዋል።

• እንደ አሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ብሊንከን የኤርትራ ኃይሎች በፍጥነት ከኢትዮጵያ ለቀው መውጣት አስፈላጊነት ላይ የተወያዩ ሲሆን ይህም ከትግራይ ታጣቂዎች ትጥቅ መፍታት ጋር ጎን ለጎን መሆኑ ተመላክቷል።

• አሜሪካ፣ በአፍሪካ ኅብረት የሚመራውን የሰላም ስምምነት ለማሳለጥ እንዲሁም ስምምነቱ መተግበሩን ከሚያረጋግጠው ኅብረቱ ጎን ለመቆም ያላትን ቁርጠኝነት ገልጻለች።

@tikvahethiopia
" የሀብት ምዝገባ መረጃው ለህዝብ ክፍት ይደረግ "

የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የፌዴራል ሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን #በተሿሚዎች#በተመራጮች ወይም #በመንግሥት_ሠራተኞች ላይ እያከናወነ ያለው የሀብት ምዝገባ መረጃ ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ ጠይቋል።

በ2002 ዓ/ም በወጣው የሀብት ማሳወቂያና ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 668/2002 ድንጋጌ መሠረት፦
👉 የአገሪቱ ፕሬዚዳንት፣
👉 ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣
👉 ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣
👉 ሚኒስትሮች፣
👉 ሚኒስትር ዴኤታዎች፣
👉 ኮሚሽነሮች፣
👉 ምክትል ኮሚሽነሮች፣
👉 ዋና ዳይሬክተሮች፣
👉 ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች፣ እንዲሁም #ሌሎች የመንግሥት ሠራተኞች ሀብታቸውን እንዲያስመዘግቡ #ግዴታ ጥሎባቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ባወጣው መግለጫ፣ ግለሰቦቹ ለኮሚሽኑ ያስመዘገቡትን ሀብት መረጃ በሚስጥር መያዝና ለሕዝብ ይፋ አለማድረግ ከአዋጁ ጋር  የሚፃረር ድርጊት እንደሆነ አስረድቷል፡፡

በተለይም በመንግሥት ተቋማት የሚገኙ የሥነ ምግባር መከታተያ የሥራ ክፍሎች በየተቋማቸው ያለውን የሀብት ምዝገባ መረጃን ለማንኛውም መረጃ ጠያቂ እንዲሰጡ አለማድረግ፣ ወይም ምቹ ሁኔታ አለመፍጠር የሕገ መንግሥቱን የግልጽነትና ተጠያቂነት ድንጋጌንና የሀብት ማስመዝገቢያና ማሳወቂያ አዋጅ ቁጥር 668/2002 ጽንሰ ሐሳብና መሠረታዊ ዓላማን ግምት ውስጥ ያላስገባ መሆኑን አስታውቋል፡፡

መረጃ ያለመስጠት ድርጊት ለተጀመረው የሙስና ትግል ምንም ዓይነት አበርክቶ የሌለው በመሆኑ የሀብት ምዝገባ መረጃ ለሕዝብ ክፍት እንዲሆን የዕርምት ዕርምጃ እንዲወስድ ተቋሙ ጠይቋል፡፡

(የኢ/ሕ/ዕ/ጠ/ተቋም ወቅታዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የሰጠው መግለጫ ከላይ ተይይዟል)

#Reporter
#EthiopiaInstitutionoftheOmbudsman

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

108 ድርጅቶች ተሽከርካሪ ለማስገባት የተሰጣቸው እድል ተሰረዘ።

የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር ተሽከርካሪ ወደ ሃገር ውስጥ እንዲያስገቡ ፍቃድ ሰጥቷቸው ከነበሩ 168 ድርጅቶች ውስጥ በተለየየ ምክንያት ማስገባት ያልቻሉ 108 ድርጅቶችን በመሰረዝ ለሌላ አስመጪዎች እድሉን መስጠቱን አስታውቋል።

ፍቃዳቸው ከተሰረዙት ውስጥ የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ አገልግሎት አንዱ ነው።

ዕድሉ የተሰረዘባቸው አስመጪዎች ከዛሬ አንስቶ በሁለት ተከታታይ የስራ ቀናት ማስረጃቸውን ማቅረብ ከቻሉ ማስረጃ ማቅረብ ይችላሉ ተብሏል።

የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር በሚያዚያ ወር 2013 ዓ/ም የከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎችን ቢያንስ በሁለት ዓመት ሰፕላይ ክሬዲት የግዢ ሂደት መሰረት ገዝተው ወደ ሀገር ውስጥ ማስመጣት ፍላጎት ላላቸው የትራንስፖርት ድርጅቶች እድሉን ለመስጠት በተካሄደ ልየት ለ168 ድርጅቶች ተሽከርካሪዎች እንዲያስገቡ ፈቅዶ ነበር።

@TIKVAHETHIOPIA
TIKVAH-ETHIOPIA
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ፦ • አንቶኒ ብሊንከን የሰላም ስምምነቱን አፈጻጸምን አድንቀዋል። • የኢትዮጵያ መንግስት የሰብአዊ አቅርቦትን ለማሻሻል እና አስፈላጊ አገልግሎቶችን ወደነበረበት ለመመለስ የወሰደውን እርምጃ አድንቀዋል። • ብሊንከን የስምምነቱ ተፈፃሚነት የተፋጠነ እንዲሆን አሳስበው ፤ ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ የሰብአዊ መብቶች ተቆጣጣሪዎች ግጭት በተከሰተባቸው ቦታዎች እንዲንቀሳቀሱ…
#Ethiopia

በአሜሪካን ዋሽንግቶን ዲሲ የሚገኙት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከአሜሪካ - አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ከተለያዩ ተቋማት ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል።

- ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ ከአሜሪካ የንግድ ተወካይ አምባሳደር ካትሪን ታይን ተገናኝተው ተውያይተዋል። የሁለቱን ሀገራት የንግድ ግንኙነት ማስፋፋት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ጥሩ ውይይት መደረጉን ገልጸዋል።

- ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ IMF ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋር ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን ገልፀዋል። ውይይቱ በኢትዮጵያ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ፣ በዕዳ ማቅለያ አስፈላጊነትና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር ብለዋል። " ያለፉትን ስኬቶቻችንን ለማስጠበቅ እና የጀመርናቸውን ለውጦች የበለጠ ለማጎልበት ቁርጠኝነታችንን እገልጻለሁ " ሲሉ አክለዋል።

- ጠ/ሚሩ ከዓለም ባንክ ቡድን ፕሬዝዳንት ዴቪድ ማልፓስ ጋር ተወያይተዋል። " የሠላም መስፈን ምርታማነትን እና የስራ ዕድል ፈጠራን የሚያጎለብት የኢኮኖሚ ሽግግር አጀንዳን ለማፋጠን እድል ይሰጣል " ብለዋል። ውይይቱ ባንኩ የኢትዮጵያን ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች በሚደግፍበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ እንደነበር ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ፥ የዓለም ባንክ በድረገፁ ባሰራጨው መረጃ ፕሬዝዳንት ማልፓስ ለጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ የውስጥ ግጭቶችን ማስቆም እና ዘላቂ ሰላም ማስፈን አስፈላጊነትን አስገንዝበዋል። በቅርቡ የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑንም አሳስበዋል።

https://www.worldbank.org/en/news/statement/2022/12/14/readout-from-world-bank-group-president-david-malpass-s-meeting-with-prime-minister-abiy-ahmed-of-ethiopia

@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ፤ ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ኃይል ለማቅረብ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

ተቋሙ ፤ " መንግሥት በኤሌክትሪክ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት የነዳጅ ፍጆታን ለመቀነስ የጀመረውን ጥረት ለማገዝ እየሰራሁ ነው " ብሏል።

ኢትዮጵያ ውስጥ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ሲሆን እነዚህ ተሽከርካሪዎች የነዳጅ ወጪ በማስቀረት በኩል ከፍተኛ አስተዋፅኦ ስላላቸው ለተሸከርካሪዎቹ አስተማማኝ የኃይል አቅርቦቱን ለማቅረብ የሚያስችል ዕቅድ ተዘጋጅቷል ሲል ተቋሙ አሳውቋል።

የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በስፋት ወደ ሀገር ውስጥ እየገቡ መሆናቸውን ተከትሎ ተጨማሪ የኃይል ፍላጎት ጥያቄ ይኖራል ተብሎ እንደሚታሰብ ተጠቁሟል።

ተቋሙ ከኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ጋር በተያያዘ ከትራንስፖርትና ሎጅስቲክ ሚኒስቴር ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሆነና ከሁለቱም ተቋማት የተውጣጡ የቴክኒክ ባለሙያዎች ቡድን ተቋቁሞ ወደ ሥራ መግባቱን ገልጿል።

@tikvahethiopia