TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58K photos
1.45K videos
208 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

በተለያዩ የሀገራችን ፊልሞች ላይ በድንቅ ብቃት በመተወን በተለይ ደግሞ በወጣቶች ዘንድ እጅግ የሚወደደው አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ለማረጋገጥ ተችሏል።

አርቲስት ታሪኩ (ባባ) አርባ ያህል ፊልሞች ላይ የተወነ ሲሆን በህመም ምክንያት ህይወቱ ማለፉን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት (ኢፕድ) ከአርቲስቱ የቅርብ ሰዎች ለማረጋገጥ መቻሉን አሳውቋል።

አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ የአንድ ልጅ አባት ነበረ።

አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ፦
- ወጣት በ97፣
- ወንድሜ ያዕቆብ፣
- ላውንድሪ ቦይ፣
- ማርትሬዛ፣
- ይመችሽ-የአራዳ ልጅ 2 ፣
- ሞኙ የአራዳ ልጅ 4፣
-  አንድ ሁለት ፣
- ብር ርርር፣
- ወደው አይሰርቁ፣
- ወፌ ቆመች፣
-  እንደ ቀልድ ፣
- ወቶ አደር ፣
- አባት ሀገር
- የሞግዚቷ ልጆች፣
- ይዋጣልን ፣
- ዋሻው፣
- ወሬ ነጋሪ እና ሌሎችም ፊልሞች ላይ ተውኗል።

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ የቤኒሻንጉል ሕዝብ ነጻነት ንቅናቄ (ቤሕነን) ታጣቂ ቡድን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት ጋር የሰላም ስምምነት መፈራረሙና ወደ ሀገር መግባቱ ዛሬ ክልሉ አሳውቋል።

የቤሕነን ታጣቂ ቡድን እና የቤኒሻንጉሙዝ ክልል መንግሥት የሰላም ስምምነት ላይ የደረሱት በሱዳን #ካርቱም መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በዚህም ቡድኑ የሰላም አማራጮችን በመከተል ወደ ክልሉ ተመልሷል ተብሏል።

በሰላም ስምምነቱ መሠረት የቡድኑ አባላት ትጥቃቸውን ፍትተው ተሃድሶ በመውሰድ በክልሉ የሰላም እና የልማት ሥራዎች ላይ እንደሚሰማሩ ክልሉ ገልጿል።

(የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኮሚኒኬሽን)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። በተለያዩ የሀገራችን ፊልሞች ላይ በድንቅ ብቃት በመተወን በተለይ ደግሞ በወጣቶች ዘንድ እጅግ የሚወደደው አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ለማረጋገጥ ተችሏል። አርቲስት ታሪኩ (ባባ) አርባ ያህል ፊልሞች ላይ የተወነ ሲሆን በህመም ምክንያት ህይወቱ ማለፉን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት (ኢፕድ) ከአርቲስቱ የቅርብ ሰዎች ለማረጋገጥ…
#Update

የኢትዮጵያ የዓይን ባንክ ፤ ዛሬ ከሰዓት ባወጣው መግለጫ ፤ በታዋቂው እና ተወዳጁ አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ህልፈት ሀዘን እንደተሰማው ገልጿል።

በመግለጫው ፤ አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) በህይወት በነበረበት ወቅት የዓይን ባንኩ አምባሳደር እንደነበርና ህልፈት በሚያጋጥምበት ጊዜ የዓይን ብሌኑን ለመለገስ ቃልገብቶ እንደነበር ጠቁሟል።

አርቲስቱ በገባው ቃል መሰረትም በቤተሰቦቹ እና በጓደኞቹ ቀና ትብብር ቃሉ ተፈፃሚ መሆኑን ባንኩ አሳውቋል።

የኢትዮጵያ ዓይን ባንክ ፤ አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) " ስሙንም ብርሃኑንም ከመቃብር በላይ ህያው አድርጎ ያለፈ መልካም አርቲስት " ሲል ጠርቶታል።

በሌላ በኩል ፤ የአርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ)ን ስርዓተ ቀብር ለማስፈፀም ኮሚቴ ተዋቅሮ እየሰራ ሲሆን ይኸው ኮሚቴ የአርቲስቱ ስርዓተ ቀብር ነገ ታህሳስ 3 ቀን 2015 ዓ/ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ወዳጅ ዘመዶቹ በተገኙበት እንደሚፈፀም ገልጻል።

ከስርዓተ ቀብሩ ቀደም ብሎ ከጠዋቱ 5:00 ሰዓት ጀምሮ በኢትዮዽያ ብሔራዊ ቴአትር ሽኝት ይደረጋልም ተብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የክቡር ዶ/ር ቄስ በሊና ሳርካ ስርዓተ ቀብር ዛሬ ይፈፀማል።

ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ አገልጋይ የነበሩት ቄስ ዶ/ር በሊና ሳርካ ባለፈው ህዳር 27 ቀን 2015 ዓ.ም ማረፋቸው ይታወሳል።

የእኚህ በቤተከርስቲያንም ሆነ በአገር ደረጃ ተወዳጅ የነበሩት አባት አሸኛኘት አገልግሎት ዛሬ ሰኞ ታህሣሥ 3 ቀን 2015 ዓ/ም ይካሄዳል ፤ ከአሸኛኘት ስነ ስርዓቱ በኃላ ስርዓተ ቀብራቸው ይፈፀማል።

ለቄስ ዶ/ር በሊና ሳርካ የቀብር ስርዓትን ለማስፈፀም በወጣውና በተመለከትነው መርሃ ግብር መሰረት ፦ በአሁን ሰዓት (እስከ 4:00 ድረስ) አስክሬናቸው ከመኖሪያ ቤታቸው ወደ እንጦጦ ማህበረ ምዕመናን እየተሸኘ ነው።

ከ4:00 - 6:00 የአስክሬን ሽኝት በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ እንጦጦ ማ/ምዕመናን ይደረጋል።

በተጨማሪ በወጣው መርሃግብር መሰረት በወዳጅነት አደባባይ ሽኝት የሚደረግ ሲሆን ከዚህ በኃላ ከ9:00 - 10:00 አስክሬናቸው በጴጥሮስ ወ. ጳውሎስ መካነ መቃብር በክብር ያርፋል።

ፎቶ ፦ የክቡር ቄስ ዶ/ር በሊና ሳርካ የሽኝት ኘሮግራም በመኖሪያ ቤታቸው

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ የዓይን ባንክ ፤ ዛሬ ከሰዓት ባወጣው መግለጫ ፤ በታዋቂው እና ተወዳጁ አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ህልፈት ሀዘን እንደተሰማው ገልጿል። በመግለጫው ፤ አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) በህይወት በነበረበት ወቅት የዓይን ባንኩ አምባሳደር እንደነበርና ህልፈት በሚያጋጥምበት ጊዜ የዓይን ብሌኑን ለመለገስ ቃልገብቶ እንደነበር ጠቁሟል። አርቲስቱ በገባው ቃል መሰረትም በቤተሰቦቹ እና…
#Update

ከአርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ስርዓተ ቀብር ጋር በተያያዘ #ካሜራ ይዘው ቪድዮ ለመቅረፅ እና በየማህበራዊ ሚዲያው ለማስራጨት የሚሞክሩ ከድርጊታቸውን እንዲታቀቡ ስርዓተ ቀብሩን ለማስፈፀም የተቋቋመው ኮሚቴ አሳስቧል።

ከኮሚቴው አባላት አንዱና የአርቲስቱ የቅርብ ወዳጅ ዲጄ ቢቢ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ሬድዮ በሰጠው ቃል ፤ " ከማህበራዊ ሚዲያ ጋር በተለይም ፌክ ኒውስ፣ የተለያዩ ቪድዮ እየቀረፁ ፣ ፎቶዎችን እያነሱ ርዕስ እየሰጡ የሚለጥፉ አሉ ወጣቶቻችን ፤ ታናናሾቻችን በዚህ ላይ ጥንቃቄ ያድርጉ። " ብሏል።

ትላንት የስርዓተ ቀብሩ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በአርቲስት ታሪኩ (ባባ) መኖሪያ ቤት በነበሩበት ሰዓት ካልተጠበቁ ሰዎች ቪድዮ ተቅርፆ ርዕስ እየሰጡ በቲክቶክ ...በማህባዊ ሚዲያ ላይ ሲለጥፉ እንደነበር ፤ ይህም የአካባቢውን ልጆች ፣ አብሮ አደጎቹንና የኮሚቴውን አባላት እንዳስደነገጠ ገልጿል።

ወጣቶች እንዲያህ ያለውን ነገር እንዳያደርጉ ሲልም ጥሪ አቅርቧል።

የአርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ስርዓተ ቀብር ለማስፈፀመው በወጣው መርሃ ግብር ዛሬ ጥዋት 5:00 ላይ በብሄራዊ ትያትር አዳራሽ የሽኝት ፕሮግራም ይኖራል ፤ ፕሮግራሙ ላይ የሞያ አጋሮቹ፣ ጓደኞቹ ፣  የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ይገኛሉ።

ከዚህ በኃላ ከቀኑ 9:00 ሰዓት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ወዳጅ ዘመዶቹ በተገኙበት ይፈፀማል።

@tikvahethiopia